Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ጀልባ’

ከኻዲው ግራኝ የክርስቶስን እና ጀልባውን ታሪክ ያነሣው ወደ ኤርታ አሌ እሳት ስለሚጣል ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 19, 2021

😈 የበሻሻውን ቆሻሻ! የወራዳውን፣ አረመኔውና ከሃዲውን የግራኝ አብዮት አህመድ አሊን እና ሕዝበ ክርስቲያኑን በማስጨረስ ላይ ያሉትን ጭፍሮቹን አውሬነት ዘርዝሬ ለመግለጽ በቂ ቃላት ማግኘት አልችልም። ይህ አውሬ አሁን ክርስቲያን ኢትዮጵያን አውድሞ፣ አፈራርሶ እና ኦሮሞን አንግሦ እንዲሁም የድኻውን ኢትዮጵያዊ ወርቅና ገንዘብ ሁሉ ዘርፎ ለመሸሽ በመዘጋጀት ላይ ነው። ሆኖም የትም አያመልጣትም፤ የተሳፈረባት ጀልባ እየሰጠመች ነው፣ የገባበት ቢገባም እንደ አክዓብ እና ኤልዛቤል እንደሚገደልና ስጋውም ለውሾች ተሰጥቶ እጅግ ዘግናኝ ሞትን እንደሚሞት ከወዲሁ ይወቀው።

💭 የሚከተለውን ጽሑፍ እና የሥላሴ ተዓምርን፤ ግራኝ ያን አውሬው ብቻ ለመናገር የሚደፍረውን ንግግሩን ከማሰማቱ ከሁለት ወራት በፊት ነበር ያቀረብኩት፤

ይህ በዛሬው በሥሉስ ቅዱስ ዓርብ ዕለት የምናነበው ተዓምር የግራኝ አብዮት አህመድን እና ጭፍሮቹን ማንነት እና እጣ ፈንታቸውን በከፊል ይገልጥልናል።

ቀደም ሲል ጄነራል ጻድቃን አዲስ አበባ እያሉ ለፋሺስቱ የኦሮሞ አገዛዝ መሪ ለግራኝ አብዮት አህመድ ትግራይን እንዳይተናኮል እና በሕዝቡም ላይ ጦርነት እንዳይከፍት፣ ሕዝቡን ፈጽሞ ማንበርከክ እንደማይቻል መክረውት እንደነበር ሰምተናል። ግራኝ ግን የመለሰላቸው፤ “በገንዘብ እና በጦር ኃይል የማንበረከክ ሕዝብ የለም!” በማለት ነበር መልስ የሰጣቸው።

ጄነራል ጻድቃን እና ባልደረቦቻቸው አሁን ወደ ማንነታቸው ተመልሰዋል ለሥላሴ ይሰግዳሉ፣ ጽዮን ማርያምን ይማጸናሉ የሚል ተስፋ አለኝ። ከዚህ ሁሉ ዕልቂትና ጥፋት በኋላ ዛሬም ይህን ካላደረጉ ግን የትግራይን ሕዝብ ሊመሩት አይችሉምና እነርሱ ለንስሐ የሚያበቃቸውን ገድል ፈጽመው ከአመራርነት በክብር እንዲሰናበቱ ይደረጋሉ፤ ከዚያም የከንቱ ምድራዊ ርዕዮተ ዓለም ባሪያ ያልሆነና ለሕዝቡ የቆመ ጽዮናዊ የሆነ መሪ ይነሳ ዘንድ ግድ ይሆናል።

አንጐት = ጨለቖት

የተረፈው አስተዋዩ፣ ታማኙ ነጋዴ = በቅድስት ሥላሴ ፍቅር የተጠመደ ጽዮናዊ መሪ

😈 በገንዘብ ፍቅር ተታለው ነፋሱ ጠራርጎ ያጠፋቸው ከሃዲዎቹ ነጋዴዎች = ግራኝ አሊ ባባ እና የዋቄዮአላህ ጭፍሮቹ

❖❖❖የሥላሴ ተአምር❖❖❖

. ይቅርታቸውና ሀብተ ረድኤታቸው በወዳጃቸው…….ላይ ይደርና የአብ የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ተአምራታቸው ይህ ነው።

. አንጐት በሚባል አገር ብዙ ነጋዴዎች ነበሩ።

. እኒህ ነጋዴዎች ኢየሩሳሌም ወርደው በሥላሴ ሥዕል እነሆ እንዲህ ሲሉ ተማፀኑ።

. ከሄድንበት ሀገር ከጥልቅ ባሕር መሰጠምና መርዘኛ ከሆነው ከአዞ መበላት ወይም መነከስ ድነን በሰላም ወደ ቤታችን ብንመለስ።

. እነሆ ከአተረፍነው ትርፍ ወርቅና ብሩን ግማሽ በግማሽ ለሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንሰጣለን ተባባሉ።

. ይህንም ካሉ በኋላ ለንግድ ወደ ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ወረዱ።

. ወደ መርከብ በገቡ ጊዜ የባሕሩ ማዕበል ፀጥ አለላቸውና የሰላም ጉዞ ሆኖላቸው ተጓዙ።

. በዚህ ጊዜ ከሀገሩ ሰዎች አንዱ እንዲህ አላቸው።

. ይህ ጥልቅ ባሕር ሳያሰጥማችሁ እንደምን ተሻገራችሁ ሰውን የሚውጠው አዞስ እንዴት ሳያገኛችሁ ቀረ አላቸው።እኒህ ነጋዴዎችም በእምነታችን መሠረት በብዙ ወርቅ የሥላሴን መርከብ ተከራየን (ለሥላሴ ብፅዓት አደረግን)

፲፩. ወደ ሀገራችንም በሰላምና በደህንነት ብንመለስ ከገንዘባችን ሁሉ እኩሌታውን ለሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ብፅዓት አድርገን እንሰጣለን ብለናል አሉት።

፲፪. ከጥቂት ቀን በኋላም እኒህ ነጋዴዎች ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በተነሡ ጊዜ ከመካከላቸው አንዱ ነጋዴ ወንድሞቼ ሆይ ባሕሩን ተሻግረን እዚህ ለመድረስ አስቀድመን የተናገርነውን አንርሳ በማናውቀውም ሀገር ብዙ ወርቅና ብር አትርፈናልና ብፅዓታችንን ወይም ስእለታችንን እንዳንተው ሲል አሳሰባቸው።

፲፫. አሁንም ወንድምቼ ሆይ በእውነት የምነግራችሁን ስሙኝ እንደ ሥእለታችን ከገንዘባችን ካልሰጠን ዳግመኛ ለንግድ በምንሄድበት ጊዜ እሊህ ሦስቱ ሥላሴ ገንዘባችንን ሁሉ ያጠፉብናል አላቸው።

፲፬. እነሱ ግን እኛ አንድ ብር እንኳ አንሰጥም አንተ ግን ከፈለግህ ስጥ ለራስህም አንተ ራስህ እወቅ።

፲፭. እኛስ ነገርህን አንሰማም እንደ አንተ ያለም መካሪ አንሻም በሥላሴ ስም ከቶ አልተማፀንምና አሉት።

፲፮. ይህም ነጋዴ ወንድሞቼ ሆይ የተናገራችሁትን ቃል እንዴት ታጥፋላችሁ ወይም እኮ ሰይጣን

ኃላፊና ጠፊ በሚሆን በገንዘብ ፍቅር አታለላችሁ ይሆን አላቸው።

፲፯. ይህ በቅድስት ሥላሴ ፍቅር የተጠመደ ነጋዴም ይህን ተናግሮ ዝም አለ።

፲፰. ከዚህ በኋላ ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በመርከብ ተሳፈሩ።

፲፱. በዚህ ጊዜ ከነፋሱ ኃይል የተነሣ መርከቡ ተነዋወጠ ሊያሰጥማቸውም ተቃረበ።

. በዚህ ጊዜ መርከቡ ተሠበረና ሰዎቹ በባሕር ውስጥ ሰጠሙ።

፳፩. ይህን ታማኝ ነጋዴ ግን ሥላሴ ከባሕር አውጥተው በባሕር ዳርቻ አስቀመጡት።

፳፪. ከጣፈጠ አነጋገርህ የተነሣ ታማኝ አገልጋይ አደረግንህ አሉት።

፳፫. እንግዲህ የአንተን ገንዘብ አንፈልግም እምነትህ ይበቃናል።

፳፬. እነዚህ ከሐዲዎች ጓደኞችህ ግን በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንደሰጠሙ ተመልከት አስተውል አሉት።

፳፭. እንግዲህ አንተ ወደ ምድረ አንጐት ውረድና የሆነውን ነገር ሁሉ ለዘመዶቻቸውና ለቤተ ሰባቸው ሁሉ ንገር አሉት።

፳፮. ነጋዴውም እናንት የሀገር ታላላቅ አባቶች ሆይ እናንተ እነማን ናችሁ ስማችሁስ ማን ይባላል አላቸው።

፳፯. እነሱም እኛ ዓለሙን ሁሉ የፈጠርን ሥላሴ እንባላለን አሉት።

፳፰. ይህንንም ቃል ከአብና ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ አንደበት በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው።

፳፱. የደረሰበትን ነገር ሁሉ ነጋዴዎቹም በከንቱ እንደጠፉና እሱ ግን ሥላሴን በማመን እንደዳነ ለአንጐት ሰዎች ነገራቸው።

. ይህን የሰሙ ሰዎች ሁሉ ስለ ነጋዴዎቹ የተደረገው ነገር ሁሉ እጅግ አስደናቂ ነው በማለት አደነቁ።

፴፩. በዚህ ጊዜ ይህ ነጋዴ ብሩንና ወርቁን ሁሉ ለድኆችና ለችግረኞች በሥላሴ ስም መፀወተ።

፴፪. ኃላፊና ጠፊ ከሚሆን ከዚህ ዓለም ድካም እስከ ዐረፈ ድረስ በየወሩ በ፯ ቀን ይልቁንም በጥርና በሐምሌ ወር የበዓላቸውን መታሰቢያ አብዝቶ ያደርግ ጀመር።

፴፫. ይቅርታቸውና ሀብተገ ረድኤታቸው ከወዳጃቸው ከ…….ጋር ለዘለዓለሙ ይኑር አሜን።

💭 ቅዳሜ / ጥቅምት ፰/8 ፪ሺ፲፪ / 2012 ዓ.ም ላይ እባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ በትግራይ ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ሊጀምር ፩ ዓመት ሲቀረው የጨለቖት ቅድስት ሥላሴ ዘውድ ወደ ትግራይ እንዲመለስ ፈቀደ። እዚያ ክቡር ዘውድ ላይ እጁ ሲያርፍ ሳየው እጅግ በጣም ነበር ያንቀጠቀጠኝና ያስቆጣኝ!

👉 ያኔ የወጣው መረጃ የሚከተለው ነበር፤

/20 ዓመታት በላይ በኔዘርላንድ የቆየው የዘውድ ቅርስ ትግራይ ክልል ለሚገኘው የጨለቆት ሥላሴ ቤተክርስቲያን ተመለሰ

ከመቐለ ፲፮/16 ኪሎ ሜትር በደቡብ ምሥራቅ አቅጣጫ የሚገኘውና ረዥም ዕድሜ ያስቆጠረው የሥላሴ ጨለቆት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በርካታ ንዋየ ቅድሳት እንዳሉ ይነገራል። በተለይም ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስትያኑ እልፍ ንዋየ ቅዱሳን ማበርከታቸውን ቤተ ክርስትያኑ ግቢ ውስጥ ለዓመታት የኖሩ አባቶች ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ።

ለአሥራ ስድስት ዓመታት መንነው በቤተ ክርስቲያኗ የሚኖሩት የ፹፪/82 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ አባ ገብረሥላሴ፤ ሦስት ዘውዶችን ራስ ወልደሥላሴ ለቤተ ክርስቲያኗ መስጠታቸውን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

በጎርጎሳውያኑ አቆጣጠር ከ፲፯፻፵፭–፲፰፻፷፭/1745-1865 በወቅቱ የእንደርታ ዙሪያ የሚባለውን ሰፊ ግዛት ያስተዳደሩት ራስ ወልደሥላሴ በአራት ቦታዎች ማለትም በጨለቆት፣ በሕንጣሎ፣ በፈለግዳዕሮና በመቐለ ቤተ መንግሥቶችን ገንብተው ነበር። በአንድ ወቅትም ጨለቆትን ዋና ከተማቸው አድርገዋታል።

ራስ ወልደሥላሴ ካበረከቷቸው ዘውዶች መካከል አሁን በኔዘርላንድ የተገኘው ዘውድ አንዱ ሲሆን፤ ከ፳/24 ዓመታት በፊት መሰረቁንና ከዚያም መሰወሩን ተናግረዋል።

ከኢትዮጵያ ተሰርቆ የተወሰደው ዘውድ ኔዘርላንድ ውስጥ መገኘቱንና በዛሬው ዕለት ወደ አገሩ መመለሱን ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሳውቀዋል።

ይህ ዘውድ ንብረትነቱ የጨለቆት ሥላሴ መሆኑ የማያጠራጥር በመሆኑ ወደቦታው ተወስዶ በክብር ሊቀመጥ ይገባዋል።”

_____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጲያዊነታቸውን በመካዳቸው “ኤርትራውያን” በመሰቃየት ላይ ናቸው | ሌሎቻችሁ ከዚህ ተማሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 29, 2019

ምከረው፣ ምከረው እምቢ ካለ መከራ ይምከረው!

በጣም አሳዛኝ ነገር ነው! ወገን ለመማር አለመቻሉ ደግሞ ብዙ ንዴትንና ቁጣን ይቀሰቅሳል።

በኤርትራ የሚኖሩ ወገኖቻችን ኢትዮጵያዊነታቸውን በመካድ ኤርትራ የምትባል አዲስ ሃገር ሲቆረቁሩ፤ በቃ ማርና ወተት የሚጎርፍባት የበለጸገች ሃገር ትሆናለች ብለው በጽኑ ያምኑ ነበር። በእውነት ለመናገር ስድስት ሚሊየን ብቻ ነዋሪዎች ያሏት ኤርትራ በቀይ ባሕር ጠረፍ ላይ የሚገኙትን ቦታዎች በማልማት በቱሪዝም ብቻ ትበለጽግ ነበር፤ ህዝቡም ታታሪ ስለሆነ እነ ምጽዋ እና የዳህላክ ደሴቶች ከግብጾቹ የቀይ ባሕር ቱሪስቶች ማዕከላት፡ ከ ሻርም አልሼክ እና ሁርጋዳ በበለጠ መልክ አውሮፓውያን ጎብኝዎችን በብዛት የመሳብ እድል ነበራቸው።

ነገር ግን ያው እንግዲህ የኢትዮጲያን ካባ አውልቀው ከጣሉ ሃያ ዓመታትን አስቆጥረዋል፤ ምንም የተሳካ ነገር የለም፤ ዜሮ! ናዳ! እንዲያውም ትውልዱ ኢትዮጵያዊነቱን በመካዱ ብቻ ታይቶ የማይታወቅ መቀመቅ ውስጥ ለመግባት ተገድዷል። አንድ የሃበሻ ትውልድ ተሰድዶ በማለቅ ላይ ይገኛል፤ ወጣት ኤርትራውያን ድኻ ዘመዶቻቸው ለፍተው ያጠራቀሙላቸውን ገንዘብ ይዘው በመጓዝ የአረብ ሕገወጥ አዘዋዋሪዎች ምሳ በመሆን ላይ ናቸው፣ ከዚያ የተረፉት በሰሜን እና ምስራቅ ባሕራት ላይ የአሳ ነባሪዎች እራት ናቸው፤ የአባይ ወንዝ ቅዱሱን የጽዮን ተራሮች አፈር ጠራርጎ በመውሰድ ለአውሮፓው ባሕር ኢትዮጵያ ግብር የምትከፍለው አልበቃ ብሎ ኤርትራውያኑም ለዲያብሎስ የደም ግብር በውሃው ላይ እየከፈሉ ነው፣ በአረብ በርሃዎች ደግሞ የኩላሊትና ጉበት መለዋወጫ የሚገኙባቸው ሳጥኖች ሆነዋል፤ ሁሉም በነፃ፣ ሁሉም በፈቃዳቸው።

ቀደም ሲል፡ እነ ግራኝ አብዮት አህመድ ለቀመሙት ዲያብሎሳዊ ሴራ ማጣፈጫ ይሆን ዘንድ የሰሜኑን ድንብር ለኤርትራውያን ክፍት ሲያደርጉ ኤርትራውያኑ ኢትዮጲያዊነታቸውን መልሰው እንዳገኙት ሆኖ ስለተሰማቸው በብዙ መቶ ሺህ የሚቆጠሩት ወደተቀረው የኢትዮጵያ ግዛት መጉረፍ ጀመሩ። ነገር ግን ይህ “የኩሽ መንገስት እንመሠርታለን” ብለው የተነሱትን እባቦቹን እነ ግራኝ አብዮት አህመድን አላስደሰታቸውም፤ “ኦሮሞ እንጅ ኢትዮጵያን መውረር ያለበት፣ ኢትዮጵያውያን ኢትዮጵያን መያዝ አይችሉም” በሚል የድንጋጤ ምላሽ፡ የኤርትራና ኢትዮጵያ ድንበር ወዲያው እንዲዘጋ አዘዙ።

አሁን ኤርትራውያን እንደገና በአረብ በረሃ ላይ እና በሜዲተራንያን ባሕር ውስጥ እያለቁ ነው። ኢትዮጵያዊነታቸውን ለመክዳት በመዘጋጀት ላይ ያሉት ሌሎቹ ግብዞች እና ከሃዲዎች በእውነት ሉሲፈርን በማገልገል አገር ለማጥፋት አቅደው ካልሆነ በቀር፡ እውነት በጎ ነገር ካሰቡ እንዴት ከዚህ መማር ያቅታቸዋል? እንዴት መንደርተኘነቱን እንተው፣ የጠላት መጫወቻዎች መሆኑ ይብቃን ማለት ያዳግታቸዋል???

በ “ሀበሻ” ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ ትውልድ እያለቀ ነው፡ ወገን!

በ “ሀበሻ” ላይ ከሁሉም አቅጣጫ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ ትውልድ እያለቀ ነው፡ ይህ በዝምታ የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡ ወገን!

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: