በዛሬው ዕለት የጦጣዎች ቡድን በሕንድ ወደ አንድ የህክምና ኮሌጅ በመግባት የላብራቶሪ ቴክኒሺያኖቹን ካጠቁ በኋላ ከሰዎች የተወሰዱትን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ናሙናዎችን ሰርቀዋል፡፡
ጦጣዎቹ ዛሬ ጠዋት በህንድ ግዛት በኡታራ ፕራዴሽ ከሚገኘው ኮሌጅ ሶስት የሙከራ ናሙናዎችን ወስደው ዛፍ ላይ ወጥተዋል። ጦጣዎቹ ቢልቃቶቹን ይዘው በዛፍ ላይ ሲወዛወዙ ይታያሉ፡፡ አንደኛው ጦጣ እንዲያውም ናሙና የያዘውን ቢልቃጥ ሲያኝከው ይታያል።
አሁን ጦጣዎቹ ናሙናዎችን ስለወሰዱ ቫይረሱ በመኖሪያ አካባቢዎች ዙሪያ ሊሰራጭ ይችላል የሚል ከፍተኛ ፍራቻ አለ፡፡
ዝንጆሮዎችና ላሞች በሕንድ “ቅዱስ” ናቸው፤ በጣም ይመለካሉ፤ ሕንዶች (ሂንዱዎቹ)”ሃኑማን” የተባለ ዝንጀሮ–አምላክ አላቸው።
ቀደም ሲል “ድምጻችን ይሰማ!” የሚል መፈክር የነበራቸው ዝንጆሮዎች በኮሮና ቫይረስ ፕሮፓጋንዳ ባለመደሰታቸው ጭር ወዳሉት የህንድ ጎዳናዎች ለተቃውሞ ሰልፍ በመውጣት ሲንጎራደዱ ታይተው ነበር። (ምናለ ወደ አዲስ አበባ ቢሄዱ?!)
ሆኖም ድምጻቸውን የሚሰማቸው ስላጡ ጦጣዎቹ የሕንድን ፓርላማ በቁጥጥራቸው ሥር ለማድረግ ተገደው ነበር።
Monkey Business!
_________________________________