Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ግሸን ማርያም’

ፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ ላሊበላን እና ግሸንን በቱርክ ድሮን ለማፈራረስ ዝግጅቱን አጠናቋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 5, 2021

💭 የትግራይ ሠራዊት በዛሬው ዕለት ግሸን ማርያምን እንዲቆጣጠር ተደርጓል!

ይህ “መንኩሴ ነኝ፤ እዘምታለሁ፤ እገድላለሁ ፥ እስካሁን ድረስ በጸሎት ሞክረናል፣ ግን አልተሳላንም እናም አሁን በጥይት እናሸንፋለን” የሚለው ሰው ለዚሁ ለጥፋት ሤራ የተዘጋጀ የእባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ እና “እኅተ አቴቴ” ፕላስቲክ ችግኝ ነው። በጭራሽ መነኩሴ እና ክርስቲያን ሊሆን አይችልም፤ ይህ ወራዳ ትክክለኛ ክርስቲያን ቢሆን ኖሮ ላለፉት ሦስት ዓመታት በኦሮሞዎች ያለማቋረጥ በጅምላ እየተጨፈጨፉና በጅምላ በግሬደር እየተጠረጉ ለሚቀቀበሩት አማራ ክርስቲያኖች እንዲሁም እንደ ችቦ ተቃጥለው የረገፉት ካህናት እና ምዕመናን አሳዛኝ ጉዳይ አሳስቦት አሁን በትግራይ ክርስቲያኖች ላይ ለመዝመት እንዳሳየው ዓይነት ወኔ በማሳየት ” በሁለቱም እዋጋለሁ፤ በጸሎቱ እና ጥይት” ብሎ ወደ ወለጋ እና ጂማ በዘመተ ነበር፤ ግን እርግጠኛ ነኝ እንኳን ለመዝመት አፉንም ከፍቶ ድርጊቱን ለማውገዝ ብቃት የሌለው ግብዝ ነው፤ እስኪ ዲያብሎሳዊ ገጽታውን እንመልከተው። ከዚህ በተጨማሪ ይህን መረጃ ከብዙ ተንኮል አዘል ደስታ ጋር ያቀረበልን የሉሲፈራውያኑ ልሳን ፤ ‘ቢቢሲ’ በቦሌ መድኃኔ ዓለም የክርስቶስን ኃውልት የደመራው እሳት ውስጥ አስገብቶ ያወጣውን ምስል እና እ.አ.አ በ1995 ዓ.ም ላይ በደብረ ዳሞ ገዳም ብዙ ቅርሶችን ያወደመውን እሳት አስመልክቶ የመረጠልንን ምስል ከጉዳዩ ጋር በማገናዘብ እንመለከተው። አዎ! ሕዝበ ክርስቲያኑ እርስበርሱ በመበላላቱ የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ኤዶማውያን እና እስማኤላውያን በደስታ ጮቤ እየረገጡ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ይህን መረጃ ከብዙ ተንኮል አዘል ደስታ ጋር ያቀረበልን የሉሲፈራውያኑ ልሳን ፤ ‘ቢቢሲ’ በቦሌ መድኃኔ ዓለም የክርስቶስን ኃውልት የደመራው እሳት ውስጥ አስገብቶ ያወጣውን ምስል እና እ.አ.አ በ1995 ዓ.ም ላይ በደብረ ዳሞ ገዳም ብዙ ቅርሶችን ያወደመውን እሳት አስመልክቶ የመረጠልንን ምስል ከጉዳዩ ጋር በማገናዘብ እንመለከተው። አዎ! ሕዝበ ክርስቲያኑ እርስበርሱ በመበላላቱ የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ ኤዶማውያን እና እስማኤላውያን በደስታ ጮቤ እየረገጡ ነው።

አይ አማራ! አይ ኦሮሞ! ለእግዚአብሔር አምላክ፣ ለኢትዮጵያ እና ተዋሕዶ ክርስትናዋ ያላችሁ ጥላቻ ይህን ያህል ዘልቋል! 😠😠😠 😢😢😢

😈 ከምንኩስና ወደ ውትድርና – ቤተክርስቲያንን የከፈለው ጦርነት

በላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናቷ በምትታወቀው አገር መስቀልን እና መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ተሸክመው የነበሩ አንድ ኢትዮጵያዊ መነኩሴ፣ በአሁኑ ወቅት አገሪቷን በሚያፈርስ ጦርነት ከትግራይ አማጺያን ጋር ለመዋጋት ጠመንጃን አንስተዋል።

በዚህ ጦርነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንም ተከፋፍላለች።

በሁለቱም እዋጋለሁ፤ በጸሎቱ እና ጥይትይላሉ አባ ገብረማርያም አደራው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ህወሓትን ለመዋጋት ሁሉም አቅም ያለው ኢትዮጵያዊ እንዲዘምት ጥሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ የስማቸው ትርጉጉም የማርያም አገልጋይ የሆነው መነኩሴው አባ ገብረ ማርያም፣ የኢትዮጵያን ሠራዊት ለመቀላቀል ተመዝግበዋል።

በፖለቲካው ተሃድሶው ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር መራራ ቁርሾ መፈጠሩን ተከትሎ በጥቅምት መጨረሻ ጦርነት መቀስቀሱ የሚታወስ ነው።

እሳቸው በሚኖሩበት የአማራ ክልልም ከሚሊሻው አስቀድመው ሥልጠና ማግኘታቸውንም ያስረዳሉ።

በጦርነቱ መቁሰልንም ሆነ ሞትን አልፈራም። ሁሉንም ለመቀበል ዝግጁ ነኝ። ምላክን ብቻ ነው የምፈራውበማለት ያክላሉ።

ጦርነቱ ሲጀመር የአማራ ክልል ኃይሎች በትግራይ ክልል ውስጥ የነበሩ ግዛቶችን በመቆጣጠራቸው ምላሽ በሚመስል ሁኔታ የህወሓት ኃይሎች በነሐሴ ወር በአማራ ክልል በርካታ ቁልፍ ከተሞችን ተቆጣጥረዋል።

ከእነዚህም መካከልም በ12ኛው እና በ13ኛው ክፍለ ዘመን ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍለው የተሰሩትንና በዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የሚገኑባት ላሊበላ ትጠቀሳለች።

በላሊበላ ከ700 በላይ ካህናት ነበሩ፣ አሁን ግን አካባቢው በህወሓት ቁጥጥር ስር በመሆኑ ምክንያት ምንም ዓይነት መሠረታዊ አገልግሎት እያገኙ አይደለም። ደመወዝም እየተከፈላቸው ባለመሆኑ ችግር ውስጥ ናቸውበማለት በጎንደር ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት ምንይችል መሠረት ይናገራሉ።

ቀለሃዎች በቤተ ክርስቲያኗ ተገኝተዋል

በላሊበላ ምንም ዓይነት ጉዳት ባይዘገብም፣ ምንይችል በክልሉ ከሚኙ ሌሎች በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ገንዘብ፣ ምግብ እና ጥንታዊ የብራና ጽሑፎች እንደተዘረፉ፣ ይህም ህወሓት ለሐይማኖታዊ ስፍራዎችና ባህላዊ ቅርሶች ተገቢውን ጥበቃ ሳይሰጥ ሁሉን አቀፍ ጦርነት እያካሄደ መሆኑን አመላክቷልይላሉ

የመንግሥት መገናኛ ብዙኃንም በአምስተኛው ክፍለ ዘመን የተቋቋማው የጨጨሆ መድኃኒዓለም ቤተክርስቲያን ከህወሓት በተተኮሰ ከባድ መሳሪያ ምክንያት ጉዳት እንደደረሰበት ዘግበዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ጉዳት በደረሰበት በጨና ተክለሐይማኖት ወለል ላይ የጥይት ቀለሃዎች መገኘታቸውን አሶሺየትድ ፕሬስ ዘግቧል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በበኩላቸው በነሐሴ ወር መገባደጃ በደረሰ ጥቃት ከተገደሉት በርካታ ሰዎች መካከል ስድስቱ ካህናት መሆናቸውን ይናገራሉ።

በጦርነቱ ውስጥ ተሳታፊ የሆኑ አካላት ብዙ ግፎች መፈጸማቸውን በተደጋጋሚ አስተባብለዋል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን 43 በመቶ የሚሆነውን የአገሪቷን ሕዝብ የሚሸፍኑ ሲሆን፣ ይህም በአገሪቱ ውስጥ ትልቁና ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሐይማኖት አድርጓት ቆይቷል። በአሁኑ ወቅት ጦርነቱ በርካታ ምዕመኑን ከፋፍሏል።

የትግራይ የሐይማኖት አባቶች እንደሚሉት በክልሉ ውስጥ ከጎረቤት ኤርትራ በመጡ ወታደሮች የተደገፈ ወታደራዊ ዘመቻ ያደረገው የኢትዮጵያ መንግሥት ወደ 325 ገደማ የሚሆኑ የሐይማኖት መሪዎች እንዲገደሉ ምክንያት ሆኗል ይላሉ።

አክለውም ከአናሳ ሙስሊም ማህበረሰብ የተወሰኑትን ጨምሮ በጦርነቱ የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ውስጥ በ12 አብያተ ክርስቲያናት እና መስጊዶች ላይ ጥቃት እንደደረሰ ይናገራሉ።

ዐቢይ የሐይማኖትና የመንግሥት መለያየትን ችላ ብለዋል

በሰሜን አሜሪካ ቤተክርስቲያን ስመ ጥር አባል የሆኑት ካናዳዊው ምሁር ጌታቸው አሰፋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ጥቃቶቹ ትግራዋይን ለመስበርእና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና በኤርትራ አጋራቸው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ፊት እንዲንበረከኩየሚደረግ ሙከራ እንደሆነ ያምናሉ።

በትግራይ ተራሮች ላይ 24 ሜትር የተራራ ከፍታ ላይ የተገነባው የ6ኛው ክፍለ ዘመን ደብረ ዳሞ ገዳም፣ የኤርትራ ወታደሮች የጥንታዊ ብራና ጽሁፎችንና ባህላዊ ቅርሶችን ዘረፉ ከተባሉባቸው ቦታዎች አንዱ ነው።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ጦርነቱ በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ ጥልቅ መከፋፈል እንዳስከተለ እና የትግራይ ቅርንጫፍ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የራሱን መንገድበመጓዝ ላይ መሆኑን ይናገራሉ።

በዲያስፖራው በኩል እንኳን ከአሁን በኋላ አብረው መጸለይ የማይፈልጉ አሉ። በኦንታሪዮ [በካናዳ] አንድ ቤተ ክርስቲያን የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተብሎ ተሰይሟል። በአሜሪካ በፊላደልፊያ ውስጥ እንዲሁም በአውስትራሊያ ውስጥ ተመሳሳይ ሁኔታ ተከስቷልይላሉ።

ፕሮፌሰር ጌታቸው እንደሚሉት የጴንጤቆስጤ ክርስቲያን እምነት ተከታይ የሆኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥትና ሐይማኖት የተለያዩ ናቸው ከሚለው መሰረታዊ የኢትዮጵያ ጽንሰ ሃሳብ አፈንግጠዋል።

እሳቸው ጦርነቱን እንደ መንፈሳዊ ውጊያ አድርገው ያቀርቡታል። ጦርነቱን ለማቆም ስላለው ዓለም አቀፍ ግፊት ዐቢይ ሲናገሩ፣ አገሪቱ ኢየሱስ በመስቀል ላይ እንዲጠጣ የተገደደውን መራራ ሃሞት ለመውሰድ ፈቃደኛ እንደሆነች እና በመጨረሻም እናሸንፋለንእያሉ ነውበማለት ያስረዳሉ።

ፕሮፌሰር ጌታቸው አክለውም “ሰዎች ለሰላም መጸለይ ሲገባቸው በሐይማኖታዊ በዓላት ላይ እንኳን ዐቢይ እንደዚህ ያሉ ነገሮችን ይናገራሉ” ብለዋል።

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አማካሪዎች አንዱና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በተለይም በወጣቶች መካከል ብዙ ተከታይ ያላቸው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ህወሓትን መጥፋት ያለባቸው ሰይጣኖችብለዋቸዋል።

እንደነሱ አይነት አረም በዚህች መሬት ላይ ዳግም መፈጠር የለበትምበማለት ዲያቆኑ መናገራቸውን የኤኤኤፍፒ ዘገባ ያመለክታል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው ዲያቆኑ ጓደኛቸው እንደነበሩና ጦርነቱ ከተነሳ በኋላ ብዙም ሳይቆይ መገናኘታቸውን እንዳቆሙ ይናገራሉ።

አክለውም በትግራይ ውስጥ እየተከናወነ ባለው ውስጥ የእሱን ሚና ተገነዘብኩ። የእሱ ትርክት የዘር ማጥፋት ነውይላሉ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት የዲያቆኑን አስተያየት አደገኛእና ጥላቻን ያዘለበማለት ካወገዘ በኋላ ዲያቆን ዳንኤል ንግግራቸው የሚመለከተው የትግራይ ሕዝብን ሳይሆን አሸባሪ ድርጅቱንነው ሲሉ ተናግረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ቃል አቀባይ በትግራይ ደጋፊዎች ዘንድ የተሳሳተ ትርጓሜ እንደነበረ ለኤኤፍፒ ገልጸዋል።

ምንይችል ጥላቻንእና የብሔር ክፍፍልን አስፍኗልበማለት ህወሓትን ለጦርነቱ ተጠያቂ ያደርጋሉ።

ሌላው ቀርቶ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ከቀድሞው የአማራ ነገሥታት ጋር የሚመሳሰል የኢምፔሪያሊዝም ራዕይ እንዳላቸው ሲከሱ ይሰማሉ። ይህም ህወሓት ተጋሩዎችን ወደ ውጊያ ለማነሳሳት የተጠቀመበት ግልጽ የብሔር ፕሮፓጋንዳ ነውይላሉ።

ፕሮፌሰር ጌታቸው በመንግሥትና በህወሓት መካከል የሚደረግ ውይይት ብቻ ጦርነቱን ሊያስቆም እንደሚችል ያምናሉ።

ከጅምላ ግድያ እና ረሃብ በኋላ እነሱ መደራደር አለባቸውየሚሉት ፕሮፌሰሩ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ለድርድር እንዲስማማ ጫናውን እንደሚቀጥል ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

ቀደም ሲል በትግራይ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ መሆኑን የተናገሩት የቤተክርስቲያኒቱ ፓትርያርክም ለሰላም ጥሪ አድርገዋል።

በልብሳችን ላይ የታተመው እና በሰውነታችን ላይ የምንነቀሰው መስቀል ለውበት አይደለም። የመስቀሉ ትርጉም ሰላምና እርቅ እስከሆነ ድረስ ሰላምና እርቅ በመካከላችን እና ከእግዚአብሔር ጋር መጠበቅ አለብንብለዋል አቡነ ማትያስ በቅርቡ በተከበረው የመስቀል በዓል።

ነገር ግን አባ ገብረማሪያም ህወሓትን ለማሸነፍ በጦር ሜዳ ላይ ይቆያሉ።

እስካሁን ድረስ በጸሎት ሞክረናል፣ እናም አሁን በጥይት እናሸንፋለን። የኢትዮጵያን ጠላቶች ቀብረን ኢትዮጵያን አንድ እናደርጋለንብለዋል።

ምንጭ

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰይጣን ጥልቅ ጉድጓድን አስቆፍሮ ፀሐይን (መስቀሉን) ለመሰወር ሞክሮ ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 1, 2020

ነገር ግን ዲያብሎስ ድካሙ ከንቱ ሆኖ ቀረ ፥ ፀሐይን መስወር አይቻልም፤ ፀሐይን ማጥለቅም ማውጣትም የሚቻለው እግዚአብሔርን ብቻ ነው ፥ ስለዚህ ፀሐይን መሰወር እንደማይቻለው ሁሉ፤ ዓለምን ያበራው፣ ጨለማውን ዓለም ያስወገደ እውነተኛው ፀሐይ የተባለ መስቀል ተቆፍሮ ተቀብሮ አልቀረም፤ መስቀል ወጥቷል፣ የምንበላውን የምንጠጣውን አስገኘትቶልናል።

ግሩም ነው፤ ይህ ትምህርት የተሰጠው ዓምና ልክ በዛሬው ዕለት መስከረም ፳፩ / ፪ሺ፲፪ .ም በ እመቤታችን ክብረ በዓል ወቅት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም / ፭ኪሎ አዲስ አበባ ፥ ዓ.ም ነበር።

የሚገርም ነው! ልክ ከዓመት በኋላ በኦሮሚያ ሲዖል ውዳቂዎቹ የዋቄዮ-አላህ ልጆች መስቀሉን ጉድጓድ ቆፍረን እንቀብረዋለን ብለው ዛቱ።

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግራኝ ጂሃድ በቂልጦ ሎዛ ማርያም | የቃየል ልጆች የያዙት መንግስት በቤተክርስቲያን ላይ ለሚፈጽመው ጥቃት እራሱ ተጠያቂ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 28, 2020

ያው ዛሬ ደግሞ ግራኝ አብዮት አህመድ በአባይ ጉዳይ የደረሰበትን ድንጋጤ ለማብረድና ነገሮችን ለማስቀየስ ስልጢ ሙስሊም ወንድሞቹን ዓብያተ ክርስቲያናትን ያጠቁና አባቶችንም ይደበድቡ ዘንድ ቀሰቀሳቸው። በዛሬው ዕለት የሚከበረውን የእመቤታችንን ክብረ በዓል ለማክበር ከአዲስ አበባ ወደ ስልጤ ዞን ቂልጦ ሎዛ ማርያም የሄዱ መርጌቶችና ምዕመናን በስልጤ ፖሊሶችና በስልጤ ወጣቶች መደብደባቸው ተነግሯል። በሚቀጥሉት ሳምንታትም ተመሳሳይ ማስቀየሻና ውሃውን መሙላት አልቻልንምማስባያ ድራማዎችን እንጠብቃለን።

እግዚአብሔር በደመና ውስጥ ኾኖ “ቃየል ቃየል ወንድምኅ አቤል ወዴት ነው?” አለው፡፡ ቃየል ግን በትዕቢት ኾኖ “እኔ ምን አውቃለኹ፤ እኔ የወንድሜ የአቤል ጠባቂው ነኝን?” ሲል መለሰ፡፡ እግዚአብሔርም መልሶ “እንግዲኽ ጠባቂው ካልኾንኅ ስለምን ገደልከው? አኹንም ባለ ዘመን ኹሉ በምድር ኹሉ ላይ ድንጉጥና ተቅበዝባዥ ኹን” በማለት እግዚአብሔር ቃየልን ረገመው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቃየል በጣም ፈሪ፣ ሰዎችን የሚሸሽ፣ የሚጨነቅ፣ ባጠፋው ጥፋት እግዚአብሔርን የሚያፍር ኾኖ ኖረ፡፡

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፰፡፲፩]

ቃየልም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን? አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።

ከማን አፍ ነው ይህን የሰማነው? አዎ! ኢትዮጵያን በቱርክ ባዛር ለመሸጥ ከተቀጠረው፣ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ፀረኢትዮጵያ ዘመቻውን በመጣጧፍ ላይ ከሚገኘውና በግብረሰዶማውያኑ ኢሉሚናቲዎች ከተሸለመው የቃየል ልጅ፤ ከገዳይ አብይ አፍ፦

አላየሁም! አልሰማሁም! እኔ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ነኝን? እኔ ቤተ ክርስቲያን አላቃጠልኩም: ካህናትን አልገደልኩም: ግፍ አልሰራሁም ስለዚህ ይቅርታ አልጠይቅም

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ገዳይ አብይ በጣም ፈሪ፣ ሰዎችን የሚሸሽ፣ ቀጣፊ፣ የሚጨነቅ፣ ባጠፋው ጥፋት እግዚአብሔርን የሚያፍርና ብርሃኑን የሚፈራ ኾኖ ይኖራል። አቤት የእነዚህ የቃየል ልጆች መጨረሻቸው! እነርሱን አያድርገን!

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ብቻ እንጅ የሁሉም አይደለችም!

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ ኤርምያስ | የቃየል ልጆች የያዙት መንግስት በቤተክርስቲያን ላይ ለሚፈጽመው ጥቃት እራሱ ተጠያቂ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 13, 2019

ከ ፫ ሚልዮን ምዕመናን በላይ በተገኙበት በግሸን ደብረ ከርቤ ክብረ በዓል ላይ የሰሜን ወሎ ዞን ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤርምያስ ትምህርት ሲሰጡ፦

ቤተ ክርስቲያን ተደፍራለች ፤ምእመናን ታርደዋል፡፡ እንደ ዘርዐ ያዕቆብ አይነት መሪ በመጥፋቱ አሁን ችግር ነው፡፡ ወንጌሉን እኛ እናስተምራለን፤ የሚያምጹትን መንግሥት መቅጣት ይገባዋል፡፡ እንግዳ ተቀብላ ወርቅ አበድራ መልሷ ግን ጠጠር ተመለሰላት፣ የኢህዴግ መንግስት ሊያስብበት ይገባል፡፡ የስም መለዋወጥ ሀገር አይለውጥም፤”እኔ የአቤል ጠባቂ ነኝ” ማለት አያዋጣም፡፡ መንግስት ስሙን እንጅ ግብሩን አልቀየረም፤ ዶክተር አቢይ ይህንን ቢያስተካክል ይሻላል የመንግስት አካል በጀት በጅቶ እቅድ አውጥቶ ፕሮግራም ነድፎ ቤተክርስቲያን እንድትቃጠል ንዋያተ ቅድስቱ እንዲነዱ ምዕመናን እንዲታረዱ ማድረግ፡ ቃየል አቤልን ገድሎ እግዚአብሔር ሲጠይቀው፤ እኔ የአቤል ጠባቂው ነኝ ማለቱ አላዳነውምና መንግስት ሊያስበት ይገባል ሲሉ እሳስበዋል። ምክርና ስብከት በቂ አይደለም፤ ስብከቱንም ማስተማሩንም ለእኛ ተውልን፤ እኛ እናከናውነዋለን። “ዛሬ እንደ ዘርዐ ያዕቆብ ያለ መሪ በማጣት ቤተክርስቲያን ችግር ላይ ናት” ካሉ በኋላም አባታችን አያይዘውም “ሶማሊያ ላይ የታረደው ገብረማርያም ማን ሊጠየቅበት ነው?” ይሉና “ካልሆነ ጠንከር ያለ ፓርቲ አዘጋጅቶ ማስረከብ ይሻላል!” ሲሉም ጠቁመዋል። “የገቢያ ግርግር ለብዙ ቀጣፊዎች ጠቅሟቸዋል፣ መንግሥት የያዘውን አካሄድ እንዲያስተካክልና ሕዝበ ክርስቲያኑ ኢትዮጵያን ደኅንነቷን ጠብቆ ለትውልድ የማስተላለፍ አደራውን እንዲወጣ፣ በቤተ ክርስቲያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ጥቃትም መንግሥት ሕግን ባለማስከበሩ የመጣ መሆኑን

በማሳወቅ ኃይለኛ መልዕክት አስተላልፈዋል።

እግዚአብሔር በደመና ውስጥ ኾኖ “ቃየል ቃየል ወንድምኅ አቤል ወዴት ነው?” አለው፡፡ ቃየል ግን በትዕቢት ኾኖ “እኔ ምን አውቃለኹ፤ እኔ የወንድሜ የአቤል ጠባቂው ነኝን?” ሲል መለሰ፡፡ እግዚአብሔርም መልሶ “እንግዲኽ ጠባቂው ካልኾንኅ ስለምን ገደልከው? አኹንም ባለ ዘመን ኹሉ በምድር ኹሉ ላይ ድንጉጥና ተቅበዝባዥ ኹን” በማለት እግዚአብሔር ቃየልን ረገመው፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ቃየል በጣም ፈሪ፣ ሰዎችን የሚሸሽ፣ የሚጨነቅ፣ ባጠፋው ጥፋት እግዚአብሔርን የሚያፍር ኾኖ ኖረ፡፡

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፬፥፰፡፲፩]

ቃየልም ወንድሙን አቤልን። ና ወደ ሜዳ እንሂድ አለው። በሜዳም ሳሉ ቃየል በወንድሙ በአቤል ላይ ተነሣበት፥ ገደለውም። እግዚአብሔርም ቃየልን አለው። ወንድምህ አቤል ወዴት ነው? እርሱም አለ። አላውቅም፤ የወንድሜ ጠባቂው እኔ ነኝን?አለውም። ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።

ከማን አፍ ነው ይህን የሰማነው? አዎ! ኢትዮጵያን በቱርክ ባዛር ለመሸጥ ከተቀጠረው፣ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ፀረኢትዮጵያ ዘመቻውን በመጣጧፍ ላይ ከሚገኘውና በግብረሰዶማውያኑ ኢሉሚናቲዎች ከተሸለመው የቃየል ልጅ፤ ከገዳይ አብይ አፍ፦

አላየሁም! አልሰማሁም! እኔ የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ ነኝን? እኔ ቤተ ክርስቲያን አላቃጠልኩም: ካህናትን አልገደልኩም: ግፍ አልሰራሁም ስለዚህ ይቅርታ አልጠይቅም

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ገዳይ አብይ በጣም ፈሪ፣ ሰዎችን የሚሸሽ፣ ቀጣፊ፣ የሚጨነቅ፣ ባጠፋው ጥፋት እግዚአብሔርን የሚያፍርና ብርሃኑን የሚፈራ ኾኖ ይኖራል። አቤት የእነዚህ የቃየል ልጆች መጨረሻቸው! እነርሱን አያድርገን!

ኢትዮጵያ የኢትዮጵያውያን ብቻ እንጅ የሁሉም አይደለችም!

___________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: