ሁለቱ የዓለማችን ጥንታውያን የክርስቲያን ሃገራት የክርስቶስ ተቃዋሚውን በጣም መማረካቸው ሊያስደንቀን አይችልም።
ከመቶ ዓመታት በፊት ሁለት ሚሊየን አርሜናውያን ክርስቲያን ወገኖቻችንን የጨፈጨፈችው ቱርክ ዛሬም አርሜኒያን በማሳደድ ላይ ነች። የገዳይ ግራኝ አል–አብይ አጋር የሆነው እብዱ የቱርክ ፕሬዚደንት ኤርዶጋን አሥር ሺህ ኪሎሜትር ያህል ተጉዞ ወደ ደቡብ አሜሪካ በመሄድ አርሜኒያ ተብላ በተሰየመችው የኮሎምቢያ ከተማ አንድ የቱርክ ኃውልትን ለመትከል በቅቷል። ይህ በጣም የሚገርም ነገር ነው።
እንደምናየው ቱርክን የክርስቲያን ሰማዕታት ደም በጣም ያቁነጠንጣታል ያለው። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት አክሱምን ለመቆጣጠር በመሻት ግራኝ አህመድን በመልመል በሃገራችን ላይ ብዙ ጥፋቶችን አስከትላ ነበር። ዛሬም እኛ በጉለሌ ጉዳይ እርስበርስ ስንባላ ለስለስ ባለ መንገድ በሐረር በኩል በመግባት ላይ ናት። በአንድ በኩል፡ ትምህርት ቤቶችን፣ የባህል ማዕከላትን፣ ምግብ ቤቶችንና መስጊዶችን ልስራ እያለች ሰላማዊ በሆነ መልክ ሰተት ብላ ስትገባ ፥ በሌላ በኩል ደግሞ በሶማሊያ ከፍተኛ የጦር ዝግጅት በማድረግ ላይ ትገኛለች። እርኩሷ የክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ደም ጠምቷታል፤ ስለዚህ ለአርሜኒያ ያሰበችው ለኢትዮጵያም ይሆናል። ከመቶ ዓመታት በፊት በዘመነ ግራኝ አህመድ ከሶማሌዎች ጋር ጥብቅ ግኑኝነት የነበራት ቱርክ ዛሬም በዳግማዊ ግራኝ አህመድ ዘመን ለሶማሌዎች ያላት ዲያብሎሳዊ ፍቅር በጣም ጥብቅ ነው። ዓይናችንን በተለይ በቱርክ ላይ ይሁን!
ሁለቱ ጥንታውያን ክርስቲያን ሃገራት ለቱርክ ውድቀት ምክኒያት ይሆናሉ። ታዋቂው የግሪክ ኦርቶዶክስ አባት ፓይሲዮስ እንደተነበዩት ከሆነ ቱርክን በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ እርዳታ የምታጠፋት በዛሬው ታሪካዊ ዕለት የመከላከያ ሮኬቶችን ለቱርክ የሸጠችላት ኦርቶዶክስ ሩሲያ ናት። Elder Paisios’ Amazing Prophecies About Constantinople
ከቱርክ ጋር የሚያብር፣ ለቱርክ የሚሠራ የሃገረ ኢትዮጵያና አምላኳ ጠላት ነው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ነው። ተዋሕዶ መሪዋ ክርስቶስ ይባላል፤ ኢትዮጵያን(ኃይማኖቷን ተዋሕዶን)የነካ ሐያሉ አምላክ ይገስፀዋል።