እኛ የተሠወሩባቸውንና ቤተሰብ እያሳለፋቸው ያሉትን የሰቆቃ ቀናት እንቆጥራለን ፤ ዓለም የኮሮና ተጠቂዎችን ሰዎች ትቆጥራለች። ለአንድ መቶ ሃያ ስምንት ቀናት! እንኳን በወላጅ ላይ በእኛ ላይ እየደረሰ ያለው የህሊና ግርፋት ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለመገመት አያዳግትም። መንግስት ተብዬው 99% ተጠያቂ ቢሆንም፤ አብረው የተሰለፉትና የእነዚህን ምስኪን እህቶች ጉዳይ ቸል ያለ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በመጭው ትውልድ እና በፈጣሪ ዘንድ በጽኑ ይጠየቃል።
እንደው ባካችሁ ንገሩኝ፤ ለመሆኑ ከቤተ ክህነት ወይም ከማህበረ ቅዱሳን ይህን አስመልክቶ ምን የተነገረና የተሠራ ነገር አለ? ካልሆነ ምን ይሆን ምክኒያቱ?