Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • October 2022
  M T W T F S S
   12
  3456789
  10111213141516
  17181920212223
  24252627282930
  31  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጋብቻ’

ረሀብ በአረብ አገር | የሦስት ዓመት ሕፃናት ሴቶች ለጋብቻ በመዳረግ ላይ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 6, 2019

በቦምብ የሚጨፈጭፋቸው የራሳቸው ወንድሞች የሆኑት ሳውዲዎች ናቸው…. እንግዲህ ኢስላም ይህ ነው! አቤት ቅሌት፤ እግዚኦ! እንዴት ይቀፋል። ለዘመናት ስንራብና ስንጠማ የነበርን ኢትዮጵያውያን እንሞታታለን እንጂ እንደ ነጮችና እንደ አረብ ሙስሊሞች ይህን ያህል ሰውን እስከ መብላት ወይም ሕፃናትን ለዚህ ዓይነት አጸያፊ ተግባር እስከማጋለጥ አልደረስንም። ልዩነቱን እይየን ነው?


Yemeni Girls As Young As Three Married Off For Food


With the bloody conflict in Yemen raging on, desperate parents choose to make their daughters child brides, feeling it is the only way to let other relatives survive the famine and destruction on the ground, Oxfam told RT.

The “man-made humanitarian catastrophe” caused by the brutal civil war in Yemen forced some parents to sell off their daughters, some as young as three years old, in hopes that the dowry bride will keep the rest of the family alive, international charity Oxfam reported.

The relatives planned to use the money, paid for the child brides, to buy food and shelter.

They think this is the only way” to stay alive, Oxfam’s director for Yemen, Muhsin Siddiquey, told RT. “They can bring the dowry, and that can protect the whole family and other extended members.”

Overall, “10 million are just on the brink of famine” in Yemen, he said, adding that the four years of war also sparked “the worst cholera crisis in the century.”

If the humanitarian assistance is not provided timely” and the food supply becomes “nonfunctional even for a day… there will be much more catastrophic situations,” Siddiquey stressed.

The conflict in Yemen, exacerbated by the Saudi-led intervention in 2015, placed a heavy toll on the civilian population, with 400,000 children suffering from “life-threatening” malnutrition, according to the UN figures.

Housing also remains an acute problem since much of homes were demolished by deadly air raids.

Source

_________

Posted in Curiosity, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግብጽ | ሙስሊሟ ተማሪ “ላግባሽ!” ብሎ የጠየቃትን እጮኛዋን በማቀፏ ከዩኒቨርሲቲ ተባረረች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 14, 2019

..2009 . ወስላታው ባራክ ሁሴን ኦባማ ለሙስሊሙ ዓለም ንግግር ያሰማበት ታዋቂው የግብፅ አልአዝሃር ዩኒቨርሲቲ፡ ተማሪዋ ሴት ላግባሽ ብሎ አበባ የስጣትን እጮኛዋን በማቀፏ ከዩኒቨርሲቲው አባርሯታል። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህ ቪዲዮ በመታየቱ ነው ዩኒቨርሲቲው እዚህ አወዛጋቢ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የደፈረው። ቪዲዮው የትምህርት ቤቱን መልካም ስም ያጎድፋል፤ ሙስሊሞች መተቀቃፍ የለባቸውምብሎ በመግለጽ ተማሪዋን ለማባረር መገደዳቸውን የዩኒቨርሲቲው መስተዳደር አስታውቋል።

በ ቪዲዮ ላይ አንድ ወጣት እቅፍ አበባ በመያዝ የጋብቻ ጥያቄን እንደማቅረብ በሚመስል መልክ ወጣት ሴቷን በደስታ ሲያቅፋት ይታያል።

______

Posted in Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

የቅዱስ ሚካኤል ልጆች ሰርግ | ክርስቶስ ኢየሱስ በጋብቻው ሥነ ሥርዓት ላይ እንዲገኝልህ ጥራው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 21, 2018

እንኳን ለኅዳር ሚካኤል አደረሰን!

ሰርግ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ጳውሎስ ለቈላስይስ ሰዎች በላከው መልእክት ም.፬፥፲፪ ላይ ያለውን ኃይለ ቃል በተረጎመበት ፲፪ኛው ድርሳኑ በዘመኑ የሚፈጸመውን የሰርግ ሥርዐት መሠረት በማድረግ ሰርግን አስመልክቶ ሰፋ ያለ ትምህርትን ሰጥቶአል ። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በሰርግ ምክንያት የሚወጡትን ወጪዎችና ግርግርና ሁካታ አጥብቆ የሚቃወም አባት ነው። በዚህም ጽሑፍ ይህን ወደማስተዋል ልንመጣም እንችላልን ። መልካም ንባብ!

ስለዚህ እንዲህ ብሎ ያስተምራል ፡ትዳር ምንድን ነው? ትዕይንት(ትያትር) ነውን ? አይደለም። ምንም እንኳ እናንተ ለትዳርና ለምሳሌው አክብሮት ባይኖራችሁ ትዳር ግሩም ምሥጢርና የታላቅ መንፈሳዊ ምሥጢር ምሳሌ ነው ። ቅዱስ ጳውሎስ ስለዚህ ሲያስተምር “ይህ ምሥጢር ታላቅ ነው” ይልና ጨምሮ “እኔ ግን ስለ ክርስቶስና ስለ ቤተ ክርስቲያን እላለሁ” ይላል። (ኤፌ.፭፥፴፪) ጋብቻ የቤተ ክርስቲያንና የክርስቶስ ምሳሌ ነው ፤ እንዲህ በከበረ ምሥጢር ላይ ዳንኪረኞችን በመጋበዝ ዝሙትን ታስተዋውቁበታላችሁን ? ነገር ግን ከእናንተ መካከል አንዱ እኔን፡እንዲህ ስትል ደናግል ወይም ያገቡት አይጨፍሩ እያልክ ነው ፤ እንግዲያ እነርሱ በዚህ ሰርግ ላይ ካልጨፈሩ ማን ሊጨፍር ነው ? ብሎ ሊጠይቅ ይችላል ። ማንም አይጨፍር ነው መልሴ።

በአሕዛብ ዘንድ ይህን በመሰሉ ሥርዐቶቻቸው ዳንኪረኞች ዳንኪራቸውን ያቀርባሉ። በእኛ ግን ማንኛውም ምሥጢራት ሲከናወኑ በጸጥታ፣ በትሕትናና በጥሩ ሥነምግባር እንዲሁም በመልካም ሥርዐት ነው። ይህ የጋብቻ ሥርዐት አመንዝሮች ከተጠሩበት እግዚብሔርን የማይፈሩ ከተጋበዙበት እንዴት ብለን ነው መንፈሳዊ ጋብቻ ብለን ልንጠራው የምንችለው ? እንዲህ ከሆነ እንዴት ተብሎ ነው ሁለቱ አካላት አንድ ሆነዋል ልንል የምንችለው ?

ክርስቶስ በተገኘበት ጋብቻ ግን ዳንኪራ የለም የእምቢልታም ድምፅ አይሰማበትም። ነገር ግን ግሩም የሆነ ጸጥታ የሰፈነበት፣ በታላቅ መንፈሳዊ ሥርዐት የሚከናወን ነው። በዚህ ሥርዐት አንድ አካል ወደመሆን ሲመጡ አንድነታቸው ሕይወት አልባ ፍጥረታት እንደሚኖራቸው አንድነት ወይም በዚህ ምድር የሚታየውን ዓይነት አንድነት አይደለም። ነገር ግን የእግዚአብሔር አርዓያና አምሳል ሆነው አንድ ይሆናሉ። ይህ ታላቅ የሆነ ምሥጢር በሚከናወንበት ሥፍራ እንደ አራዊት ታላቅ ሁካታና ረብሻ እንዲሁም ነፍስን የሚያሳድፉ ታላቅ የሆነ በደል ይፈጸማልን?

ሁለቱ አንድ አካል በመሆናቸው በዚህ ያለውን የፍቅርን ምሥጢር አስተውል። እነዚህ ሁለት አካላት ሁለትነታቸውን ይዘው የሚቀጥሉ ከሆነ ብዙ ሊሆኑ አይችሉም። ነገር ግን አንድ ወደመሆን ሲመጡ ብዙዎች ይሆናሉ። ከዚህ ምን እንማራለን ? የትዳርን ታላቅነት አይደለምን ? ሥላሴ ሁለት የሆነው አካል አንድ አድርጎ ፈጠረው ስሙንም ሰው አለው። ይህን አንድ የሆነው አካልንም ሁለት በማድረግ ገለጠው ። ምንም እንኳ እነዚህ አካላት ሁለት ቢሆኑ የእግዚአብሔር ፈቃድ ግን አንድ ይሆኑ ዘንድ ነበር ።

በዚህም ምክንያት አንዱ አምሳሉን ለመውለድ ብቻውን ብቁ እንዲሆን አላደረገውም ። ስለዚህ ከተቃራኒው አካል ጋር አንድነትን ላልመሠረተ ሰው አንድ አካል የሚባለው ስያሜው አይሰጠውም ነገር ግን የሌላኛው ግማሽ አካል ይባላል። ለዚህም ምስክሩ ልጅን መውለድ አለመቻሉ ነው። ይህ እግዚአብሔር አስቀድሞ የሠራው ሥርዐት ነው። የጋብቻን ምሥጢር አስተዋላችሁን ? አስቀድሞ አንድ አድርጎ ፈጠራቸው በኋላም ነጣጠላቸው ፤ እንደገና ሁለት የነበሩትን እነዚህን ወገኖች ወደ አንድነት አመጣቸው ። እንዲህም አድርጎ ስለሠራው ሰው በትዳር አንድ ከሆኑ ወገኖች እንዲፈጠር ሆነ ።

ባልና ሚስት ሁለት አካላት አይደሉም ነገር ግን አንድ አካል ናቸው ።…. ይህን “ሰውን በአርዓያችንና በአምሳላችን እንፍጠር …ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ.127) በሚለው ቃል ማረጋገጥ ይቻላል። ባል ራስ ነው ፤ ሚስት ደግሞ ቀሪው አካል ናት ። ስለዚህ አንዱ የደቀመዝሙርነት ማዕረግ ሲኖረው አንዱ የመምህርነት ቦታ ይይዛል አንዱ መሪ ሲሆን ሌላው ደግሞ ታዛዥ አደረገው። ሔዋን ከአዳም ጎን ትገኝ እንጂ ወደ ኋላ መለስ ብለን የእርሱዋን ልደት ስንመረምረው አንድ አካል እንደነበሩ ማስተዋል እንችላለን። በዚህ ምክንያት አንድ አካል እንደሆኑ ለማስረዳት ሲል እግዚአብሔር አምላክ ሴቲቱን ረዳት አላት። (ዘፍ.218) በአንድነት ከመኖራቸውና አባትና እናት ከመሆን ባለፈ አንድ አካል በማድረግ አከበራቸው። (ዘፍ.224)

በሌላ መልኩ ደግሞ አባት ወንድ ልጁ ወይም ሴት ልጁ የራሳቸውን አካል አግኝተው በመጣመራቸው እጅግ ደስ ይሰኛል። አባት ምንም ሀብት የተረፈው ባለጠጋ ቢሆን ወንድ ልጁ ወይም ሴት ልጁ ያላገቡ ከሆኑ ውስጡ ምንም ዓይነት መረጋጋት አይኖረውም። ይህን ታግሶ መኖርም አይቻለውም። በሌላ በኩል ደግሞ ምንም ልጅ ከእናቱ አካል ተከፍሎ የተወለደ ቢሆን በዚህ ምድር ዘሩ እንዲቀጥል ብቻውን በቂ አይደለም። ስለዚህም በራሱ ሙሉ አይደለም ማለት ነው። ስለዚህም ነቢዩ ሚልክያስ “እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድን ነው? ዘር አይደለምን? (ሚል.፪፥፲፭) ይለናል።

እንዴት ነው ታዲያ አንድ ሥጋ ወደ መሆን የሚመጡት? እጅግ ንጹሕ የሆነን ወርቅን ማግኘት ከፈለግህ ወርቅህን ከሌላ ወርቅ ጋር ትቀይጠዋለህ፤ ከእነዚህም አንድነት ልዩ የሆነ ወርቅ ይገኛል። በዚሁ መልክ እናት በደስታ ዘርን ተቀብላ ከራሱዋ ጋር በማዋሐድ፣ ፅንሱን በመመገብና እንክብካቤ በማድረግ ሰው ሆኖ ወደዚህ ዓለም እንዲመጣ የራሱዋን ድርሻ ትወጣለች።ልጅ እንደ ድልድይ ነው ። በእርሱም ምክንያት ሦስቱ አንድ ሥጋ ይባላሉ ። ልጅ ሁለቱ አካላት ፍጹም አንድ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል ። በመካከላቸው ባለው ታላቅ ወንዝ ምክንያት የተለያዩ ከተሞች በወንዙ ላይ በሚሠራው ድልድይ ምክንያት ሁለት መሆናቸው ቀርቶ አንድ እንዲሆኑ እንዲሁም ልጅም እንዲህ ነው ።

ልጅ በፊት በባልና በሚስት መካከል የተፈጠረውን አንድነት ይበልጥ ያጠናክረዋል። ለባልና ሚስት ድልድይ የሆነው ልጅ የሁለቱ ተዋሕዶ ውጤት ነውና ። ራስና ቀሪው አካል በአንገት አንድ እንዲሆን ፣ እንዲሁ ልጅም በባልና በሚስት መካከል ሆኖ በእነርሱ መካከል ያለውን አንድነት ይበልጥ ያጠብቀዋል ። ከልዩነታቸው ይልቅ አንድነታቸውን በልጅ ምክንያት ይበልጥ እየጠበቀ ይመጣል ።

እንዲሁም ዘማርያን በአንድነት ሲዘምሩ ዝማሬው አንድ ሆኖ ይወጣል። ወይም ሁለት ወገኖች እጃቸውን እርስ በእርሳቸው ቢያቆላልፉ ከእንግዲህ አንድ እንጂ ሁለት አይደለንም ማለታቸው እንደሆነ እንዲሁ ባልና ሚስትም በአንድነታቸው በሚፈጠሩት በልጅ በኩል ፍጹም የሆነ አንድነትን ይመሠርታሉ ። ስለዚህ ጌታችን ግሩም በሆነ ቃሉ “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ አለ” በተለይ በልጆቻቸው። እንዲህ ሲባል ባልና ሚስት ልጅ ካልወለዱ ሁለት እንደሆኑ አይቀጥሉም ማለት ነውን ? በፍጹም አይደለም ፤ ሁለቱ በሥጋ ሲተባበሩ አንድ አካል ወደ መሆን ይመጣሉ ። የሽቶ ዘይትን ከሌላ የሽቶ ዘይት ጋር ሲደባልቁት አንድ እንዲሆኑ ከተቀየጡም በኋላ አንድ የሽቶ ዘይት እንዲሆኑ እንዲሁ በዚህም እንዲሁ ነው ።

እኔ አሁን እንዲህ በግልጽ ስለዚህ ጉዳይ በመናገሬ አንዳንዶች ነውር ነው በማለት ትምህርቴን እንደሚጠየፉት እረዳለሁ። ለዚህ ምክንያቱ ምንድነው? ይህን አሁን የምናገረውን እንደ ብልግና ንግግር ስለሚቆጥሩት ነው። እነዚህ ወገኖች በትዳር ውስጥ የሚፈጠረውን እንደዚህ ላለው አንድነት ልዩ የነቀፋ ስም ይሰጡታል (ብልግና ይሉታል)። ነገር ግን ቅዱስ ጳውሎስ “መጋባት በሁሉ ዘንድ ክቡር መኝታውም ንጹሕ ይሁን”(ዕብ.፲፫፥፬) ብሎ አስተምሮናል።

ስለምን እናንተ ክቡር የሆነውን እንደ ነውር ፣ ንጹሕ የሆነውን እንደ ርኩስ ትቆጥሩታላችሁ ? ይህ ጋብቻን እንደ ርኩሰት የሚቆጥሩትና በራሳቸው አካል ላይ ዝሙትን የሚፈጽሙ የከሃድያን አመለካከት ነው። ስለዚህም ነው ይህን ክፉ አስተሳሰብ ለማጥራትና ወደ ቀድሞው ክብሩ ለመመለስ ስል በዚህ መልክ ያስተማርኩት። በዚህም እስተምህሮ የከሃድያን አፍ ይዘጋል።

እነርሱ የእግዚአብሔርን ድንቅ ስጦታንና የልደታችን መሠረት የሆነውን ተራክቦን ሲነቅፉት ይሰማሉ።

ይህን የመገኛችን ምንጭ የሆነውን ተራክቦ እንደ ቆሻሻና እንደማይጠቅም ረብ የለሽ ከንቱ ነገር አድርገው ይቆጥሩታል። ስለዚህ እኛ ይህን አስተምህሮ ከዚህ ዓይነት አመለካከት ንጹሕ ልናደርገው ይገባናል።ተወዳጆች ሆይ ይህ ጉዳይ ሲነሣ እንደሚጠየፉት ከሃዲያን እንድንሆን አልሻም፤ ይልቁንስ ከእነርሱ አጸያፊ ሥራ ትሸሹ ዘንድ እመክራችኋለሁ። ነገር ግን በዚህ እነርሱን የምትመስሉዋቸው ከሆነ በቀጥታ እግዚአብሔርን እየተሳደባችሁ ነው።

ትዳር ለቤተ ክርስቲያን የተፈጸመላት ምሥጢር ምሳሌ እንደሆነ ላስረዳችሁን? ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንን የራሱ ሲያደርጋትና በመንፈሳዊ ተዋሕዶ ከእርሱዋ ጋር አንድ ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ “እንደ ንጽሕት ድንግል” ይልና “እናንተን ለክርስቶስ ላቀርብ ለአንድ ወንድ አጭቻችኋለውና” ይለናል። (፪ቆሮ.፲፪፥፪) ታዲያ እኛ ምን ሆንን? የእርሱ የአካል ሕዋሳቶችና “ሥጋው” ሆንን። ይህን ሁሉ በማስተዋል ታላቅ ምሥጢር የሆነውን ትዳርን ከማቃለል እንቆጠብ። ሰርግ ማለት የክርስቶስ በሰዎች መካከል ሰለመገኘቱ የሚመሰልበት ታላቅ ምሥጢር ነው። ታላቅ የሆነው ይህ ምሥጢር በሚፈጸምበት ቦታ ስካር የሚገባ ነውን? ንገረኝ የንጉሥ ምስል በቆመበት ስፍራ ሆነህ እርሱን ማዋረድ ትጀምራለህን? ይህን ፈጽሞ አታደርገውም።

አሁን ግን ሰርግ ሲሲረግ ሰርጉ ለተመሰለበት ምሳሌ ተገቢውን አክብሮት ከመስጠት ይልቅ ቦታውን የኃጢአት መፍለቂያ ምንጭ አድርገነዋል። ሥርዐቱ ሙሉ ለሙሉ ተለውጦ ሕገወጥ ሥራዎች የሚፈጸሙት ሥርዐት ሆኗል። ቅዱስ ጳውሎስ “የሚያሳፍር ነገርም የስንፍና ንግግርም ወይም ዋዛ የማይገቡ ናቸው” አላለንምን? እንዲሁም “ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ።” (ኤፌ.፭፥፬፤፬፥፳፱) ብሎ አላስተማረንምን? አሁን ግን በዚህ ታላቅ በሆነ ምሥጢር ላይ የስንፍና ንግግር፣ ዋዛ ፈዛዛ ነገሮች፣ ፌዝና ቀልዶች ሞልተውበታል።

እነዚህ ከንቱ ነገሮች በቀላሉ የሚቀርቡም አይደሉም እኮ እነዚህ ከንቱ ነገሮች እንደ ጥበብ ተቆጥረው በአቅራቢዎቻቸው ተቀናብረው በሰርጉ ለታደሙት ይቀርባሉ። ይህንንም ለሚያቀርቡ ሰዎችም ታላቅ ክብርና ምስጋና ይሰጣቸዋል። ይገርማል ኃጢአት እንደ ጥበብ ተቆጠረ። ከዚህም በላይ ኃጢአትን ለእኛ የሚያስተዋውቁንን ወገኖች ትዕይንት የምንከታተለው ትኩረት ሰጥተንና በጸጥታ ነው፤ ከአንደበታቸው የሚያወጡትንም ቃል በአጽንዖት በመስማት ጭምር እንጂ እንዲያው በከንቱ አናዳምጣቸውም። ስለዚህ ዲያብሎስ በዚህ የሰርግ ቤት ለእርሱ ወታደሮች ይሆኑ ዘንድ ሠራዊቶችን ይመለምላል። ስካር ባለበት ቦታ ዝሙት አለ። ከንቱ ንግግር ባለበት ቦታ ሰይጣን የራሱን አስተዋጽኦ ለማድረግ ይመቸዋል። እስቲ ንገረኝ እንዲህ በሆነ ቦታ ሰይጣን እንዲገኝ እየጋበዝህ ክርስቶስ የሚገኝበትን ምሥጢር እየፈጸምኩ ነው ትላለህን?

አንተ እኔን ለዚህ ነገር ጠንካራ ተቃዋሚ እንደሆንኩ አድርገህ ትቆጥረኛለህ። ከዚህ ጥመትህ ትድን ዘንድ አንተን በጽኑ የሚገሥጽህንም ሰው እንዲህ እንድትመለከተው አውቃለሁ። ቅዱስ ጳውሎስ አንተን “የምትበሉም የምትጠጡም ብትሆኑ ወይም ማናቸውም ተግባር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት”(፩ቆሮ.፲፥፴፩) አላለህምን ? አንተ ግን ሥራዎችህን ሁሉን ራስህን ለማዋረድና የሰውን ልጅ ለሚጎዱ ነገሮች ታውላዋለህ ። ነቢዩስ “ለእግዚአብሔር በፍርሃት ተገዙ በረዓድም ደስ ይበላችሁ”(መዝ.፪፥፲፩) አላለህምን ? አንተ ግን ሥርዐት አልባ ሆነህ ትመላለሳለህ ።

በአንድ ጊዜ ደስታውንና ጥንቃቄውንም ማስኬድ ትፈልጋላችሁን? አጥንትን የሚያለመልም መዝሙርን መስማትስ ትሻላችሁን? በእርግጥ ከመዝሙሮች ሁሉ የሚልቅ መዝሙርን ልትሰሙ ትችላላችሁ። እናንተ ግን አትፈቅዱም፤ ብትፈቅዱ ግን ሰይጣናዊ ዘፈኖች ከመስማት ይልቅ መንፈሳዊ ዝማሬን ለመስማት ትበቃላችሁ። የመዘምራንን ግሩም የሆነ መጓደድ መመልከት ትሻላችሁ? እነሆ የመላእክት ዝማሬና መጓደድ። እንዴት ሆኖ ነው የእነርሱን ዝማሬን መስማት በልዑል ፊት መጓደዳቸው መመልከት የሚቻለው ብሎ የሚጠይቀኝ ካለ “እነዚህን ግሳንግሶችን ከነአካቴው ከተውክና በሰርግህ ክርስቶስ እንዲገኝ ከፈቀድክ ይህ ይሆናል። ክርስቶስ በሰርግህ የታደመ ከሆነ መላእክትም ከእርሱ ጋር በሰርግህ ይገኙልሃል።

ከአንተ ዘንድ ፈቃዱ ካለ እርሱ በአንተ ሰርግ መገኘት ብቻ አይደለም ውኃውን ወደ ወይን ጠጅነት በመቀየርም ሰርግህን ያደምቅልሃል። እንደ ውኃ ቀዝቃዛና ወራጅ የሆነውን የዚህን ዓለም ደስታና ፈንጠዝያ አጥፍቶ መንፈሳዊ ደስታን ከሚያጎናጽፈው ከዚህ ተአምር በላይ ምን ድንቅ ተአምር አለ!! ይህ ነው ውኃውን ወደ ወይንነት የመቀየሩ ትርጉም። እንቢልታ ነፊዎች ባሉበት ክርስቶስ ፈጽሞ አይገኝም። እርሱ በዚህ ሰርግ ቢገኝ እንኳ መጀመሪያ ይህንን አስወግዶ ነው። ከዚያም የራሱን ተአምርን ይፈጽማል። ከዚህ የሰይጣን መሳሪያ ከሆነ እቢልታ በላይ ምን የሚጠላ ነገር አለ? ሁሉ በሥርዐት ካልሆነ ምንም ነገር ያለጥቅም ይሆናል። ድካማችን ሁሉ ያለፍሬ ይቀራል እኛንም ወደ ውርደት ይጥለናል።

ከመልካም ሥነምግባር የበለጠ አስደሳች ነገር የለም፣ ሥርዐት ወዳድ ከመሆን የበለጠ ጣፋጭ የሆነ ነገር የለም፣ ጽድቅ ለመፈጸም ቆራጥ ከመሆን የበለጠ ተወዳጅ ነገር የለም። ሁሉም ሥርዐቶቻችን ልክ እኔ ስለጋብቻ ሥነ ሥርዐት ባስተማርኩት መልክ ይሁኑ። እንዲህ ከሆነ ደስተኛ ልንሆን እንችላለን።

ነገር ግን ጋብቻን ሊያደርግ የሚሻ ሰው ከማን ጋር ጋብቻውን መፈጸም እንዳለበት ይጠንቀቅ። ሴት ልጅ ያለችው ሰው አስቀድሞ እውነተኛና እርሱዋን ሊንከባከባት የሚችል ባልን ሊፈልግላት ይገባል። እንዲህ ዓይነት ወንድ ለአካል ራስ እንዲሆን ሊመረጥ ይገባዋል። ለእርሱ ስትሰጥም እንደ ባሪያ አድርጎ ሊይዛት ሳይሆን እንደ ልጁ ሊያያት ሊሆን ይገባል።

ሀብት ስላለው ወይም ከከበረ ቤተሰብ በመሆኑ ወይም ሰፊ ግዛት ስላለው እርሱን ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ አትምረጡ። ነገር ግን በነፍሱ ትሑት፣ አስተዋይ፣ ቅንነት ያለውና እግዚአብሔርን የሚፈራ የሆነን ሰው ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ ምረጡ። እንዲህ ከሆነ የምታፈቅሩዋት ልጃችሁ በደስታ ልትኖር ትችላለች። ባለጠጋ ሆኖ በምግባሩ ግን ብልሹ የሆነን ሰው ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ ያጫችሁት ከሆነ እርሱዋን አለመጥቀማችሁ ብቻ ሳይሆን እርሱዋን ነጻ ሰው ከማድረግ ይልቅ የእርሱ ባሪያ በማድረግ ትጎዱአታላችሁ። ልጃችሁ የእርሱ ሚስት በመሆኑዋ ምክንያት በምታገኛቸው ሀብት ደስ ከመሰኘት ይልቅ እርሱዋን እንደ ባሪያ ቆጥሮ በእርሱዋ ላይ የሚያደርስባት በደል የከፋ ይሆናል።

እንዲህ ዓይነት ድርጊትን ከመፈጸም ትቆጠቡ ዘንድ እለምናችኋለሁ። ነገር ግን ከእርሱዋ ጋር ተቀራራቢ ኑሮ ያለውን ለልጃችሁ ባል ይሆን ዘንድ ታጩ ዘንድ እመክራችኋለሁ። ይህ ባይሆን ምንም ሀብት ለሌለው ነገር ግን በጎ ሕሊና ላለው ሰው ትድሩዋት ዘንድ አሳስባችኋለሁ። እንዲህ በማድረጋችሁ ልጃችሁን ሌላው ቢቀር ለአንድ ጌታ ልጃችሁን እንደባሪያ ከመሸጥ ተቆጥባችሁ በትክክለኛው ትርጉም እንደ ባል ሊሆናት ለሚችል ሰው መስጠት ይቻላችኋል ።

ለልጅህ ባል የሚሆናትን ጥሩ ሥነ ምግባር የተላበሰውን ሰው በጥንቃቄ መርምረህ በማግኘት ልትድራት ስትዘጋጅ ክርስቶስ ኢየሱስ በጋብቻው ሥነ ሥርዐት ላይ እንዲገኝልህ ጥራው። በዚህ የደስታ ቀንህ እርሱን በእንግድነት እንዲገኝ ስለጋበዝከው ቅር አይሰኝም። ምክንያቱም እርሱ የሚገኝበት ምሥጢር ነውና። አዎን ከዚሀ ይልቅ ግን አስቀድመህ ለልጅህ ባል አድርገህ ያጨኸውን ሰው እርሱ እግዚአብሔር ተወዳጅ ባል ያደርገው ዘንድ ለምነው።

የአብርሃም ባሪያ እንኳ ያላደረገውን አስከፊ ድርጊት ከማድረግ ግን ራስህን ጠብቅ። እርሱ በጌታው በአብርሃም በተላከ ጊዜ እግዚአብሔርን መንገዱን ያቀናለት ዘንድ ለምኖት ነበር። እንዲህ በማድረጉም ሁሉን ነገር ሰመረለት። እንዲሁ አንተም ለልጅህ ባልን በመፈለግ አእምሮ ቢባክን ወደ እግዚአብሔር “ጌታ ሆይ አንተ የፈቀድከውን አድርግ” ብለህ ጸልይ። ለእርሱን እንዲህ በማለት ፈቃድህን አሳልፈህ ስጠው። በዚህ መልክ ለእርሱ ክብርን ስጥ፤ እርሱም በምላሹ ፈቃድህን በመፈጸም ያከብርሃል። በእርግጥ አንተን ሁለት ሥራዎች ይጠብቁሃል። እነርሱም ፈቃድህን ለእርሱ ሙሉ ለሙሉ መስጠትና፣ እርሱ የመሰከረለትን በጥሩ ሥነ ምግባር የታነጸውን ሰው መሻት ናቸው።

የልጅህን ሰርግ ለመሰረግ በምትዘጋጅበትም ጊዜ እቃዎችንና ልብሶችን ለመዋስ ስትል ቤት ለቤት አትዙር። ምክንያቱም ሰርጉ የሚፈጸመው ትዕይንትን ልታቀርብ ወይም የልጅህን ቁንጅና ልታሳይበት አይደለምና። በመሆኑም ሰርግህን ልትፈጽም በምትዘጋጅበት ጊዜ ባለህ ነገር ብቻ ቤትህ ለማስዋብ ሞክር። በመቀጠል ጎረቤቶችህን ወዳጆችህንና የቅርብ ዘመዶችህን ጥራ። እንዲሁም ጥሩ ባሕርይ አላቸው የምትላቸውን ሰዎች በሰርጉ እንዲታደሙልህ ጋብዝ። ሙዚቀኞችን ግን ፈጽመህ አትጥራ ለእነርሱ የምታወጣው ወጪ በራሱ ከፍተኛና ሊሆን የማይገባ ነው።

ከእነዚህ ሁሉ አስቀድሞ ግን ክርስቶስን በሰርግህ እንዲገኝ ጋብዘው። እርሱን እንዴት አድርገህ እንደምትጋብዘው ታውቃለህን? “ንጉሡም መልሶ፡እውነት እላችኋለሁ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳ ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል”(ማቴ.፳፭፥፵) እንዲል ድሆችን በሰርግ እንዲገኙ በማድረግ ክርስቶስን በሰርግህ እንዲገኝ ማደረግ ይቻልሃል። ስለክርስቶስ ብለህ ድሆች በሰርግህ እንዲገኙ ስላደረግህ ሰርግህ የተበላሸ አድርገህ አትቁጠር፤ ነገር ግን ሴሰኞችን በሰርግህ ብትጋብዝ ሰርግህ በእርግጥ የረከሰ ይሆናል። ድሆችን ወደ ሰርግህ መጥራትህ ሀብት ወደ ቤትህ እንዲገባ መጥራትህ ነው። ቅምጥሎችን ከሰርጉ እንዲታደሙ የጠራህ እንደሆነ ግን ውርደትን እየጠራህ ነው።

ሙሽሪትን በወርቅ ጌጣ ጌጦች አታስጊጣት ነገር ግን በጥሩ ሥነ ምግባርና በጭምትነት አስጊጣት እነዚያን ነገሮች ፈጽመህ አትፈልጋቸው። ግርግርና ሁካት በሰርግህ ፈጽሞ አይኑር። ሙሽራውን ጥራና ሚስቱን ይዞ ወደ ቤቱ ይግባ። በምሳና በራት ግብዣህ ላይ አስካሪ መጠጦች አይገኙ። ነገር ግን ሰርግህ በደስታ የሞላበት ይሁን።

እንዲህ አድርገህ ሰርግህን በመከወንህ ምን ያህል ተጠቃሚ እንደሆንክ ለማስተዋል እንድትችል በዘመኑ ሰርግ ተብለው ከሚቆጠሩት ጋር ያንተን የሰርግ ሥነ ሥርዐት አስተያይ። ሌላው ይቅርና ያንተን ሰርግ የተመለከተ ሰው ሁሉ የቁንጅና ውድድር ሳይሆን በእውነተኛ ትርጉም ሰርግን እንዳየ ምስክርነትን ይሰጥሃል። በዘመኑ ሰርግ ተብለው ከሚጠሩት ውስጥ ግን እጅግ የበዙ ክፋቶች ታጭቀው ይገኙበታል። በአዳራሽ የሚፈጸመው ሰርግ በጥንቃቄና እግዚአብሔርን በመፍራት ከሚደረገው ጋር ሲነጻጸሩ በቶሎ የሚጠናቀቁ ሰርጎች አይደሉም። ከዚህም ባለፈ በውሰት የመጡት እቃዎች ሊጠፉም ስለሚችሉ ፍጻሜው ከደስታ ይልቅ ሊቋቋሙ ከማይችሉት ከባድ ሃዘን ውስጥ ሊጥል ይችላል። ይህ የከበደ ሃዘን በአማች ላይ የሚታይ ነው ። ነገር ግን ሙሽሪትም ከዚህ ሃዘን ነጻ ልትሆን አትችልም ። በሰርጉም ፍጻሜም የቤቱ ውበቱ ጠፍቶ በሃዘን ታወሮ ይታያል ።

በጥንቃቄና እግዚአብሔርን በመፍራት በሚከናወነው ሰርግና በአሕዛብ ልማድ በሚፈጸመው ሰርግ መካከል ሰፊ የሆነ ልዩነት አለ። በዚህ ክርስቶስ ሲገኝ በዚያ ግን ሰይጣን ነግሦ ይታይበታል ። በዚህ ፍጽም የሆነ ፍስሐ ሲታይ በዚያ ደግሞ ጥቅ ያጣ አለባበስ ይተዋወቅበታል ። በዚህ ፍጹም ደስታ ሲኖር በዚያ ግን ሕማምና ሰቆቃ ይተርፈዋል ። በዚያ የወጣው ወጪ ታላቅ ሲሆን በዚህ ግን እዚህ ግባ የማይባል ወጪ ብቻ ያስተናግዳል ። በዚያ ግርግርና ሁካታ ሲታይ በዚህ ግን ግብረ ገብነት ጎልቶ ይንጸባረቅበታል። በዚያ ኃጢአት ሠልጥና ስትታይ በዚህ ግን ኃጢአት ፈጽማ አትኖርም ። በዚያ ስካሮች ሲኖሩባት በዚህ ግን ሰላም ወዳዶች ይታዩባታል ። በዚያ ሁካታና ጠብ ሲኖር በዚህ ግን እርጋትና ሰላም ሰፍነው ይታዩበታል ።

እነዚህን ሁሉ ልብ በሉ ። እግዚአብሔርን ደስ በማሰኘት እርሱን ለሚያፈቅሩት ካዘጋጀው ከመንግሥቱ ተካፋዮች እንድንሆን ከዚህ ቀን ጀምረን ይህን ክፉ ልማድ ከራሳችን አርቀነው እናስወግደው። የሰውን ልጅ ከመውደዱ የተነሣ ሰው በሆነው በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር አብ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጋር ክብር ምስጋና ዛሬም ዘወትርም እስከዘለዓለሙ ይሁን አሜን !!

ምንጭ

እንዲህም ሆነ የእግዚአብሔር ወዳጅ የሆነ ስሙ ዱራታዎስ የሚባል አንድ ሰው ነበረ። የሚስቱም ስም ቴዋብለት ነው። እነርሱም ሁልጊዜ ያለ ማቋረጥ የዚህን የከበረ መልአክ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ያረጉ ነበር። ከዚህም በኋላ በሀገር ውስጥ ችግር በሆነ ጊዜ ገንዘባቸው አለቀ። በዚህም የተነሳ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል ለበዓሉ መታሰቢያ የሚያደርጉትን አጡ። ዱራታዎስም ሽጦ ለበዓሉ መታሰቢያ ያደርገው ዘንድ የእርሱን ልብስና የሚስቱን ልብስ ይዞ ወጥቶ ሄደ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ መኮንን አምሳል ለዱራታዎስ ተገለጠለት፤ ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስን ወደ በጎች እንዲሔድና በእርሱ ዋስትና በአንድ ዲናር አንድ በግ እንዲወስድ አዘዘው፤ ሁለተኛም ወደ ዓሣ አጥማጅ ሔዶ አንድ ዓሣ እንዲወስድ አዘዘው። መልአኩም ወደ ቤት ሳይደርስ የዓሣውን ሆድ እንዳይቀድ አስጠነቀቀው። ወደ ባለ ስንዴም እንዲሔድና የሚሻውን እንዲሁ በእርሱ ዋስትና እንዲወስድ አዘዘው ዱራታዎስም ቅዱስ ሚካኤል እንዳዘዘው አደረገ።

ወደ ቤቱም በተመለሰ ጊዜ በረከትን ሁሉ ቤቱ ተመልቶ አገኘው፤ እጅግም አደነቀ፤ የዚህንም የከበረ መልአክ የበዓሉን መታሰቢያ እንዳስለመደው አደረገ። የተራቡ ድሆችን ሁሉንም ጠርቶ መገባቸውና ወደ ቤታቸው አሰናበታቸው።

ከዚህም በኋላ ለዱራታዎስና ለሚስቱ ቅዱስ ሚካኤል ለሁለተኛ ጊዜ ተገለጠላቸው ዱራታዎስንም የዓሳውን ሆድ እንዲሰነጥቅ አዘዘው፤ በሰነጠቀውም ጊዜ ሦስት መቶ የወርቅ ዲናር በዓሳው ሆድ ተገኘ። ቅዱስ ሚካኤልም ዱራታዎስንና ቴዋብስታን እንዲህ አላቸው። ‹‹ከዚህ ዲናር ወስዳችሁ ለባለ በጉ ለባለ ዓሳውና ለባለ ስንዴው ዕዳችሁን ክፈሉ የቀረውም ለፍላጎታችሁ ይሁናችሁ፤ እግዚአብሔር አስባችኋልና በጎ ሥራችሁን መስዋዕታችሁን ምጽዋዕታችሁን በዚህ ዓለም አሳመረላችሁ። በኋላኛውም መንግስት ሰማያትን አዘጋጅቶላችኋል።››

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም ገናና የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ልመናውና አማላጅነቱ ፈጽሞ ይጠብቀን። ከጽኑ ጠላት እጅ በክንፎቹ ጋርዶ ይሰውረን። ለዘለዓለሙ አሜን።

______

Posted in Ethiopia, Faith, Life, Love | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚኦ! | ትውልደ ኢትዮጵያዊው ሙስሊም ኢድሪስ መሀመድ፤ “ሁለት ልጆቼንን እና ሚስቴን በቤንዚን አርከፍክፌ ያቃጠልኳቸው“ ገንዘብ ስላልበቃኝ ነው!„ አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 17, 2017

በጣም የሚያስገርም ነው! ልክ ይህን ቪዲዮ ዮቱብ ላይ ከላኩት ከጥቂት ሰዓታት በኋላ ነበር የሚከተለውን አሳዛኝ ዜና፡ ደይሊ ሜል መጀመሪያ ገጽ ላይ ፡ተለጥፎ ያየሁት፤ ይህን ዜናም በተልይ አሁን ማቅረባቸው ያለምክኒያት አይደለም፦

Asylum Seeker Uber Driver Said He Murdered His Two Young Children With A Petrol-Soaked Cloth During a Downstairs Sleepover Because He Was ‘struggling Make Enough Money to Support Them’

Uber driver Endris Mohammed also tried to kill his wife and was pictured horribly disfigured in a police mugshot after attempting to take his own life by setting his car ablaze (left). The warped father, 47, tried to take his own life after murdering his two children, Saros, eight and Leanor, six, by smothering them with a petrol-doused cloth (centre). Chilling footage of Mohammed before the murders shows the Ethiopian asylum-seeker arriving at a garage and purchasing a jerrycan full of petrol (top right). Emergency services rushed to the family home following a blaze at the property in Handsworth, Birmingham, at around 3.30am on October 28 last year, where they discovered the lifeless bodies of the two children. Mohammed fled the scene in his rented Vauxhall Insignia – which he used for work – and was later found 40 miles away inside the burning vehicle, having tried to take his own life (bottom right). When asked by a psychiatrist why he had murdered his children and attempted to murder his wife, Mohammed said that he ‘did not want them to suffer’.

Selected Comments:

What a thoroughly evil man, to kill his children and attempt to kill his wife. The injuries to himself does not mean a thing and I have no sympathy for him.

Useless animal, couldn’t even kill himself properly

I’m glad he’s not dead. I hope he suffers for the rest of his life

Hopefully he’s in complete agony until he dies a violent death.

That’s horrific, those poor children! He deserves whatever is coming his way in the way of pain and torment!

Those poor children they never had a chance with evil living amongst them.

Continue reading…

ቀደም ሲል ዩቲውብ ላይ የላኩት መልዕክት፦

ወደ እስልምና ተቀይራ ሙስሊሙን ገባችው ሴት፡ ባሏ በቢለዋ ካረዳት በኋላ ጫካ ውስጥ ጥሎ አቃጠላት

የባሏ ወንድም እና እናቱ ተረዳድተው ነበር የሴትየዋን ሬሳ ለማቃጠል የበቁት፤ በእንግሊዟ ሊድስ ከተማ ነው። ይታየን፤ አራት ልጆች ወልዳለታለች።

ወደ አገራችንም እየመጣ ያለው ጭካኔ ይህ ነው፤ ትዕቢት፣ ቅናት፣ ቁጡነት፣ ጥላቻ፣ ግድያ፥ እነዚህ ሁሉ ከእስልምና እና ከአምልኮቱ ፈጣሪ ከዲያብሎስ የተገኙ ናቸው። አብሮ ከመኖርና ከመነካካት የተነሳ ወደ ህዝበ ክርስቲያኑ እየገቡ ያሉ ርኩስ ባሕርያት ናቸው። ቅዱሳን ፀበላት በየቦታው እየፈለቁ መሆናቸው እግዚአብሔር ይህን ሞኝነታችንን በማየቱ አይደለምን? ግን እስከ መቼ ነው አምላካችንን ብዙ ሳናስቸገር ሞኝነቱ በቃን! በማለት እራሳችን የራሳችንን የቤት ሥራ ለመሥራት ዝግጁ የምንሆነው?

ባለፈው ዓመት ላይ እንዲሁ በእንግሊዝ አገር ሁለት ኢትዮጵያውያን ህፃናት በሙስሊም አባታቸው መቃጠላቸውን እናስታውሳለን፤ እዚህ እናንብብ፦

Birmingham Tragedy: House Fire Set By Dad Killed Two Ethiopian Children

ተጠንቀቁ! እስልምና ጧ! ያደርጋል፣ ነፍስን ይገድላል።

በተጨማሪ፡ ቪዲዮው ላይ፡ ክርስቲያን እናቱ ሙስሊም በማግባቷ፡ በጣም የተቆጨው ብልሁ ዋሊድ ሹባት የቤተሰቡን ታሪክ ያወሳልናል።

በእስልምና፤ ሙስሊም ወንድ ክርስቲያን ሴት ማግባት ይፈቀድለታል! ሙስሊም ሴት ግን ክርስቲያን ወንድ ማግባት አይፈቀድላትም!

የእባብን ተንኮል አየን፡ አይደል!?

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ መሆን የለባትም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 5, 2014

EthioChild

(ሪፖርተር ጋዜጣ – ከተቆርቋሪ ዜጋ)

ምንም እንኳን በሚዲያዎች በግልጽ ባይነገርም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ከመስከረም 20 እስከ 25 ቀን 2006 .ም የተደረገ ስብሰባ ነበር፡፡ ይህም የዓለም አቀፍ የሥነ ሕዝብና የዕድገት ኮንፈረንስ (አይሲፒዲ) ከፍተኛ ግብረ ኃይል ያልተቋጨ አጀንዳ በተለያዩ አገሮች እ..አ ከ2014 ጀምሮ ሊተገበር የሚገባ ብሎ ያስቀመጣቸውና በስብሰባው በስተመጨረሻ ለጉባዔው ይፋ የተደረጉና በዋናነት የተቀመጡ ነጥቦች አሉ፡፡ ከእነዚህም መካከል ከአገራችን ሕግ፣ ደንብና ባህል እንዲሁም እሴቶቻችን ጋር ፈጽሞ አብረው ሊሄዱ የማይችሉ ጉዳዮች ነበሩበት፡፡

የመጀመሪያው የወሲብና ተዋልዶ መብቶችን ማክበር፣ መንከባከብና ተፈጻሚ ማድረግ የሚል ነው፡፡ ለዚህም ሕጋዊ ውርጃን ማስፋፋትና ማዳረስ፣ የወሲብና የተዋልዶ መብትን ከሌሎች መብቶችና ከተዛማች ሕጐች ጋር በማያያዝ ማስተማር፣ ግለሰቦች ያላቸውን የወሲብ ዝንባሌያቸውን በሚፈልጉት ሁኔታ ከተመሳሳይ ፆታም (ሆሞሴክሸዋሊዝም) ጋር ቢሆን ያለምንም ገደብ መብታቸውን እንዲለማመዱ ያበረታታል፡፡

ከጋብቻም ውጪ ቢሆን ማንኛውንም የወሲብ ኅብረቶች በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ እስከሆነ ድረስ መብታቸውን የሚከለክሉ ድንጋጌና ሕጐች እንዲነሱ ይጠይቃል፡፡ የወሲብና የተዋልዶ ጤና መረጃና ትምህርት ማቅረብና ተደራሽነቱን ማረጋገጥ ሌላኛው ዓላማው ነው፡፡ ለዚህም በዋናነት ወጣቶችን በተለይም አፍላ ወጣት ሴቶች ላይ ያነጣጠረ መረጃ በትምህርት ቤቶችና ከትምህርት ቤቶችም ውጪ በመስጠት አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያና ሌሎች የወሊድ መቆጣጠሪያ (ሕጋዊ ውርጃንም ጭምር) የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡

እንዲሁም ትምህርቱን በመቅረፅና በማዘጋጀት የሕግና ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲያገኝ ማድረግ የሚል ሲሆን፣ ይህንንም ለማድረግ የብሔራዊ ጤና ፕሮግራም አካል ሆኖ የራሱ በጀት እንዲኖረውም በማድረግ በአንዳንድ በውርጃ ሥራ ላይ በተሰማሩ ድርጅቶች የሚከናወን ነው፡፡ (ለምሳሌ በሪፖርተር ጋዜጣ ሐምሌ 2005 .ም በሜሪስቶፕስ ቃለ ምልልስ ላይ በወር 42 ሺሕ ሴቶች ለፅንስ ማቋረጥ ወደ እኛ ይመጣሉ ሲሉ ያለዕፍረት ተናግረዋል) ይህ እንግዲህ አንዱ ድርጅት ብቻ ነው፤ ሙሉ በሙሉ ሕጋዊነቱ ሲዳረስ ምን ሊሆን እንደሚችል መገንዘብ ያሻል፡፡

እስቲ ፍረዱ እኛ በልተን ያልጠገብንና ለማደግ የምንፍጨረጨር ዜጐች፣ የአውሮፓውያንና የምዕራባውያን ቆሻሻ ማራገፊያ የምንሆንበት ምክንያት ምንድን ነው? ይሄ ኢትዮጵያ ነው፡፡ እኛም ኢትዮጵያዊያን ነን፤ ሁለተኛ ዜጋ አይደለንም፡፡ ስለአገራችን ሁኔታ ያገባናል፡፡ ይህ ድብቅ በሆነ መንገድ ቀስ በቀስ ገጽታችንን የሚያጠፋ ጉዳይ ነው፡፡ በጣም የሚያሳፍረው ደግሞ ከግብረ ኃይሉ አባላት ውስጥ አስፈጻሚ ሆነው ልጆቻችንን የመሸጥ ያህል በመሯሯጥ ላይ ያሉት ባለሥልጣኖቻችን መሆናቸው ነው፡፡ እንርሱን ታሪክም ትውልድም ይጠይቃቸው፡፡ ዛሬ ከውጭ ለሚገኘውና በልማት ስም ለሚመጣ ገንዘብ ብለው ጤናማ ትውልድ ሊያሳጡን ነው፡፡ እኛ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሌሎች አገሮች እንኳን ስንሄድ የምንኮራበት የራሳችን የሆነ ባህልና ሞራል እንዲሁም ታሪክ ያለን ሕዝቦች ሆነን፣ በዕድገትም ስም ተቀበሉ እያሉ በገንዘባቸው እያስፈራሩና እየደለሉን ነው፡፡ እኛ የምንመርጠው ከድህነታችን ጋር ጤናማ ኅብረተሰብና ታሪካችንን ነው፡፡

ታዲያ የአባቶቻችንና የቀደሙት መሪዎችቻችን ድፍረትና ወኔ ወዴት ነው ያለው? የአሁኖቹ መሪዎች ካደጉ አገሮች በልማት ስም ለሚገኘው ገንዘብ አሳልፈው ይሰጡን ይሆን? ሕጋችንን፣ ባህላችንንና ታሪካችንን ያከብሩልን ዘንድ እባካችሁ ጠይቁልን!

ግብረሰዶማዊነትና ልቅ የወሲብ መብቶች ከትምህርት ቤት ጀምሮ እንደ ዳቦ ሲታደል ምን ዓይነት ቀጣይ ትውልድ ይኖረናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን? ጠቃሚ ስለሆኑት መመርያዎች ቅሬታ አይኖረንም፡፡ ነገር ግን በተከበረች አገራችን ላይ የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ/ግንኙነት እንዲሁም ልቅ ወሲባዊ መብት ልንሸከመው የምንችለው አይደለም፡፡ እንኳን ይህ ሁኔታ ተመቻችቶ ሚዲያዎች መጤና አጉል ልማዶችን እያስተዋወቁን ይገኛሉ፡፡ ታዲያ የሥነ ምግባርና የሞራል ውድቀት ሲጨመርበት ምን ሊሆን ይችላል? መንግሥት በዚህ ለተማሪዎች ሥነ ምግባር አሳቢ እየመሰለ በዚያ ለሺሻ ቤት ፈቃድ እየሰጠ የሚጣረስ ነገር በመሥራት ላይ ነው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ዛሬ ለአንድ ወላጅ ተማሪ ጥሩ ውጤት አምጥቶ ዩኒቨርሲቲ ሲገባ የነበረው ደስታ ጠፍቶ ልጄ ምን ይገጥመው/ይገጥማት ይሆን በሚል ሥጋት መወጠር ጀምሯል፡፡

ፍረዱ ይህ ለችግሮች መፍትሔ ነው እየተባለ በየቀኑ ኢቲቪ የሚነግረን እውን መፍትሔ ነው? ውርጃን በየክሊኒኩ ማስፋፋትና አጣዳፊ የእርግዝና መከላከያ አቅርቦት ለወጣቶቻችን መፍትሔ ነው?

ቀደም ሲልም ግብረሰዶማዊነትን ለማውገዝ የእምነት አባቶች በተነሱ ጊዜ እንዳንድ የመንግሥት ባለሥልጣናት መከልከላቸውን እናውቃለን፡፡ ይህ ታሪክ ከማጥፋትና ትውልድ ከመሸጥ አይተናነስም፡፡ በመስከረሙ ሥነ ሕዝብና አኅጉራዊ ስብሰባ ላይ ይህንን የተቃወሙ አገሮች አሉ፡፡ እንደ ቻይና ያሉ አገሮችም በጭራሽ እንዳልተቀበሉት ከኢንተርኔት ለማየት ችለናል፡፡ የእኛስ መሪዎች የተቀበሉት በልማት ስም ትውልድን መረን ለመልቀቅ ነው? ስለዚህ በጦርና መሳሪያ ለማንበርከክ/ቅኝ ለመግዛት ያልቻሏትን አገር፣ ዛሬ አንገት የሚያስደፋንን ውሳኔ መሪዎችን እንዳያስተላልፉ ሥጋት አድሮብናል፡፡

እንደ ኢትዮጵያዊና እንደ ወላጅ የነገን ጤናማና ፍሬያማ ትውልድ እንደሚናፍቅ ዜጋ ይህንን ጽፌያለሁ፡፡ ለነገም ትልቅ የማኅበረሰብ ቀውስ ነውና መንግሥታችንም ሆነ የሚመለከተው ክፍል ዛሬ አንድ በሉልን፡፡ የሕግ ያለህ! የፈጣሪ ያለህ!

__

 

Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: