በጤናማው ዓለም። ግን ምግባረ ብልሹ ከሆነው ከዚህ የሰይጣን ዓለም ብዙም አይጠበቀም። የዲያብሎስ ልጆች እርስበርስ እየተሿሿሙና እየተሸላለሙ በዚህ የዋሕ ሕዝብ ላይ ይሳለቁበታል። ግድ የለም፡ ጊዚያቸው በጣም አጭር ነው!
እየበረረ ከሰማይ
************
እየበረረ ከሰማይ
ምሕረትን ይዞ ከአዶናይ
የሙሴ ረዳት የእስራኤል
ሊረዳኝ መጣ ሚካኤል
ዐይኖቹ እንደርግብ ልብሱ እንደመብረቅ
መስቀሉን ጨብጦ ምልክቱን የእርቅ
የመላእክት አለቃ ከፍ ያለ መንበሩ
ኢዮርና ራማ ኤረር ነው ሀገሩ
ያላገዘው የለም ያልረዳው ሚካኤል
በምልጃው ተማምኖ ከሚጠሩት መሐል
ዘወትር የሚሰግድ በእግዚአብሔር ፊት
መጋቤ ብሉይ ነው ሊቀ መላእክት
ታሪክ መዝግቦታል መጋቤ መሆኑን
መንገድ እየመራ ህዝበ እስራኤልን
በሚፈሩት ዙሪያ በክንፎቹ ጋርዶ
ከጭንቅ ይሰውራል ከሰማያት ወርዶ
መሪ ነው ሚካኤል በቃዴስ በሲና
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
ከሰማይ ወደ ምድር ዘንዶውን ጥሎታል
ከመላእክት መሐል ማንስ ይመስለዋል