የሰላም፣ የፍቅርና የበረከት በዓል ያድርግልን!
ግን እስኪ አሁንም ደግመን እናስበው፤ ይህን ተወዳዳሪ የሌለውን ፀጋና በረከት ትይዝ ዘንድ “ደብረ ዘይት” ለመባል የበቃቸውን ከተማ “ቢሸፍቱ” ያሉት ምስጋና ቢሶች ምን ያህል ቢያብዱ ነው? ከ ፍየሉ ጋር ተሰልፈዋል፡ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ ጠላት መሆኑን መርጠዋል ማለት ነው። በጣም ይገርማል፤ ቤተ ክርስቲያንን ለማጥፋት ይጮሃሉ፣ አሸዋና ሲሚንቶ ተቀላቅሎ ለተሠራው ኮንዶሚኒየም ግን እስከ መጨረሻው እንሞታለን ይላሉ፤ ነፍሳቸውን ሸጠው ዓለምን ለመውረስ በጥላቻ ኃይል ይጓዛሉ። ነፍሳቸውን ለሸጡለት ዲያብሎስ ዛፍ ሊተክሉለት በመሻት ናዝሬትን አዳማ፣ ደብረ ዘይትን “ቢሸፍቱ” ብለው ሰየሟቸው፣ ወርቅን እምቢ ብለው መዳብን መረጡ። አቤት ምስጋና ቢስነት፣ አቤት እብደት! አቤት ቅሌት! አቤት ንቀት! አቤት ትዕቢት፤ አቤት የሚመጣባቸው ፍርድ!
በሌላ በኩል አንድ ሌላ የሚያሳዝነው ነገር፤ ልክ ብፁዕ አቡነ ጎርጎሪዮስ ትምሕርቱን መስጠት ሲጀምሩ ገንዘብ ቆጠራውም አብሮ መጀመሩ ነው፤ ክቡር ታቦቱ ፊት፣ የድምጽ መቅጃው አጠገብ፤ ይህም ከበስተጀርባው በሚረብሽ መልክ ይሰማል። እንደው ምናለ ስነ ሥርዓቱ ሁሉ ተገባድዶ ሁሉም ወደየቢቱ ከተመለሰ በኋላ ለገንዘቡ ጊዜ ቢሰጥ? ምናለ ገንዘብን የተመለከት ነገር ሁሉ እንዲህ በቤተ ክርስቲያን አደባባይ ባይሠራ! ወይስ ተንኮል ነገር አለ? መቼስ ዲያብሎስ ሁሌ ከቤተክርስቲያን አይርቅምና።