Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጎዴ’

የጎዴ ጉድ | ወላጅ-አልባ የተዋሕዶ ሕፃናትን ወደ እስልምና እንዲቀይሩ የሚያስገድደው የልጆች መንደር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 8, 2018

ሰለጠፉት በጎቼ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ ልጆቼ ተሠርቀዋል፣ ለእምነታቸው በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂው እኔ ነኝ!አባ ፍሬው።

ይህ አሳሳቢ ሪፖርት ሰሞኑን በአንጋፋው የስፔን ጋዜጣ፡ “ኤል ፓይስ” የወጣ ነው። መረጃው ብዙ ስፓኛውያን ክርስቲያን አንባቢዎችን አንገፍግፏል፣ አስደንግጧል።

ተዋሕዶ ሕፃናትን መስረቅ ከእግዚአብሔር እየነጠቋቸው ነው!” በማለት ሁለት የኦርቶዶክስ ቀሳውስት የድርጊቱን አሳሳቢነት ደም በሚያስለቅስ መንገድ ገልጸውታል። ይህ ጉዳይ ሁላችንንም፤ በተልይ የወንጀሉን ተባባሪዎች አውሮፓውያኑንና ኢትዮጵያውያን ጨምሮ ሁላችንንም በጥብቅ ሊያሳስበን ይገባል፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ያስወነጅላልና፣ ያስቀጣልና።

  • ሠላሳ የሚሆኑ ተዋሕዶ ሕፃናት ወደ እስልምና እንዲቀይሩ ተገድደዋል

  • ክርስቲያን ነች” የምትባለዋ ኦስትርያ በእዚህ መንደር አንድ መስጊድ ሠርታለች

  • የመንደሮቹ አስተዳዳሪ ጣልያናዊ ነው

  • ገንዘብ ለጋሾቹ አውሮፓውያን ናቸው

እነዚህ ፃናት ወደ ሕፃናት መንደሮች ሲገቡ በአክራሪነት ውስጥ እንዲካኑ እየተደረጉ ናቸው ሠላሳ የሚሆኑ ክርስቲያን ሕፃናት እስልምናን እንዲቀበሉና በቀን እስከ አምስት ሰዓት ድረስ በመንደሩ መስጊድ ውስጥ እንዲፀልዩ ይገደዳሉ

ይህ ሁሉ ጉድ የሚፈጸመው በኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው ዓለም አቀፉ መንግስታዊ ያልሆነ መንደር ውስጥ ነው

ዜናው ለመጀመሪያ ጊዜ የመጣው..አ በ ሁለት ሺህ አስራአራት ዓ.ም የበጋ መጀመሪያ ቀናት ውስጥ ነበር። አባ ፍሬው ክርስቲያን ልጆችን፣ ወጣቶችንና ጎልማሶችን እስላም ለማድረግ ሤራ መጠንሰሱን፡ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን የበላይ አለቆቻቸው አስቀድመው ማስጠንቀቂያ ልከው ነበር።

አደጋው ያንዣበበው በሶማሌ ክልል በጎዴ ከተማአስራ ሁለት የ አልዲያስ ኢንፋንቲል ድርጅት መጠለያዎች ውስጥ ተከፋፍለው በሚገኙ መቶ ሃያ ህፃናት ላይ ነው።

ተንከባካቢና አሳዳጊና የእንጀራ እናት ሆነው ልጆቹን የሚነከባከቡት ሶማሊያውያን አክራሪ እስላሞች ናቸው።

በጣም የሚገርመው አንድ የኦስትሪያ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በእዚህ የሕፃናት መንደር መስጊድ መስራቱ ነው። በተጨማሪም መስጊዱ እንደ ቁርአን ትምህርት ቤት ወይም መድረሳ ሆኖ ያገለግላል። በዚህ መስጊድ ክርስቲያኑ ሕፃናት በቀን አምስት ጊዜ እንዲሰግዱ ብሎም የቁርአን ሱራዎችን (መቶ አስራ አራት አንቀጾች አሉት) እና ተጨማሪ ጥቅሶችን እስኪደክማቸው ድረስ እንዲያነበንቡና በቃላቸው እንዲሸመድዱ ገና ከልጅነታቸው ይገደዳሉ።

አባ ፍሬውና አጋራቸው ህይወታቸው ለአደጋ የተጋለጥች ብትሆንም፡ ስለዚህ የሕጻናቱ አሳዛኝ ሁኔታ ለሚመለከታቸው የበላዮቻቸው ከማስታወቅ ወደ ኋላ አላሉም። እንደርሳቸው ከሆነ እስከ ሠላሳ የሚሆኑ ሕጻናት በመስጊዱ ግፊት ወደ እስልምና እንዲገቡ ተገድደዋል።

የሕጻናቱ መንደር በሚገኝበት ቦታ ያሉ ባለስልጣናት መስጊድ የሚለውን ስም በይሉኝታ በማለሳለስ “የጸሎት ቤት ብለው ሊጠሩት መርጠዋል።

አባ ፍሬው ለህይወታቸው አስጊ የሆነ ሁኔታ ቢፈጠርም በጎዴ የ ኢስ..ኤስ የህፃናት መንደሮች ምን ዓይነት ጉድ እየተካሄደ እንደሆነ ያው ለሦስት ዓመታት ያህል ድምጻቸውን ከማሰማት ወደ ኋላ አላሉም። “ሰለተሰረቁት በጎቼ ምን እንደማደርግ አላውቅም፣ ልጆቼ ተሠርቀዋል፣ ለእምነታቸው በእግዚአብሔር ፊት ተጠያቂው እኔ ነኝ!„ በማለት አባ ፍሬው በደከመ መልክ እና እንባ እየተናነቃቸው ተናግረዋል። ሙስሊሞቹ አደጋ ሊጥሉብኝ እንደሚችሉ ቢሰማኝም፡ ለጠፉት በጎቼ ጥብቅና ለመቆም ደሜን ለመፈወስ ፈቃደኛ ነኝ። ልጆቼን ለመከላከል ዝግጁ ካልሆንኩ በእግዚአብሔር አምላክ ዘንድ እኔ ነኝ ለነፍሳቸው ተጠያቂ የምሆነው።”

ነገር ግን የድኽነት ስሜት ይሰማኛል፣ ጥንካሬም ጎድሎኛል፣ ማንም ሊሰማኝ ፈቃደኛ አይደለም፣ ወደ ህፃናቱ መንደ ውስጥ እንድገባና ከተዋሕዶ ልጆቼ ጋር እንድነጋገር እንኳይፈቅዱልኝም።ብለዋል፡ አባ ፍሬው።

ተዋሕዶ ክርስቲያን ሆነው ወደ ህፃናት መንደ መጡትና ወደ “እስልምና” እንዲቀየሩ የተገደዱት ወላጅ አልባ ልጆ ስም መካከል በጥቂቱ የሚከተሉት ይገኙበታል ፦

  • ንዋሜ ደጀኔ

  • ጃፈር አቢ

  • ሞሆ አቢቹ

  • ሰላም

  • ቤዛዊት

  • ሊዲያ

  • መስከረም

  • ብሩክ

  • ብርቱካን

  • ሃይማኖት

  • ሃሊ

  • ነፃነት

  • ዮርዳኖስ

  • ናርዶስ

አሁን ግን ሙስሊም ስሞች ተሰጥቷቸዋል፣ ዘራቸውን እንዲያጡ ተደርገዋል፤ ከሌሎቹ ቤተሰቦቻቸው ጋር ከአያቶቻቸው፣ ከአጎቶቻቸው እና ከሌሎች ዘመዶቻቸው ጋር ግኑኝነት እንዲያቋርጡ ተደርገዋል። ዘመዶቻቸው አልፎ አልፎ ለመጠየቅ ሲመጡ ሙስሊሞቹ “ሞግዚቶቻቸው” አይነጠሏቸውም፡ ምክኒያቱም ከክርስቲያን ዘመዶቻቸው ጋር ለብቻቸው እንዲሆኑ አይፈቅዱላቸውምና ነው።

ህፃናቱን እስላም ለማድረግ ገንዘብ ይሰጣልን?

በንዴት የቆሰሉት አባ ፍሬው እንዲህ ብለዋል፦ እርግጠኛ ነኝኤስ ኦ ኤስ (SOS) የሕፃናት መንደሮች ገንዘብ የሚሰጡ የውጭ ሰዎች በአብዛኛው ክርስቲያኖች ናቸው። ነገር ግን እነሱን የሚደግፉ ሰዎች ልጆቻቸውን ለአክራሪ እስልምና አሳልፈው እየሰጧቸው እንደሆነ የሚያውቁ አይመስለኝም።”

በእነዚህ መንግሥታዊ ልሆኑ ድርጅቶች (NGO) አማካኝነት በተቋቋሙት የሕፃናት መንደሮች ምን ዓይነት ጉድ እየተሠራ እንድሆነ ለማጣራት የስፔይን ኤስ ኦ ኤስ መንደሮች መርማሪ ወገን በቦታው ተግኝቶ ነበር። ከገንዘብ ለጋሾቹ መካከል፦

  • ስፔይን

  • አውስትርያ

  • ጣልያን

ይገኙበታል። የጎዴን የህፃናት መንደር የሚያስተዳድረው ጣልያናዊው ክላውዲዮ ክሮቼ ይባላል።

ምንጭ፦ El País

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: