👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
✞✞✞ [ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፱፥፳፩፡፳፫]✞✞✞
“ገናም በጸሎት ስናገር አስቀድሜ በራእይ አይቼው የነበረው ሰው ገብርኤል እነሆ እየበረረ መጣ፤ በማታም መሥዋዕት ጊዜ ዳሰሰኝ። አስተማረኝም፥ ተናገረኝም እንዲህም አለ። ዳንኤል ሆይ፥ ጥበብንና ማስተዋልን እሰጥህ ዘንድ አሁን መጥቻለሁ። አንተ እጅግ የተወደድህ ነህና በልመናህ መጀመሪያ ላይ ትእዛዝ ወጥቶአል፥ እኔም እነግርህ ዘንድ መጥቻለሁ፤ አሁንም ነገሩን መርምር፥ ራእዩንም አስተውል።”
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን። እኛንም በአማላጅነታቸው የምታመን ሁላችንን የብርሃናዊውን መልአክ የቅዱስ ገብርኤልን፣ የሕጻኑ ቂርቆስንና የቅድስት ኢየሉጣን ረድኤት በረከታቸውን ያሳድርብን። በጸሎታቸው ይማረን።
________________________________