Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ገድል’

የሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዝርዎተ አጽም መታሰቢያ | ሃገርንና የቤተ ክርስቲያንን ክብር ለባዕድ አሳልፎ የሰጠ ትውልድ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 26, 2022

✞ …ዳግመኛም ያ ከሃዲ ንጉሥ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንዱ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ ፤ በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ ፤ ከዚህም በኃላ እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሠራ የስቃይ መሣሪያ ላይ አወጡት ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ፤አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ እንዲሁ አደረጉበት ነፍሱ ከሥጋው ተለየች የሰማዕቱን ሥጋ አቃጠሉት ፈጩት አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው ወታደሮቹ የታዘዙትን ፈጽመው ተመለሱ። ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሠረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በብሩህ ደመና ወረደ በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማዕቱን ሥጋ እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ፤ ከዚህ በኃላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው ህልቶን፤አግሎሲስ፤ሶሪስና አስፎሪስ ነው፤ ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፤ በኃላም በሰማዕትነት ሞተዋል፤ ይህ የሆነው ጥር 18 በዛሬዋ ቀን ነው ይህንንም ቀን ” ዝርዎተ አጽሙ ” ስትል ቤተክርስቲያን ሰማዕቱን አዘክራ ትውላለች፤ በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ሕጉ ወጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል። አራዳ ጊዮርጊስን የተከሉት ደጉ ንጉሥ እምዬ ምኒልክ ናቸው ታዲያ የዚህን ታላቅ ደብር መሠረቱን ሲጥሉ የቅዱስ ጊዮርጊስ መቃብር ከሚገኝበት ቦታ አፈሩን በመርከብ አጓጉዘው በበቅሎ በፈረስ አስጭነው መሠረት አድርገውታል፤ ይህንን ከአባቶቻችን የሰማነው ነው፤ ከበዓሉ በረከት ያሳትፈን። [ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምዕራፍ ፮፥፲፭፡፲፰]

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

ከኢትዮጵያ ጠባቂ እረኞች አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው

የጊዮርጊስ ወዳጂ የት ነው የሚገኘው

በመሃል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው

ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው፡፡

ይነሳ ጊዮርጊስ ይመስክር ምስጢር

የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በስማችሁ ብዙ ተአምራትን ያደረገና ‘ኮከብ ክብር’ የተባለ የሰማዕታት አለቃ በሚሆን በኃያሉ በቅዱስ ጊዮርጊስ ላይ ለመፍረድ በልዳ ሀገር የተሰበሰቡትን ፯ (ሰብዓ) ነገሥታትን ደምስሰው እንዳጠፏቸው፡ የተነሱብንን የጽዮንን ተቃዋሚዎች፣ የኔንም/የኛንም ጠላቶች ሁሉ ይደመስሱልን ዘንድ እማፀናለሁ። አሜን! አሜን! አሜን! ❖

_______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: