ይህ ጽሑፍ ከሰባት ዓመት በፊት በዚሁ ጦማሬ ላይ የቀረበ ነበር፦
በአይሁድና ክርስትና እምነቶች ላይ የሚካሄደው ጦርነት – የ፬ ሺህ ዓመት መለኮታዊ ሥርዓት ላይ የተመዘዘው ሳንጃ
“በዓለ ግዝረት” መሢሑ ሕፃን ከቅድስት ድንግል ማርያም በቤተልሔም በበረት ከተወልደ በኋላ “ስምንት ቀንም በተፈጸመ ጊዜ ሕፃኑን ሊገዝሩት ወሰዱት ስሙኑም ገና በማሕፀን ሳይፀነስ አስቀድሞ መልአኩ እንደሰየመው ‘ኢየሱስ አሉት።‘” በሚለው የወንጌላዊው ቃል መሠረት፤ በ፰ኛው (8ኛው) ቀን ፡ “ኢየሱስ” ተብሎ የኪዳነ አብርሃምን ሥርዓት የፈጸሙበትን ዕለት በማስታወስ የምናከብረው በዓል ነው፤ እርሱም “በዓለ ግርዘተ ኢየሱስ” ተብሎ በጥር ፮ ቀን ይክበራል። [ሉቃ.፪፥፳፩]። ንቡረ እድ ኤርምያስ ወልደ ኢየሱስ መስከረም ፰ ነው የሚከበረው ይላሉ። የክርስቶስ ልደት መስከረም ፩ ነው የሚል ፅንሰ–ሃሳብ ስላላቸው።
እኛ ኢትዮጵያውያን ይህን በዓል የምናከብረው የኢየሱስ ክርስቶስን ግዝረት ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን ሥርዓቱን ቀድሞም በኪዳነ ልቦና ማለትም ከአብርሃም በፊት በኖርንበት አምልኮተ እግዚአብሔር ስንፈጽመው የቆየን ኋላም በኪዳነ ኦሪቱ በአብርሃም በመጨረሻም በኪዳነ መንፈስ ቅዱስ ምክንያት ያንኑ ጥንታዊ ሥርዓታችንን አጽንተን የቀጠልን መሆናችንን ለማረጋገጥ ጭምር ነው። በዚህም እየራሳችን በቅዱሱ ኪዳን ጸጋ በነፍስ የሃይማኖትን ግዝረት፡ በሥጋም የምግባርን ግዝረትን ተቀብለን በመንፈስ ቅዱስ አማናዊውን የእግዚአብሔር ልጅነትን ክብር የተቀዳጀን መሆናችንን እናዘክርበታለን።
እኛ ኢትዮጵያውያን፡ ልክ እንደ አይሁዳውያን፡ ላለፉት 4ሺህ ዓመታት ያለማቋረጥ ወንዶች ሕፃናትን ከተወለዱ ከ8 ቀናት በኋላ እንዲገረዙ እናደርጋለን። ይህን ቅዱስ አይሁደ–ክርስቲያናዊ ሥርዓት የተቀረው የክርስቲያን ዓለም አልተከተለውም። ሙስሊሞችም ይህን ስነሥርዓት ከኛ ወስደው ሕፃናቶቻቸውን ከ 4 – 14 ባለው እድሜአቸው ይገርዛሉ። ግን ይህን አስመልክቶ በትውፊት ከአይሁዶችና ክርስቲያኖች ያገኙት እንጂ በቁራናቸው የተገለጸ ነገር የለም፤ ነብያቸውንም ተገርዞ ነው የተወለደው ነው የሚሉት።
የአውሮፓ ክርስቲያኖችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሆነ የግዝረትን ሥርዓት አይከተሉም፡ ነገር ግን በተውፊት ስላገኙት ከ10 – 15% ብቻ የሚሆኑት አውሮፓውያን ወንዶች ተገርዘዋል፡ ይህም በጎልማሳ እድሜቸው። 75% የሚሆኑት አሜሪካውያን ተገርዘዋል። በብዛት ግን አይሁዳውያንና አፍሪካውያን ናቸው የሚገረዙት።
ግዝረት ሥጋዊና መንፈሳዊ ተልዕኮ ያለው ሥርዓት ስለሆነ፡ በሥጋ የተወለዱትና ለሥጋ ብቻ የሚኖሩት፡ ለኃጢአትና ለሞት የተዳረጉት ሉሲፈራውያኑ የሰው ልጆች፡ በአሁኑ ጊዜ ጦራቸውን በመምዘዝ ግዝረትን በመዋጋት ላይ ናቸው።
ጀርመን አገር በኮሎኝ ከተማ የሚገኝ አንድ ፍርድ ቤት ከጥቂት ቀናት በፊት ግዝረት ወንጀል ነው፡ በሕፃናት ላይ የሚሰነዘር ጥቃት ነው፡ ሕፃናት “ያለፈቃዳቸው” ሲገረዙ ለሥጋዊና ሥነ ልቦናዊ ቀውስ ይጋለጣሉ፡ ስለዚህ ሕፃናትን የሚገርዙ ወላጆች በፌደራል ሕግ መሠረት ይቀጣሉ የሚል ሕግ አስተላለፈ። እዚህች ይመልከቱ ። በታሪክ ተመሳሳይ የሆነ ፍርድ ለመጀመሪያ ጊዜ ተሰጥቶ የነበረው በአምባገነናዊው የናዚ ዘመን ነበር። አንዳንድ የስካንዲኔቪያ አገሮችም እስካሁን ድረስ እንደከለከሉ ናቸው።
ይህን መሠረተ–ቢስና አሳፋሪ የሆነ ድርጊት በሥራ ላይ ለማዋል፡ እንደሁልጊዜው የሚጠቀሙት ሙስሊሞችን ነው። ወደ አገሮቻቸው ሙስሊሞችን በብዛት ያጎረፉበት አንዱ ምክኒያትም የአይሁድ–ክርስቲያናዊውን ሥልጣኔ ከሥር መሠረቱ ነቃቅሎ ለማጥፋት የሺህ ዘመን ዕቅድ ስላላቸው ነው።
በአውሮፓ ግዝረትን እንደ ዋና የኃይማኖታቸው ምሰሶ አድርገው የሚወስዱት አይሁዶች ብቻ ናቸው። ያልተገረዘ አይሁድ አይሁድ ሊባል አይችልም! ታች ያለው እንግሊዛዊ ጽሑፍ ላይ እንደተቀመጠው፤ ከጥቂት ቀናት በፊት በኮሎኝ ከተማ አንድ 4 ዓመት እድሜ የሞላው ሙስሊም በሚገዘርበት ወቅት ብዙ ደም ፈስሶት ጤንነቱ ተቃውሷል የሚል ምክኒያት በመስጠት የከተማዋ ፍርድ ቤት ይህን ጸረ–ግዝረት ሕግ አጸደቀ። ይህን አስመልክቶ በዜና ማሰራጫዎች ከፍተኛ ውይይት በመካሄድ ላይ ይገኛል፤ 2/3 የሚሆኑት ጀርመናውያንም ግዝረትን ያወግዛሉ፤ የተላለፈውንም ሕግ ይደግፋሉ።
ምንም እንኳን ኮሎኝ የካቶሊኮች ከተማ ብትሆንም፤ ላለፉት 20/30 ዓመታት የአውሮፓ ሰዶማውያን ዋና ከሆኑት ከተሞች መካከል አንዷ ለመሆን በቅታለች። የፕሮቴስታንታዊው እንቅስቃሴ፤ ቅዱሳንን በማግለል፣ ቅዱሳዊ ሥርዓቶችን በመተው እንዲሁም ቅዱሳን ምስሎችና ምልክቶች በተከታዮቹ ዘንድ ተቀባይነት እንዳያገኙ ካደረገ በኋላ አውሮፓዊውን ለነፍሳዊና መንፈሳዊ ድክመት አጋለጠው። አሁን ደግሞ ለስጋዊው ድክመት በመጋለጥ ላይ ይገኛል። ግዝረትም ቁልፍ የሆነ ሚና እንደሚጫወት ተደርሶበታል።
ሰዶማዊነትን ወደ አፍሪካ ለማሰራጨት የሚካሄደው ዓይን ያወጣ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል ለማወቅ እዚህች ላይ ይመልከቱ
ከዚህ ፀረ–ግዝረት እንቅስቃሴ ጀርባ፤ ሰዶማውያን፤ ኢ–ዓማንያን እና ጂሃዲስቶች ቆመዋል። እንዴት ጂሃዲስቶች? ብለን እንጠይቅ ይሆናል። አዎ! ምክኒያቱም፤ በእስልምና አንድ ልጅ 14 ዓመት እድሜ ሲሞላው ሊገዘር ስለሚችል፤ ቁራንም ስለ ግዝረት ስለማይናገር፤ ግዝረት በተለይ ለአይሁዳውያን ትልቅ ትርጉም ስላለው ነው። ኢ–ዓማንያኑንና ሰዶማውያንን የሚወክሉት የፍርድ ‘ሊቆች‘፡ ጠበቃዎችና ፖለቲከኞች የሚሉትም፡ ሕፃኑ 14 ዓመት ዕድሜ ሲሞለው ነው መገረዝ አለበት ነው። አሁን አይሁዳውያንና እስላሞች አንድ ላይ ሆነው የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወማቸው ሁለቱም ተበዳዮች/ተጠቂዎች እንደሆኑ አድርገን ልንወስድ እንችል ይሆናል፤ ነገር ግን ይህ ትልቅ ስህተት ነው። ለአይሁዳውያኑ፡ ግዝረት፡ በምንም ዓይነት ለድርድር የሚቀርብ ጉዳይ ስላልሆን ለወንጀል የሚያበቃቸው ከሆነ አውሮፓን ለቅቀው ይወጣሉ፤ ከስካንዲኔቪያ ቀስበቀስ በመውጣት ላይ ናቸው(እስላሞች በሚያደርጉባቸው ጥቃቶች ሳቢያ)። በተፈጥሮዊው አካባቢአችን ንቦች እየጠፉ የሚሄዱ ከሆነ በዙሪያችን የተበላሸ ነገር እንዳለ፤ አደጋ እየመጣብን እንደሆነ እንረዳለን፤ በማሕበረሰብም ደረጃ በአውሮፓ አይሁዳውያን ለዘመናት ከሚኖሩቧቸው ቦታዎች የሚፈናቀሉ ከሆነ አስከፊ ጊዜ፡ ተመሳሳይ አደጋ እየመጣ እንደሆነ መገንዘብ ይኖርብናል።
ነፃ የወጡ የሳይንስ ሰዎች ግዝረት ከብዙ በሽታዎች (ኤይድስን ጨምሮ)እንደሚከላከል በግልጽ ይናገራሉ። እዚህች ይጫኑ ።
የሦስቱ ሉሲፈራውያን (ሰዶማውያን፤ ኢ–ዓማንያን፤ ጂሃዲስቶች) ተልዕኮ በዚህ ብቻ አይገታም። ተከታዩ ትኩረታቸው “ጥምቀት” ላይ ይሆናል፤ አዎ! የክርስቲያን ህፃናት ጥምቀት ላይ። “ሕፃናት ያለፈቃዳቸው መጠመቅ የለባቸውም” የሚል መፈክር በቅርቡ ይዘው እንደሚመጡ አንጠራጠር። የዓብያተ ክርስቲያናትን ደወሎች ለማስከልከልም በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው።