Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የጽዮን ተራራ’

እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2021

💭 ድንቁ ገዳም ማርያም ታምባ ቆላ ተምቤን ትግራይ

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

❖ አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ። እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

🌞መለአክ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል🌞

ኡራኤል የሚለው ስም ‘ዑር’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ‘ዑራኤል’ ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ” ፣ “የአምላክ ብርሃን” ማለት ነው ። ከምወዳቸው መላዕክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል ከ፯/7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ አለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።

በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፮፥፪] ሚስጢር ሰማይና እዉቀትንም ሁሉ ለአባታችን ሔኖክ የገለፀለት፤ የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሔኖክ ነግሮታል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፲፰፥፲፫] ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ መንገድ የመራ ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ፤ እዉቀት ለተሰወረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ፅዋ ጥበብን ያጠጣ መለአክ ነው።

❖❖❖ ለትግራይ ጾም፣ ፀሎት፣ ምሕላ እና ስግደት በሚደረግባቸው በእነዚህ ሦስት ልዩ ዕለታት ሦስቱ የጽዮን ቀለማት ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ (ትክክለኛው ቅደም ተከተል) ሦስት ሆና የምትታየዋን ፀሐይዋን አጅበው እንዲህ አንጸባረቁ! የሥላሴ ሥራ ድንቅ ነው! ድንቅ ነው! ድንቅ ነው!❖❖❖

🌞🌞🌞 እግዚአብሔር በገናንነቱ ታላቅ ነው፤ ሦስት ስም አንድ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ ፀሐይን በቀን ጨረቃና ክዋክብትን በሌሊት ያሠለጠነ እሱ ከሃሊ ነው። የሚያስደነግጥ መለኮታዊ መብረቅ የተንቦገቦገ መለኮታዊ ፍሕም ተወርዋሪ መለኮታዊ ቀስት። የሚያቃጥል መለኮታዊ እሳት የሚያበራ መለኮታዊ ፋና አንጸባራቂ መለኮታዊ ፀሐይ። 🌞🌞🌞

💭“ሦስት ፀሐይ” በኦሮሚያ ሲዖል | የፀሎተ ትግራይ ፍሬ? | የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ወዮላችሁ!“

❖❖❖ የቅዱስ ኡራኤል በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን፤ አሜን!❖❖❖

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፮]✝✝✝

፩ እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ሐሤትን ታድርግ፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይበላቸው።

፪ ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

፫ እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።

፬ መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፤ ምድር አየችና ተናወጠች።

፭ ተራሮችም ከእግዚአብሔር ፊት፥ ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።

፮ ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።

፯ ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት።

፰ አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፤

፱ አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።

፲ እግዚአብሔርን የምትወዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የቅዱሳኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።

፲፩ ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።

፲፪ ጻድቃን፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፰]✝✝✝

፩ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።

፪ እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

፫ ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመስግኑ።

፬ የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።

፭ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።

፮ ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው። እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።

፯ በደመና ዓምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።

፰ አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ ሥራቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።

፱ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አውሮፓውያን በኢትዮጵያ የሠሩትን ችቦ ለማቃጠል ሲዘጋጁ፤ እራሳቸው እግዚአብሔር በፈጠራት ፀሐይ ተቃጠሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 25, 2019

ፓሪስ፣ ለንደን፣ በርሊን፣ ማድሪድ፣ ወዘተ ታይቶ በማይታወቅ ሙቀት እየተቃጠሉ ነውከሦስት ቀናት በፊት በማርክሮን ፈረንሳይ እንዲህ ሃይሎ የማያውቅ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር (5.1)…

የዛሬዋ ኢትዮጵያ “አርኤል”ን (የጽዮን ተራራን) ታስታውሰናለች፦

[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፳፱፥]

ዳዊት ለሰፈረባት ከተማ ለአርኤል ወዮላት! ዓመት በዓመት ላይ ጨምሩ፥ በዓላትም ይመለሱ።

አርኤልንም አስጨንቃለሁ፥ ልቅሶና ዋይታም ይሆንባታል፤ እንደ አርኤልም ትሆንልኛለች።

በዙሪያሽም እሰፍራለሁ፥ በቅጥርም ከብቤ አስጨንቅሻለሁ፥ አምባም በላይሽ አቆማለሁ።

ትዋረጂማለሽ፥ በመሬትም ላይ ሆነሽ ትናገሪያለሽ፥ ቃልሽም ዝቅ ብሎ ከአፈር ይወጣል፤ ድምፅሽም ከመሬት እንደሚወጣ እንደ መናፍስት ጠሪ ድምፅ ይሆናል፥ ቃልሽም ከአፈር ወጥቶ ይጮኻል።

ነገር ግን የጠላቶችሽ ብዛት እንደ ደቀቀ ትቢያ፥ የጨካኞችም ብዛት እንደሚያልፍ ገለባ ይሆናል።

ድንገትም ፈጥኖ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በነጐድጓድ፥ በምድርም መናወጥ፥ በታላቅም ድምፅ፥ በዐውሎ ነፋስም፥ በወጨፎም፥ በምትበላም በእሳት ነበልባል ይጐበኛታል።

በአርኤልም ላይ የሚዋጉ፥ እርስዋንና ምሽግዋንም የሚወጉ የሚያስጨንቋትም፥ የአሕዛብ ሁሉ ብዛት እንደ ሕልምና እንደ ሌሊት ራእይ ይሆናል።

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: