በቆጵሮስ ደሴት፡ የግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን ተከታዮች፡ ልጆቻቸውን በጠበቀ መንፈሳዊ ሥነስርዓት ያጠምቃሉ። በዚህ መልክ ለሁለት ሺህ ዓመታት ያህል ያጠመቋቸው ህፃናት ያው ስንቱን መከራና ስቃይ አልፈው የዛሬው ዘመን ላይ ደርሰዋል።
የጥምቀትን ጥቅም ያውቃሉ፤ ጥምቀት የማትደገም፣ የማትከለስ አንዲት ናትና። ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ልጅነትን የምናገኝባት ጥምቀት የማትደገምና የማትከለስ አንዲት ብቻ መሆንዋን ሲያስተምር ‹‹አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት…አለ›› ብሏል (ኤፌ.፬÷፭)። ሃይማኖታቸው የቀና 318ቱ ሊቃውንትም ‹‹ኃጢአትን በምታስተሠርይ በአንዲት ጥምቀት እናምናለን፡፡››ብለው አስተምረዋል።
አሁን በሜዲያና በማህበረሰባዊ ድኽረ ገጾች ላይ፡ ሥርዓተ ጥምቀቱን በማጥላላት፡ “ተመለከቱ! ኦርቶዶክሶች ሕፃናትን በሚረብሽ መልክ ያጠምቃሉ” እያሉ የአውሬው ደቀመዛምርት በመለፈፍ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ዘመን የምንጠብቀውና፡ ከፀረ–ክርስቶሱ ወታደሮች ጋር የመፋለሚያ መስኮቹ ከሆኑት አንዱ አንዱ ሥርዓተ ጥምቀት ነው። በአንድ በኩል ለሰው ልጅ አሳቢዎችና ተቆርቋሪዎች ሆነው ለመታየት ይሻሉ፤ በሌላ በኩል ግን ለልጆቻቸው ሥርዓተ ጥምቀትን በመንፈግ፣ ብሎም ጥሩውን ከመጥፎ ሳይለዩ ያለ እመንት እንዲያድጉ በማድረግ የሚሠሩት ተወዳዳሪ የሌለው ኃጢአትና ግፍ በጭራሽ አይታያቸውም። እንዲያውም ቀዳዳ እየፈለጉ ክርስትናን ማጥቃት ይመርጣሉ።
በተለይ የእንግሊዙ DailyMail ጋዜጣ በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሌታም የሆነ ጽሑፍ ይዞ ወጥቷል፤ እጅግ በጣም ብዙ አንባቢዎችም ዘግበዋል፤ 95 % የሚሆነው ከአውሬው አፍ የወጣ ነው። (https://addisabram.wordpress.com/ )
የሚገርመው፡ የእንግሊዟ ንግሥት ኤልሳቤጥ ባለቤት፡ ልዑል ፊሊፕ በግሪክ ተወልደው አድገዋል፤ በግሪክ ኦርቶዶክስ ቤ/ክርስቲያን የተጠመቁና አጥባቂ ኦርቶዶክስ ክርስቲያን እንደሆኑም ይነገርላቸዋል።