Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ግብረሰዶማዊነት’

እኅተ ማርያም | ሰይጣን አብይን ልክ ወደ ሥልጣን ሲያመጣው የእሱ የሆኑትን ሰዶማውያኑንና መሀመዳውያኑን ለማሰልጠን ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2019

ክርስቲያኖች በመላው ዓለም በሙስሊሞችና በሰዶማውያን እየተጨፈጨፉ ነው! የኢትዮጵያን ታሪክ ያጠፋ ዘንድ በሉሲፈራውያኑ የተመረጠው ዶ/ር አህመድ ሁለቱን የክርስቶስ ጠላቶች፤ እስልምናን እና ግብረሰዶማዊነትን በሃገራችን ኢትዮጵያ ለማስፋፋት ቆርጦ የተነሳ አውሬ ነው። እስኪ ጋዜጠኞች ስለዚህ ጉዳይ በቀጥታ ጠይቁት? ስለ እስልምና ያለውን አመለካከት እናውቃለን፤ ሰለ ግብረሰዶማዊነትስ? እስኪ“የግብረሰዶማዊነት መስፋፋት ለኢትዮጵያ ማሕበረሰብ ጠንቅ አይሆንም ወይ?“ ብላችሁ ጠይቁት። “ዲሞክራሲ ለሁሉም ሰው ነፃነቱን ሰጥቷል” ብሎ እንደሚመልስላችሁ እርግጠኛ ነኝ።

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እኅተ ማርያም | አቤቱ ሕዝብህን አድን ርስትህንም ባርክ፤ ጠብቃቸው፥ ለዘለዓለሙ ከፍ ከፍ አድርጋቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 27, 2019

__________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ መሆን የለባትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 5, 2014

EthioChild

(ሪፖርተር ጋዜጣ – ከተቆርቋሪ ዜጋ)

ምንም እንኳን በሚዲያዎች በግልጽ ባይነገርም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ከመስከረም 20 እስከ 25 ቀን 2006 .ም የተደረገ ስብሰባ ነበር፡፡ ይህም የዓለም አቀፍ የሥነ ሕዝብና የዕድገት ኮንፈረንስ (አይሲፒዲ) ከፍተኛ ግብረ ኃይል ያልተቋጨ አጀንዳ በተለያዩ አገሮች እ..አ ከ2014 ጀምሮ ሊተገበር የሚገባ ብሎ ያስቀመጣቸውና በስብሰባው በስተመጨረሻ ለጉባዔው ይፋ የተደረጉና በዋናነት የተቀመጡ ነጥቦች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ከአገራችን ሕግ፣ ደንብና ባህል እንዲሁም እሴቶቻችን ጋር ፈጽሞ አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ጉዳዮች ነበሩበት፡፡

የመጀመሪያው የወሲብና ተዋልዶ መብቶችን ማክበር፣ መንከባከብና ተፈጻሚ ማድረግ የሚል ነው፡፡ ለዚህም ሕጋዊ ውርጃን ማስፋፋትና ማዳረስ፣ የወሲብና የተዋልዶ መብትን ከሌሎች መብቶችና ከተዛማች ሕጐች ጋር በማያያዝ ማስተማር፣ ግለሰቦች ያላቸውን የወሲብ ዝንባሌያቸውን በሚፈልጉት ሁኔታ ከተመሳሳይ ፆታም (ሆሞሴክሸዋሊዝም) ጋር ቢሆን ያለምንም ገደብ መብታቸውን እንዲለማመዱ ያበረታታል፡፡

ከጋብቻም ውጪ ቢሆን ማንኛውንም የወሲብ ኅብረቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እስከሆነ ድረስ መብታቸውን የሚከለክሉ ድንጋጌና ሕጐች እንዲነሱ ይጠይቃል፡፡ የወሲብና የተዋልዶ ጤና መረጃና ትምህርት ማቅረብና ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ሌላኛው ዓላማው ነው፡፡ ለዚህም በዋናነት ወጣቶችን በተለይም አፍላ ወጣት ሴቶች ላይ ያነጣጠረ መረጃ በትምህርት ቤቶችና ከትምህርት ቤቶችም ውጪ በመስጠት አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያና ሌሎች የወሊድ መቆጣጠሪያ (ሕጋዊ ውርጃንም ጭምር) የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

እንዲሁም ትምህርቱን በመቅረፅና በማዘጋጀት የሕግና ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲያገኝ ማድረግ የሚል ሲሆን፣ ይህንንም ለማድረግ የብሔራዊ ጤና ፕሮግራም አካል ሆኖ የራሱ በጀት እንዲኖረውም በማድረግ በአንዳንድ በውርጃ ሥራ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች የሚከናወን ነው፡፡ (ለምሳሌ በሪፖርተር ጋዜጣ ሐምሌ 2005 .ም በሜሪስቶፕስ ቃለ ምልልስ ላይ በወር 42 ሺሕ ሴቶች ለፅንስ ማቋረጥ ወደ እኛ ይመጣሉ ሲሉ ያለዕፍረት ተናግረዋል) ይህ እንግዲህ አንዱ ድርጅት ብቻ ነው፤ ሙሉ በሙሉ ሕጋዊነቱ ሲዳረስ ምን ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ያሻል፡፡

