Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የጌታ ልደት’

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው | ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 7, 2023

😇 ዛሬ ተወለደ ዛሬ ተወለደ የዓለም ቤዛ ወገኖቹን በደሙ ሊገዛ

🔔 ይህ የዛሬው የልደት በዓል፤ ታኅሣሥ ፳፱ / ጃንዋሪ 7 በ፤

  • ❖ ኢትዮጵያ (ኤርትራን ጨምሮ)
  • ❖ እስራኤል
  • ❖ ግብጽ
  • ❖ አርመኒያ
  • ❖ ጆርጂያ
  • ❖ ሩሲያ
  • ❖ ዩክሬን (በሉሲፈራውያኑ ሮማውያን ግፊት ከፊሉ ወደ ዲሴምበር 25 እየቀየረ ነው)
  • ❖ ቤላሩስ
  • ❖ ሞልዶቫ
  • ❖ ካዛክስታን
  • ❖ ሰርቢያ
  • ❖ ማኬዶኒያ
  • ❖ ሞንቴኔግሮ

ይከበራል

የቤተልሔም ኮከብ በመጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ኪዳን መሠረት ሦስቱን ጠቢባን ከምሥራቅ ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ የትውልድ ስፍራ የመራቸው ኮከብ ነው ፡፡

የቤተልሔም ኮከብ የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስን ልደት ያመለክታል. በዚህ ምክንያት ነው ፣ በገና ወቅት ፣ ይህ ክስተት ሲዘከር ፣ የቤተልሔም ባህርይ ኮከብ በገና ዛፍ ላይ የተቀመጠው። የገና ዛፍን ይመልከቱ።

የቤተልሔም ኮከብ ከባለ አምስት ፈርጡ የሉሲፈር ኮከብ በመለየት ተቃራኒው ነው። የቤተልሔም ኮከብ ለእኛ ለክርስቲያኖች እንደ አማኝ ሕይወታችንን የሚመራ ብርሃን ፣ ተስፋ እና እምነት የሚወክል ነው። ይህ ኮከብ ዝነኞቹን ሶስት ጠቢባን ሰዎችን(ሰብዓ ሰገልን) የመራቸው ኮከብ ነው። ለዚህም ነው ለገና በዓል አከባበር እና መታሰቢያ እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ምልክቶች አንዱ ይህ ኮከብ የሆነው።

ታዲያ ዛሬ የአማኑኤል ጌታችንን ልደት ፣ የእመቤታችንን ቅድሥት ማርያምንና የባለ እግዚአብሔርን በዓልን ስናከብር በከሃዲዎቹና ጨካኞቹ የሉሲፈራውያኑ አሽከሮች በእነ ግራኝ አብዮት አህመድ፣ ኢሳያስ አፈቆርኪና ደብረጽዮን አማካኝነት እስከ ዛሬዋ ዕለት ድረስ ላለፉት ሦስት ዓመታት የሚጨፈጨፉትን፣ የሚራቡትንና የሚሰደዱትን አክሱም ጽዮናውያንን ልናስታውሳቸውና ልናስብላቸው ዘንድ ግድ ነው። ዓለምና በዚህች ዓለም የባርነት ቀንበር ሥር የወደቁት የእኛዎቹ ቃኤላውያን ዝም ጭጭ ብለዋል፤ ይህም ግን ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዛሬም ሁሌም ከእነርሱ ጋር መሆኑን ነው የሚጠቁመን።

አዎ! ቅዱስ የሆነውን ብሶታችንን፣ ጩኸታችንና ለቅሷችንን ለእግዚአብሔር አምላክ እንጂ ለዚህች ዓለም ማሰማት/መስጠት አያስፈልገንም/የለብንም፤ አይገባትምና። የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ!

❖❖❖ ብሩክ የጌታችን ልደት በዓል!❖❖❖

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው | ብሩክ የልደት በዓል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 7, 2022

🔔 ይህ የልደት በዓል፤ ታኅሣሥ ፳፱ / ጃንዋሪ 7 በ፤

  • ❖ ኢትዮጵያ (ኤርትራን ጨምሮ)
  • ❖ እስራኤል
  • ❖ ግብጽ
  • ❖ አርመኒያ
  • ❖ ጆርጂያ
  • ❖ ሩሲያ
  • ❖ ዩክሬን
  • ❖ ቤላሩስ
  • ❖ ሞልዶቫ
  • ❖ ካዛክስታን
  • ❖ ሰርቢያ
  • ❖ ማኬዶኒያ
  • ❖ ሞንቴኔግሮ

በቆንጆ መልክ ይከበራል፤ ብሩክ የጌታችን ልደት እና የእመቤታችን ቅድሥት ማርያም በዓል ለሁላችንም!

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ዮሴፍ | በሚቀጥሉት ቀናት በመላው ዓለም ትልቅ ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡንን ክስተቶችን እናያለን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 4, 2022

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 😇 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

💭 የመጭውን የጌታችንን የልደት በዓል ተከትሎ በሚቀጥሉት ቀናት በመላው ዓለም ትልቅ ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡንን ክስተቶች እናያለን

ኢትዮጵያ = የአዲስ ኪዳን ርስት ምድር = እስራኤል ዘነፍስ❖

💭 “ቅዱስ ጳውሎስ” ከሚለው ፊልም የተወሰደው ምስል የሚያሳየን ትክክለኛው ክርስቲያናዊ አለባበስ ኢትዮጵያኛው አለባበስ መሆኑን ነው።

[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ፲፩፥፳፫]

ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።”

ሰባዓሰገል መጥተው ለጌታ ሲሰግዱ ዮሴፍ አየ አምላክ ነህ ሲሉ እጣን ንጉሥ ነህ ሲሉ ወርቅ ፍቅር ነህ ሲሉ ከርቤ ለጌታ ሲገብሩ ዮሴፍ አየ ለካ ይሔ የተወለደው ሕፃን ተራ አይደለም ነገሥታት የሰገዱለት የነገሥታት ንጉሥ ቢሆን ነው ብሎ ድንግል ማርያም የንጉሥ እናት ኢየሱስን የነገሥታት ንጉሥ አምላክ መሆኑን የበኩር ልጅዋን ስትወልደው አወቀ።

ዮሴፍ ታላቅ ነገር ተመለከተ ደማቅ ኮከብ ከሰማይ ዝቅ ከምድር ከፍ ብሎ በቤተልሔም ዋሻ ፊት ለፊት ሲቆም አየ አሀ ልክ ኢያሱ አሞራውያንን በገባዖን ሲዋጋ በጸሎቱ ፀሐይን እንዳቆማት ኢየሱስ ገና በሕፃንነቱ በቤተልሔም ኮኮብን አቁሟል ስለዚህም ይህ ኮከብ የተገዛለት የጌቶች ጌታ ቢሆን ነው ብሎ ኢየሱስ ጌታ ፈጣሪ ድንግል ማርያም እመ ፈጣሪ የጌታ እናት መሆንዋን አወቀ።

________________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጌታችን የብርሃን ጎርፍ በጐረፈባት በቤተልሔም / በቤተ ክርስቲያን ተወለደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 6, 2020

ውድ የተዋህዶ ልጆች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመደሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ለበዓለ ልዴት በሰላም በጤና አደረሰን፡ አደረሳችሁ

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

መሀመዳውያኑ ደም ለማፍሰስ ቀይ ባንዲራ ሰቀሉ Vs. ክርስቲያኖች ለመድኃኔ ዓለም ቀይ መስቀል አለቀሱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 6, 2020

በገና እና ጥምቀት ዋዜማ ከዚህ የተሻለ የተቃርኖ ምልክት የለም፦

በኢራን መሀመዳውያኑ ደም ማፍሰስ አለበን በሚል መርሆ ቀዩን ባንዲራ መስጊዳቸው ላይ ሲሰቅሉ፤ ጎን ለጎን በሃገራችን የክርስቶስ ልጆች በኦሮሚያ ሲዖል ቀይ ቀለም ለተቀባው የመድኃኔ ዓለም መስቀል ፍቅራቸውን በሃዘንና በእንባ ይገልጻሉ።

________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዛሬ በቅዱስ ዮሴፍ ዕለት ደግሞ ይህ አስገራሚ ነገር ታየኝ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 5, 2020

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ

ሰባሰገል መጥተው ለጌታ ሲሰግዱ ዮሴፍ አየ አምላክ ነህ ሲሉ እጣን ንጉሥ ነህ ሲሉ ወርቅ ፍቅር ነህ ሲሉ ከርቤ ለጌታ ሲገብሩ ዮሴፍ አየ ለካ ይሔ የተወለደው ሕፃን ተራ አይደለም ነገሥታት የሰገዱለት የነገሥታት ንጉሥ ቢሆን ነው ብሎ ድንግል ማርያም የንጉሥ እናት ኢየሱስን የነገሥታት ንጉሥ አምላክ መሆኑን የበኩር ልጅዋን ስትወልደው አወቀ።

ዮሴፍ ታላቅ ነገር ተመለከተ ደማቅ ኮከብ ከሰማይ ዝቅ ከምድር ከፍ ብሎ በቤተልሔም ዋሻ ፊት ለፊት ሲቆም አየ አሀ ልክ ኢያሱ አሞራውያንን በገባዖን ሲዋጋ በጸሎቱ ፀሐይን እንዳቆማት ኢየሱስ ገና በሕፃንነቱ በቤተልሔም ኮኮብን አቁሟል ስለዚህም ይህ ኮከብ የተገዛለት የጌቶች ጌታ ቢሆን ነው ብሎ ኢየሱስ ጌታ ፈጣሪ ድንግል ማርያም እመ ፈጣሪ የጌታ እናት መሆንዋን አወቀ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

ወለወላዱቱ ድንግል

ወለመስቀሉ ክቡር

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምር በዕለተ ጽዮን | ሰማዩ በኢትዮጵያ የማርያም መቀነት ህብረ ቀለማት ተቀባ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 1, 2019

ድንቅ ነው፤ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ ወደ ሙሉ ቀይ ከመለወጣቸው በፊት በደንብ ቁልጭ ብለው ይታዩ ነበር፤ ልክ ፀሐይ ስትወጣ ነበር ይህ የታየኝ፤ ካሜራየን እስካወጣ ትንሽ ድብዝዝ አለ ሆኖም ቀለማቱ ይታያሉ፤ ብርሃኑም አለ። ፀሐይ ስትወጣ ነጋ ፥ ጨለማው ጠፋ!

ነቢያት የአምላክን ማዳን ከጠበቁባቸው እና ከገለጡባቸው መንገዶች አንዱ ብርሃን ነው፡፡ ዘመነ ብሉይ መከራ ሥጋ፣ መከራ ነፍስ የፀናበት፣ ሁሉ ነገር አስጨናቂ የሆነበት፣ ሰው ብርሃን ከሆነው አምላክ ጋር የተራራቀበት ስለነበር ያሉበትን ዘመን «ጨለማ» ብለው በመግለጥ ይህንን ጨለማ የሚያስወግድና ወደ ትክክለኛው መንገድ የሚመራ ብርሃን እንዲመጣ እንዲህ እያሉ ይፀልዩ ነበር፡፡ “ብርሃንህንና ጽድቅህን ላክ፤ እነርሱም ይምሩኝ፡፡ አቤቱ ወደ መቅደስህ ተራራና ወደ ማደራያህ ይውሰዱኝ፤” [መዝ. ፵፪፥፫]፡፡ ጌታችንም ወደዚህ ዓለም በመጣ ጊዜ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ” በማለት ለዚህ ጸሎት ምላሽ ሰጥቷል (ዮሐ. ፰፥፲፪)፡፡ ደቀ መዛሙርቱም ስለ ብርሃንነቱ መስክረዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ስለ ጌታችን ሰው መኾን (ምሥጢረ ሥጋዌ) በተናገረበት በወንጌሉ የመጀመሪያ ክፍል ጌታችንን ብርሃን ብሎታል፡፡ ‹‹ሕይወት በእርሱ ነበረ፤ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረ፡፡ ብርሃንም በጨለማ ያበራል፤ ጨለማም አላሰነፈውም፤” [ዮሐ. ፩፥፬]፡፡

ቅዱስ ጳውሎስ ጌታችን በሚያንጸባርቅ ብርሃን አምሳል እንደ ተገለጠበት ተናግሯል፡፡ “እኩል ቀን በኾነ ጊዜ በመንገድ በሔደ ከፀሐይ ይልቅ የሚበራ መብረቅ በእኔና ከእኔ ጋር ይሔዱ በነበሩት ላይ ከሰማይ ሲያንጸባርቅ አየሁ … አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ አለኝ፤” [ሐዋ. ፳፮፥፲፫]፡፡

በፈርንጆቹ ዘንድ ዛሬ የወሩ መጀመሪያ ታህሣሥ ፩ ነው፤ እነርሱ ከሚያከብሩት የልደት በዓል በፊት ባሉት ሦስቱ የጾመ ነቢያት ሳምንታት የመጀመሪያ ሰንበትና በጨለማማው የክረምት ወር ሻማ የሚያበሩበት ዕለት የሚጀምረው ዛሬ ነው።

ያው እንግዲህ፤ ጌታችን የዓለም ብርሃኑ ምልክቱን እያሳያቸው/ እያሳየን ነው። በማርያም መቀነት ላይ፣ በኢትዮጵያ ቀለማት ላይ ግልጽ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ነው፤ የዚህ ጦርነት ቀስቃሾችም የዲያብሎስ የግብር ልጆች የሆኑት ዔሳውያን (ምዕራባውያን) እና እስማኤላውያን (ምስራቃውያን) ናቸው።

ለሃገራችን ለኢትዮጵያ ሰላምን ለህዝባችን ፍቅር በረከትን ያዉርድልን፡፡ ጽዮን በምልጃዋ ለሁላችንም ትድረስልን!!!

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን ምርጥ ዘር ነው | በአረቡ አለም አንጋፋው ቤተክርስቲያን በግብጽ ተመረቀ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 7, 2019

ከ ካይሮ በስተ ምሥራቅ በሚገኝ ቦታ ላይ በመካከለኛው ምስራቅ አንጋፋ የሆነውን ቤተክርስቲያን ሕንፃ ፓትሪያርክ ታዎድሮስ እና የግብጹ ፕሬዚደንት አብዱልፋታህ አሌሲሲ መርቀው ከፈተዋል። ሕንፃው “የልደት ካቴድራል” የሚል ስም ተሰጥቶታል።

ቀደም ሲል፡ በቅዳሜው ዕለት፡ ሙስሊሞች ቤተከርስቲያኑን በቦምብ ለማፈንዳት ባቅራቢው በሚገኝ ትልቅ መስጊድ ጣራ ላይ ቦምብ አጥምደው ተገኝተው ነበር። ቦምቡን ያከሸፍ ዘንድ ወደ መስጊዱ ተልኮ የነበረው አንድ ፖሊስ በፍንዳታ ሳቢያ ሕይወቱን አጥቷል።

የግብጽ ፕሬዚዳንት በመክፈቻው ሥነ ሥርዓት ላይ ይህ ታሪካዊና አስፈላጊ ጊዜ ነው

ነገር ግን፤ እኛ እዚህ በአንድ ላይ የተከልነውን የፍቅር ዛፍ መጠበቅ አለብንበማለት ተናግረዋል።

የመሀመድ አርበኞች የክርስቶስ ተከታዮችን ክፉኛ በመምታት ላይ በሚገኙበት በዚህ ዘመን፡ በእስያ እና አፍሪቃ ክርስትና እንደ ምስማር በመጥበቅ ላይ ነው።

ይህ ድንቅ የገና ተዓምር ነው! በእውነት ለክርስቲያን ወገኖቻችን ትልቅ ድል ነው፤ እንግዲህ ዲያብሎስና አርበኞቹ አሁን እርር፡ ፍርክስክስ ይበሉ፤ ጊዚያቸው አጭር ነው።

እውነት ነው፤ የሰማዕታት ደም የቤተ ክርስቲያን [ምርጥ] ዘር ነው። እኛ ክርስቲያኖች እንገፋለን እንጂ አንወድቅም፤ አዎ! ክርስቲያን እንደ ምስማር ሲመቱት የሚጠብቅ ነው።

+++የባሪያይቱን መዋረድ አይቶ+++

+++ንጉሥ ወደደሽ ከሴት ለይቶ+++

+++ዝቅ ማለትሽ ከፍ አድርጐሻል+++

+++ድንግል ትሕትናሽ ፍቅር አስጊጦሻል+++

__________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 6, 2018

በዓለ ልደት፣ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የተፈጸመበት በዓላችን ነው፡፡ ለሞት ከመገዛት የዳንበት፤ ጨለማው ተወግዶልን የብርሃን ልጆች የኾንበት፤ የእባብ ራስ የተቀጠቀጠበት፤ ከምድር ወደ ሰማይ ያረግንበትና ከመላእክት ጋር ኾነን ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀረብንበት፤ ከነቢያት ኅብረት ጋር አንድ የኾንበት በዓል ነው፡፡

የጌታችን ልደት እና የመላእክት አገልግሎት

ለአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዘመን በዓለም ላይ ሠልጥኖ የነበረውን ጨለማ ያስወግድ ዘንድ እግዚአብሔር አምላክ ሰው ኾነ፡፡ ከቅድስት ድንግል ማርያም የተወለደው አማናዊው ብርሃን ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ በሥጋ ተገለጠ፡፡ ‹‹ብርሃን ዘበአማን ዘያበርህ ለኵሉ ሰብእ ለእለ ይነብሩ ውስተ ዓለም፤ በጨለማ ውስጥ ለሚኖር ሕዝብ ታላቅ ብርሃን ወጣላቸው›› እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴው (ኢሳ. ፱፥፪)፡፡ ቀዳሚ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው በኾነ ጊዜም ቅዱሳን መላእክት በቤተ ልሔም ተገኝተዋል፡፡ ይህንም ቅዱስ ሉቃስ ‹‹ወግብተ መጽኡ ብዙኃን ሐራ ሰማይ፤ የሰማይ መላእክት በድንገት መጡ›› በማለት ገልጾታል (ሉቃ. ፪፥፲፫)፡፡ በድንገት መባሉም አመጣጣቸው ግሩም በመኾኑ ነው፡፡ ቅዱሳን መላእክት ቀድሞ አመጣጣቸው ጻድቃንን ለመርዳት፣ ሰማዕታትን ከስለት ለመታደግ፣ የተቸገረውን ለማጽናት ነበር፡፡

ዛሬ ግን ስለ ሰው ፍቅር ከሰማይ የወረደውን፣ በጎል (በበረት) የተጣለውን፣ በጨርቅ የተጠቀለለውን አምላክ ከሰው ልጅ ጋር በአንድነት ለማመስገን መጡ፡፡ ‹‹ዮም አሐደ መርዔተ ኮኑ መላእክት ወሰብእ ከመ ይሰብሕዎ ለክርስቶስ ንጉሥ፤ ሰውና መላእክት፣ ንጉሥ ክርስቶስን ያመሰግኑ ዘንድ ተባበሩ›› እንዲል፡፡ መላእክት በተፈጥሯቸው የማይሞቱ (ሕያዋን) ሲኾኑ ሰው ደግሞ ሟች ነው፤ ሞት ይስማማዋል፡፡ በጌታችን ልደት ግን መላእክትና የሰው ልጆች በአንድ ማኅበር፣ በአንድ ቃል ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር›› እያሉ እግዚአብሔርን አመስግነዋል፡፡ በአዳም ኀጢአት ምክንያት ፈርሶ የነበረው የመላእክትና የሰው ልጆች ማኅበር ከተቋረጠ ከብዙ ዘመን በኋላ በኢየሱስ ክርስቶስ ልደት እንደ ገና ተጀመረ፡፡ ይህ የምስጋና ኅብረትም ምድር እንደ ልብስ ተጠቅልላ ስታልፍ ወደ ፊት በምትመጣዋ በአዲሲቷ ዓለም፣ በአዲሱ ሰማይ፣ በአዲሱ ቤተ መቅደስ ይቀጥላል (ራእ. ፳፩፥፩)፡፡

አንድነታችን እንደማያቋርጥና በሰማይም እንደሚቀጥል አረጋዊ መንፈሳዊ ሲገልጥም ‹‹እሉሂ ወእልክቱሂ በአሐዱ ኁባሬ አልቦ ማዕከሌነ ወማዕከሌሆሙ፤ በእኛ በደቂቀ አዳም እና በቅዱሳን መላእክት መካከል ልዩነት የለም›› ይላል፡፡ ይህም የኾነው በጌታችን መወለድ ምክንያት ነው፡፡ በጌታችን ልደት ምክንያት እኛም ዳግመኛ ተወለድን፡፡ የጌታችን ልደት የእኛም የክርስቲያኖች ዅሉ ልደት ነው፡፡ ከሦስቱ የቀጰዶቅያ አባቶች (The three Cappadocian Fathers) አንዱ፣ ታላቁ የቤተ ክርስቲያን አባት ሊቁ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ይህን ምሥጢር ሲገልጥ ‹‹The nativity of Christ is the birthday of the whole human race – የክርስቶስ ልደት የመላው ሰው የልደት ቀን ነው›› ሲል መስክሯል (Hyman of praise to the mother of God)፡፡

ሊቃውንት እንዳስተማሩን እግዚአብሔር አምላክ ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተወለደበት እና ዓለምን ያዳነበት ምሥጢር ከምሥጢራት ዅሉ በላይ ነው፡፡ ይህን ምሥጢር ከማድነቅ ሌላ ሊናገሩት አይቻልም፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም በመገረም ይህን ጥበብ እንዲህ ሲል ይገልጸዋል፤ ‹‹ምን እላለሁ? ምንስ እናገራለሁ? ከዘመን አስቀድሞ የነበረው እርሱ ሕፃን ኾኗልና፡፡ እኔ ፈጽሜ አደንቃለሁ፡፡ ከሰማየ ሰማያት በላይ የሚኾን፣ በዘለዓለማዊ ዙፋን የሚኖር እርሱ በበረት ተጣለ፡፡ ከሥጋዌ አስቀድሞ አይዳሰስ የነበረ አንዱ እርሱ በምድራውያን እጅ ተዳሰሰ፡፡ ኀጢአትን የሚያስተሰርይ እርሱን በጨርቅ ጠቀለሉት፡፡ ይህን ወዷልና፤›› (ሃይማኖተ አበው ዘዮሐንስ አፈ ወርቅ፣ ፷፮፥፲፯)፡፡ ቅዱስ ዲዮስቆሮስም በቅዳሴው የእግዚአብሔርን ሰው የመኾን ምሥጢር እንዲህ በማለት ገልጾታል፤ ‹‹በጐለ እንስሳ ተወድየ አሞኀ ንግሡ ተወፈየ ወከመ ሕፃናት በከየ እንዘ ይስእል እምአጥባተ እሙ ሲሳየ፤ በእንስሳት በረት ተጨመረ፡፡ የንጉሡንም እጅ መንሻ ተቀበለ፡፡ ከእናቱ ጡቶች ምግብን እየለመነ እንደ ሕፃናት አለቀሰ፤›› (ቅዳሴ ዲዮስቆሮስ ቍ. ፲፯)፡፡

በዚህ ታላቅ በዓላችን የምናደንቀው ሌላው ምሥጢር እግዚአብሔር ወልድ በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን፣ በኅቱም ድንግልና ተፀንሶ በኅቱም ድንግልና የመወለዱ ረቂቅ ምሥጢር ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይህን ድንቅ የሥጋዌ ምሥጢር ግሩም፣ ዕፁብ እያሉ ያደንቁታል፡፡ ሐዋርያውያን አበውን ተከትለው ከተነሡ የቤተ ክርስቲያን ጠባቆች (Apologists) መካከል አንዱ ቅዱስ ሄሬኔዎስም ፩ኛ የእመቤታችን ዘለዓለማዊ ድንግልና፣ ፪ኛ ድንግል ማርያም አማኑኤል ጌታን መውለዷ እና ፫ኛ የማይሞተው አምላክ መሞት በእግዚአብሔር የዝምታ ሸማ የተጠቀለሉ ሦስት ምሥጢሮች መኾናቸውን ይናገራል፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ የተባለው አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫም በመጸሐፈ አርጋኖን ድርሰቱ ይህን ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር በሚከተለው መልኩ ይገልጠዋል፤

‹‹ሦስቱን ደጆች ያልከፈተ የአብን ልጅ ጥበብ አደንቃለሁ፤ ያለ መለወጥ በኅቱም ድንግልና በመወለዱ፣ የመቃብሩን ደጅ ሳይከፍት በመነሣቱ፣ ደቀ መዝሙርቱ ተሰብስበው ወዳሉበት ቤት በተዘጋ ቤት በመግባቱ እና በሩን ሳይከፍት በመውጣቱ ስለነዚህም ሦስት ደጆች ልቤ አደነቀች፡፡ ከሁለቱ ይልቅ የመጀመሪያው እጅግ ያስደንቀኛል፡፡ ምክንያቱም ሁለቱን ከዚህ በፊት በመጽሐፍ ቅዱስ አውቃቸዋለሁ፡፡ የመቃብሩን ደጅ የሚመስለው ነገር አለ (ዮሐ. ፳፥፲፱)፡፡ ብልጣሶር የተባለ ዳንኤልን በአንበሶች ጕድጓድ ውስጥ በጣሉት ጊዜ ጕድጓዱን በታላቅ መዝጊያ ዘጉት፡፡ ዳንኤልም በረሃብ እንደ ተጨነቀ ልዑል እግዚአብሔር ባየ ጊዜ መልአኩን ወደ ነቢዩ ዕንባቆም ላከ (ዳን. ፮፥፲፮፲፯)፡፡ በራሱም ፀጕር አንሥቶ ተሸክሞ ወስዶ ዳንኤል ወዳለበት ጕድጓድ አገባው፡፡ ዳንኤልና ዕንባቆም እንጀራውንና ንፍሮውን በልተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ዕንባቆምም ደጅ ተዘግቶ ሳለ ወጣ፡፡ ስለ ቤቱ ደጅም የሚመስል ነገር አለ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ ወርዶ ጴጥሮስን ከግዞት ቤት እንዳወጣው በሐዋርያት ሥራ ተጽፏል፡፡ ጴጥሮስንም ካወጣው በኋላ ደጁ ተቈልፎ ዘበኞች በዅሉ ወገን ይጠብቁ ነበር (ሐዋ. ፲፪፥፮)፡፡ ለእነዚህ ለሁለቱ ደጆች ለቅዱሳን የተገኘውን ምክንያት አገኘሁ፡፡ ስለ ድንግልናሽ ደጅ እጠናለሁ፤ ግን ምክንያት አላገኘሁም፡፡ በድንግልና የኖረች ሴትም አላየሁም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ነገር ኾኖ አያውቅም፡፡ ኢኮነ እምቅድመ ዝ ወኢኮነ እምድኅረ ዝ – ከዚህ በፊት አልተደረገም፤ ከዚህ በኋላም አይደረግም፤›› (አርጋኖን ዘቀዳሚት)፡፡

በአጠቃላይ በዓለ ልደት፣ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል እርቅ የተፈጸመበት በዓላችን ነው፡፡ ለሞት ከመገዛት የዳንበት፤ ጨለማው ተወግዶልን የብርሃን ልጆች የኾንበት፤ የእባብ ራስ የተቀጠቀጠበት፤ ከምድር ወደ ሰማይ ያረግንበትና ከመላእክት ጋር ኾነን ለእግዚአብሔር ምስጋና ያቀረብንበት፤ ከነቢያት ኅብረት ጋር አንድ የኾንበት በዓል ነው፡፡ ድንቅ የተዋሕዶ ምሥጢር የተፈጸመበትን ይህን ልዩ በዓል በመንፈሳዊ ሥርዓት ማክበር ይገባናል፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡

ምንጭ

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሰይጣን መገለጫዎቹ እየተጋለጡ ነው | ጸረ-ክርስቶሱ ሙስሊም የናዝሬት ከንቲባ ገና በዓል በጌታችን ቅድስት ከተማ እንዳይከበር አዘዘ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 17, 2017

ምክኒያቱ፦

ቅናት፣ ጥላቻና ክፋት ነው!

እንደ ከብቲማው ግን፦

ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ እየሩሳሌምን የእስራኤል ዋና ከተማ መሆኗን በማወጃቸው።

የሚገርመው፤ የግብጽም ሆነ የሌሎች “አረብ” ዓብያተ ክርስቲያናት የፕሬዚደንት ትራምፕን ውሳኔ እንደማይቀበሉ ቀደም ሲል ገልጸው ነበር፤ ያውም የናዝሬትን ክርስቲያኖች ከክርስቶስ ከተማ እንዲወጡ፣ ያልወጡትም በሙስሊሞቹ እጅ ለመታረድ እንዲበቁ ከተደረጉ በኋላ። ግን ትዕቢታኛው ሙስሊም ከንቲባ ይህ ሁሉ አለበቃ ብሎት የጌታችንን የልደት በዓል እንዳይከበር ትዕዛዝ ለማስተላለፍ ቃጣ።

አይገርምም?! አይ ፈረዖናዊ ትዕቢት! አቤት ድፍረት! ይህ የዲያብሎስ ሥራ አያስቆጣንምን? ሁልጊዜ በዳዮቹም ተበዳዮቹም እነርሱ ናቸው። ይታየን፤ የመሀመድ የልደት ቀን አይከበረም ብለን አዲስ አበባ ላይ አዋጅ ብናወጣ፤ መቼም መሀመዳውያኑ ምን ዓይነት ቴአትር ይሠሩ እንደነበር አሁን እናውቀዋለን።

እንዲያውም ለሁሉም ሲባል መከልከል ያለበት የእስልምና አምልኮት ነበር። በቅርቡ መከልከሉም የማይቀር ነው፤ ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ።

ተመሳሳይ የሆነ ነገር በጣዖተኛው የምዕራቡ ዓለምም እየታየ ነው፦

አገራቱን እያመሷቸውት ያሉት የዱር አህዮቹ እስማኤላውያን ናቸው፣ ንጹሐኑን ሁሉ እየጨፈጨፉ ያሉት እነርሱ ናቸው፣ ሴቶቻቸውንና ህፃናቱን እየደፈሩ ያሉት ሙስሊሞች ናቸው፣ ባጠቃላይ ምዕራባውያኑን እያታለሉ፣ እየመነዘበሩ፣ እያሸበሩና እየገደሉ ያሉት ሙስሊሞች ናቸው፤ ታዲይ ይህ እንዲህ ሆኖ ሳለ ምዕራባውያኑ ቀደመው የሚወነጅሉትና የሚኮንኑት ክርስቲያኖችንና አፍሪቃውያኑን ነው፤ ምንም ያላደረጓቸውን። የተገለባበጠ ዓለም!

የቪዲዮው መጀመሪያው ክፍል ላይ፤ ኢትዮጵያውያን ጎብኚዎች ጌታችን ያደገባትን የናዝሬትን ከተማ ሲጎበኙ ይታያሉ፤ የእስራኤል ቴሊቪዥን ያዘጋጀው ነው። አስጎብኚዋ እህታችን ቤተ እስራኤላዊት መሰለችኝ፤ አንዳንድ ቦታ ላይ እህቶቻችን ሲያርሟት ይሰማል፤ እንደነርሱም ነጠላ አላደረገችም።

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: