ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ
በዚህች ቀን ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ሞትን ሳይቀምስ የተሰወረበት ቀን ነው፤ ዮሐ 21 ፤ 20።
ዮሐንስ ወንጌላዊ
ዮሐንስ ማለት ‹‹ የእግዚአንሔር ጸጋ ነዉ››፤ደስታ ማለት ነዉ፡፡አባቱ ዘብዴዮስ ፤ እናቱ ማርያም ባዉፍልያ ትባላለች፡፡ቁጥሩ ከዐሥራ ሁለቱ ሐዋርያት የሆነ ያዕቆብ የተባለ ወንድም ነበረዉ፡፡ ማቴ 4፡21 ፤ ማር 1፡20 ፤ማቴ 20፡20 ቅዱስ ዮሐንስ አስቀድሞ የዮሐንስ መጥምቅም ደቀ መዝሙር ነበር፡፡ ዮሐ 1፡ 35 ቅዱስ ዮሐንስ ከአባቱና ከወንድሙ ጋር ዓሣ በሚያጠምድበት በገሊላ ባህር ላይ መረቡን ሲያበጅ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐዋርያነት ጠራዉ፡፡ እሱም አባቱን ሌሎቹንና ታንኳን ትቶ ከወንድሙ ያዕቆብ ጋር ጌታን ተከተለዉ፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ስሞች አሉት፦
- ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ
- ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ
- ዮሐንስ ቁጽረ ገጽ
- ዮሐንስ ታኦሎጎስ
- ዮሐንስ አቡቀለምሲስ
- ዮሐንስ ወንጌላዊ
- ዮሐንስ ዘንስ
ከሐዋርያት መካከል ሞትን ያልቀመሰ በህይወተ ሥጋ እያለ ወደ ሰማይ የተነጠቀ እንደ ሔኖክ ፣እንደ ኤልያስ በብሔረ ሕያዋን የሚኖር ሐዋርያ ነዉ፡፡ጌታችንም ለቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹‹‹ዮሐንስ እኔ እስክመጣ ድረስ በሕይወት ይኖር ዘንድ ብወድስ ምን አግዶህ??›››ዮሐ 21፡20 ይህም እስከ ምጽአት ድረስ እንደሚኖር መናገሩ ነዉ፡፡በማቴ 16፡18 ላይ ‹‹እዉነት….……ሞትን የማይቀምሱ አንዳንድ አሉ›››››ያለዉ ቃል ለቅዱስ ዮሐንስና መሰሎቹ የተነገረ ቃል ነዉ፡፡
የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በረከቱ ረድኤቱ ከሁላችን ጋር ይሁን፡ ራዕዩ ይገለጥልን!