እስቲ ፍረዱ እኛ በልተን ያልጠገብንና ለማደግ የምንፍጨረጨር ዜጐች፣ የአውሮፓውያንና የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ የምንሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ይሄ ኢትዮጵያ ነው፡፡ እኛም ኢትዮጵያዊያን ነን፤ ሁለተኛ ዜጋ አይደለንም፡፡ ስለአገራችን ሁኔታ ያገባናል፡፡ ይህ ድብቅ በሆነ መንገድ ቀስ በቀስ ገጽታችንን የሚያጠፋ ጉዳይ ነው፡፡ በጣም የሚያሳፍረው ደግሞ ከግብረ ኃይሉ አባላት ውስጥ አስፈጻሚ ሆነው ልጆቻችንን የመሸጥ ያህል በመሯሯጥ ላይ ያሉት ባለሥልጣኖቻችን መሆናቸው ነው፡፡ እንርሱን ታሪክም ትውልድም ይጠይቃቸው፡፡ ዛሬ ከውጭ ለሚገኘውና በልማት ስም ለሚመጣ ገንዘብ ብለው ጤናማ ትውልድ ሊያሳጡን ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሌሎች አገሮች እንኳን ስንሄድ የምንኮራበት የራሳችን የሆነ ባህልና ሞራል እንዲሁም ታሪክ ያለን ሕዝቦች ሆነን፣ በዕድገትም ስም ተቀበሉ እያሉ በገንዘባቸው እያስፈራሩና እየደለሉን ነው፡፡ እኛ የምንመርጠው ከድህነታችን ጋር ጤናማ ኅብረተሰብና ታሪካችንን ነው፡፡

ታዲያ የአባቶቻችንና የቀደሙት መሪዎችቻችን ድፍረትና ወኔ ወዴት ነው ያለው? የአሁኖቹ መሪዎች ካደጉ አገሮች በልማት ስም ለሚገኘው ገንዘብ አሳልፈው ይሰጡን ይሆን? ሕጋችንን፣ ባህላችንንና ታሪካችንን ያከብሩልን ዘንድ እባካችሁ ጠይቁልን!

ግብረሰዶማዊነትና ልቅ የወሲብ መብቶች ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንደ ዳቦ ሲታደል ምን ዓይነት ቀጣይ ትውልድ ይኖረናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን? ጠቃሚ ስለሆኑት መመርያዎች ቅሬታ አይኖረንም፡፡ ነገር ግን በተከበረች አገራችን ላይ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ/ግንኙነት እንዲሁም ልቅ ወሲባዊ መብት ልንሸከመው የምንችለው አይደለም፡፡ እንኳን ይህ ሁኔታ ተመቻችቶ ሚዲያዎች መጤና አጉል ልማዶችን እያስተዋወቁን ይገኛሉ፡፡ ታዲያ የሥነ ምግባርና የሞራል ውድቀት ሲጨመርበት ምን ሊሆን ይችላል? መንግሥት በዚህ ለተማሪዎች ሥነ ምግባር አሳቢ እየመሰለ በዚያ ለሺሻ ቤት ፈቃድ እየሰጠ የሚጣረስ ነገር በመሥራት ላይ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ ለአንድ ወላጅ ተማሪ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ የነበረው ደስታ ጠፍቶ ልጄ ምን ይገጥመው/ይገጥማት ይሆን በሚል ሥጋት መወጠር ጀምሯል፡፡

ፍረዱ ይህ ለችግሮች መፍትሔ ነው እየተባለ በየቀኑ ኢቲቪ የሚነግረን እውን መፍትሔ ነው? ውርጃን በየክሊኒኩ ማስፋፋትና አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት ለወጣቶቻችን መፍትሔ ነው?

ቀደም ሲልም ግብረሰዶማዊነትን ለማውገዝ የእምነት አባቶች በተነሱ ጊዜ እንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት መከልከላቸውን እናውቃለን፡፡ ይህ ታሪክ ከማጥፋትና ትውልድ ከመሸጥ አይተናነስም፡፡ በመስከረሙ ሥነ ሕዝብና አኅጉራዊ ስብሰባ ላይ ይህንን የተቃወሙ አገሮች አሉ፡፡ እንደ ቻይና ያሉ አገሮችም በጭራሽ እንዳልተቀበሉት ከኢንተርኔት ለማየት ችለናል፡፡ የእኛስ መሪዎች የተቀበሉት በልማት ስም ትውልድን መረን ለመልቀቅ ነው? ስለዚህ በጦርና መሳሪያ ለማንበርከክ/ቅኝ ለመግዛት ያልቻሏትን አገር፣ ዛሬ አንገት የሚያስደፋንን ውሳኔ መሪዎችን እንዳያስተላልፉ ሥጋት አድሮብናል፡፡

እንደ ኢትዮጵያዊና እንደ ወላጅ የነገን ጤናማና ፍሬያማ ትውልድ እንደሚናፍቅ ዜጋ ይህንን ጽፌያለሁ፡፡ ለነገም ትልቅ የማኅበረሰብ ቀውስ ነውና መንግሥታችንም ሆነ የሚመለከተው ክፍል ዛሬ አንድ በሉልን፡፡ የሕግ ያለህ! የፈጣሪ ያለህ!

__

 

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: