✞✞✞[ድጕዓ ኤርምያስ ምዕራፍ ፫፥፵፰]“ብጥፍኣት ሕዝበይ ካብ ዓይነይ ከም ማይ ርባ ንብዓት ይውሕዝ ኣሎ።”
✞✞✞[ሰቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፫፥፵፰] “ስለ ወገኔ ሴት ልጅ ቅጥቃጤ ዓይኔ የውኃ ፈሳሽ አፈሰሰች።”
“ደጕዓ” የሚለው የትግርኛ ቃል “ሰቆቃው” ማለት መሆኑን ዛሬ ተማርኩ። ስለ ዘማሪት እኅታችን ትርሃስ ገብረ እግዚአብሔር ከሰማሁ በጣም ቆየሁ፤ እስኪ ዛሬ ባለ እግዚአብሔር ነውና ትርሃስን ልፈልግ ስል ይህን ድንቅ መዝሙር አገኘሁና እምባዬ መጣ። ከሁለት ቀናት በፊት በዕለተ መድኃኔ ዓለም “መልክአ መድኃኔ ዓለም”ን ለማንበብ ወደ በረንዳ ስወጣ ሁለት ነጫጭ እርግቦች መጥተው ደረጃው ላይ አረፉ፤ ያኔም በደስታና በመገረም እምባዬ መጣና መልክ አ መድኃኔ ዓለምን ሳነብ የሚከተለው አንቀጽ ትኩረቴን በይበልጥ ሳበው፤
❖❖❖“ፈጣሪዬ ክርስቶስ ሆይ አቤቱ ከችግርና ከፈተና አድነኝ፣ አባትህም ‘በምስሕ ደብረ ጽዮን‘ በሚያደርገው ታላቅ የምሳ ግብዣ ላይ ይዘኽኝ ግባ፣ ከአንተ በቀር ሌላ የማውቀው ዘመድ የለኝምና።”
እንግዲህ ወዲያው ብልጭ ብለው የታዩኝ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ነበሩ። “ምን ሊሆን ይችላል?” ብዬ በመጠየቅ እስካሁን በማሰላሰል እና መልሱን ለመገመት በመሞከር ላይ ነኝ። በጣም ይገርማል!
❖ባለ እግዚአብሔር ሆይ በዕለተ ቀኑ ሐገራችን ኢትዮጵያን ከነገሡባት እርኩስ ጠላቶቿ አድነህ ስላም አድርግልን፣ በትግራይ የሚሰቃዩትን አባቶቻችንን፣ እናቶቻችንን፣ ወንድሞቻችንን እና እኅቶቻችንን ሁሉ ጠብቅልን፣ ለታመሙት ምሕረት ላጡት ማግኘቱን፣ በስደት ዓለም ያሉትንም በያሉበት ጠብቅልን። መልካም ዕለተ ስንበት፣ መጭዎቹንም የተባረኩና የተቀደሱ ሳምንታት፣ ወራት እና ዓመታት አድርግልን።❖
____________________________________