Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ገድለ አቡነ አረጋዊ’

አቡነ አረጋዊ | ትግራዋዩ እንጀራ ሻጭ ወጣት ቤተክርስቲያኑን በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ እንዲቀባ በራዕይ ታዘዘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 22, 2021

ትዕዛዙንም በሥራ ላይ አዋለው። ይህችን ውብ ቤተክርስቲያን በቀለሞቻችን እንዲቀባት ራዕይ የታየው ወንድማችን እንጀራ ጋግሮ በመሸጥ የሚተዳደር ወጣት ነው። ቤተክርስቲያኗን እና አካባቢዋን ከቀባ በኋላ በዚሁ በሳሪስ አቦ ኮረብታ ላይ በ አዲስ መልክ ለሚሰራው ለ አቡነ አረጋዊ ቤተከርስቲያን ህንፃ የግንብ አጥር በመገንባት ላይ ይገኛል።

በእውነት የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው!

❖ ❖ ❖ የደብረዳሞው ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ የእመቤታችን የአሥራት ሃገር የሆነችውን እናት ኢትዮጵያን ያጸደቋት፣ በአባታችን በኖህ በኩል ያገኘናቸውን የጽዮን ማርያም ቀለማትን ለዓለም ያሳዩ ድንቅ አባት ናቸው።

ጻድቁ አባታችን አቡነ አረጋዊ ዛሬ በተለይ በትግራይ በበደልና ግፍ ከሚሰቃዩት አባቶቻችን እና እናቶቻችን፣ ወንድሞቻችን እና እኅቶቻችን ጋር ናቸው፤ ረድኤት በረከታቸው ለሁላችን ይድረሰን!

💭 ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ሰሞን የሚከተለውን ጽፌ ነበር፦

👉 በተዋሕዶ ልጆች ላይ በኦሮሚያ ሲዖል እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ በግራኝ ዐቢይ አህመድ መስተዳደር በደንብ ተጠንቶበትና በቅደም ተከተልም እንደሚካሄድ በአርሲ ነገሌ የተፈጸመው ጂሃዳዊ ዘመቻ ይጠቁመናል።

እስኪ ተመልከቱ፦ አታላዩ ዐቢይ አህመድ አገር-አቀፍ ምርጫውን ከግንቦት ወር አንስቶ የክረምቱንና የፍልሰታ ጾም ሳምንታት በመጠቀም ወደ ነሐሴ መጀመሪያ አዘዋውሮት ነበር ከዚያም ነሐሴ መጨረሻ እንዲሆን ወሰነ። ኮሮና ከመምጣቷ በፊት ይህ ምርጫ እስኪደርስ ድረስ አሁን በምናያቸው ሁለት ጉዳዮች የሕዝቡን ቀልብ ለመግፈፍ አቀዱ። እነዚህም፦

👉 ፩ኛ. የሕዳሴውን ግድብ በሐምሌ ወር ላይ “እንሞላዋለን ፥ አንሞላውም”

👉 ፪ኛ. አጫሉን ገድሎ ጂሃድ ማካሄድ”

💭 ኦሮማራዎች እና አህዛብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነቱን እንደከፈቱ ደግሞ ይህን ጠቁሜ ነበር፦

👉“እናስታውሳለን ባለፈው ዓመት ላይ ምርጫውን መጀመሪያ ላይ ሆን ብሎ በፍልሰታ ጾም ወቅት ለማድረግ ወስኖ እንደነበር። አዎ! ዛሬ ደግሞ ልክ በዕለተ አቡነ አረጋዊ ሲውልና የገና/ የነብያት ጾም ሲቃረብ የተዋሕዶ ልጆችን ለመጨፍጨፍ በመዛት፣ በማሸበር እና በመሰናዳት ላይ ነው። “ደብረ ዳሞ!””

“Nobel Peace Laureate Treating a Whole City as a Military Target | War Crimes”

ዋው! ፋሺስቱ ሙሶሊኒ እና ናዚው ሂትለር እንኳን ለመናገር ያልደፈሩትን ነገር ነው እነዚህ አውሬዎች በመናገር ላይ ያሉት!

👉 ግራኝ ሰኔ ፲፬/14ትን ለ’ምርጫው’የመረጠበት ‘ምስጢር’አቡነ አረጋዊ + ጾመ ሐዋርያት (የሰኔ ጾም)

💭 ዘንድሮም እባቡ ግራኝ እና መንጋው ኢትዮጵያን በብርሃን ፍጥነት እያፈራረሱ በሚያንቀላፋው ሕዝብ ላይ ተመሳሳይ ድራማዎችን በመሥራት ላይ ይገኛሉ። ልክ ከወር በኋላ በኦሮማራ ቃኤላውያኑ ተከታዮቹ “ተመርጫለሁ” የሚሉበትን “የምርጫ ቀን” ሆን ብሎ በማዛወር ሰኔ ፲፬/14የሰኞ ዕለትን መርጠዋል። አዎ! ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ከቤታቸው እና ከቤተ ክርስቲያናቸው የማይርቁበትን የጻድቁ አባታችን የአቡነ አረጋዊ ዕለትን። ጾመ ሐዋርያት(የሰኔ ጾም)የሚገባውም በዚሁ ዕለት ነው።

ኃይለኛ መንፈሳዊ ውጊያ ላይ ነን!!!

👉 “አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል”

❖ “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” [ኤፌሶን ፮፡፲፪]

👉 ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – (ተክለሃይማኖት ነው) ሰበታ የሚገኘው የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ወደመ።

👉 ጥር ፲፬ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – ስለዚህ ቆሼ አስከፊ ቆሻሻ ሽታ እንዲሁም አካባቢው በመስጊድ ጩኽት ስለመበከሉ፤ ብሎም ዲያብሎስ እንደዚህን በመሳሰሉት መሰናክሎች በኩል ምዕመናኑን እየተዋጋ ከቤተክርስቲያን በማራቅ ከክርስቶስ ለመለየት እነደሚሞከር አወሳን።

👉 መጋቢት ፪ ቀን ፳፻፱ ዓ.ም – በተለምዶ ቆሼ ሚባለው ስፍራ የተከሰተው አሳዛኝና አስደንጋጭ ዜና በመላው ዓለም መነጋገሪያ ለመሆን በቃ።

👉 በሰበታ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ቃጠሎ ሙሉ በሙሉ ስትወድም ጽላቶቹ ግን በተአምር አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ተገኝተዋል

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይግቡ፦ (ቪዲዮዎቹን ሌላ ጊዜ እንደገና አቀርባቸዋለሁ)

👉 “የአማሌቃዉያን ጂሃድ በአርሲ| መሀመዳውያን በነጌሌ ከተማ የሚገኘውን መስቀል ማየት የለብንም ብለው አነሱት”

“ጂሃድ በአርሲ | መጀመሪያ መስቀሉን አነሱ ፥ ዝም ተባሉ ፥ አሁን የመሰቀሉን ልጆች እያረዱ ነው”

አርሲ ነገሌ ቡሄ ፪ሺ፲፪ ዓ.ም

የተዋሕዶ ልጆች ዝምታ ብዙ መስዋዕት እያስከፈለ ነው!

በራዕይ የታየው ትግራዋይ ኢትዮጵያዊ | የአቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያንን በጽዮን ቀለማት ቀባው ክፍል ፩ ❖

👉 በክፍል ፩ ቪዲዮ የቀረበ ጽሑፍ፦

❖ አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን(አዲስ አበባ-ሳሪስ)

መስከረም ፪ሺ፯/2007 ዓ.ም(ያለ ጽዮን ማርያም ቀለማት) አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን (አዲስ አበባ-ሳሪስ)

❖ መስከረም ፪ሺ፲፩/2011 ዓ.ም (ከጽዮን ማርያም ቀለማት ጋር)

አንድ ባካባቢው የሚኖርና እንጀራ በመሸጥ የሚተዳደር ትግራዋይ ወጣት የቤተ ክርስቲያኗን ጣራ በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማት እንዲያስቀባ በታየው ራዕይ በመታዘዙ በራሱ ወጭ እንዲህ አሳምሮ አስቀብቶታል። (ድንቅ ነው!)

👉 በትናንትናው የአቡነ አረጋዊ ዕለት፤ የነነዌ ጾም በሚገባበት ወቅት፤ የአህዛብ የጥፋት (ሰ)አራዊት በትግራይ ላይ የመጨረሻ የሚሆነውን ጭፍጨፋውን ማጧጧፉና ወደ ተከዜ ግድብ ማምራቱም በደንብ ታስቦበት ነው።

በአቡነ ተክለ ሐይማኖት ዕለት በትግራይ ላይ የክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ የኢትዮጵያ ጠላቶች የጀመሩት ስጋዊ ጥቃት ለምን አክሱም ጽዮንን፣ ደብረ አባይን እና ደብረ ዳሞ ገዳማትን አስቀድመው ማጥቃት እንዳስፈለጋቸው ሁላችንም እያየነው ነው። ይህ ከዚህ በፊት በሺህ አራት መቶ ዓመታት ውስጥ ያልታየ ክስተት እንደሆነ ልብ እንበለው።

ዘንድሮ በትግራይ ላይ የተከፈተው ጥቃት ከመቶ ሰላሳ ዓመታት በፊት ኤዶማውያኑ አውሮፓውያንና እስማኤላውያኑ አረቦች በአፄ ምኒሊክ በኩል የጀመሩትን ጥቃት አጠናክሮ የቀጠለ ነው። በተለይ ኤርትራ እና ጂቡቲ በክርስቶስ ተቃዋሚው ኃይል ቁጥጥር ውስጥ እንዲገቡ ሲደረጉ ልክ ዛሬ አህዛብ መናፍቃኑ ግራኝ አብዮት አህመድ እና ኢሳያስ አፈቆርኪ ተግተው በስኬት እየሠሩት እንዳሉት ፥ ዋናው ዓላማቸው፤

፩ኛ. ኢትዮጵያዊነትን

፪ኛ. አክሱም ጽዮንን(ጽላተ ሙሴን)

፫ኛ. አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቁን

፬ኛ. ተዋሕዶ ክርስትናን

❖ የኢትዮጵያና ተዋሕዶ ክርስትና የጀርባ አጥንት ከሆኑት ከትግራውያን መንጠቅ ነው።

👉 በዚህም ተጠቃሚዎቹ፤

፩ኛ. ኢትዮጵያ/እስራኤል ዘ-ስጋ

፪ኛ. አህዛብ የዋቄዮ-አላህ ልጆች

፫ኛ. መናፍቃን

፬ኛ. ኢ-አማንያን

፭ኛ. ሰዶምና ገሞራ(ግብረ-ሰዶማውያን)

👉 ሁሉም ኢ-አማንያን 666 የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ናቸው።

ጽላተ ሙሴን የአክሱም ጽዮን ልጆች ውስጥ እንደተቀበረ አድርገን እንውሰደው። ምዕራባውያኑ የቴክኖሎጂው ባለቤቶች የጽላቱን ‘ጨረር’ እያንዳንዱ ያልተበከለ የአክሱም ጽዮን ልጅ ውስጥ እንዳለ የመለካት/የማየት ችሎታው/አጋጣሚው አላቸው። ይህንንም ጨረር ከግለሰቦቹ ፈልቅቀው ለማውጣት (ጽላተ ሙሴን ለመስረቅ) እንደማይቻላቸው አይተዋል። ስለዚህ ልክ የአውሬውን 666 ምልክት በፈቃዱ ግንባሩና እጁ ላይ ለማስቀበር እንደሚሻው የወደቀ ሰው እያንዳንዱ የጽላተ ሙሴ ‘ተሸካሚ’ የአክሱም ጽዮን ልጅም ኢትዮጵያዊ መልኩን፣ ተዋሕዶ እምነቱንና ሰንደቁን በፈቃዱ እንዲያስረክብ የተለያዩ ፈተናዎችን እያቀረቡለት ነው። ዛሬ በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት ከመቶ ሰላሳ ዓመታት በፊትም በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት(አደዋ)ቀጣይ ደረጃ ነው። ያኔ አባቶቻችን እና እናቶቻችን ኢትዮጵያዊነታቸውን፣ ተዋሕዶ እምነታቸውንና ጽዮን ማርያም እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ያስዋቡትን ሰንደቃቸውን ለጥያቄ እንኳን አቅርበዋቸው አልነበረም፤ በዚህም እስካፍንጫው የታጠቀውን ወራሪ የዔዶማውያን ኃይል ድል ሊያደርጉት ተችሏቸው ነበር።

ይህ ትውልድም እራሳቸውን ለአውሬው አሳልፈው በሸጡ ደካሞች ተንኮል ሳይታለልና ሳይሸነፍ “እምብዬው ማንነቴንና ምንነቴን አሳልፌ አልሰጥም!” ማለት አለበት። አልያ ከኢርትራውያን የከፋ ዕጣ ፈንታ ነው የሚደርሰው።

ከአድዋው ድል በኋላ የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ደቡባውያን(ጋላማሮች)ኢትዮጵያን መረከብ እንደጀመሩ የአደዋውን ድል የመንፈስ ማንነትና ምንነት ያላቸው የአክሱም ጽዮን ልጆች እንዳስገኙት በመገንዘባቸውና እነርሱንም/ይህንም ለመዋጋት በክህደት ወደ አህዛብ እውቀትና ጥበብ በመዞር በተለይ ኤዶማውያኑን አውሮፓውያኑን በጣም ማስጠጋት ጀመሩ። በመጀመሪያ ያኔም አፄ ምንሊክ ኤርትራንና ጂቡቲን ለአውሮፓውያኑ አሳልፈው በመስጠት የሞትና ባርነቱን መንፈስ ወደ አክሱም ጽዮን ለማምጣት ከኤዶማውያኑ ጋር አስቀድመው ተፈራረሙ፤ በስምምነቱም ጦርነቱ በደቡብ ኢትዮጵያ ሳይሆን ልክ እንደ ዛሬው በአክሱም/አደዋ እንዲካሄድና የአክሱም ጽዮን ልጆች ጦርነቱን ተከትሎ በሚመጣው ጥፋትና ውድመት ለዘመናት ተቸግረውና ተጎሳቁለው እንዲኖሩ ተደረጉ።

ከአርባ ዓመታት በኋላም ፋሺስቱ ሙሶሊኒ በተመሳሳይ መልክ ወደ አክሱም ጽዮን ተመልሶ ተምቤንና አካባቢዋን በኬሚካል ቦምብ ጨፈጨፋቸው።

ዛሬም ፋሺስቶቹ ግራኝ አብዮት አህመድና ኢሳያስ አፈቆርኪ የኤዶማውያኑን ተልዕኮ ለማስፈጸም በደቡብ ኢትዮጵያ ሳይሆን አሁንም በአክሱም ጽዮን ላይ ጭፍጨፋውን ተያይዞታል። አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ በትግራይ ሕዝብ ላይ በጣም አደገኛ ኬሚካሎችንና ራዲዮ አክቲቭ ዝናቦችን በኤሚራቶች ድሮኖች አውርዶባቸዋል፤ ኤሚራቶች ከአሰብ ተጣድፈው የወጡት ለዚህ ነው! ገለልተኛ መርማሪዎችንም የማያስገባው ይህ እጅግ በጣም አስከፊ ወንጀል ስላስደነገጠው ነው። በእኔ በኩል ገና ከዓመት በፊት ግራኝ የኑክሌር ወይንም የኬሚካል መሳሪያዎችን ካገኘ ሰሜን ኢትዮጵያን ላይ እንደሚጠቀምባቸው በደንብ ታይቶኝ ነበር። ይህ አውሬ እጅግ በጣም አረመኔ እንደሆነ ገና ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳየሁት ነበር የተገለጸለኝ።

_______________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያን አገራችንን አሁን ላለችበት ውድቀት የዳረጓት የዲያብሎስ ማደሪያዎቹ አህዛብና መናፍቃን ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 22, 2021

ግሩም ትምህርት ነው፤ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ለአስተማሩን ወንድማችን! 

ኢትዮጵያን አገራችንን አሁን ላለችበት እየዳረጓት ያሉት የዲያብሎስ ማደሪያዎቹ አህዛብና መናፍቃን ናቸው፤ ሁለቱም ዲያብሎስን ነው የሚያመልኩት”።

ትክክል! ኢትዮጵያ ወደ ጥፋት የተጓዘችው እንዲህ ዓይነት ውድቀት ውስጥ የገባችው አህዛብና መናፍቃን በዙፋኖቿ ላይ መደላደል ከጀመሩ በኋላ ነው። የጥፋት አሰራሩ እየተፋጠነ የመጣው በተለይ ከአደዋው ጦርነት በኋላ በአፄ ምንሊክ እና በዘመናችን ሔዋን በሴቲቱ እቴጌ ጣይቱ ብጡል አማካኝነት ነው።

አፄ ምኒልክ ለአህዛብአውሮፓውያኑ ማንነትና ምንነት እጅግ ጥልቅ ፍቅር ነው የነበራቸው። ምንሊክ ኢትዮጵያዊ ማንነትና ምንነት የሌላቸው “ዲቃላ/ባሪያ” እንደነበሩ ስራቸውና ባህሪያቸው ብሎም ድርጊታቸውም ይመስከክርላቸዋል። ምንሊክ የአህዛብአውሮፓውያኑን የመንግስት ህግና ሥርዓት “እግዚአብሔር” ብለው ያመልኩት ነበር። ልክ እንደ እስራኤል ልጆች “እርሱ እግዚአብሔር ነው” ብለው በእኛ ላይ ይንገስብን ያሉት ይህን የአህዛብን የስጋ ህግና ሥርዓት ነበር። ይህም ማለት አፄ ምንሊክ “እግዚአብሔር” የሚሉት “ዲያብሎስ ሰይጣንን” እንደነበር በደንብ ይመሰክርልናል። ከ አፄ ዮሐንስ ጋር በዚህ ጉዳይ ብዙ ጊዜ ይጋጩ ነበር። አፄ ዮሐንስ ምንሊክ በሸዋ ውስጥ የሚያኖሯቸውን አህዛብ የውጭ ሀገር ዜጎች እንዲያስወጡ አድርገዋል።

ጸሐፊ ጳውሎስ ኞኞ፤ “አጤ ምንሊክ” በሚለው መጽሐፋቸው ምንሊክ ባዕዳውያኑ አህዛብን እንዲያስወጧቸው አፄ ዮሐንስ እንደጠየቋቸው እንዲህ ሲሉ መልስ መስጠታቸውን ጠቅሰው ነበር፦ “ሚስተር ጆን ሜየር ሸዋ ካለው የቅዱስ ክሪስኮና ሚሲዮን ለመደባለቅ ወደ ሸዋ ሔደ። መሄዱን አጤ ዮሐንስ እንደ ሰሙ በሸዋ ያሉትን ኤሮፓውያን በሙሉ እንዲያስወጡ ምኒልክን ጠየቋቸው። ምኒልክም “አገሬን ከኤሮጳውያኖች ለይቼ ልዘጋት አልፈልግም። ምክኒያቱም እወዳቸዋለሁ” ብለው መለሱላቸው…” ዋልድሜየር። “እወዳችዋለሁ”፤ ለምን ይህን የጥፋት ማንነትና ምንነት ወደዱት? ምን ማለትስ ይሆን? መልሱ፤ የስጋ ልጅ ስለሆኑ የሚል ይሆናል። የተቀደሰችውን የኢትዮጵያን ምድር በር ወለል አድርገው ከፍተው ለአህዛብ እና መናፍቃን መጫወቻ ያደረጓት ምንሊክ ነበሩ። ህዝቡና ካህናቱ፣ ሊቃውንቱ፣ ባላባቱና መኳንንቱ ሁሉ “ኧረ ኡ ኡ ኡ!” እያሉ በአደባባይ ህጓን፣ ክብረ ንጽህናዋን በአውሮፓውያን ያስወሰዱ ክብረቢስ ወራዳ ንጉስ (ዲያብሎስ) ነበሩ። ያሳዝናል። “እኔ ብቻ አዋቂ፣ እኔ ብቻ ጠቢብ፣ እኔ ብቻ ኃይለኛ ብለው እስከ ዛሬ ድረስ የዘለቀ የሞትና ባርነት ማንነት በኢትዮጵያውያን ላይ አመጡባቸው፤ ሁሉን ዛሬ ለምናየው ሞት ዳሩት።

ለእግዚአብሔር ስምና ክብር በተለየ ሕዝብ ላይም ይሁን በተለየች/በተመረጠች ምድር የዲያብሎስ መንግስት የሚነግሰው በአህዛብ መንግስታዊ ሥርዓት በኩል መሆኑን በሳኦል ታሪክ በኩል ማየት እንችላለን። በምስክሩ መዝሙርም በኩል “እግዚአብሔር አምላክ ለእርሱ ስምና ክብር ለተጠራ ሕዝብ ሞትና ጥፋት ይሆንበታል” ያለው አህዛብ የተባሉትን ሕዝቦች የመንግስት ህግና ሥርዓት መሆኑን እናስተውለው።

የአህዛብን ዕውቀት፣ ጥበብና ኃይልም በተቀደሰችው ምድር ላይ እንደ “መንግስት” ያነገሱት ምኒልክ ነበሩ። ምንም እንኳ ውጥኑና ጅማሮው በፄ ቴዎድሮስ የተተለመ ቢሆንም ፍጻሜውን ያገኘውን ሁሉንን እንደሚገዛ መንግስት በዓለም ሁሉ ላይ የነገሰው በምኒልክ መንግስት ህግና ሥርዓት በኩል ነበር። እግዚአብሔር አምላክ “ሞትና ባርነት” ያለውን የዲያብሎስን መንግስት ህግና ሥራዓት በኢትዮጵያ መንግስታዊ ዙፋን ላይ ቀብተው ያነገሱት ምኒልክ ነበሩ።

አፄ ምኒልክ የዲያብሎስ ማደሪያዎች ለሆኑት መናፍቃን፣ አህዛብ የዋቄዮአላህአቴቴ ልጆች እጅግ ትልቅ፣ ትልቅ ባለውለታ ናቸው። ኦሮሞዎቹ የምኒልክ ጠላት እንደሆኑ ለእኛ የሚያሳዩን አንዱ የዲያብሎስ አቴቴ ስልታቸውን ሊጠቀሙብን ስለሚሹ ነው። ይህም ተዋሕዶ ክርስቲያኑን በተለይ ትግራዋይኑን እና አማራውን እንደ ሴት እና ሕፃን ልጅ “ተቃራኒውን” ነገር በመስራት “ተቃራኒ” የሆነ እንዲሰሩላቸው በመሻት ነው። አፄ ምኒልክን አስመልክቶ በአማራዎች ላይ እስካሁን በደንብ እየሰራላቸው ነው። ኦሮሞዎች አፄ ምኒልክን “ጡት ቆራጭ ነበሩ፤ ኃውልታቸው መወገድ አለበት፣ ለእቴጌ ጣይቱም ኃውልት አነስሰራም፣ እኛ ግን የአኖሌን የጡት ኃውልት እንተክላለን ወዘተ” ማለታቸውት በሴቲቱ “ሔዋን/አቴቴ በኩል የእቴጌ ጣይቱን ንግሥትነት ከፍ ከፍ ማድረጋቸው ነው። አፄ ምኒልክም ከወንድ ይልቅ ሴት እንድትነግሰ መሻታቸው ይህን ያረጋግጥልናል።

በእቴጌ ጣይቱ ብጡል ሲነዱ የነበሩት አፄ ምኒልክ እግዚአብሔር አምላክን በመካድ ከደጋማውና ተራራማው ከእንጦጦ የተቀደሰ ቦታ ወርደው በአዲስ አበባ ንጽጽረንት “ቆላማ/በርሃማ” ወደሆነው ወደ ፍልውሃ በመውረድ፤ መጀመሪያ እቴጌ ጣይቱ ፍልውሃ ምንጭ አጠገብ አካባቢውን “ፊንፊኔ” የሚል መጠሪያ ሰጥተው ለራሳቸው ቤት ሠሩ፤ ከዚያም የምኒልክን ቤተ መንግስት በአህዛብአውሮፓውያን አሳነጹ። ይህም አንድ ሌላ ማረጋገጫ ነው። ኦሮሞዎችም ይህን የአቴቴ መንፈሳቸውን ተከትለው አዲስ አበባን “ፌንፊኔ፣ ፌንፊኔ” በማለት ላይ” የሚገኙት ዲያብሎስን ለማንግስ ሲሉ ነው። ያው በግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ባለቤት በአቴቴ ዝናሽ በኩል ስራቸውን በመስራት ላይ ናቸው። ናዝሬትንም “አዳማ” ደብረ ዘይትንም “ቢሸፍቱ” ያሉበት ምክኒያት ከናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ እነዚህን ሁለት ዝቅተኛ/ቆላማ ከተማዎች ለዲያብሎስ ዋቄዮአላህአቴቴ የደም ግብር የመስጫ ቦታዎች ሁሉ መዲናዎቻቸው ይሆኑ ዘንድ ነው። በደብረዘይት(ሆራ)የአየር መንገዳችንን አውሮፕላንን አስከስክሶ የመቶ ሃምሳ ሰባት ሰዎችን ነፍስ ለዲያብሎስ አባታቸው ሰውቷል። ባለፈው ዓመት በትንሣኤ (ቀዳሚት ሰንበት) ናዝሬት/አዳማ ዲቢቢሳ ቅዱስ ዮሃንስ ቤተክርስቲያን የሰንበት ትምህርት ቤት አባል የሆኑትንና ለዋቄዮአላህአቴቴ አንታዘዝም ያሉትን ስድስት ኦሮምኛ ተናጋሪ ልጃገረድ እህቶቻችንና እና አንድ ወንድማችንን እንዲሁ በጋዝ አፍነው በመግደል የደም ግብር ለዋቄዮአላህአቴቴ አቅርበውላቸዋል።

አማራውንም የምኒልክ “አምላኪ” እንዲሆን ያደርጉባት ዋናው ስልታቸው የምኒልክ ጠላት በመሆን በእልህ፤ በአቴቴ የእልህ መንፈስ ከአፄ ምኒልክ ጋር ተጣብቀው በመቅረት እንደ ሴትና እንደ ህፃን ተቃራኒውን እየሰሩ የዲያብሎስን ስራ ይሰሩላቸው ዘንድ ነው፤ ዲያብሎስን ያመልኩ ዘንድ ነው። “የተከለከለ ነገር ኹሉ ይጣፍጣል ፥ የሌላ ሰው ውኃ ማር ማር ይላል”፡ እንዲሉ። (በኦሪት ዘፍጥረት የዕፀ በልሱ ህግ የሴቲቱ ሔዋን የገዥነት ስምና ክብር የተዘጋጀበት የዲያብሎስ መንግስት ህግና ሥርዓት ነው። በዚህ የሞት ህግ የወንድ ልጅ የገዥነት ስምና ክብር አልተዘጋጀም። የምኒልክ አዋጆችና ተግባራት የወንድ ልጅን ሞትና ባርነት የሚያውጅ የሴቶች የበላይነት የመንግስት ግና ሥርዓት ነበር። ምክኒያቱም የአዳም “ሞት” የተባለው ይህ የዕፅዋት ህግ ነውና። “ይህን የዛፍ ፍሬ አትብላ” የሚለው ሕግ የተሰጠው ለሔዋን (ሴት) ሳይሆን ለአዳም (ወንድ) ነበርና። 

የዲያብሎስ አምላኪው አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ባለፈው የአደዋ ክብረ በዓል ላይ የአፄ ምኒልክን ምስል ተክቶ የራሱን የሰቀለበት ትልቁ ምስጢር ከዚህ ጋር የተያያዘ ነው።

ቀዳማዊት እቤት” በሚሏት በባለቤቱ በሴቲቱ ሔዋን በአቴቴ ዝናሽ አህመድ አሊ የሚመሩት የአማራ ሚሊሺያዎች በትግራይ የሰሩትን ባይተዋር የሚመስል ወንጀልና “’አንድ የትግራይ ማህፀን በጭራሽ መውለድ የለበትም’ እያሉ በእኅቶቻችን ላይ የሚፈጽሙት ዲያብሎሳዊ ተግባር ከዚሁ ከዋቄዮ-አላህ-አቴቴ-ምኒልክ-ጣይቱ መንፈስ የተገኘ ስለሆነ ነው። በጭራሽ ኢትዮጵያዊ አይደለም! ለዚህ ነው ዛሬ፻/100% እርግጠኛ ሆኜ ትግራይን ክፉኛ እየጨፈጨፈችና በመላዋ ሃገሪቷ በመግደልና በማፈናቀል ላይ ያለችው ምስኪኗ ቅድስት “ኢትዮጵያ” ሳትሆን እርኩሷና ዲያብሎሳዊቷ “ኦሮሚያ” ነች የምለው።

በትግራዋያንም ላይ ተመሳሳይ “ተቃራኒውን አድርግ” የተሰኘ የአቴቴ ስልት ለመጠቀም በመሞካከር ላይ ናቸው። ለምሳሌ፤ ቤተ ክርስቲያን ጭፍጨፋውን አስመልክቶ ዝም እንድትል መደረጓ። ሌላው ደግሞ በቅርቡ በመቀሌ ከተማ የአረመኔው ግራኝ የዋቄዮ-አላህ-አቴቴ ሰአራዊት አባላት በከተማዋ እየተዘዋወሩ የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የህወሃት ባንዲራ እያነቀሉ ሲቦጫጭቁ የሚያሳይ ቪዲዮ ታይቶ ነበር። አዎ! እዚህም ላይ ትግራዋይን እልህ ውስጥ አስገብቶ ከዚህ የዲያብሎስ ሉሲፈር ባንዲራ እንዳይላቀቁና ለወደፊትም የሃገር ባንዲራ እንዲያደርጉትና በዚህም ዲያብሎስን ያመልኩ ዘንድ ነው ነው። እካሄዳቸው ሁሉ ልክ እንደ እባብ ነው፤ ለእባብ መርዝ መድኃኒቱ የራሱ የእባቡ መርዝ ነውና እኛም እንደ እባብ ልባሞች (ለጠላት) እንደ ርግብም የዋሆች (ለወዳጅ) ልንሆን ይገባናል።

ለዛሬ ይበቃኛል! ቸር አውለን!

የአባታችን የአቡነ አረጋዊ ረድኤት በረከት አይለየን በፀሎታቸው ይማሩን!

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: