ላሊበላን ከጎበኙ በኋላ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ነበር የታሠሩት። ይህ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፤ እ.አ.አ እ.አ.አ በ 2014 ዓ.ም፤ ወስላታው ሽታይንማየር ገና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር እያሉም በአዲስ አበባ ተመሳሳይ ችግር ገጥሟቸው ነበር።
በብዙ ጀርመኖች ዘንድ የሚጠሉት ሶሻሊስቱ ፕሬዚደንት፡ ፍራንክ–ቫልተር ሽታይንማየር ለተንኮል ነበር ወደ
ኢትዮጵያ የተጓዙት።
ይህን ዜና ሁሉም የጀርመን ሜዲያዎች በሰፊው አቅርበውታል፤ በተለይ በኢንተርኔት ጋዜጦች ላይ የሚሰጡት በጣም ብዙ የአንባብያን አስተያየቶች ለፕሬዚደንቱም ሆነ ለኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያውያን ጥላቻና ንቀት የተሞላባቸው ነው።
ለምሳሌ፦
“ፕሬዚደንቱ እዚያው ይቅሩ፤ አውሮፕላናቸውም በአዲስ አበባ ይቆይ ምናልባት የኢትዮጵያ ወጣቶች ወደ አውሮፓ ከሚሰደዱ የሥራ ዕድል ይፈጥርላቸው ይሆናል።”
„ፕሬዚደንቱ በታክሲ እስክ ሜዲተራንያን ባሕር ድረስ ይምጡና በጀልባ እንዲሻገሩ እናደርጋቸዋለን።”
„ምናለ ሁሉም የፓርላማ አባላት አጅበውት ቢሆን እና ሁሉም እዚያ ተቀርቅረው ቢሆን?!“
„ይሄ ሰውዬ አይናፍቀንም፤ እዚያው በርበሬ የሚበቅልበት አገር ቢቀር ይሻለዋል”
„ኢትዮጵያ ቆንጆ ነች አሉ፤ ግን የፕሬዚደንቱ እዚያ መሆን፡ ለኢትዮጵያውያኖች የስደት መንስኤ ይሆናቸዋል”
____________