Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የጸሐይ ግርጃ’

ከሀሪከን ጥፋት የተረፈችው ጥቁር አሜሪካዊቷ እህታችን | የኢትዮጵያ መላእክት ሁልጊዜ ይጠብቁኛል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2017

ቢዮንሴን ወይም አንጄሊና ጆሊን ስላልመሰለች እንዳንንቃት፤ በእኔ በኩል ባራክ ና ሚሼል ኦባማን ከመሳሰሉ ከሃዲ ገለባዎች ከማዳምጥ ይህችን ምስኪን እህታችንን ማዳመጥ እመርጣለሁ፡ ብዙ ቁምነገሮችን ነው የምትናገረውና። ልብ እንበል፦ ይህ ሁሉ ጉድ በአሜሪካ፣ ቃጠሎ ሙቀት የሚከሰተው መሀመዳውያን ወደ መካ ለመጓዝ በሚዘጋጁበት ወቅት ነው። ይህ ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡ ወደነሱ ተጠራቅሞ የሚመጣው ጥፋትና እልቂት ግን በታሪክ ታይቶ ተሰምቶ የማይታወቅ ይሆናል! ይህን እናስታውስ!

እህታችን ከሞላ ጎደል እንዲህ ትላለች፦

የኢትዮጵያ መላእክት ሁሌ በሕልሜ ይታዩኛል። እንደ ካተሪና እና ሳንዲ ከመሳሰሉት የዓውሎ ንፋሶች፡ ጥፋት ያዳኑኝ የኢትዮጵያ መላእክት ናቸው።

በሰው ልጅ የባርነት ቀንበር ያልወደቁት ኢትዮጵያውያን ብቻ መሆናቸው ያስገርመኝ ነበር። አሁን መላእክቱ ነገሩኝ። ብዙ የተሳሳቱ ክርስቲያን ነን ባዮች እዚህ አሜሪካ እንዳሉ ታሪክ አስተምሮናል፡ አሁንም እያየን ነው።

ከሌሎች ጋር ያልተቀየጡና ንጹህ ክርስትናን የሚከተሉ ሁልጊዜ ለተበደሉ ሕዝቦች ይቆረቆራሉ፡ ይታገላሉ። ብዙ ጥቁሮች ግን ተታለዋል፡ ከሚበድሏቸው ጋር አብረው መሰለፍና ለነርሱም መቆም መርጠዋል።

የኔሽን ኦፍ ኢስላም የሚባለው ድርጅት ብዙዎችን እያታለለ ነው። ባርነት ሁሌ የእስልምና አካል ነበር፤ አሁንም እስላሞች ብቻ ናቸው ባርነትን የሚያካሂዱት፤

ታዲያ የእነርሱን አምልኮ የተቀበሉትና ከእነርሱ ጋር የሚተባበሩት ጥቁሮች የወደቁት ብቻ መሆን አለባቸው። ብዙ ጥቁሮች በቩዱ ጣዖት አምልኮ ሥር ስለወደቁ ከሉሲፈራውያኑ እና ከሙስሊሞች ጋር አብረው ይጓዛሉ። ያሳዝናል!

አይሁዶች እንደሚያሸንፉና ወደክርስቶስ እንደሚመጡ ታይቶኛል፤ ታዲያ ሁሉም እስራኤልን የሚጠሉት፡ ክርስቶስ ከአይሁዶች በኩል እንደሚመጣ ሰይጣን አለቃቸው ስለሚያውቅ ነው።

ባለፈው ሳምንት የጸሀይግርጆሽ ወቅት የታየኝ ነገር፤ በመሰከረም አንድ በኒዮርክ የሽብር ጥቃት ጊዜ የታየኝን ዓይነት ነገር ይመስላል። በዚያን ጊዜ፡ ትዕቢተኞች የነበሩት የኒውዮርክ ከተማ ነዋሪዎች፤ ከሽብሩ በኋላ፤ መተሳሰብና መፈቃቀር ጀምረዋል፤ ስለዚህ፣ ምናልባት አደጋው ሁሉ ለጥሩ ነገር ሊሆን ይችላል።

ዲሞክራቶችን ወይም ሌሎች ፓርቲዎችን ስለመረጥን ነፃ አንሆንም፤ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ለነፃነታችን ቁልፍ ሚና የሚጫወተው።

በአሜሪካ ነባር ነዋሪዎች (ኢንዲያንስ) እና በጥቁሮች ላይ የደረሰው በደል ይህችን አገር እሥር አድርጓታል፤ ለእነዚህ ህዝቦች የሚደረገውን ፍትህ የሆነ እንቅስቃሴ ሊበራሎች፥ ዘረጆች፥ ፊሚንስቶችና ጂሃዲስቶች ጠልፈውታል፤ ሁሉም ሰይጣናውያን ናቸው!

ዌልፌር (የመንግስት ገንዘብ) የአውሬው ምልክት ነው! ዌልፌርን (የመንግስት ገንዘብ) አልደግፍም፡ ወንጀለኛ ያደርጋልና፣ ሂፕሆፕ ሙዚቃንም አልደግፍም ሰይጣናዊ ሙዚቃ ነውና!

አል ሻርፕተንና ኦባማን፤ ጥቁር ስለሆኑ ብቻ አልደግፋቸውም፥ ሂላሪ ክሊንተንንም ሴት ስለሆነች ብቻ አልደግፋትም።

ከጸሀይግርጆሹ በኋላ የታየኝ አንድ ጥሩ ነገር አለ፦

ሁሉም ዓይነት ዘረኞች፥ ፊሚኒስቶች፥ ኢአማንያን ሊበራሉች፥ ጂሃዲስቶችና ሉሲፈራውያን ሁሉ ይገረሰሳሉ!!!

ዘረኞች፥ ናዚዎች፣ ወንጀለኞችና ሙስሊም ሽብርተኞች ሁሉ በቅርቡ ይፈረድባችኋል፤ ወዮላችሁ!

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ባሕር ዛፍ ፍሬ ላይ መስቀል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 19, 2015

  • –ዛሬ ፡ መስቀል ኢየሱስበዓለ መስቀል የሚውልበት ዕለት ነው
  • –በነገዋ ዓርብ የጸሐይ ግርጃ ክስተት ይከሰታል
  • –የነገው ዕለት ናውረዝየፋርስ (ዛራቱስትራውያን) አዲስ ዓመት ነው
  • –ከ22 ቀናት በኋላ፡ ዓርብ ስቅለት ነው
  • –ከ2ሺህ ዓመታት በፊት፡ በዓርብ ዕለት፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሞት ምድር በፀሐይ ግርጃ ጨልማ ነበር

 CrossOnBahirzaf4 እውነት ባሕር ዛፍከባሕር ማዶ መጥቶ በአገራችን እንዲበቅል የተደረገ ተክል ነውን? የሚያጠራጥር ነው። አገራችን የመጀመሪያዎቹ ፍጥረታት ሁሉ የተፈጠሩባት፣ አዳምና ሔዋን እግራቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያሳረፉባት፡ ባሕር ዛፍእና ሐመልማላት ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የበቀሉባት ምድር መሆኗ እየታወቀ ታዲያ ባሕር ዛፍ ከአውስትራልያ ነው የመጣውገለመሌ ምን ያስብለናል?

እግዚአብሔር ጨለማውን አስቀድሞ ብርሃንን በስተኋላ የፈጠረው ጨለማ የዚህች ዓለማችን፡ ብርሃን የወዲያኛው ዓለም ምሳሌ ስለሆነ ነው። ይህቺ ዓለም በጨለማ መመሰሏም ሕሊናን የሚያደነዝዝ፡ ልቡናን የሚያናውዝ ኃጢአት ይሠራባታል። የዲያብሎስ ፈቃድ ይፈጸምባታልና ነው። ባሁን ጊዜ በዚህች የጨለማዋ ዓለም የዲያብሎስ ልጆች በእግዚአብሔር አምላክ፡ በክርስቶስ ልጆች ላይ እየፈጸሙት ያለው ጭካኔ የተሞላበት በደል ወደ ገሐነም እሳት የሚያስጥላቸው ነው። ህፃናቱን፣ አረጋውያንን፣ ሴቶችን ያርዳሉ፣ ቅዱሳን ቦታዎችን ያረክሳሉ፣ የእግዚአብሔርን ውብ ፍጥረታት ሁሉ ይዋጋሉ።

ዲያብሎስ ከቅዱሳን፣ ከቅዱሳት ቦታዎች አይርቅምና በቅድስቲቷ አገራችንም ገሩ ሕዝባችንን ለዘመናት ሲፈታተን ቆይቷል፡ አሁንም የተለቀቀበት ዘመን ነውና ከሁሉም አቅጣጫ ወገናችንን በመወጋታ ላይ ይገኛል። በዚህች ባጭሩዋ የነጻነት ጊዜው ዲያብሎስ ብዙ ግዳይን ለመጣል በብርቱ ይራወጣል። የዲያብሎስ ጦርነት የተከፈተበት ሕዘብ ክርስቲያኑ ነው። መንፈሣዊውን የእለት እንጀራችንን እንዳናገኝ በረቂቅ ጥበቡ ያዘናጋናል፣ በአካልም የምንመገበውን ምግባችንን ሊበክልብንና ሊነጥቀን፣ የፈጣሪያችን እስትንፋስ የሚገለጥባቸውንም አዕጽዋታት ሁሉ ሊያወድምብን ይታገላል።

በአገራችን፡ ብዙ የሚያነቃቁና የሚያስደንቁ እድገቶች በብዙ መስኮች በመታየት ላይ ቢሆንም፡ ምግቦቻችን በተመለከተ እንደ ሞንሳንቶ ያሉ የሣጥናኤል ድርጅቶች፣ በቱርክ እና አረብ ኩባንያዎች ሥር አንድባንድ እንዲወድቁ መደረጉ ትልቅ ስህተት ነው። ይህ ስህተት ቶሎ ሊታረም ይገባል። የስኳር እጥረት (ስኳር ቢቀርብንስ!) በነገሠባት፡ የስኳር በሽታ በብዛት እየተስፋፋ በመጣባት አዲስ አበባችን ስኳር እያሸገCrossOnBahirzaf3 የሚያከፋፍለው፡ ኢትዮጵያዊ ድርጅት ሳይሆን ቱርካዊ ድርጅት ነው። መንቀሳቀስ የሚችለው የዋናዋ ከተማችን ዜጋ ላይ ላዩን “2+1” “4-wheel….” ቅብርጥሴ በማለት አላፊ በሆኑ የኃብት ማካበቻ ቁጥሮች ሲዘናጋ፣ ከታች እባቦቹ የሳዑዲ ባቢሎን ወኪሎች የከብቱን፣ ጤፉን፣ ዱቄቱን፣ ወተቱን፣ የፍራፍሬ ጭማቂውን ምናልባትም ለወደፊት የውሃ ኃብታችንን በመቆጣጠር የምንመገበውን ምግብ በእጃቸው በማስገባት ላይ ናቸው። ይህም፡ በንግዱ ዓለም ለዘመናት ሲዘጋጁበት የነበረ፤ ለረጅም ጊዜ ያቀዱት አላማቸው እንደሆነ አሁን የተረዳነው ይመስለኛል። በሳዑዲ መርዝ ያልተመረዘው ጨዋው የኢትዮጵያ ሙስሊም ሁለት አማራጭ ይኖረዋል፡ 1. ከአረብ አምልኮት ተላቅቆ በክርስቶስ ስም እራሱን ከዲያብሎስ ወጥመድ ነጻ መውጣት፡ ወይንም፡ 2. ታማኝነቱን ጡት ላጠባችው አገሩ ሳይሆን፤ ለሳዑዲና ለቱርክ በማድረግ እናቱን መንከስ፣ የመርዝ ጂሃድ፣ የ ፍቅርጂሃድ፣ የደን ቃጠሎ ጂሃዱን ማጣጧፍ ይሆናል። ይህ በቅርቡ ለሁሉም ግልጽ ሆኖ መታየቱ አይቀርምና የእግዚአብሔር ልጆች ሁልጊዜ ነቅተው በተጠንቀቅ መቆም ይኖርባቸዋል።

ምስሎቹ ላይ የሚታዩት የባሕር ዛፋችን ፍሬዎች የኦርቶዶክስ መስቀል ቅርጽ ይዘው እንደሚያድጉ ዘንድሮ ነበር ለመጀመሪያ ጊዜ የታዘብኩት። ይህ የሚያስደንቅ ነገር አይደለምን?! በጣም እንጂ! ታዲያ፡ ክቡር መስቀሉ ያረፈባቸውን እነዚህን ዛፎች ያላግባብ መቁረጥ፣ ወደ አረብ አገር መላክ ትልቅ ወንጀል ነው። በዚህ ጤንንት ለጋሽ ድንቅ ዛፍ ደን የተከበቡትን ቅዱሳት ገዳማት እየቆሰቆሱ በእሳት ቃጠሎ፡ መተናኮልም፣ ነፍስን ለዘላለማዊው የእሳት ቃጠሎ አሳልፎ እንደመስጠት ያህል ነው።

መጪዎቹ ቀናት ብዙ ነገሮችን ግልጥልጥ አድርገው ያሳዩናል፤ ተዘጋጁ እንዘጋጅ!

ድ ል  በ መ ስ ቀ ል!

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: