Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት’

ሰቆቃ ቤተ ክርስቲያን ትግራይ | ጂሃድ በአባ ዘ-ወንጌል ማዕቢኖ ደብረሲና መስቀለ ክርስቶስ ገዳም ላይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 19, 2021

😠😠😠 😢😢😢

‘ክርስቲያን ነኝ! ኢትዮጵያዊ ነኝ!’ የሚል ወገን እንዴት ከአህዛብ ቱርክ ጋር አብሮ ክርስቲያንና ኢትዮጵያዊ የሆነውን ወንድሙን ይወጋል? ከአምስት መቶ ዓመታት በፊት፤ በዘመነ ግራኝ ቀዳማዊ፤ ኦሮሞዎችና/ጋሎችና ሶማሌዎች ልክ እንደዛሬው ከክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ጋር መሰለፋቸው የሚታወቅ ነው፤ ግን “አማራ” የተባሉትስ በወቅቱ ተመሳሳይ ክህደት ፈጽመዋልን? ታሪክ እኮ የዛሬው እና የወደፊቱ መስተዋት ነው! እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!!!

😈 በአማራዎች፣ በሶማሌዎች እና በኦሮሞዎች የሚደገፈው የፋሺስቱ ኦሮሞ እና ቤንአሚር ኤርትራ አገዛዝ አህዛብ ሰአራዊት እንዲህ ነበር አባቶቻችንን እናቶቻችንን የጨፈጨፋቸውና ✞ የቤተ ክርስቲያኑንም ሕንፃ ያፈራረሰው! ዋይ! ዋይ! ዋይ!

በትግራይ አሲምባ ተራሮች ላይ የሚገኘው እንዳ መስቀለ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ❖

Enda Meskel Kristos Church in the Asimba Mountains

[፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፬፥፳]

ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?”

❖❖❖[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፯፥፳፩፡፳፫]❖❖❖

በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ የሚለኝ ሁሉ መንግሥተ ሰማያት የሚገባ አይደለም። በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል። የዚያን ጊዜም። ከቶ አላወቅኋችሁም፤ እናንተ ዓመፀኞች፥ ከእኔ ራቁ ብዬ እመሰክርባቸዋለሁ።”

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፲፱]✞✞✞

፩ በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኽሁ፥ ሰማኝም።

፪ ከዓመፀኛ ከንፈር ከሸንጋይም አንደበት፥ አቤቱ፥ ነፍሴን አድናት።

፫ ስለ ሽንገላ አንደበት ምንም ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?

፬ እንደ በረሃ እንጨት ፍም የኃያላን ፍላጾች የተሳሉ ናቸው።

፭ መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፤ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።

፮ ሰላምን ከሚጠሉ ጋር ነፍሴ ብዙ ጊዜ ኖረች።

፯ እኔ ሰላማዊ ነኝ፤ በተናገኋቸው ጊዜ ግን በከንቱ ተሰለፉብኝ።

____________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር አብ ፥ የአጽናፈ ዓለሙ ፈጣሪ እና ገዥ ተዓምሩን በቅርቡ ያሳየናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 22, 2021

💭 በአስደናቂ ልዩ ጥበብ የተሠራውና “አዲሱ ገበያ” ተብሎ በሚጠራው ሠፈር የሚገኘው ውቡ የእግዚአብሔር አብ ቤ/ክርስቲያን ሕንፃ፤ አዲስ አበባ ፳፻፲ ወ ፩ ዓ.ም።

💭 እንዲሁም ፳፯/ 27 ጥንታውያን የኢትዮጵያ ነገዶችን ጨፍጭፈው ከምድረ ገጽ ያጠፏቸው ወራሪዎቹ የዋቄዮ-አላህ አርበኞች የሆኑ ኦሮሞዎች/ ጋሎች ወደ አብርሃ ወአጽበሐ እና ንጉሥ ዳዊት ከተማ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ከመስፈራቸውና “ፊንፊኔ ኬኛ” የሚለውን የእባብ ገንዳ መዝሙራቸውን ከመጻፋቸው ከሺህ ዓመታት በፊት የታነጸው ታሪካዊው የካ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን / ዋሻ

ዛሬ የእግዚአብሔር አብ ዕለት ነው፣ ወደ ጸሎት በምንገባበት ወቅት የወገኖቻችንን ሰቆቃና ለቅሶ በይበልጥ እየሰማን ነው፤ የአቤል ደም እየጮኸ ነው፤ የጽዮን ጠላቶች እየተርበተበቱ ነው፤ ግን የትም አያመልጧትም፤ ለዓመታት ስናስጠነቅቅ ቆይተናል፤ አሁን አንድ በአንድ በመለኮታዊ ሰይፍ የሚጠረጉበት ጊዜ ተቃርቧል፤ ቀጣዮቹን ቀናት በጥሞና እንከታተላቸው፤ የጽዮናውያን ድልና የዋቄዮ-አላህ አህዛብ ሽንፈት ወቅት በጣም እየተቃረበ ነው!

ቅድስት በኾነች በጽርሐ ጽዮን በሐዋርያት ላይ የወረደው የእግዚአብሔር አብ ጸጋ፣ የእግዚአብሔር ወልድ ፍቅር፣ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አንድነት በዅላችን ላይ ይደር፤ እጽፍ ድርብም ይኹን።

___________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ተዓምር በመስቀል (የመጣበት) ዕለት | በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 20, 2021

💭 ይህ የመገለጥና የመለያ ጊዜ ነው!

✞✞✞[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩]✞✞✞

፳፭ በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ

፳፮ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና

፳፯ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል

፳፰ ይህም ሊሆን ሲጀምር ቤዛችሁ ቀርቦአልና አሻቅባችሁ ራሳችሁን አንሡ

ትናንትና እሑድ ማታ፤ መስከረም ፱/9 ፪ሺ፲፬ ዓ.ም ፥ የሔኖክ ሰማይ ሰሌዳ በጨርቆስ ዕለት። ሙሉ ጨረቃዋን የከበበው የፊቱ ገጽታ ይታየናልን?

ዛሬ ሰኞ መስከረም ፲/10 ፪ሺ፲፬ ዓ.

የሔኖክ ሰማይ ሰሌዳ በመስቀል ኢየሱስ/ በጴዴኒያ /በመስቀል (የመጣበት)ዕለት ፥ ደመናውና ፀሐይዋ መስቀሉን ሠርተዋል። ባትሪ አልቆ ሙሉው አልገባልኝም እንጂ ለአሥር ደቂቃ ያህል የቆየው ትዕይንት በጣም ድንቅ ነበር።

የመላዕክትና የቅዱሳን ቅርጾች፣ ብርሃናት፣ የኢትዮጵያ ካርታ፣ ከማርያም መቀነት ያገኘናቸው ቀይ፣ ቢጫና አረንጓዴ ቀለማት፣ መስቀልና ሌሎች ብዙ አስደናቂ ምልክቶች በሰማዩ፣ በደመናዎች፣ በባሕሩ እና በነጎድጓዶች ላይ በየጊዜው እየታዩን ነው።

ባለፈው መስከረም ፪ የመጥምቀ መለኮተ ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕትነት ዕለት የገጠመኝንና የታየኝን ድንቅ ነገር ሲፈቅድልኝና ሰብሰብ ስል ለማቅረብ እሞክራለሁ።

✞✞✞[ትንቢተ ዳንኤል ምዕራፍ ፯፥፲፫]✞✞✞

በሌሊት ራእይ አየሁ፤ እነሆም፥ የሰው ልጅ የሚመስል ከሰማይ ደመናት ጋር መጣ በዘመናት ወደ ሸመገለውም ደረሰ፤ ወደ ፊቱም አቀረቡት።

✞✞✞[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፩፥፯]✞✞✞

እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።

አዎ! በእውነት ድንቅ ዘመን ላይ ነን!“ዓይን የሌለው ያዳምጥ፤ ጆሮ የሌለው ይመልከት!“ የምንልበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ማወቅ እና መተዋወቅ፣ መለየትና መለያየት የሚገባን ዘመን ላይ ነን።

ወስላታው ጋንኤል ክብረት የኢትዮጵያ እና ተዋሕዶ መሠረት፣ ጠባቂ ባለውለታዋ በሆኑት የጽዮን ልጆች ላይ የዘር ማጥፋት ጥሪ አድርጎ አንድም “አባት”፣ አንድም “መምህር” ወጥቶ እግዚአብሔርን ሳይሆን ዋቄዮአላህዲያብሎስን በማገልገል ላይ ያለውን ሙቱን ጋንኤል ክስረትን ለማውገዝና ግለሰቡም ቤተ ክርስቲያንንም ሆነ ኢትዮጵያን ሊወክል እንደማይችል ከሃዘን እና እንባ ጋር ለማውስት ፈቃደኛ ሆኖ ፈሪሃ እግዚአብሔር እንዳለው ለማሳየት ማንም የኦሮማራ ሰባኪ፣ ፈቃደኛ አለመሆኑን እስኪ እንታዘበው።

‘መምህር’ ወይንም ‘ዲያቆን’ አልላቸውም፤ ግን ለትህትና ስል ላክብራቸውና “አቶ” ልበላቸው፤ አንድ የትግርኛ ተናጋሪ አባት ትግራይን “ቅድስት ምድር” በማለታቸው ለሳምንትት፤ “እርርይ! ያዙን ልቀቁን!” ሲሉ የነበሩትና ለረጅም ጊዜ ሳከብራቸው እና ሳደንቃቸው የነበሩት እንደ እነ አቶ ዘበነ ለማ፣ አቶ ምሕረተአብ አሰፋ፣ አቶ ግርማ ወንድሙ፣ ሸህ አቡ ፋና a.k.a አቡነ ፋኑኤል፣ አቶ ዘመድኩን በቀለ፣ እነ አቶ ኤፍሬም እሸቴ፣ እነ አባይነህ ካሴ እና የመሳሰሉት ግብዝ የሆኑት ሌሎች ታዋቂ “ሰባኪያን/መምህራን”

ኦሮማራዎቹ የሰአራዊቱ አባላት ዘጠኝ ንጹሐን የጽዮን ልጆችን ከገደሏቸው በኋላ በአሰቃቂ ሁኔታ እሳት ሲያቃጥሏቸው፣

በትግራይ የተከሰተውን ረሃብ የሚያሳዩ ምስሎችን “የወሎ ነው!” እያሉ በሐሰት ሲመስክሩ፣

ተጋሩ ተጎድተውና ተጨፍጭፈው “እኛ ነን የተጨፈጨፍነው” ብለው በዳዮቹ እግዚአብሔር በሚጠላው መልክ ተበዳዮች ለመሆን ሲሠሩ፣

ጽዮናውያን ምግብና መድኃኒት እንዳይደርሳቸው መንገድ ሲዘጉባቸው፣

ጋንኤል ክስረትና ሌሎች ብዙ እሱን መሰል ሙታኖች በኦሮሚያ ሲዖል ሕዝባቸውን የሚጨፈጭፉትን መሀመዳውያንና ኦሮሞዎችን ትተው ምንም ባላደረጓቸው በክርስቲያን ተጋሩ ላይ የዘር ማጥፋት ጥሪዎችን ሲያቀርቡ፣

ተዋሕዶ ነን” የሚሉት ጎንደሬዎች ምንም የማያውቁ ገበሬዎችን ታቦት አሸክመው ወንድሞቻቸውን ይገድሉ ዘንድ በድግስ እና ጭፈራ ሲሸኟቸው፣

ባጠቃላይ የክርስቶስ ተቃዋሚው ፋሺስቱ የኦሮሞ አህዛብ አገዛዝ ከታሪካዊ የሃገራችን ጠላቶች ጋር አብሮ በሃገራችን፤ በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ግልጽ የሆነ የጥፋት ጂሃድ ሲያካሂድ፤

😈 ሁሉም እነዚህን ዓለም አይቷቸው ሰምቷቸው የማያውቁትን እጅግ በጣም አሰቃቂና አስቀያሚ ተግባራት ከመቃወም፣ ከማውገዝና ጉዳዩንም አስመልክቶ ተገቢውን ትምህርት ከመስጠትና ሕዝቡንም በአግባቡ ከማንቃት መቆጠቡን መርጠዋል። ትክክለኛ ኢትዮጵያውያንና ክርስቲያኖች ቢሆኑ ኖሮ ለ666ቱ የኮሮና ክትባት ድጋፍ ቅስቀሳ ከማድረግ ተቆጥበው/ወይንም ክትባቱን አውግዘው በተናገሩ ወይንም ቤታቸውን ዘግተው በማልቀስ ለንስሐ የሚበቁበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር። እነዚህ ወገኖችበተለይ ላለፉት አሥር ወራት አፍርተው የምናየው ፍሬዎቻቸው የኢትዮጵያ እና ተዋሕዶ ክርስትናዋ ጠላቶች፤ የክርስቶስ ተቃዋሚው የቱርክ እና አረቦች ውኪል የግራኝ አብዮት አህመድ አሊ አህዛብ አገዛዝ ተባባሪዎች መሆናቸውን ነው። እነዚህ ግለሰቦች ሁሉም ቆለኞች/ደቡባውያን ኢትዮጵያ ዘስጋ መሆናቸውን ልብ ብለናል?። ወዮላቸው!

💭 የሚከተለው ከዓመት በፊት የቀረበ ነው፤

የማንቂያ ደወል | አህዛብ ለአሠርተ ዓመታት የደገሱልን ድግስ ፍንጣቂ እየታየን ነው

ትንፋሽ የሌለው ሰው የሞተ እንደሆነ ሁሉ፣ የማትናገር ቤተክርስቲያንም የሞተች ነች” – አባ መዓዛ ክርስቶስ በየነ

ለሃገር የቆመች ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ብቻ ናት!”

ቃለ ሕይወት ያሰማለን፡ መምህር ዮርዳኖስ፤ የደፋሩን ሸህ እና የ666እስልምና ጣዖት አምልኮ እባባዊ አካሄድን በደንብ ደርሰህበታል። የአገራችን ተቀዳሚ ችግር ይህ መሆን በተገባው ነበር፤ የማንቂያው ደወልም ወደዚህ እውነት ሊወስደን በተገባው ነበር።

አብዛኞቹ እራሳቸውን በማታለልና በመሸጥ ከገዳይ አብይ ጎን ቆመው ወለም ዘለም በሚሉበት በዚህ የመተዛዘቢያና የመለያያ ዘመን እንዲህ በግልጽና በቀጥታ የሚናገር መምህር መኖሩ ተስፋ የሚሰጥ ነው። በተለይ በዚህ ዘመን ጊዜውን እየዋጀ የአብይ አህመድ አሊን እና የ666እስልምናን አደገኛነት በግልጽ ወጥቶ የማያጋልጥና የማያወግዝ መምህር ወይም ሰባኪ ከቁምነገር ሊቆጠር አይገባውም። የፈለገው ችሎታና እውቀት ይኑረው፤ ለዚህ ዘመን ካልተገለገለበት ሁሉም ነገር ዝርያ ነው፤ ለመቼስ ሊሆን ነው?

እስኪ ይታየን፤ ምን ዓይነት የክርስትና መምህር ነው ሁሉም በየእምነቱ ጸሎት ያድርግ፣ እኔ ለእግዚአብሔር አምላክ፣ እናንተ ደግሞ ለዋቄዮአላህ ዲያብሎስ ፥ ተቻችለን እንኑር፤ እኔ ብቻ ገነት ልግባ እንጅ ሌላው አይመለከተኝምበማለት የወገኑን ወደ ሲዖል መግባት የሚመኝ? ምን ዓይነት ስንፍና፣ ግድየለሽነትና ጭካኔ ነው? ምናለ በአንዷ ሴት በእህተ ማርያም ላይ ያሳዩትን ዓይነት ወኔ እና ጀግንነት ኢትዮጵያውያንን ጠፍሮ ባሠረው የእስልምና ዲያብሎስ ላይ ቢያሳዩት! የሚገርም ነው እኮ፤ አንዱ መምህር የሽሁን እጅ ይስማል ሌላው የስየጣን ቤት መስጊድ ያሠራልጉድ እኮ ነው!

እውነቱን ለመናገር፤ በዚህ ዘመን እኛ ክርስቲያኖችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጌትነት ደጋግሞ ከሚሰብከን ሰባኪ ይልቅ የእስልምናን 666ትነት፣ የመሀመድን ሐሰተኛ ነብይነትና ክርስቶስ ተቃዋሚነት የሚያጋልጠውን ሰባኪ አምነዋለሁ፣ አከብረዋለሁ ፤ ታታሪ ነህ!” እለዋለሁ።

ብዙዎች ግን ዛሬ ሁሉም ነገር ግልጥልጥ ብሎ እየታየ አውቀው ተኝተዋል። መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያን ነቅተው ሲነሱ ኢትዮጵያም አብራ ትነሳለች። የኢትዮጵያ ስምና ክብር የተዘጋጀው በመንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን ስኬት በኩል ብቻ ነው። መንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን ነቅተው ተነስተው የሃገሪቱን አመራር ከስጋውያን ኢትዮጵያውያን በፍጥነት ካልተረከቡ ኢትዮጵያ ትሞታለች። ኢትዮጵያ የበለጸገችና ገናና እንዲሁም ልዕለ ኃያል የሚለውን ስሟንና ክብሯን እንደገና ማመለስና መውረስ የምትችለው መንፈሳዊ ኢትዮጵያውያን በማንነትና በምንነታቸው ሲገለጡና ሲነግሱ ብቻ ይሆናል። ጠላት ይህን ያውቃል።

በሃገራችን፣ በቤተ ክርስቲያናችን እና በሰላማዊ ልጆቿ ላይ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ወንጀል፣ ግፍና መከራ በዚህ በአህዛብ መንግስት በየቀኑ ሲፈጸሙ እያዩ ለምንድን ነው ሌሎች መምህራን ወጥተው እውነቱን ለመናገር የማይደፍሩት? ምንስ የሚይዛቸው ነገር አለ? እውነት ለስጋቸው፣ ለተወዳጅነታቸውና ለዝናቸው አስበው ይሆን?” የሚሉት የብዙ የተዋሕዶ ልጆች ጥያቄውች ናቸው።

በርግጥ መምህራኑ ከእኔ እና እናንተ የበረታ ፈተና የሚገጥማቸው ናቸው፤ ሆኖም ግን ለረጅም ጊዜ ሳከብራቸው እና ሳደንቃቸው የነበሩት እንደ መምህር ምህረት አብ አሰፋ፣ መምህር ዳንኤል ክብረት፣ መምህር ዘመድኩን በቀለ፣ መምህር ዘበነ ለማ እና መምህር ግርማ ወንድሙ የመሳሰሉትን ታዋቂ መምህራን በሃገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የአህዛብ መንግስት እየፈጸመው ያለውን ጂሃድ በግልጽ ከማውገዝና ጉዳዩንም አስመልክቶ ተገቢውን ትምህርት ከመስጠት መቶጠባቸው የግብረሰዶማዊው የአብይ አህዛብ መንግስት ተባባሪዎች አያደርጋቸውምን?

የመምህራኑን የህይወት ታሪክና የአገልግሎት ጉዟቸውን መለስ ብለን ብንመረምር፤ ሁሉም የተጠሩት የአህዛብን እና መናፍቃንን አስተምህሮዎች ለማጋለጥ በዚህም ተዋሕዷውያንን ለማንቃት ነበር። በዚህም ግርም ሥራ ሠርተው ነበር! ነገር ግን በኋላ ላይ ሁሉም ይህን እርግፍ አድርገው በመተው በባቢሎን ሃገራት መንሸራሸሩን መርጠዋል። እስኪ እንታዘበው፤ መምህር ምህረተ አብ እነዚያን የተደሰትንባቸውን የማንቂያ ደወል መርሃ ግብሮች በአፈቄሳር ዳንኤል ክብረት አጋዥነት ካቆመ በኋላ ኢትዮጵያን ለቅቆ ወደ ሰዶም እና ገሞራ ላስ ቬጋስ አመራ። በጣም ነበር ያዘንኩት፤ እስኪ ይታየን የአውሬው መንግስትን ከንቱ አዋጅ አልቀበልም ብሎ የማንቂያ ደወሉን ቢቀጥልበት ምን ዓይነት ድንቅ የሆነ ክርስቲያናዊ ዐቢይ በኢትዮጵያ ሊቀስቀስ ይችል እንደነበር።

ዛሬ እንደምናየው፤ ላለፉት 150 ዓመታት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪ፣ ገዥና የበላይ መንግስት ወይም ህግ የደቡብ ህዝብ ስጋዊ ማንነትና ምንነት ነው። መንፈሳዊው የሰሜኑ ህዝብና መንግስት ጸጋውንና በረከቱን በፈቃዱ ለስጋዊው የደቡብ ህዝብ አበርክቷል። ገዥ ስምና ክብር የሚሆነው የዚህ እንግዳ ፣ ባዕድ ፣ አዲስና ጸጉረልውጥ ህዝብ ማንነትና ምንነት ነው የሚሆነው። ይህ አንዳንድ ሙሉ በሙሉ ያልነቁትን ወገኖቼን ይከነክናቸው ይሆናል፤ ነገር ግን አፄ ሚኒሊክ፣ አፄ ኃይለ ሥላሴ እና ህወሃቶች የመንፈሳዊው ሰሜን ህዝብን ጸጋና በረከት ለስጋዊ ደቡብ ሕዝቦች አበርክተዋል። በተለይ ባዕድ ለሆኑት ኦሮሞዎችና ሶማሌዎች። ከሰሜን የተነሱት ህወሃቶች በሰሜንነታቸው እጅግ በጣም ለሚጠሏቸው፣ ኢትዮጵያን ለሚጠሏት ለስጋውያኑ ለኦሮሞዎችና ለሶማሌዎች በጭራሽ የማይገባቸውን አንጋፋውን የኢትዮጵያን ምድር ቆርሰው መስጠታቸው አይገርምምን? በጣም እንጅ!

የመንፈሳዊውን የሰሜኑን የኢትዮጵያ ህዝብ ጸጋና በረከት የወሰደውና ለራሱ ስምና ክብር ያደረገው ስጋዊው የደቡቡ ህዝብ ሲሆን ይህም እውነት ዛሬ በምናየው የኢሀዴግ ብሔር ብሔረሰቦችበሚለው ተልካሻ ስጋዊ ህገመንግስት ተገልጦ በሁሉ ላይ ነግሶ ይታያል።

የዛሬዋ ኢትዮጵያ ሁለት በተፈጥሯቸው ጠላት የሆኑ ማንነቶችና ምንነቶች ያላቸው ህዝቦች የሚኖሩባት አገር ናት። እግዚአብሔር ይቅር ይበለኝ ከተሳሳትኩ እንጂ እነዚህ ላይ የተጠቀሱት ስጦታው የተሰጣቸውና ሳከብራቸው የነበሩ መምህራን ምናልባት የተፈጠሩበት ስጋዊው የደቡብ አፈር የነገሰውን ስጋዊ የደቡብ ኢትዮጵያ መንግስት ማንነትና ምንነት የራሳቸው አድርገው በመቀበላቸው የሚፈጽማቸውን በደሎች ከማውገዝ እንዲቆጠቡ አድርጓቸው ሊሆን ይችላል።

የሚገርም ነው፤ ሁሉም መምህራን ከደቡብ ኢትዮጵያ ናቸው፦

. መምህር ምህረት አብ አሰፋ (መቱኢሉባቦር)

. መምህር ዳንኤል ክብረት(ስጋዊ ደቡብ ነው)

. መምህር ዘመድኩን በቀለ (ሐረር)

. መምህር ዘበነ ለማ (???)

. መምህር ግርማ ወንድሙ(ጎባ – ባሌ)

እና ብዙ ሌሎችም…

__________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 30, 2021

💭 ድንቁ ገዳም ማርያም ታምባ ቆላ ተምቤን ትግራይ

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

❖ አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፤ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ። እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

🌞መለአክ ብርሃን ቅዱስ ዑራኤል🌞

ኡራኤል የሚለው ስም ‘ዑር’ እና ‘ኤል’ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው። ‘ዑራኤል’ ማለት ትርጉሙ “የብርሃን ጌታ” ፣ “የአምላክ ብርሃን” ማለት ነው ። ከምወዳቸው መላዕክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ዑራኤል ከ፯/7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ከፍጥረተ አለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልአክ ነው።

በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፮፥፪] ሚስጢር ሰማይና እዉቀትንም ሁሉ ለአባታችን ሔኖክ የገለፀለት፤ የፀሐይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሠራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሔኖክ ነግሮታል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፲፰፥፲፫] ቅድስት ድንግል ማርያም ፣ ከልጇ ከአምላካችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ግብፅ ስትሰደድ መንገድ የመራ ፤ ክርስቶስ ለዓለም ቤዛ በተሰቀለ ጊዜ ፣ ክቡር ደሙን በብርሃን ፅዋ ተቀብሎ ፣ በብርሃነ መነሳንስ በዓለም ላይ የረጨ ፤ እዉቀት ለተሰወረባቸው ለነቢዩ ዕዝራ ሱቱኤል ፅዋ ጥበብን ያጠጣ መለአክ ነው።

❖❖❖ ለትግራይ ጾም፣ ፀሎት፣ ምሕላ እና ስግደት በሚደረግባቸው በእነዚህ ሦስት ልዩ ዕለታት ሦስቱ የጽዮን ቀለማት ቀይ፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ (ትክክለኛው ቅደም ተከተል) ሦስት ሆና የምትታየዋን ፀሐይዋን አጅበው እንዲህ አንጸባረቁ! የሥላሴ ሥራ ድንቅ ነው! ድንቅ ነው! ድንቅ ነው!❖❖❖

🌞🌞🌞 እግዚአብሔር በገናንነቱ ታላቅ ነው፤ ሦስት ስም አንድ እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን በቃሉ የፈጠረ ፀሐይን በቀን ጨረቃና ክዋክብትን በሌሊት ያሠለጠነ እሱ ከሃሊ ነው። የሚያስደነግጥ መለኮታዊ መብረቅ የተንቦገቦገ መለኮታዊ ፍሕም ተወርዋሪ መለኮታዊ ቀስት። የሚያቃጥል መለኮታዊ እሳት የሚያበራ መለኮታዊ ፋና አንጸባራቂ መለኮታዊ ፀሐይ። 🌞🌞🌞

💭“ሦስት ፀሐይ” በኦሮሚያ ሲዖል | የፀሎተ ትግራይ ፍሬ? | የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ወዮላችሁ!“

❖❖❖ የቅዱስ ኡራኤል በረከቱ በሁላችንም ላይ ይደርብን፤ አሜን!❖❖❖

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፮]✝✝✝

፩ እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ሐሤትን ታድርግ፥ ብዙ ደሴቶችም ደስ ይበላቸው።

፪ ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፤ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

፫ እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።

፬ መብረቆቹ ለዓለም አበሩ፤ ምድር አየችና ተናወጠች።

፭ ተራሮችም ከእግዚአብሔር ፊት፥ ከምድር ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።

፮ ሰማያት የእርሱን ጽድቅ አወሩ፥ አሕዛብም ሁሉ ክብሩን አዩ።

፯ ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ፥ ስገዱለት።

፰ አቤቱ፥ ስለ ፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፥ የይሁዳም ሴት ልጆች ደስ አላቸው፤

፱ አንተ፥ እግዚአብሔር፥ በምድር ላይ ሁሉ ልዑል ነህና፥ በአማልክትም ሁሉ ላይ እጅግ ከፍ ከፍ ብለሃልና።

፲ እግዚአብሔርን የምትወዱ፥ ክፋትን ጥሉ፤ እግዚአብሔር የቅዱሳኑን ነፍሶች ይጠብቃል፥ ከኃጥኣንም እጅ ያድናቸዋል።

፲፩ ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።

፲፪ ጻድቃን፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፥ ለቅድስናውም መታሰቢያ አመስግኑ።

✝✝✝[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፰]✝✝✝

፩ እግዚአብሔር ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፤ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።

፪ እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።

፫ ግሩምና ቅዱስ ነውና ሁሉ ታላቅ ስምህን ያመስግኑ።

፬ የንጉሥ ክብር ፍርድን ይወድዳል፤ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ ለያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ አደረግህ።

፭ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ ቅዱስ ነውና ወደ እግሩ መረገጫ ስገዱ።

፮ ሙሴና አሮን በካህናቱ ዘንድ፥ ሳሙኤልም ስሙን በሚጠሩት ዘንድ ናቸው። እግዚአብሔርን ጠሩት፥ እርሱም መለሰላቸው።

፯ በደመና ዓምድም ተናገራቸው፤ ምስክሩንና የሰጣቸውን ትእዛዝ ጠበቁ።

፰ አቤቱ አምላክችን ሆይ፥ አንተ ሰማሃቸው፤ አቤቱ፥ አንተ ማርሃቸው፥ ሥራቸውን ሁሉ ግን ተበቀልሃቸው።

፱ አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፥ በቅዱስ ተራራውም ስገዱ፤ አምላካችን እግዚአብሔር ቅዱስ ነውና።

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የግራኝ ጂሃድ በመስቀል አደባባይ ላይ | ልደታ እና የዋቄዮ-አላህ ልጆች ቅቤ በዛፍ ላይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2021

ይህ የእባቡ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ ሴራ እንደሆነ እርግጠኛ መሆን ይቻላል። “አል ነጃሽ” የተባለ መስጊድ የአፍሪቃው ሕብረት ሕንፃ ፊት ለፊት፤ የሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ንብረት በሆነው ቦታ ላይ ከታከለ ኡማ ጋር ፈቃዱን ሰጥቷቸው የለ። አሁን ደግሞ ግራኝ አማራዎችን ወደ አደባባይ እየወጡ፤ “ዳውን ዳውን አብይ!” እንዲሉ አድርጎ በትግራይ ሕዝብ ላይ ከሚሰራው ወንጀልና ዲያብሎዊ ተግባር እራሱን ነፃ ለማድረግ እንደሞከረው ዛሬ ለሙስሊሞቹ፤ “ወደ መስቀል አደባባይ ሂዱና፤ ‘ዳውን ዳውን አብይ!’ በሉ”ብሏቸዋል። ግራኝ ኦሮሞዎች ቀስበቀስ ተደላድለው ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ከተማዋን ይቆጣጠሩ ዘንድ መሀመዳውያኑን እንደ መጥርጊያ አድርጎ እየተጠቀመባቸው ነው። የኦሮሞውም የሙስሊሙም ዓላማ አንድ ዓይነት ነው፤ እርሱም፤ ኢትዮጵያን ማፈራረስ፣ ተዋሕዶ ክርስትናን ማዳከምና ክርስቲያኖችን ለዋቄዮ-አላህ መስዋዕት አድርጎ መጨረስ።

እናታችን ቅድስት ማርያም ግን አትፈቅድላቸውም!

እንደሚታወቀው ኦሮሞዎች ልክ በግንቦት የልደታ ማርያም ዕለት የአምልኮ ዛፎቻቸውን በቅቤ መቀባት ይጀምራሉ። አዎ! “ዋቄዮ-አላህ”

👉 ከሦስት ዓመታት በፊት ይህን አቅርበን ነበር፦

✞✞✞“በልደታ ማርያም ዕለት የጣዖቱ ዋቄዮአላህ ድል ተነሳ ፥ ተዓምረኛ የቅድስት አርሴማ ጸበል ፈለቀ”✞✞✞

በጎጃም ይኖሩ የነበሩ ሁለት ክርስቲያኖች በራዕይ ተመርተው ወደ አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመምጣት ቪዲዮ ላይ የሚታየውን የቅድስት አርሴማን ተዓምረኛ ጸበል ለማግኘት በቅተው ነበር።

ጸበሏ በፈለቀችበት ቦታ ላይ፡ ከ20 ዓመታት በፊት፡ ጣዖታዊውን አምላክ ዋቄዮን የሚያመልኩት ወገኖች ከአርሲ እና ባሌ ድረስ ወደዚህ ቦታ በመምጣት ከግንቦት ልደታ ማርያም አንስቶ ለአንድ ወር ያህል የዋንዛ ዛፉን ቅቤ እየቀቡ ይቀቡበት ነበር። በራዕይ የተመሩት ወገኖች ልክ እዚህ ቦታ ላይ እንደደረሱ በመቶ የሚቆጠሩ ታዛቢ ም ዕመናን በተገኙበት የፀበሉ ውሃ ፊን ብላ ወጣች። ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በቦታው የቅድስት አርሴማ እና ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያናት ህንጻዎች ጎን ለጎን ተሠሩ፡፡

በአዲስ አበባ ነፋስ ስልክ ለቡ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በምትገኘው በዚህች ጸበል ብዙ ወገኖች፤ አህዛብ ሳይቀሩ እንደተፈወሱ የተለያዩ ምስክርነቶች ለመስማትና በቦታውም ሱባኤ ገብተው እየተፈወሱ ያሉ ብዙ እህቶችና ወንድሞችን በዓይኔ ለማየት በቅቼ ነበር።

እንግዲህ ይታየን፤ ላለፉት 150 ዓመታት ለኢትዮጵያ ውድቀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱት ዛፍአምላኪዎቹ “ኦሮሞዎች”እዚህ ድንቅ ቦታ ላይ ከግንቦት ልድታ አንስቶ ለአንድ ወር ያህል የጣዖቱን ኦዳ ዛፍ ቅቤ እየቀቡና ደም እያፈሰሱ ሲያመልኩበት ነበር። መንፈሳውያን ኢትዮጵያውያን መምጣት እንደጀመሩና ጸበሉም እንደፈለቀ የስጋ ፍጥረታቱ እንደ ጉም ብትን ብለው ሄዱ። እስኪ ዛሬ የዋቄዮአላህ አህዛብ መንግስት ቦታውን ያስመልስ እንደሆነ እናያለን፤ የ፮ ወር ጊዜ ነው ያለው።

በጎጃም ይኖሩ የነበሩ ሁለት ወጣቶች በራዕይ ተመርተው ወደ አዲስ አበባ ንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ በመምጣት ይህችን ተዓምረኛ ጸበል ለማግኘት በቅተዋል። ጸበሏ በፈለቀችበት ቦታ ላይ፡ ከ20 ዓመታት በፊት፡ ጣዖታዊውን አምላክ ዋቄዮን የሚያመልኩት ወገኖች የዋንዛ ዛፉን ቅቤ ይቀቡበት ነበር።

አንድ ሌላ የገረመኝ ነገር፡ ቪዲዮው ላይ እንደሚሰማው፡ አንድ አባት እኔን በቅድስት አርሴማ ጸበል በሚያጠምቁበት ወቅት አንዲት እርግብ በርራ በመምጣት እራሳቸው ላይ ልታርፍባቸው መብቃቷ ነው። በዕለቱ እንዴት ከሩቅ ሠፈር ወደዚህ ቦታ ተመርቼ ለመሄድ እንደበቃሁ አላውቅም፤ ታክሲው ዝምብሎ አወረደኝ፤ ያውም እዚያ የደረስኩት የመጠመቂያው ሰዓት ካለፈ በኋላ ነበር። ተዓምር ነው!

በአዲስ አበባ ለቡ አካባቢ በምትገኘው በዚህች ጸበል ብዙ ሱባኤ የሚገቡ እህቶችና ወንድሞችን ለማየት በቅቼ ነበር።

እንኳን አደረሰን!”

_____________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት – ረቡዕ ፤ የይሁዳ ክህደት፥ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 28, 2021

ለምን የምክር ቀን ተባለ?

ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ፣ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ፣ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ [ማቴ. ፳፮፥፩፡፲፬ ፣ ማር. ፲፬፥፩፡፪ ቁ ፲.፲፩፣ ሉቃ. ፳፪፥ ፩፡፮]

የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል

ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ፣ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት፣ /ባለሽቱዋ ማርያም/፤ “ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ፣ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ” ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ፣ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ፣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ /በራሱ/ ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ነው ረቡዕ የመዓዛ ቀን የተባለው፡፡

የእንባ ቀንም ይባላል

ይህም ይህቸው ሴት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ፣ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በዕንባዋ እግሩን አጥባዋለችና፣ በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና፡፡ [ማቴ.፳፮፥፮፡፲፫ ፣ ማር.፲፬፥፫፡፱፣ ዮሐ.፲፪፥፩፡፰] ከዚህ ልንማር የሚገባው ነገር አለ፤ ይኸውም የራስን ኃጢአት በማሰብ ማልቀስና የተወደደ መሥዋዕት አድርጐ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ነው፡፡ የማርያም እንተ ዕፍረትን ኃጢአት ይቅር ብሎ መብዓዋን የተቀበለ አምላክ ዛሬም በመካከላችን አለና፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳ ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው። ምህሩንና ጌታውን ክዶ፣ ስሞ ለግርፋት እና ለመስቀል ሞት ተስማማ። ይህንን የጌታን ሕማማት፣ ስቅላት፣ ሞትና ትንሣኤ በምናስብበት በአሁኑ ወቅት የትግራይ ሕዝብ ለሕማም፣ ለስቅላት እና ለሞት አሳልፎ ተስጥቷል። ይሁዳ ለ፴/30 ዲናር ጌታችንን አሳልፎ ሰጠው፤ ከዚያም ዲናሩን መልሶ እራሱን አጠፋ። የዘመናችን ሰቃልያን የሆኑት ኦሮማራዎቹ የዋቄዮ-አላህ ጭፍሮች ደግሞ “አክሱም ጽዮን ለብዙ ሺህ ዓመታት ያፈራችውን እውቀት፣ ስልጣኔና ሀብት በሙሉ ለመዝረፍ፣ አሳልፎ ለመስጠትና ለማውደም ጊዜው አሁን ነው” ብለው የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ከሆኑት አህዛብ፣ መናፍቃንና ግብረ-ሰዶማውያን ጋር ተባበሩ። በዚህም በዚያም ትልቅ ክህደት እና ስቅለት። በተለይ ተዋሕዶ ክርስትናን የተቀብሉትና ማሕተብ ያጠለቁት አማራ ወገኖች ክህደት ታሪክ የማይረሳው ነው፤ ብዙ ዋጋም የሚያስከፍላቸውና ከሌሎቹ ሁሉ የከፋው ክህደት ነው። ከይሁዳ ይልቅ የጴጥሮስ ዓይነት ክህደት ያድርግላቸው።

የአስቆሮቱ ይሁዳ ክህደት + የቃኤል ቅናት = ☠️

አወቁትም አላወቁትም፤ ዛሬ በአማራዎችና ኦሮሞዎች ህብረት በትግራይ ሕዝብ ላይ እየተካሄደ ያለው ጂሃዳዊ የጭፍጨፋ ዘመቻ የመጨረሻው ግብ፤ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ትግራዋያንን ከአኩም ጽዮን አጽድቶ የሕይወት ዛፍ እና ጽላተ ሙሴ የሚገኙበትን ቅድስት ምድር ለተለከፉት ባዕዳውያኑ ውሾች ማስረከብ ነው። አዎ! ኢትዮጵያን/አክሱም ጽዮንን ለባዕዳውያኑ ሉሲፈራውያን ለማስረከብ በትግራይ ሕዝብ ላይ ጦርነት ከፈቱ። እስኪ እናስበው! ዋው!

በሰባዎቹ ዓመታት ሉሲፈራውያኑ ድርቅና ረሃብ ፈጥረው በዚህ አካባቢ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሃገራት፤ በተለይ ብሪታኒያ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ ሰራዊቶቻቸውን በእርዳታ ስም አስፍረው እንደነበር እናስታውስ። ከዚያ በሰማኒያዎቹ እና በባድሜው ጦርነት የተባበሩት መንግስታት “ሰላም አስከባሪዎች” እንዲገቡ ተደርጎ ነበር። ዛሬም ዓለም የተራቡ የትግራይን ሕፃናት ምስሎች በበቂ እንድታይ ከተደረገች በኋላና የተረፉትንም ትግራይ ወገኖቼንም በስደት የተቀደሰችውን ምድር እየለቀቁ እንዲወጡ (የአውሮፓን እና አሜሪካን ድንበሮች ይከፍቱላቸዋል፤ ከጥቂት ከፍተኛ ቦታ ላይ ከሚገኙት የዓለማችን ቦታዎች በቀር አውሮፓና አሜሪካ ሌሎችም አኅጉራት ይጠፋሉ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰዋል) ከተደረጉ በኋላ የምዕራባውያኑ ኔቶ ሠራዊቶች በትግራይ ይሰፍራሉ።

ገና ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት “ኔቶ በአፍጋኒስታን የሚገኘው ለኢትዮጵያ ለመለማመድ ነው፤ ተመሳሳይ የመልከዓ ምድር አቀማመጥ ስላላቸው…” በማለጥ ጽፌ ነበር። ምዕራባውያኑ እዚያ መስፈር ከጀመሩ በኋላ ቀስ በቀስ ዜጎቻቸውን ማስገባት ይጀምሩና በመጨረሻም “ኢትዮጵያውያኑም ተዋሕዶ ክርስቲያኖቹም እኛ ነን” በማለት እያታለሉና ደማቸውን እያፈሰሱ ለብዙ ሺህ ዓመታት ጠብቀውት የነበረውን ብኩርናቸውን በምስር ወጥ እንዲሸጡ ብሎም የመንፈስ ማንነታቸውንና ምንነታቸውን እየተነጠቁ “ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን” ቀስበቀስ እንዲከዱ ይደረጓቸውን “የቀድሞ ኢትዮጵያውያን” “አናስገባም!” ብለው ከኢትዮጵያ ድንብር ይመልሷቸዋል። ይህ ትንቢት ሳይሆን የሉሲፈራውያኑ ግልጽ የሆነ ተልዕኮ ነው። እግዚአብሔር ይህን ተልዕኳቸውን እንደሚያጨናግፈው አልጠራጠረም፤ ነገር ግን በኢትዮጵያውያኑ ደንቆሮነት፣ ስንፍና እና እንደ ግራኝ ያሉትን የውስጥ ጠላታቸውን በሰዓቱ ለማስወገድ ባለመድፈራቸው ብሎም አክሱም ጽዮንን ለመከላከል ባለመሻታቸው ብዙ መስዋዕት ይከፍሉ ዘንድ ግድ ይሆናል። በተለይ ከሃዲዎቹ ኦሮማራዎች!

የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሕማማተ እግዚእ †ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ | ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

✞✞✞ ሰሙነ ሕማማት ዕለተ ማክሰኞ (ዘሰሉስ)✞✞✞

የጥያቄና የትምህርት ቀን❖

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፫፡፳፭ ፤ ማር.፲፩፥፳፯ ፣ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡

ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ በአንድ አገር የንግድ ቦታን የሚያጸድቅ መንግሥት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልመለሰም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሷል፡፡ “በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ፤ በማን ሥልጣን ነው ይህን የምታደርገው?” ነበር ያሉት፡፡ በራሴ ሥልጣን ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡

ጌታችን እኩይ የሆነውን የፈሪሳውያንን አሳብ በመረዳት “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር ሲል” ጠይቋቸዋል፡፡ ከሰማይ ያልነው እንደ ሆነ ለምን አላመናችሁበትም ይለናል÷ ከሰው ያልነው ከሆነ ሕዝቡ ይጣላናል፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ከዚህ የተነሣ ያቀረቡት የፈተና ጥያቄ ግቡን ሳይመታ ከሽፎባቸዋል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፭]፤ [ማር.፲፩፥፳፯፡፴ ፤ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡

ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡

በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

👉መድኅንኤል 👉ሕይውታኤል 👉አውካኤል 👉ተርቡታኤል 👉ግኤል 👉ዝኤል 👉ቡኤል

የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከልዩ ድንጋፄና ፍርሃት እድን ዘንድ ይህን የቅዱስ ገብርኤልን ድርሳን እንዲህ እያልኩ እጸልያለሁ፤ መድኅንኤልሕያውታኤልአውካኤልተርቡታኤልግኤልዝኤልቡኤል ፤ ይህን አስማተ መለኮት እግዚአብሔር ለቅዱስ ገብርኤል የሰጠው መልአኩ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በጀመረ ጊዜ ድል እንዲነሣበት፤ እንዲሁም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማብሠር በተላከ ጊዜ ከቃሉ ግርማ የተነሣ እንዳትደነግጥና እንዳትፈራ መጽንዔ ኃይል እንዲሆናት ነው።

አቤቱ ለእኔ ለአገልጋይህም እንደዚሁ ኃይልና ጽንዕ ሰጥተህ ከመዓልትና ከሌሊት ድንጋፄ አድነኝ፤ አሜን።

ከላይ ከሰማይ ወደ ድንግል የተላክህ ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ደስታን አብሣሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ፅንሰ ቃልን አስተምረህ የምታሳምን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ሰማያዊ ነደ እሳት ዖፈ ርግብ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ፍጹም ደስታን ተናጋሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ከእደ ሞት የምታድን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። የአንተን አማልላጅነት በመዓልትም በሌሊትም ተስፋ ስለምናደርግ ጥበቃህ አይለየን። በነፍስም በሥጋም ታደገን። የእግዚአብሔር ልዩ ባለሟል ነህና፤ ለዘላለሙ አሜን።

አቡነ ዘመሰማያት።

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሆሣዕና ፪ሺ፲፫/ 2013 ዓ.ም | ሁለት ጨረቃዎች? | Two Moons?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2021

በትናንትናው ዕለት ቴዎድሮስ “ርዕዮት” ፀጋዬን እና አቶ ታምራት ላይኔን እያዳማጥኳቸው (ስለ ትግራይ እነደሚጠበቅባቸው ብዙ አልተናገሩም፤ በተለይ የአማራ ፋሺስት ፋኖ ሚሊሺያ በምዕራብ ትግራይ ስለሚፈጽመው ወንጀል: ይሉኝታ/PC?) የምሽት ሰማዩ ላይ የታየኝ ይህ አስደናቂ ክስተት ነበር። አምና ልክ በዚሁ በሆሣዕና ዕለት እመቤታችንን እና ልጇን አማላካችንን ጨረቋዋ ላይ “ታዩኝ” በማለት ቪዲዮ አንስቼ የዲያብሎስ ጭፍሮች ባዘጉብኝ ዩቲውብ ቻኔሌ ላይ ለቅቄው ብዙ አድናቂዎችን አግኝቶ እንደ ነበር አስታውሳለሁ። ዘንድሮ ደግሞ ያው!

በነገራችን ላይ ዘንድሮም ልክ በዚሁ የሑዳዴው ጾም ወቅት እነ ግራኝ + የተባበሩት መንግስታት ወኪሎቹ ይህኛውን ቻነሌንም ለማዘጋት ሞክረው ነበር፤ በሌላ ጊዜ እመለስበታለሁ።

_____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት ሰኑይ | መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2021

✞✞✞ የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ✞✞✞

ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅዳስ የተፈጸመበት ሰኞ::

ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን::

ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን::

ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ::

ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ::

ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሆሣዕና በአርያም | ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ ተገለጠ | Hosanna in The Highest!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 24, 2021

ሰውን ከወደቀበት የበደል ጉድጓድ ያወጣው ዘንድ እግዚአብሔር ክንዱን ወደ ዓለም ላከ፡፡ ሰው ሆኖ የተገለጠው የእግዚአብሔር ክንድ በጉድጓድ ተጥሎ የነበረን በዚያም በሥጋ በነፍስ፤ በውስጥ በአፍአ ቆስሎ የነበረ አዳምን በትህትና ሁለተኛ አዳም ሆኖ በሥጋ የቆሰለውን በለበሰው ሥጋ ቆስሎ;በነፍስ የታመመውን በትምህርት አዳነ፡፡ ከእርሱ አስቀድሞ ሰውን ከሞት ወደ ሕይወት፤ ከባርነት ወደ ነፃነት የሚያመጣ ባለመኖሩ እርሱ ሁሉን የፈጠረ ሁሉን የሚያኖር እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ለሰው መድኃኒት ሆነ፡፡ በሞቱም መድኃኒትነትን አሣየ፡፡ በነቢይ መድኃኒተ ፈነወ እግዚአብሔር ለሕዝቡ፤ እግዚአብሔር ለሕዝቡ መድኃኒትን ሰደደ፡፡ (መዝ.፻፲፡፱) ተብሎ የተነገረው ተፈጸመ፡፡

ክርስቶስ ባለ መድኃኒት ሆኖ በኃጢአት ለታመሙ ደቂቀ አዳም ሁሉ ሕይወትን ይሰጥ ዘንድ ወደዚህኛው ዓለም መጣ፡፡ በምድራዊ ሥርዓት እንደምናየው መድኃኒትና ባለ መድኃኒት እንደሚለያዩ አይደለም፡፡ ሁለቱንም እርሱ በመምጣቱ (ሰው በመሆኑ) ፈጸመ እንጂ፡፡ መድኃኒት አድርጎ ሥጋውን ደሙን የሰጠ እርሱ ነው፡፡ በካህናት አድሮ ሰው በንስሐ ሲመለስ መድኃኒት ወደሆነው ወደ ራሱ የሚመራ እርሱ ነው፡፡

ክርስቶስ መድኃኒት መሆኑ በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ በእመቤታችን ማኅፀን የተጀመረው የእርሱ መድኃኒትነት እና ፍቅሩ ፍፃሜውን ያገኘው በሕማሙ እና በሞቱ ነው፡፡ መሐሪ ንጉሥ እርሱ መሆኑን ይገልጥ ዘንድ በፈቃዱ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፡፡ ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ከመግባቱ አስቀድሞ ከኢየሩሳሌም ፲፮ ያህል ምዕራፍ በምትርቀው በቤተፋጌ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ነበር፡፡

ከደቀ መዛሙርቱም ሁለቱን (ማለትም ጴጥሮስን እና ዮሐንስን) በፊታችሁ ወዳለችው መንደር ሂዱ ወዲያውም ወደ እርሷ ገብታችሁ ከሰው ማንም ገና ያልተቀመጠበትን ውርንጫ ታስሮ ታገኛላችሁ ፈትታችሁ አምጡልኝ፡፡ (ማር ፲፩፡፪) በማለት አዘዛቸው፡፡ ዳግመኛም ሰው ወዳልገባባት የተዘጋች የምሥራቅ ደጅ ወደ ምትባል ወደ ድንግል መጥቶ ዘጠኝ ወር ማኅፀኗን ከተማ አድርጎ እንደኖረ፤ ማኅየዊት ከምትሆን ሕማሙ በኋላም ሰው ባልተቀበረበት መቃብር እንደተቀበረ፤ አሁንም ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም ለመግባት ማንም ሰው ያልተቀመጠባቸውን በሌላ መንደር የሚገኙ አህያንና ውርንጫን እንዲያመጡ ደቀመዛሙርቱን አዘዘ፡፡

የፍጥረት ሁሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በልደቱ እስትንፋሷን የገበረችለትን አህያ አሁን ደግሞ በፈቃዱ ስለ ሰው ሁሉ ሊሞት ሲል ንጉሥነቱን ሊያስመሰክርባት ወደደ፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እስከ ኢየሩሳሌም ድረስ ካለው ፲፮ ምዕራፍ አሥራ አራቱን በአህያ ላይ ሳይቀመጥ በእግሩ ሄደ፡፡ ከዚያም ሁለቱን ምዕራፍ በአህያ ላይ በመቀመጥ ከተጓዘ በኋላ የኢየሩሳሌምን መቅደስ ሦስት ጊዜ በውርጫዋ ላይ በመሆን ዞረ፡፡ በዚህም ለሰው ሁሉ ያለው ቸርነቱ፣ ሕግ የተሰጣቸው አይሁድ እና ሕግ ያልተሰጣቸው አሕዛብ ላይ እኩል ቀንበርን መጫን እንዳይገባ አጠየቀ፡፡

ወደ ኢየሩሳሌምም ሲሄድ ብዙ ሰዎች ልብሳቸውን በመንገድ ላይ አነጠፉ፣ ሌሎችም ከዛፍ ቅጠሎችን እየቆረጡ ያነጥፉ ነበር፡፡ (ማር. ፲፩፡፰)፡፡ ከዚያም ሰዎች ሆሣዕና በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው (ማር. ፲፩፡፱) በማለት አመሰገኑ፡፡ ይህም ዛሬ ለቤተ ክርስቲያን እኛ ክርስቲያኖች ቡሩክ ስሙ ለእግዚብሔር ወቡሩክ ዘይመጽእ በስመ እግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔር ስሙ ምስጉን ነው፡፡ እግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ እርሱ ክርስቶስም ምስጉን ነው በማለት የአብ እና የወልድን መስተካከልን ገልጸን ጌታን እናመሰግናለን፡፡ ጌታን የሚከተሉት ሰዎች ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር (ማር.11፲፩፡፲) ይኸውም በልዕልና፣ በሰማይ ያለ መድኃኒት፣ ከሰማይ የመጣ መድኃኒት ማለት ነው፡፡

የእግዚአብሔር ፍቅር እና መሓሪ መሆን በክርስቶስ ሕማም እና ሞት ከመቼውም ጊዜ በላይ ተገልጧል፡፡ ክርስቶስ የተቀበለው ሕማም እና ሞት የእርሱን አምላክነት እና ንጉሥነት አልሸሸገውም፡፡ እንደውም ዙፋኑን መስቀል በማድረግ ንጉሥነቱን በመድኃኒትነቱ ገልጿል እንጂ፡፡ በነቢይ እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር፣ እግዚአብሔር ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፤ በምድር መካከልም መድኃኒትን አደረገ መዝ. ፸፫፤፲፪ ተብሎ የተነገረው እግዚአሔብር ድኅነትን በፈጸመበት ማዕከለ ምድር ሲሰቀል በመድኀኒትነቱ ንጉሥነቱን መግለጡን ያመለክታል፡፡ ዳግመኛም አንሰ ተሰየምኩ ንጉሠ በላዕሌሆሙ በጽዮን በደብረ መቅደሱ፤ እኔ ንጉሥ ሆኜ ተሸምኩ በተቀደሰው ተራራ ላይ (መዝ.፪፡፮) ተብሎ የተነገረው ኦርቶዶክሳውያን አበው እነርሱ (አይሁድ) ሰቅለነው ገድለነው ኋላ ፈርሶ በስብሶ ይቀራል ይሉኛል እንጂ እኔ ደብረ መቅደስ በምትባል በመስቀል ላይ ነግሻለሁ በማለት ይተረጉሙታል፡፡

ጌታ ንግሥናው ክብሩ የተገለጠበት ሆነ እንጂ መታመሙ እና መሞቱ ውርደት ክብሩንም የሚሸሽግ አይደለም፡፡ ሊቁ ዮሐንስ አፈወርቅ ይትባረክ እግዚአብሔር ዘሰመየ ሕማማት ወልዱ ክብረ ወስብሐት፣ የልጁን ሕማማት ክብርና ምስጋና አድርጎ የሰየመ እግዚአብሔር ይመስገን አለ፡፡ እኛን ያከበረበት በመሆኑ ሕማሙ ክብር እንደተባለ እናስተውል፡፡ በመስቀል ላይ ሆኖም በቀኝ የተሠቀለው ወንበዴ አቤቱ በመንግሥትህ በመጣህ ጊዜ አስበኝ (ሉቃ ፳፬ )በማለት ንጉሥነቱ መስክሮለታል፡፡ ለዚህ ነው ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በምስጋና መግባቱ መድኃኒትነቱን እና ንጉሥነቱን ያሳያል ያልነው፡፡ ዳግመኛም ሁሉን የያዘ ጌታ በአህያ ላይ መቀመጡ ትህትናው ያስረዳል፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ዘይነብር ዲበ ኪሩቤል ዲባ ዕዋለ አድግ ነበረ፡፡ በማለት ሰማያዊ ልዑል አምላክ ትሑት ሆኖ እንደተገለጠ ተናገረ፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ድንቅ የሆኑ እና ተአምራትን ለሰዎች አሳየ (ገለጠ)፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ተአምረ ወመንክረ (ቅዳ. ጎርጎ.ዘኑሲስ) እንዲል፡፡ ይኸውም በአህያ ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ አእምሮ ጠባይዕ ያልቀናላቸው ሕፃናት ዕውቀት ተገልጾላቸው ሆሳዕና በአርያም እያሉ ጌታ በማመስገናቸው ነው፡፡ ዳግመኛም በከሃሊነቱ መናገር ለማይችሉ ዕውቀት ለሌላቸው ድንጋዮች ዕውቀት ተሰጥቷቸው መናገር ችለው ጌታን አመስግነዋል፡፡ እርሱ የባሕርይ አምላክ መሆኑ በሰውነቱም ቀድሞ በበደል ምክንያት ለሰው ከመገዛት ውጪ የሆኑ ፍጥረታት ዳግመኛ በሥጋዌ ለሰው እንደተገዙ ከዚህ ሁሉ ማስተዋል ይገባል፡፡

ጌታ ከመድኃኒትነቱ የተነሣ ልጅነት እና ተአምራት ማድረግን ገለጸ፡፡ እም ሆሳዕናሁ አርአያ ጸጋ ወኅይለ እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ)፡፡ የእርሱ ማዳን ከሰው ተወስዶበት የነበረ የጸጋ ልጅነት እንዲመለስለት አድርጋ በልጅነት ላይ ገቢረ ተአምራት (ተአምራትን ማድረግ) ገልጿል፡፡ ይኸውም እርሱ በረድኤት አድሮባቸው ድንቅ ተአምራትን ለሚያደርጉ ቅዱሳን መሠረት ነው፡፡ በተጨማሪም ልጅነትን ካገኙ በኋላ በበደል ሲገኙ ለንስሓ የሚሆን እንባን ሠጠ፡፡ እምሆሳዕናሁ ወሀበ ፈልፈለ አንብዕ ለኅጥአን እንዲል (ቅዳሴ ጎርጎ. ዘኑሲስ) ይኸውም የበደሉትን ያከብራቸው ዘንድ፣ ኀጥአንን ከኃጢአታቸው ያነጻቸው ዘንድ እንዲሁም የሳቱትን በንስሐ ይመልሳቸው ዘንድ ነው፡፡

ዳግመኛም ጌታ መድኀኒት ከመሆኑ የተነሣ ለዕውራን ዳግመኛ ብርሃንን ሰጠ፡፡ ይኸውም ለጊዜው በተፈጥሮ ዐይን ተሰጥቷቸው የታወሩትን ፈውሶ በሥጋ ብርሃን መስጠቱ ሲሆን፤ ፍጻሜው ግን በነፍስ ዕውቀትን ከማጣት የተነሣ ዕውራን የነበሩትን ትምህርትን; ዕውቀትን ገለጸላቸው፡፡ ይኸውም የእርሱ ገንዘቡ ስለሚሆን አንድነት ሦስትነት፣ አምላክነቱን መድኃኒት መሆኑን ገለጠላቸው ማለት ነው፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

❖❖❖Hosanna in The Highest!❖❖❖

Palm Sunday, also called the Triumphal Entry, is one of the Great Feasts of the Orthodox Church, celebrated on the Sunday before Pascha. On this day the Church celebrates the entry of Jesus into Jerusalem in the days before the Jewish Passover. A mere few days before His crucifixion, Jesus Christ was received by adoring throngs at his entry into Jerusalem on the back of a young donkey. The believers meet him, and spread out before him his clothes and olive branches. When He and His students approached the city Jerusalem, He ordered them to go to the near-by village, and bring him the donkey and his little who were tied-up in the beginning of the village. If they were asked, they should say that this was God’s will. When the people knew that the donkey was for Jesus, they did not prevent his students. They gave Him the donkey, and He solemnly entered Jerusalem. The news of the resurrection of Lazarus already got ahead and thousands of people went to Bethany to meet him.

_______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: