Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጉለሌ’

ክቡር መስቀሉን እንጦጦ ላይ አላሰራንም ፥ መስቀል አደባባይንም እንዳይቆፈር አልተጋደልንም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 28, 2020

ስለዚህ አውሬው እንዲህ ቢሳለቅብንና ቢፈነጭብን ሊገርመን ይችላልን?

👉 ከዓመት በፊት አቅርቤው የነበረው ጽሑፍ እና ቪዲዮ

አዲስ አበባን ከጠላቶቿ የሚጠብቃት አንጋፋ መስቀል በእንጦጦ ተራሮች ላይ ሊሠራ ነው”

እንኳን ለበአለ መስቀል አደረሰን!

👉 ደብረ መድኃኒት አቡነ ሀብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም፡ ክፍል ፫

ክቡር መስቀሉ የሚሠራው በደብረ መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም ጫፍ ላይ ነው። ከዚህ ተራራ ጫፍ ሆኖ በመላው አዲስ አበባን አካባቢዋ ሊታይ ይችላል፤ ማታ ላይም በደንብ እንዲታይ መብራት ይኖረዋል።

ይህ የተቀደሰ ሥራ ከሁሉም ሥራዎች ቀድሞ በፍጥነት መከናወን ይኖርበታል እላለሁ። ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት “እንጦጦ ማርያም ጫፍ ላይ አንድ ትልቅ መስቀል መተከል አለበት” እያልኩ ብዙ አባቶችን በየጊዜው ስወተውት ነበር፤ አሁን ህልሜ ዕውን ሆነ።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ወደ ገዳማቸው መርተውኝ ይህን የመስቀል ሥራ ንድፍ ሳይ፡ ባጋጣሚው፡ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ተገርሜም ተደስቼም ነበር። እስከ አሁንም ድረስ ብዙ ነገሮች ይታዩኛል፤ ለምሳሌ፡ በአንድ በኩል ቤተ ክህነት ኃላፊነቱን ወስዳ ቶሎ ማሠራት አለባት እላለሁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባውያን፥ ውጭ ካለነው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ባጭር ጊዜ ውስጥ – እንዲያውም ፻፹ ሜትር ከፍ በማድረግ – ማሠራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ተዋሕዶ ልጅ በፍጥነት ተረባርቦ በተግባር ሊያውለው የሚገባው ሥራ ነው።

የአቡነ ሃብተማርያምን የፀሎት መጽሐፍ በብሔረ ፅጌ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሲያከፋፍል የነበረውን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወንድማችንን፡ “መስቀል አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ጫፍ ላይ ሊተከል ነው፤ ምን ይሰማሃል” ስለው፤ ቪዲዮው ላይ የቀረበውን ግሩም ትምህርት በደስታ አካፍሎኝ ነበር። እርሱም እንደ አብዛኛው/መላው አዲስ አበቤ መስቀል እዚያ የመትከል ዕቅድ አልሰማም። ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

በመጭዎቹ ወራት አዲስ አበባውያን የተዋሕዶ ልጆች በሚከተሉት ሁለት ነገሮች ይፈተናሉ፦

፩ኛ፦ ለክቡር መስቀሉ ምን ያህል ፍቅር እንዳላቸው በማሳየት

፪ኛ፦ በሊቢያ በሙስሊሞች ለተሰውት ሰማዕታት አስከሬን እንዴት አቀባበል እንደሚያደርጉ

በመቅሰፍት የተመታችው አዲስ አበባ መዳን የምትችለው በፖለቲከኞች የተመሰቃቀለ ጭንቅላት ሳይሆን በክቡር መስቀሉ ነው። ቶሎ እናሠራው! መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው!!!

ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዲያብሎስ በዚህ ክርስቲያናዊ ትዕግስት፣ ፍቅርና የእምነት ጽናት በጣም ይቀናል፣ ይቃጠላል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 9, 2020

እጣን እጣን ይሸታል መሬቱ.…

ስለዚህ በእኛ በክርስቲያኖች ላይ ዕባባዊ ተንኮሉን፣ ፈተናውንና መሰናክሉን በማፈራረቅ ስልታዊ በሆነ መንገድ ይመጣብናል።

በትናንትናው ቪዲዮ፤ “የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር | ቤተ ክርስቲያኗን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈንድ “ለዚህም ነው ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይ ያ መስጊድ የተሠራው” ብየ ነበር።

አዎ! ለዚህም ነው ታች በሙስሊሙ በቀረበው “የመቻቻል” ጽሑፍ ላይ ረመዳንን ለማክበር የመጡ ሙስሊሞች ባልጠፋ ቦታ ቀስ ብለው ወደ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን በመጠጋትና ሆን ብለው ወደ ግቢው በመግባት ለዲያብሎስ አላሃቸው ለመስገድ የፈለጉት።

በመቻቻል” ስም ሙስሊሙ ጸሐፊ በከረሜላ ቀለም ነክሮ የጻፈልንን ቃላት አንብበን እንዳንታለል፤ መሀመዳውያኑ የአላህንና የመሀመድን ስም እየጠሩ ለዲያብሎስ አላህ እስከ ሰገዱ ድረስ ሁልጊዜ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው፣ የቤተ ክርስቲያንና ክርስቲያኖች ቀንደኛ ጠላቶች ናቸው።

ሆኖም ይህ ሙስሊም ጸሐፊ ያየውን ለመጻፍና ለመመስከር በመሞከሩ ሊመሰገን ይገባዋል። ምስክረነቱ በግልጽ የሚያረጋግጥልን በእኔ በኩል ሁልጊዜ የምናገረውን አንድ ነገር ነው፤ ይህም፡ “በፍርድ ቀን በዓለማችን ካሉ ሙስሊሞች ሁሉ ከባዱን ፍርድ የሚቀበሉት ወይም በጥብቅ የሚፈረድባቸው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ናቸው፤ ምክኒያቱም “ወንጌልን አልሰማንም””ክርስቲያናዊ ፍቅርን አላየንም” ማለት አይችሉምና ነው።” የሚለውን መራራ ሐቅ ነው።

ጸሐፊው “ፍቅር ያሸንፋል!” ይላል፤ ግን ይህ ፍቅር በእስልምና ዘንድ አለን? የለም! በጭራሽ፤ የሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ ቢሞላና ክርስቲያኖች የመስጊዱን ግቢ ለመጠቀም ቢጠይቋቸው መሀመዳውያኑ የሺህ ሆጀሌ መስጊድን በር ይከፍቱላቸው ነበርን? እ እ! በጭራሽ! ለመግባትም የሚሻ ክርስቲያን አይኖርም!

አዎ! ፍቅሩ በክርስትና እና ክርስቲያኖች ዘንድ ብቻ ነው የሚገኘው፤ ፍቅር ደግሞ አሸናፊ ከሆነ “በመቻቻል” ሳይሆን ሊገለጽ የሚችለው ይህን ፍቅር ያዩት ሙስሊሞች ወደ ክርስቶስ መምጣት ሲችሉ ብቻ ነው። ዋናው ጥያቄ ይህን ፍቅር ያየው ይህ ሙስሊም ጸሐፊ ከእስልምና ድቅድቅ ጨለማ ወጥቶ ወደ ክርስቶስ ብርሃን መጥቷልን? የሚለው ነው። ሌላው ነገር ሁሉ ከንቱ ነውና!

ሙስሊሙ ስለ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን እና ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይ ስለተሰራው መስጊድ እንዲህ ሲል ጽፏል፤ ተመልከቱ “ቤተ ክርስቲያን”ን “ቤተስኪያን” እያለ ሲጽፍ፦

27ኛዋ የረመዳን ሌሊት በቅዱስ ሩፋኤል ቤተ ክርስቲያን”

(አክረም ሐበሻዊ )

በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በረመዳን ወር የመጨረሻዎቹ ቀናት አንድ የተባረከች

ሌሊት አለች ከ 1000 ወር የምትበልጥ “የውሳኔዋ ሌሊት ” ትባላለች አማኙም የዚህ በረከት ተቋዳሽ ለመሆን ሌቱን በፀሎት ያሳልፋል። 2003 ዓ/ም ነበር እኔም በአቋራጭ መክበር ቢያቅተኝ በአቋራጭ ሀጢያቴን ላራግፍ ብዬ የዚች ሌሊት ቋሚ ተሰላፊ ለመሆን ጉዞዬን ወደ ሼህ ሆጀሌ መስጂድ አደረኩ።

ስግደቱን የሚመራው በድምፁ ውበት በሚወደደው መሀመድ ደጉ የተባለ ወጣት ነበር።

በሚገርም ሁኔታ ከአራቱም አቅጣጫ በመጡ ሰጋጆች አካባቢው ተሞልቶ መስገጃ አይደለም መቆሚያ ቦታ ጠፋ ልብ በሉ ይህ የሚሆነው ሌሊት 8:00 ሰዓት ላይ ነው!! እኔና ብዙ እንደኔው ሀጢያታቸውን ለማራገፍ የመጡ ሰዎች ሩፋኤል ደጃፍ ተሰግስገን በአይናችን መስገጃ ቦታ በምንማትርበት ጊዜ ነበር አንድ የቤተስኪያኑ ቄስ የመጡት ሌት ስለነበር መልካቸው ብዙም ትዝ አይለኝም ግን እንደ ካድሬ የሐይማኖት አባቶች በብስጭት ሳይሆን በእዝነት የሸበተ ነጭ ፂማቸው ፊቴ ላይ አለ “እንደምን አመሻችሁ ልጆቼ ” የመጀመሪያ ቃላቸው ነበር ከሁኔታችን መስገጃ ቦታ እንዳጣን ተረዱ የቤተስኪያኑንም ደጃፍ ለስግደት ሲፈቅዱልን ጊዜ አልፈጀባቸውም።

እኛም አመስግነን ስግደታችንን ቀጠልን እሳቸውም ወደ መቅደሱ ዘለቁ ግን አፍታም ሳይቆዩ ተመልሰው መጡ የመሬቱን እርጥበት ለመከላከል ይረዳል ያሉትን የሚነጠፍ ነገር ሰብስበው አመጡልን ያኔ ግን ሁላችንም እንደ መጀመሪያው ማመስገን አልቻልንም ይልቁንም የኒያን ሽማግሌ አባት ፊት እያየን አይኖቻችን እንባ አቀረሩ እንጂ !!

ኢትዮጵያዊነቴን ወደድኩት! ኮራሁበት! ሰዓቱ እየሄደ ሲመጣ ወደ ቤተስኪያኒቱ ለመሳለም የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እየበረከተ መጣ። ስግደታችንን ላለማቋረጥ የሚያደርጉት ጥረት እጅግ ልብን ይነካል “እንደምን አደራችሁ” “ሰላም ለናንተ” የሚሉ ድምፆች ይሰሙኛል። እናት ክርስቲያኖች” እኔን ልጆቼ ብርዱ ገደላቹ” ሲሉ ኢትዮጵያዊ እንባ አነባው !!

አንዳንዶቻችን ፍቅር ያሸንፋል ሲባል የሰማነው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ሊሆን ይችላል እኔ ግን በዛች በተቀደሰች የረመዳን ሌሊት በአይኔ አየሁት!!

ወዳጄ እውነታው ይሄ ነው፤

ስለመቻቻል የሚያስተምሩህ አላማቸው እንድትቻቻል አይደለም ይልቁንም ልዩነትህን እንድታውቅ ነው ከዛም ብስለት ከሌለህ የኔ ይበልጣል ማለት ትጀምራለህ፣ ታዲያ ያኔ መቻቻል ድራሹ ጠፋ አይደል የሚባለው? ከዛም ፍቅር በገሐድ ማሸነፉ ይቀርና የሙዚቃ ኮንሰርቶች ላይ ብቻ “ፍቅር ያሸንፋል”

ሲባል ትሰማለህ። ፍቅርም የሕይወት ማጣፈጫ መሆኑ ይቀርና የአልበም ማሻሻጫ ይሆናል!ይብላኝ ፍቅርና መቻቻልን ከ ETV ዶክመንተሪ ለሚጠብቁ እኔስ ፍቅር ሲያሸንፍ እንዴት እንደሆነ እኒያ ነጭ ፂም ያላቸው የሩፋኤል አባ አሳይተውኛል።

እኔም እንዲህ አልኩ፤

አቦ አትጨቅጭቁን ከተቻቻልን ዘመን አለፈን!!! ወዳጄ፤ ሃገሩን የማይወድ አቦ አይወለድ !!! ኢትዮጵያ ለዘልአለም ትኑር”

______________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር | ቤተ ክርስቲያኗን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈንድቶ ሞተ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 8, 2020

ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይም ይህ መስጊድ ተሠራለት፤ ዲያብሎስን፣ 666 ድል የሚያደርገው ቅዱስ ሩፋኤል ይህን አውሬ የአህዛብ አገዛዝ በቅርቡ ከነ ፒኮኮ ያፈነዳዋል።

ጳጕሜን ፫፥ ፪ሺ፲ በታሪካዊቷ የቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፡ ዝናባማ በነበረበት ቆንጆ የቀትር ሰዓት ላይ፡ የጸሎት ስነሥስርዓቱ ልክ እንዳለቀ የመሀመዳውያኑ ጋኔን አዛን ተለቀቀ። (ቪድዮው መጨረሻ ላይ ይሰማል) ወዲያውም ይህ የዲያብሎስ ተንኮል እንደሆነ በመረዳት ወደ አንድ አባት ጠጋ ብዬ፡ ለምን ቅዳሴና ጸሎት ሲገባደድ ይህ ሰይጣናዊ ጩኽት ይከተላል? ከየትስ ነው የሚመጣው? ብዬ አብረዋቸው ከነበሩት ሌላ ሰው ጋር ስጠይቃቸው፤

130 ዓመታት በፊት የዚህች ውብ ቤተክርስቲያን ህንፃ በተሠራ ማግስት አንድ ከቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት ይኖር የነበረ ጭራቅ/ጠንቋይ በየቀኑ እየመጣ ቤተክርስቲያኗን ካላፈረስኩ፣ ካላቃጠልኩ እያለ ለሳምንታት ሲዝት ከቆየ በኋላ አንድ ቀን እራሱ ፈንድቶ ሞተ” አሉኝ።

እኔም፡ በመገረም፡ “በዚህ ፈጽሞ አልጠራጠረም! ግን ጠንቋዩ የሞተበት ቦታ ምን ተደርጎበት ይሆን?“ ብዬ ስጠይቃቸው፤ “ያው!“ አሉኝና፤ ሦስታችንም ዘወር ስንል ለካስ ቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት (50ሜትር ርቀት)መስጊዱ ተተክሎ ይታያል። እንዴ፡ “ጠንቋዩ ፈንድቶ በሞተበት ቦታ ላይ ይህ መስጊድ ተሠርቷል ማለት ነው“ እንዳልኩ ሁላችንም በመገራረም እርስበርስ ተያየን።

አዎ! የሚያጠራጥር አይደለም፤ እስከ ቅርብ ጊዜ ግን ይህን ሁላችንም አናውቅም ነበር፤ በጣም ይገርማል!

ከዚያም ከቤተክርስቲያኗ ግቢ እንደወጣሁ፤ የኔ ቢጤዎች ከነበሩበት ቦታ አስር የሚሆኑ ወጣቶች ተነስተው ከበቡኝና “ምን ፈልገህ መጣህ? ለምን መጣህ? ምን ትሠራለህ? … ወዘተ” እያሉ በሚገርም መልክ ይጨቀጭኩኝ ጀመር። ልክ እዚህ ቪዲዮ ላይ እንደሚታየው፦ “ለንደን ሃይድ ፓርክ | ሺ ደካማ ጂቦች ጀግናውን አንበሣ አፍነው ሊገድሉት”

እኔም፡ ምንም አለመለስኩላቸውም “በ ስም ልቀቁኝ!” አልኩና ዘወር ብዬ መራመድ እንደጀመርኩ አሁንም ተከተሉኝ፤ በዚህ ወቅት መንገድ ላይ ለነበረው አንድ ፖሊስ “ኧረ እባክዎ ከነዚህ ሰዎች ይገላግሉኝ!“ አልኩት፤ እርሱም “ሂዱ!“ እያለ ይጮኽባቸው ጀመር፤ እኔም ታክሲዎች ወደሚገኙበት ቦታ አመርቼ እንደተሰለፍኩ፤ ልጆቹ አሁንም በየአቅጣጫው ቆመው ወደ እኔ ይመለከቱ ነበር፤ በዚህ ወቅት ከየት መጣ ሳልለው አንድ ደግ ባለ መኪና “ወደ ፒያሳ ነህ?” አለኝና አሳፍሮ ወሰደኝ።

በዚህ ወቅት በ “ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፲፱” ላይ ሰዶማውያን ወደ አብርሃም ዘመድ ወደ ሎጥ ቤት ወጥተው ለማጥቃት ሲሞክሩ መላዕክት በአካል ወደ ሎጥ ቤት እንግድነት ገብተው አደጋ እንዳይፈጠር በር ሲዘጉና ሎጥን ከጥፋት ሲያድኑ የተነገረን ታሪክ ትዝ አለኝ።

ታዲያ የኔ ቢጢዎች ጋር የነበሩት እነዚህ ልጆች እነማን ናቸው? እያልኩ እራሴን ጠየቅኩ። እነዚህን ከ13 እስከ20 የሚጠጉ እድሜዎች ያሏቸውን፡ በደንብ መናገር የሚችሉትን ጎረምሳዎችን ያውኩ ዘንድ የመሀመድ ዲያብሎስ ምዕመናኑን አዘጋጅቷቸው ይሆን? መቼም ሰይጣን ሁሌ ከቤተክርስቲያን አይርቅምና!

______________________________

 

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዲያብሎስ ሰላሙን፣ ፍቅሩን እና ደስታውን ሊነጥቀን ይሠራል፤ ቅዱስ ሩፋኤልን ግን ሊነጥቀን አይችልም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 7, 2020

ቅዱስ ሩፋኤል

👉 ቅዱስ ሩፋኤልን ሰይጣን አይችለውም ፤ ሰማያት ተከፈቱ፤ የምሕረት ዓመቱ በር ተከፈተ ደስ ይበላችሁ!!!

ደማቅ ክብረ በዓል በታሪካዊቷ ቅዱስ ሩፋኤል ቤተክርስቲያን፤ አዲስ አበባ ጉለሌ፡ ጳጕሜን ፫፥ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም። ከመቶ ሰላሳ ሁለት ዓመታት በፊት ተመሠረተች። ዘንድሮስ እንደዚህ በደማቅ እና በሚያምር ሁኔታ እናክብረው ይሆን?

በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከከበሩት ቅዱሳን መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል /ጦቢት ፲፪፥፲፭/፡፡

ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ መልአከ ጥዒና ወሰላም /የሰላምና የጤና መልአክ/ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሩፋኤልየሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡

የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ኹሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል /ሄኖክ ፲፥፲፫/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” እንዳለ ሄኖክ /ሄኖክ ፮፥፫/፡፡

ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው ለማኅፀን ችግር ኹሉ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት፣ በማኅፀን እያለ ተሥዕሎተ መልክዕ” (በ አርአያ መልኩ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በወሊዳቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡

አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል /ጦቢት ፫፥፰-፲፯/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል “ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ተብሎ እንደ ተጻፈ /ሄኖክ ፫፥፭-፯/ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው /ሄኖክ ፪፥፲፰/፡፡

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ለመራዡ ኡማ የ፲ሚሊየን ብር ሽልማት | ፫መቶ ታዳጊ የቅኔ ተማሪዎች ግን እየተራቡ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2019

ይሄ እንዴት ሊሆን ቻለ? የቄሳርን ለቄሣር?

ይህ በጣም ከሚያሳዝኑኝና ከሚያንገበግቡኝ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው። የአዲስ አበባን ሕፃናት በመመረዝ ላይ ላለው ለታከለ ኡማ መመረዣ ዳቦውን እና ማርመላታውን ይገዛበት ዘንድ ቤተክህነት አስር ሚሊየን ብር መለገሷን ሰምተናል፤ በቤተክርስቲያን ሥር የሚገኙ ሕፃናት ግን በመራብ ላይ ናቸው። እንዴት?

በርካታ ቀዳሚ የኢትዮጵያ ምሁራን መነሻቸው ከአብነት ትምህርት ቤት ነው። የአብነት ትምህርት ከዘመናዊ ትምህርት መስፋፋት ጋር ተያይዞ የወትሮ ሚናውን ማጣቱ ቢስተዋልም፤ አሁንም ጥቂት ለማይባሉ ወጣቶች ምርጫ መሆኑ አልቀረም።

የዕውቀት በርን የሚከፍትላቸውን የቅኔ ትምህርትን በንባብ ቤት፣ ዜማ ቤት፣ አቋቋም ቤት፣ ቅኔ ቤት፣ ቅዳሴ ቤት እና መፃሕፍት ቤት ለመከታተል ሦስት መቶ የቅኔ ተማሪዎች በድንቁ የአቡነ ሀብተ ማርያም ገዳም ይገኛሉ። ይሁንና የትምህርት ቤቶቹ ህልውና ከሚያስተዳድሯቸው ገዳማትና አብያተ ክርስትያናት መድከምና መጠንከር ጋር የተሳሰረ በመሆኑ ለፈተና ሲዳረጉ ይስተዋላሉ። ተተኪ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች በቂ የመተዳደሪያ የገቢ ምንጭ ስለሌላቸውና ከቤተክህነትም እንኳን ምፅዋት ስለማያገኙ አሁን በመቸገር እና በመራብ ላይ ናቸው። አዎ! በአዲስ አበባ፣ ያውም በጣም ሰላማዊና ገነታማ ከሆኑት የከተማዋ ክፍሎች መካከል በአንዱ።

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

ቅዱስ ሩፋኤልን ሰይጣን አይችለውም | ሰማያት ተከፈቱ፤ የምሕረት ዓመቱ በር ተከፈተ ደስ ይበላችሁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 5, 2019

በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከከበሩት ቅዱሳን መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል /ጦቢት ፲፪፥፲፭/፡፡

ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ መልአከ ጥዒና ወሰላም /የሰላምና የጤና መልአክ/ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሩፋኤልየሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡

የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ በበሽታ ኹሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነውበማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል /ሄኖክ ፲፥፲፫/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነውእንዳለ ሄኖክ /ሄኖክ ፮፥፫/፡፡

ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው ለማኅፀን ችግር ኹሉ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት፣ በማኅፀን እያለ ተሥዕሎተ መልክዕ” (በሥላሴ አርአያ መልኩ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በወሊዳቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡

አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል /ጦቢት ፫፥፰፲፯/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለውተብሎ እንደ ተጻፈ /ሄኖክ ፫፥፭/ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው /ሄኖክ ፪፥፲፰/፡፡

የቅዱስ ሩፋኤል ተአምር

የቅዱስ ሩፋኤልን ቤ/ክርስቲያን ካላፈረስኩ እያለ ሲዝት የነበረው ጠንቋይ ፈንድቶ የሞተው እዚህ ነበር፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው ጠንቋዩ በፈነዳበት ቦታ ላይም ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት አንድ መስጊድ ተሠራ!

132 ዓመታት በፊት የዚህ ውብ ቤተክርስቲያን ህንፃ በተሠራ ማግስት አንድ ከቤተክርስቲያኗ ፊት ለፊት ይኖር የነበረ ጭራቅ/ጠንቋይ በየቀኑ እየመጣ ቤተክርስቲያኗን ካላፈረስኩ፣ ካላቃጠልኩ እያለ ለሳምንታት እያጓራ ሲዝት ከቆየ በኋላ አንድ ቀን እራሱ ፈንድቶ ሞተ።

ያው እንግዲህ፡ ልክ ጠንቋዩ በሞተበት ቦታ ላይ ከቤተክርስቲያኑ ፊት ለፊት (150 ሜትር ርቀት ላይ)መስጊዱ ተተክሎ ይታያል።

ሰይጣን ሁሌ ከቤተክርስቲያን አይርቅም!

ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን!

____________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አዲስ አበባን ከጠላቶቿ የሚጠብቃት አንጋፋ መስቀል በእንጦጦ ተራሮች ላይ ሊሠራ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 19, 2019

እንኳን ለበአለ መስቀል አደረሰን!

ክቡር መስቀሉ የሚሠራው በደብረ መድኃኒት አቡነ ሃብተማርያም፣ ቅድስት ልደታ እና ቅድስት አርሴማ ገዳም ጫፍ ላይ ነው። ከዚህ ተራራ ጫፍ ሆኖ በመላው አዲስ አበባን አካባቢዋ ሊታይ ይችላል፤ ማታ ላይም በደንብ እንዲታይ መብራት ይኖረዋል።

ይህ የተቀደሰ ሥራ ከሁሉም ሥራዎች ቀድሞ በፍጥነት መከናወን ይኖርበታል እላለሁ። ላለፉት አስራ አምስት ዓመታት “እንጦጦ ማርያም ጫፍ ላይ አንድ ትልቅ መስቀል መተከል አለበት” እያልኩ ብዙ አባቶችን በየጊዜው ስወተውት ነበር፤ አሁን ህልሜ ዕውን ሆነ።

ጻድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ወደ ገዳማቸው መርተውኝ ይህን የመስቀል ሥራ ንድፍ ሳይ፡ ባጋጣሚው፡ ማመን እስኪያቅተኝ ድረስ ተገርሜም ተደስቼም ነበር። እስከ አሁንም ድረስ ብዙ ነገሮች ይታዩኛል፤ ለምሳሌ፡ በአንድ በኩል ቤተ ክህነት ኃላፊነቱን ወስዳ ቶሎ ማሠራት አለባት እላለሁ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አዲስ አበባውያን፥ ውጭ ካለነው ኢትዮጵያውያን ጋር በመተባበር ባጭር ጊዜ ውስጥ – እንዲያውም ፻፹ ሜትር ከፍ በማድረግ – ማሠራት እንችላለን ብዬ አስባለሁ። እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ተዋሕዶ ልጅ በፍጥነት ተረባርቦ በተግባር ሊያውለው የሚገባው ሥራ ነው።

የአቡነ ሃብተማርያምን የፀሎት መጽሐፍ በብሔረ ፅጌ ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሲያከፋፍል የነበረውን የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወንድማችንን፡ “መስቀል አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ጫፍ ላይ ሊተከል ነው፤ ምን ይሰማሃል” ስለው፤ ቪዲዮው ላይ የቀረበውን ግሩም ትምህርት በደስታ አካፍሎኝ ነበር። እርሱም እንደ አብዛኛው/መላው አዲስ አበቤ መስቀል እዚያ የመትከል ዕቅድ አልሰማም። ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

በመጭዎቹ ወራት አዲስ አበባውያን የተዋሕዶ ልጆች በሚከተሉት ሁለት ነገሮች ይፈተናሉ፦

፩ኛ፦ ለክቡር መስቀሉ ምን ያህል ፍቅር እንዳላቸው በማሳየት

፪ኛ፦ በሊቢያ በሙስሊሞች ለተሰውት ሰማዕታት አስከሬን እንዴት አቀባበል እንደሚያደርጉ

በመቅሰፍት የተመታችው አዲስ አበባ መዳን የምትችለው በፖለቲከኞች የተመሰቃቀለ ጭንቅላት ሳይሆን በክቡር መስቀሉ ነው። ቶሎ እናሠራው! መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው!!!

ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አቡነ ሐብተ ማርያም ገዳም | የኢትዮጵያ ጠላቶች፡ ከጣሊያን እስከ ደርግ፡ እዚህ ምሽግ በድፍረት ሰርተው ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 3, 2019

ነገር ግን፡ ሁሉም አንድ በአንድ ተፍረከሰከሱ!

ቁጥር ፪ ቪዲዮው ላይ የገዳሙን ውብ ደን፣ የፀበል ኩሬ፣ የዘጉ አባቶች ይኖሩበት የነበርውን ቦታ ፥ እንዲሁም በተዋሕዶ ልጆች ላይ የዘመቱት የፋሽስት ጣልያን እና ደርግ መንግሥታት ገዳይ ሠራዊቶቻቸውን አስፍረውባቸው የነበሩባቸውን ምሽጎች አብረን እናያለን።

ይገርማል! እነዚህ እርኩሶች እዚህ ቅዱስ የሆነ ቦታችን ላይ በድፍረትና በንቀት ምሽግ ሰርተውበ ነበር።

አዎ! ቅዱሱ አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያም የዓለም ብርሐን ናቸው፤ ይኽው ለዘላለም ያበራል ስራቸው።

አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያም ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበራ ሳለ መብራቱ ከእጁ ወድቆ ጠፋ። ስለ መምህሩ ስለ አባ ሳሙኤል ቁጣ፣ ፍራቻ፣ ታላቅ ድንጋጤ ደንግጦ ፈጥኖ ባነሳው ጊዜ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በራ፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይተው የዚህ ቅዱስ ልጅ የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል ሲሉ ትንቢት ተናገሩ።

እንኳን አደረሰን!

የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን አሜን፡

_________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ድንቁ ደብረ መድኃኒት አቡነ ሀብተማርያም ገዳም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2018

ጥርት ያለው አየሩ፣ እዚያ ታች፡ “እርይ በከንቱ”፡ የማይታየው ብሩህ ብርሃን፣ ዛፎቹ፣ ጸጥታው፣ ሰላሙ፣ ንጽህናው፣ እዚያ ታች የጠፋው ትህትና በገዳሙ መነኮሳት እና አገልጋዮች ዘንድ ይታያልበሁሉም መልክ እጹብ ድንቅ የሆነ ቦታ ነው። በጣም ከደሰትኩባቸው ዕለታት መካከል አንዱ ነበር።

በቀጣዩ ቪዲዮ ላይ የረጅም ጊዜ ህልሜ እውን ሆኖ ለማየት ስለበቃሁበት እና እያንዳንዱ የአዲስ አበባ ተዋሕዶ ልጅ በፍጥነት ተረባርቦ በተግባር ሊያውለው ስለሚገባው ትልቅ ቍምነገር አወሳለሁ።

ኢትዮጵያዊው ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም

ወር በገባ በ ፳፮ በቤተክርስቲያናችን ታስበው ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸውን ከሰጣቸው ቅዱሳን አባቶቻችን አንዱ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ይገኛሉ ታዲያ ጻድቁ ፃዲቅ አቡነ ሀብተማርያም ማን ናቸው ? ምን ቃል ኪዳን ተሰጣቸው? እናም ያደረጉትን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት፦

አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠው ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም የነበረበት ዘመን 1486 .ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ ነው፡፡ አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባላሉ፡፡ ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡

የፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም እናት ቅድስት ዮስቴና ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያምን ከመውለዷ በፊት ሰው ሁሉ ዓለሙን ቢገዛ ነፍሱን ካጣ ምን ይጠቅመዋል የሚለውን የወንጌል ቃል ተረድታ መንና ወደ በረሃ ሄደች፡፡ በበረሃ ውስጥም ከሰው ተለይቶ የሚኖር ባህታዊ በዋሻ ውስጥ አገኘች፣ የመጣሁት ለምነና ነው ጌታ በወንጌሉ እርፍን ይዞ ወደ ኋላ የሚያርስ የለም እንዳለ ወደ ዓለም አልመለሰም አለችው፡፡ ሉቃ ፱፣፷፪

ይህም ባህታዊ ምናኔ ምንኩስና ለአንቺ አልተፈቀደልሽም ከህጋዊው ባልሽ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ እርሱም ለዓለም ሁሉ ይተርፋል በፀሎቱም ብዙዎቹን ይጠቅማል እንደ መልአክትም ክንፈ ጸጋ ተሰጥቶታል በማለት ነገራት፡፡

ቅድስት ዮስቴናም ከአረጋዊ ባህታዊ ይህን ነገር ሰምታ አደነቀች የፈጣሪዬ ፈቃድ ከሆነ ወደ ቤቴ እመለሳለሁ ብላ ወደ ቤቷ ተመለሰች፡፡ ጥቂት ጊዜያት ከቆየች በኋላ ግንቦት ፳፮ ቀን ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ተወለደ፡፡ በአባቱና በእናቱ ቤት ታላቅ ደስታ ሆነ ፵ ቀን በሞላው ጊዜ በኦሪትና በሉቃስ ወንጌል እንደተፃፈ በእግዚአብሔር ፊት ያቆሙት ዘንድ ወደ ቤተክርስቲያን ወሰዱት በተጠመቀ ዕለትም ሀብተማርያም ተብሎ ተሰየመ፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፈሪሃ እግዚአብሔር በትምህርት አደገ፡፡ ከዕለታት በአንድ ቀን ካህናቱ በቤተክርስቲያን ምህላ ሲያደርሱ እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስእያሉ ሲፀልዩ ሰምቶ በልቡናው ይህች ፀሎት በጣም ጥሩና መልካም ፀሎት ናት አለ በዚህ ፀሎት ከዓለም አሳችነት ከገሃነም እሳት እንድንባት ዘንድ አውቃለሁ የንስሐ መንገድ ናት ብሎ ተናገረ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም በዚህች ፀሎት ተጠምዶ በጾምና በፀሎት በስደት የሚኖር ሆነ፡፡

አባቱ ፍሬ ብሩክ አቡነ ሀብተማርያምን የበግ ጠባቂ አደረገው እግዚአብሔር ግን በኋላ ለብዙዎች ስውራን ቅዱሳንና በዓለም ለሚኖሩ ምዕመናን በጎች ጠባቂ ያደርገው ዘንድ ወዶ መርጦታልና ያ ቀን እስኪደርስ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይጠብቀው ነበር፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም ከአባቱ አጠገብ ተኝቶ ሳለ ‹‹ሀብተማርያም ሀብተማርያም›› የሚል ድምጽ በሌሊት ከሰማይ መጣ፡፡ አባቱ በአጠገቡ ተኝቶ ስለነበረ የጠራው መስሎት አባቴ ሆይ አለሁ ሲል መለሰ ከዚህ በፊት ቃል ከሰማይ ጠርቶት አያውቅም ነበርና እንደ ሳሙኤል ጌታዬ ባሪያህ ይሰማሃል ተናገር አለ፡፡ ሳሙ ፫፤፫ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አናገረው፡፡

ከዚህም በኋላ አባቱ ከሀገሪቱ ታላላቅ ሰዎች አንዷን እጮኛ አጨለትና ታገባለህ አለው አባታችን አቡነ ሀብተማርያም አባቴ ሆይ እኔ ራሴን ለክርስቶስ በድንግልና ለመኖር አጭቻለሁ ተራክቦዬም ቃለ ወንጌልን መስማት እንጂ ሌላ አይደለምና ለምን እንዲህ ትለኛለህ አለ፡፡ አባቱም ያለ አቡነ ሀብተማርያም ፈቃድ ሙሽራይቱን ለማምጣት ሄደ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም ሀገር ጥሎ ለመሰደድ ከቤት ተደብቆ ወጣ፡፡ መንፈስ ቅዱስም በመብረቅ አምሳል አባቱን ገሰፀው በዚህ ድንጋጤ ምክንያት የስጋ አባቱ ከዚህ ኃላፊ ዓለም አረፈ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም የአባቱን እረፍት ሳያይ አፋር ወደምትባል ሀገር ወደ አሰቦት አቡነ ሳሙኤል ገዳም ሄደ አባ ሳሙኤል ከሚባሉ ደግ መነኩሴ ቦታ ገብቶ ኖረ፡፡ በዚያም ገዳም ውሃ በመቅዳት እንጨት በመስበር፣ ልብስ በማጠብ እህል በመፍጨት አበው መነኮሳትን ሲያገለግል ኖረ፡፡ በአባታችን ላይ መነኮሳት ተቆጥተው ሲነሱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በገሃድ ተገልፃ ትገስፃቸውም ነበር፡፡

በዚህ አገልግሎት ላይ ሳለ ገዳሙ ካለበት ተራራ ላይ ወደ በረሃ ወርዶ ውሃ ቀድቶ ተሸክሞ ሲመለስ ውሃውን በእንስራ እንደተሸከመ እግሩን አደናቀፈው፡፡ የቀዳው ውሃ ሊደፋበትና እንስራውም ሊሰበርበት ሲል ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ አድነኝ ትወድቅ ዘንድ አትተዋት ብሎ ፀለየ፡፡ ይህን ብሎ በተናገረ ጊዜ የውሃዋ እንስራ ሳትወድቅ ቆመች እጅም ሳይነካት ተመልሳ በትከሻው ላይ ተቀመጠች አባ ሳሙኤልም ይከተሉት ነበርና ይህን ጽኑ ተዓምር አይተው አደነቁ፡፡ ማር ፱፡፳፫

እንዲሁ ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበራ ሳለ መብራቱ ከእጁ ወድቆ ጠፋ፡፡ ስለ መምህሩ ስለ አባ ሳሙኤል ቁጣ፣ ፍራቻ፣ ታላቅ ድንጋጤ ደንግጦ ፈጥኖ ባነሳው ጊዜ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በራ፡፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይተው የዚህ ቅዱስ ልጅ የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል ሲሉ ትንቢት ተናገሩ፡፡ በዚህችም ገዳም ፲፪ ዓመት ከትህትና ጋር እየታዘዘ ቤተክርስቲያንን እያገለገለ ኖረ፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ከአባ ሳሙኤል ገዳም ወጥቶ እለ አድባር ወደ ተባለ ገዳም ሄደ፡፡ ከአባ መልኬጼዴቅ እጅ የምንኩስናን ስርዓት ተቀበለ፡፡ ከዚያም በመቀጠል በጥልቅ ባህር ገብቶ ፻፶ መዝሙረ ዳዊትና አራቱን ወንጌልና ሌሎች የፀሎት መጽሐፍትን እየፀለየ አምስት መቶ ጊዜ ይሰግድ ነበር፡፡ እህል መብላትን ትቶ እንደ በረሃ ዋልያ ቅጠል መብላት ጀመረ፡፡ አርባ ቀን የሚጾምበት ጊዜና ሰማንያ ቀንም የሚጾምበት ቀን ነበር፡፡ ቅጠልም ቢሆን እህል ቀዝቃዛ ወይም ምንም አይቀምስም ነበር፡፡ ፊቱም እንደ ንጋት ኮከብ ያበራ ነበር፡፡

አራቱን ወንጌላት እየፀለየ ሳለ ቅዱስ ገብርኤልንና ቅዱስ ሚካኤልን በቀኝና በግራ አስከትሎ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት፡፡ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን አለው ያን ጊዜ አቡነ ሀብተማርያም ከፈጣሪው ግርማ የተነሳ ደንግጦ ከመሬት ወድቆ እንደ በድን ሆነ፡፡ ጌታችንም አንስቶ ክቡራን በሆኑ እጆቹ አፀናው ታላቅ የሆነ ቃል ኪዳንም ገባለት በፀሎትህ አምኖ በጎ ስራ ለሚሰራ ሁሉ በህይወት ሳለህ ልብስ በመስጠት ወይም ምግብ በማቅረብ፣ እግር በማጠብ፣ እንጨት ሳር በማቅረብ፣ ውሃ በመቅዳትና በመርዳት ለደከመ ሁሉ እምርልሃለሁ ዳግመኛ ከሞተ በኋላ መንግስተ ሰማያትን አወርሰዋለሁ አንተ ከሞትክም በኋላ ስምህን የጠራውን ዝክርህን ያዘከረውን ሁሉ የሀብተማርያም አምላክ ሆይ ከጠላት እጅ አድነኝ ያለኝን በህሊና ያሰበውን በልቦናው የወሰነውን እፈጽምለታለሁ አለው፡፡ ማቴ ፲፡፵፩፥፵፪

ጠላቶችህ አጋንንትን ያጠፋልህ እና ይጠብቅህ ዘንድ ቅዱስ ሚካኤል ካንተ አይለይም የሰጠሁህን ቃል ኪዳን እንዳልነሳ በራሴ ማልኩልህ ከእናትህ ማህፀን ጀምሮ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ አድርጌ መረጥኩህ እንጂ በብዙ ገድልህና በድካምህ ብቻ የወደድኩህ አይደለም፡፡ ይህን ቃል ኪዳን ከሰጠው በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር፣ በብርሃን፣ በቅዳሴ፣ በስልጣን ወደ ሰማይ አረገ፡፡

ቅድስት ዮስቴናም ባሏ ከሞተ በኋላ ለራሷ ምንም ሳታስቀር ገንዘቧን እናት አባት ለሞቱባቸው፣ ለባልቴቶች፣ ለጦም አዳሪዎች፣ ለድሆች ጨርሳ ሰጠች፡፡ በጾም በፀሎትና በስግደት ሰውነቷን አደከመች፡፡ እንዲህ ባለ ገድል ሳለች ከሰማይ እንዲህ የሚል ቃል ወደ እሷ መጣ እኔን ለማገልገል ሴቶች ወንዶች ባሮችሽን፣ ወንድሞችሽን እህቶችሽን ቤትሽን ስለ ተውሽ ሰማንያ ርስት ከተሞችን ሰባት አክሊሎችን እነሆ አዘጋጀሁልሽ አላት ደጋግ ስራን ሰርታ ከፈፀመች በኋላ አረፈች፡፡ መዝ ፻፲፭/፻፲፮ ፡ ፮ እግዚአብሔር አምላክ አስቀድሞ ተስፋውን እንደነገራት ሰባቱን አክሊላት ሸለማት ሰማንያውን አህጉራት ገነት አወረሳት፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ወደ ቤተክርስቲያን በሄደ ጊዜ ወንጌል ሲነበብ የክርስቶስ ጌትነቱን የሚናገር ወንጌል ሲነበብ ወዮሴፍ ብእሊሃ ለማርያም ፃዲቅ ውእቱየሚል ከቄሱ አፍ ይህን ንባብ ሲሰማ ደንግጦ ወንጌል ወደ ሚነበብበት ስፍራ ሄደ የሚያነበውን ቄስ ገሰጸው ወዮሴፍሰ ፈሃሪሃ ለማርያም ጽድቅ ውእቱበል እንጂ ብእሲሃ አትበል ብሎ መከረው ቄሱም አቡነ ሀብተማርያም እንዳዘዘው ከስህተቱ ወደ ቀና ንባቡ ተመለሰ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ተገልጾ ወዳጄ አመሰገንኩህ እናቴን ድንግል ማርያም ስለ አከበርክ እኔም በመንግስተ ሰማያት ፈጽሜ አከብርሃለሁ አለው፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም ከጌታ ጋር በተነጋገረ ጊዜ እንደ ነብዩ ሙሴ በፊቱ ብርሃን ተሳለ፡፡ ሰዎችም የፊቱን ብርሃን አይተው መቅረቡን ፈርተው አደነቁ፡፡ አቡነ ሀብተማርያምም ጌታ ሆይ ከንቱ ውዳሴ እንዳይሆንብኝ በፊቴ ላይ የተሳለውን ብርሃን ሰውርልኝ ብሎ ፀለየ፡፡ ጌታም ፊቱን እንደቀድሞው አደረገው፡፡ በጾም በፀሎት ላይ ሳለም በሊቀ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ወደ ሰማይ ተነጥቆ ቅዱሳን የሚኖሩባቸውን ዓለማት መንግስተ ሰማያትንና ሲኦልን ተመለከተ፡፡

ሰይጣንም መጥቶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ በሀብተማርያም ላይ መከራ አፀናበት ዘንድ ፍቀድልኝ ብሎ ጮኾ፤ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር አምላክም በሰይጣን ላይ ተቆጥቶ በነፍሱም በስጋውም መከራ ታፀናበት ዘንድ አልፈቅድም ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ መርጨዋለሁና በንፅህናና በቅድስና ኃጢአት እንዳይሰራ ዘወትር እጠብቀዋለሁ በእርሱ ላይ ብቻ ሳይሆን በሀብተማርያም ፀሎት በተማፀነኝ ሁሉ ላይ እንኳን አላሰለጥንህም ብሎ አሰናበተው ሰይጣንም ይህን ቃል ሰምቶ አፍሮ እያዘነ ሄደ፡፡ ያዕ ፩፡፲፪

አባታችን አቡነ ሀብተማርያም እንዲህ ባለ ስራ ላይ ሳለ ሰውነታቸው እንደ መርግድ የሚያሸበርቅ ዘጠኙ ክቡራን ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡ አብሯቸው ያለውን መልአክ ይህን ያህል ብርሃን የከበበው ይህ ሰው ማን ነው ብሎ ጠየቀው መልአኩም አባትህ ተክለሃይማኖት ነው አለው፡፡ ክቡር የሆነ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖት ጠርቶ ልጄ ሀብተማርያም ሆይ ፈጣሪዬ እግዚአብሔር ስለወደደህ ብዙ ምርኮ እንዳገኘህ በአንተ ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ ነገር ግን የምለምንህ ነገር አለና እሺ በለኝ አለ፡፡ አባታችን አቡነ ሀብተማርያምም ጌታዬ ነገሩ ምንድን ነው አለ? ክቡር አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም ከተቀበርኩበት ቦታ እንድትቀበር ቃል ኪዳን ግባልኝ አለው፡፡

አቡነ ሀብተማርያምም ይህንን አደርግ ዘንድ ስለምን ትወዳለህ አለው አቡነ ተክለሃይማኖትም በሀገሬ ላይ የታዘዙ አምስት መቅሰፍቶች አሉና ነው፡፡

እነሱም፡

  1. መብረቅ፣

  2. ቸነፈር፣

  3. ረሃብ፣

  4. ወረርሽኝ፣

  5. የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡

የአንተም አጽም በውስጡ የተቀበረ እንደሆነ አጥንቴ የተቀበረባት ሀገሬ ከነዚህ መቅሰፍታት ትድናለችና ልጄ ሀብተማርያም ሆይ አንተ የማታውቀው ከፈጣሪያችን ከእግዚአብሔር የተሰጠህ እኔ የማውቀው ክብር አለህና ስለዚህ ነው ቃል ኪዳን ግባልኝ ብሎ ማለደው፡፡ ይህን ሲባባሉ እንዲህ የሚል ቃል መጣ፡፡ ከወዳጄ ከሀብተማርያም አንደበት ይህ ቃል ኪዳን አይወጣም እርሱ በወደደው የሚቀበር አይደለም፡፡ እንዲህም ብለህ የምታስገድደው ለምንድን ነው እኔ በወደድሁት ቦታ ይቀበራል እንጂ የሚል ቃል ተነገረ፡፡ አባታችን አቡነ ተክለሃይማኖትም እየለመነና እየሰገደ ሶስት ጊዜ ከስላሴ ዙፋን ተንበረከከ፡፡ይሁን ይደረግ የሚል ቃል ከሰማይ ሰማ በወዳጄ በሀብተማርያም አጥንት ቦታህ የምትድን ስለሆነች ፈቃዴ ነው ብሎ ጌታ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡

ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት፡፡ እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው፡፡ የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር ፱፡፳፫

ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ፡፡

  1. ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣

  2. አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣

  3. ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣

  4. ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣

  5. ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣

  6. በጾም ስለተጋደልክ፣

  7. ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡

በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡ የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን አፉን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች መዝ ፩ + ፻፲፭/፻፲፮ ፡ ፮ በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡

የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን አሜን፡

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: