ባለፈው ሳምንት ሐምራዊቷን የፋሲካ ጨረቃ አይተናታል…አሁን ደግሞ እየመጣ ያለውን እንከታተል…”ምስጋና ለኮሮና ፥ አንበጣ ይምጣ!” የምንልበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ከጠላቶቻችን ውድቀት ይልቅ የፍትሕ አምላክ እግዚአብሔር የሚሰጠው መልስ በይበልጥ ያስደስታል።
- ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን አግተህ ያንተ ልጆች ብቻ ሊማሩ?
- ኢትዮጵያውያንን አስርበህ ያንተ ልጆች ብቻ ሊመገቡ?
ፋሲካን ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩት የእስራኤል ልጆች ናቸው ። በዓሉንም ማክበር የጀመሩት ከግብጽ ነው።
ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፲፪
እግዚአብሔር በግብጻዊን ምክንያት በእስራኤላዊያን ላይ ሲደርሱ የነበሩ በርካታ ችግሮችን :- ጡብ መስራት ግርፋት መጨረሻ ላይም የእስራኤል ሴቶች የሚወልዷቸው ህጻናት ወንዶች ከሆኑ እንዲገደሉ ልምድ አዋላጆችን አሰልጥኖ ማሰማራት…ይህ ሁሉ ግፍ ሲደርስባቸው እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮሁ እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ ሙሴንና አሮንን “ያመልከኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ” የሚል መልዕክት አስይዞ ወደ ንጉሥ ፈርኦን ላካቸው። ፈርኦን ግን ልቡ ደንዳና ስለነበረ እግዚአብሔር ማነው? ህዝቡንም አልለቅቅም አለ ይልቁንስ በእስራኤል ላይ የባሰ ጫና መፍጠር ጀመረ :-ትናንት ጡብ እንዲሰሩ ገለባ ይሰጣቸው ነበር አሁን ግን ገለባውን ራሳቸው ከየትም እንዲያመጡ የጡቡ ቁጥር ግን ከትናንቱ እንዳያንስ ተወሰነባቸው ። ከዚህም የተነሳ እስራኤል አሁንም ይጮሃሉ ።
በዚህም ምክኒያት እግዚአብሔር በግብጽ ላይ መቅሰፍት ማውረድ ጀመረ።
መቅሰፍቶችም:-
- ፩.የሙሴ በትር እባብ መሆን ዘጸአት ፯፥፰፡፲፫
- ፪.የደም መቅሰፍት (የግብጽ ወሃ ሁሉ ወደ ደም መቀየር) ዘጸአት ፯፥፳፡፳፰
- ፫.የጓጉንቸር መቅሰፍት ዘጸአት ፰፥፩፡፲፭
- ፬.የተባይ (የቅማል)መቅሰፍት ዘጸአት ፰፥፲፮፡፲፱
- ፭.የዝንብ መቅሰፍት ዘጸአት ፰፥፳፡፴፪
- ፮.የእንስሳት እልቂት ዘጸአት ፱፥፩፡፯
- ፯.የእባጭ(ቁስል) መቅሰፍት በሰውና በእንስሳት ላይ ዘጸአት ፱፥፰፡፲፪
- ፰.የበረዶ መቅሰፍት ዘጸአት ፱፥፲፫፡፴፭
- ፱.የአንበጣ መንጋ መቅሰፍት ዘጸአት ፲፥፩፡፳
- ፲. የጨለማ መቅሰፍት ዘጸአት ፲፥፳፩፡፳፱
ይህ ሁሉ ሲሆን ፈርኦን እስራኤልን አልለቅቅም አለ። ስለዚህ አሁን የቀረውና የመጨረሻው የፋሲካን በዓል ማክበር ነው።
ላይ እንደተጠቀሰው የእስራኤል ልጆች ፋሲካን የጀመሩት በግብጽ ሳሉ ነው።
በእነሱ የዘመን አቆጣጠር በመጀመሪያ ወር ወሩም በገባ በ10ኛ ቀን ጸሐይ ስትጠልቅ በግ ወይም ፍየል እንዲያርዱ የሚታረደው በግ ወይም ፍየል ምንም አይነት ነውር የሌለበት ሆኖ ከታረደ በኋላ ደሙ ከስጋው የሚበሉትን ሰዎች ቤት ጉበኑንና መቃኑን እንዲቀቡት ከዚያም የበጉ ወይም የፍየሉ ስጋ ተጠብሶ በዚያች ሌሊት ከመራራ ቅጠልና ካልቦካ ቂጣ ጋር እንዲበሉት ሲበሉም በአጭር ታጥቀው ጫማቸውን አድርገው በትራቸውን ይዘው በጥድፊያ እንዲበሉ ምክኒያቱም አሁን በግብጽ ላይ የሚመጣው መቅሰፍት እጅግ ከባድ (የበጉ ወይም የፍየሉ ደም በቤታቸው ጉበንና መቃን ላይ የቀቡ እስራእል ብቻ ስለሆኑ ቢያች ሌሊት እግዚአብሔር በከተማ ውስጥ እያለፈ ደሙን በጉበኑና በመቃኑ ላይ ያልተቀባ ቤት ሲያገኝ በእያንዳንዱ ቤት ከሰው እስከ እንስሳ በኩር የተባለውን በሙሉ ስለሚገድል) ግብጾች በራሳቸው ጊዜ ወጡልን ስለሚሏቸው ነው ።
ከዚህ በኋላ ለእስራኤል ፋሲካን ማክበር የዘላለም ስርዓት እንዲሆን ተደነገገ። በመጀመሪያ እርሾ የተባለ ከቤታቸው ያወጣሉ ለሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ይበላሉ።
ሰሞኑን በመላው ዓለም እርሾ ከገበያ መጥፋቱን ልብ ብለናል?! ለምን እርሾ?