ይህን የአንበሳ ግልገል ሳይ የደምቢዶሎ እህቶቻችን ናቸው ብልጭ ብለው የታዩኝ።
እህቶቻችን የታገቱት በአላጋጩ እና ተሳላቂው አብዮት አህመድ ነው። 100%። ያው እያያችሁት ነው፤ የም ዕራባውያኑን ርካሽ የስነ–ልቦና ጨዋታ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ በሙከራ መልክ ለማዋል አማካሪዎቹ እነ ዶ/ር ወዳጄነህ የሰጡትን “አበባ” በማንሳት (ችግኙ አበበ) የታገቱትን ሕፃናትና እናቶች ሰቆቃ ለማረሳሳት፣ የሕዝቡን ቁጣ ለማቀዝቀዝ ሞክሯል። ይህ ጨካኝና አላጋጭ ግለሰብ ለሁለት ወራት ያህል ኢትዮጵያውያን ዝም ማለታቸውን ዝም ብሎ በመታዘብ ከቆየ በኋላ አሁን “አሉታዊውን” “በአዎንታዊ” የመተካት የስነ–ልቦናዊ ሙከራዎች በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ለማካሄድ በመድፈር ላይ ነው። “ምንም አታመጡም!” ነው ጨዋታው።
“ኢትዮጵያዊ ነኝ” የሚል ሁሉ ያለምንም ቅድመ ዝግጅት ወደ አራት ኪሎ በማምራት ይህ ወራዳ ከምኒሊክ ቤተ መንግሥት እስካልወጣ ድረስ የግቢውን አጥር በቁጣ መነቅነቅ ይኖርበታል።