ባለፈው ወር ሰባት ኮፕት ክርስቲያን ሴቶችና ልጃገረዶች በግብጽ ተጠልፈው ጠፍተዋል።
ሴት ልጆቻቸውን ወደ እስልምና ለመለወጥ ሲሉ ሙስሊሞች እንደጠለፏቸው ሁሉም የቤተሰቦቻቸው አባላት በአንድ ድምጽ ተናግረዋል።
የክርስቲያኖቹ መጥፋት ለፖሊስ ሪፖርት ቢደረግም ባለሥልጣናቱ ምንም ለማድረግ ፈቃደኞች ባለመሆናቸው ቤተሰቦቻቸው ክስ አቅርበውባቸዋል።
በግብፅ የሚገኙ ክርስቲያን ሴቶች ለማሰብ የሚከብዱ ብዙ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፦
ማህበራዊ መድልዎ ይደረግባቸዋል፣ ይጠለፋሉ፣ ሃይማኖታቸውን በግዳጅ እንዲለውጡ፣ እንዲገረዙ፣ በጥቁር ልብስ ተሸፋፍነው እንዲሄዱ ይገደዳሉ፣ የአካላታቸው ክፍሎች ይሠርቁባቸዋል።
“ይህ በምዕራቡ ዓለም እምብዛም የማይታወቅና አሳሳቢ የሆነ ክስተት ነው። ክርስቲያን ሴቶች እና ልጃገረዶች አስገድዶ መድፈር እና ወደ እስልምና እንዲቀይሩ መገደዳቸው እምብዛምም አይነገርለትም። ከ 2011 ዓ.ም በፊት በመላው ግብፅ ምናልባት ስድስት ወይም ሰባት ልጃገረዶች ላይ ይህ መሰል ኢ–ስበዓዊ ተግባር ይፈጸምባቸው ነበር፤ አሁን ግን ቁጥሩ በብዙ ሺዎች እየጨመረ ነው።” በማለት የኮፐት ክርስቲያኖች ጠበቃና የሰብአዊ መብት ተሟጋች የሆኑት ሳዳ ፋውዜ ይናገራሉ። በተለይ እጅግ በጣም ወጣት የሆኑ ክርስቲያን ልጃገረዶች ለሙስሊሞች ጥቃት የተጋለጡ ናቸው።
ለምሳሌ የ 14 ዓመቱ ናድያ ማካም፡ እ.አ.አ. በ 2011 ዓ.ም በቤተክርስቲያን የቅዳሴ ሥነስርዓት ላይ እያለች ተጠልፋለች። እስካሁን የትና እንዴት እንዳለች የሚታወቅ ነገር የለም፤ ከዚያን ጊዜ ወዲህ ቤተሰቦቿ ከእሷ ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም። በሃዘንና በጭንቀት የተሞሉት የናድያ እናት ልጃቸውን ሙስሊሞች እንደጠለፉባቸው በይፋ ቢያሳውቁም ፖሊሶች ግን ለመርዳት ፈቃደኞች አይደሉም፤ እንዲያውም የልጃቸውን ጉዳይ እንዳያነሱባቸው በተደጋጋሚ አስጠንቅቀዋቸው ነበር።