👉 ኬኖሻ – ሻሸመኔ =Kenoshashemene
ኬኖሻ በተባለችውና በዊስኮንሲን ግዛት በምትገኘዋ ከተማ የታጠቁ ኃይሎች የእርስበርስ ጦርነት ጀምረዋል። በግዛቲቱ ለሦለተኛ ቀን የዘለቀ ከፍተኛ ብጥብጥ ተቀስቅሷል። ዛሬ አንድ ሰው በጥይት ተመትቷል። ሕንፃዎች ወድመዋል፤ መኪናዎች ተቃጥለዋል።
የኬኖሻ ከተማ አስተዳደር ከምሽት 2 ሰዓት እስከ ጥዋት 1 ሰዓት የሚቆይ ሰዓት እላፊ ቢጥልም ተቃዋሚዎች ገደቡን ጥሰው ድምፃቸውን ሲያሰሙ አምሽተዋል። በርካታ ወጣት ተቃዋሚዎች የከተዋማ ፍርድ ቤትን ሊጠብቁ ከቆሙ የፀጥታ ኃይሎች ጋር ተጋጭተዋል። ተቃዋሚዎች ‘ፍትህ ለጄኮብ‘ በማለት ድምፃቸውን እያሰሙ እንዳሉ ከሥፍራው የሚወጡ ዘገባዎች ያሳያሉ።