Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • December 2022
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  262728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እመነት’

የሰይጣን ምልክት 666 ነው ፥ የክርስቶስ የሆኑት ደግሞ ባንገታቸው ላይ ያለው ማሕተብ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 13, 2019

ትክክለኛዋ እምነት በተዓምር፣ በማርያም መቀነት / በቀስተ ደመና የታጀበች እምዬ ኦርቶዶክስ ፥ አድዋ ዘምታ ጊዮርጊስ ድል ያደረገላት፣ መከላከያ ሚንስትሯ ጊዮርጊስ የሆነ፣ ጳጳሳቷ ለአገር የሞቱ፣ አንድነት የምትሰብክ፣ የድኾች መጠጊያ፣ ፀበሏ የሚፈውስ፣ እምነቷ የሚፈውስ፣ ደመራዋ የሚያምር፣ ጥምቀቷ የሚያምር፣ አፅዋማቷ የሚያምሩ፣ ሥርዓቷ፣ መጻሕፍቷ፣ ገዳማቷ፣ ውቅር ዓብያተክርስቲያናቷ፣ የካህናቱ ዝማሬው፣ ቅኔው፣ ማሕሌቱ፣ ቅዳሴው፣ አለባበሳችን ፥ ሁሉ ነገራችን እንደ ኦርቶዶክሶች የሚያምር የለም።

ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡ ወንድማችን!

+______________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ማሕተቡን አሥራ የተወለደችው ሕፃን እናት ሚስጥሩን ይፋ አደረገች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 11, 2019

ለኢትዮጵያውያን ክብራቸው፣ ኩራታቸውና ደስታቸው ማሕተባቸው እንጂ በደም የተቀባው የኖቤል ሜዳሊያና የአይ.ኤም.ኤፍ ዶላር አይደለም። ከእነ ማሕተቡ መወለድ የበለጠ ፀጋ አለን?

ነፍሳቸውን የሸጡት ሜዲያዎችና እንደ እስስት ተለዋዋጪዎቹ የማሕበራዊ ድህረገጽ ተዋንያዮች ስለ እነ ገዳይ አብይ የቱርክ ድራማ ሌት ተቀን ከመለፈፍ ይልቅ ለራሳቸው ሲሉ ስለ ልጃችን የማሕተብ ተዓምር በማውሳት የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ ያለማቋረጥ ማወደስ ቢችሉ ይመረጥ ነበር። ግን አለመታደል ሆኖ አብዛኛዎቹ ሜዲያዎች በአውሬው እጅ ውስጥ ገብተዋል። ስለዚህ፡ ምስክራችን ከላይ ብቻ ነው!!!

የዚህች መልአክ የመሰለች ሕፃን የማሕተብ ተዓምር ዜና የበሰረበት ወቅት ልክ ገዳይ አብይ የኖቤል ሰላም ሽልማቱን ከሚቀበልበት ወቅት ጋር መገናኘቱ ያለምክኒያት አይደለም፤ ሰውየው ከክርስቶስ ተቃዋሚዎቹ አንዱ እንደሆነ 100% እርግጠኛ ነኝ፤ ስለዚህ፡ በተፈጥሯዊው ማሕተብ በኩል እግዚአብሔር እጅግ በጣም ትልቅ የሆነ መልዕክት እያስተላልፍልን ነው። ጆሮ ያለው ይስማ ፣ ዓይን ያለው ይመልከት፣ ላልደረሰው ያድርስ፡ ለ አስራ ሁለት ሩብ ጉዳይ ሆኗል!

+ ማተብሽን ፍች በጥሽው ቢሉኝ+

እኔስ ከነ አንገቴ ውሰዱት አልኩኝ

ፊተኛ ነንና አንዳንሆን ኋላኛ

ህዝቤ ተነቃቃ ተነስ አትተኛ

ጅብ ከሄደ ውሻ እንዳይሆን ጩኽት

የተዋህዶ ልጆች አሁነ ነው ሰዓቱ

አይተን እንዳላየን ስንቱን አሳልፈናል

የእርሱ ፈቃድ ይሁን ብለን ዝም ብለናል

አሁን ግን ይበቃል ዝምታው ይሰበር

+ይገለጥ ይታወጅ የተዋህዶ ሚስጢር+

ክርስቲያን ማለት ኢትዮጵያ ማለት ነው!

+____________________________+

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አውሬው መንግስት በቤተ ክርስቲያን ላይ እያካሄደ ያለው ጦርነት ተፋፍሞ ቀጥሏል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 11, 2019

ሰሞኑን አባ ዘወንጌልን በተመለከተ አንዳንድ ሕልሞች ይታዮኝ ነበር። ሕልሞቹን ለማስታወስ እየታገልኩ ነው። አባታችን የጠቆሙን ነገሮች ሁሉ አንድ በአንድ በመፈጸም ላይ ናቸው።

አባታችን አባ ዘወንጌል በአንድ ወቅት እንዲህ ብለውን ነበር፦

ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው!”

አዎ! አውሬው ጦርነቱን አስቀድሞ በማካሄድ ላይ ያለው የቤተ ክርስቲያን በር በሆኑት በሰባቱ ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያን ላይ ነው፦

. ምሥጢረ ጥምቀት
. ምሥጢረ ሜሮን
. ምሥጢረ ቁርባን
. ምሥጢረ ክህነት
. ምሥጢረ ተክሊል
. ምሥጢረ ንስሐ
. ምሥጢረ ቀንዲል

መጀመሪያ በቁርባን(ሕብስትና ወይን / ስጋውና ደሙ) ፣ ቀጥሎም በጥምቀት ላይ ነው የዘመቱት። በኢትዮጵያ የእንጀራና ዳቦ መጋገር ባሕል ባልተለመደ መልክ የአሕዛብ ዳቦ ቤቶች በብዛት እየተከፍቱና በየትምህርት ቤቱ ለሕፃናቱ ዳቦና ማርማላታ እያጎረሷቸው መሆናቸውን እንዲሁም ዓብያተ ክርስቲያናት ባሕረ ጥምቀትን በመነጠቅ ላይ መሆናቸውን በግልጽ እያየነው ነው።  የሰው ልጅ ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ እንደማይችል ምቀኛው ጠላታችን ዲያብሎስ አጠንቅቆ ያውቃልና።

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው | በማህተብ ምክኒያት መሀመዳውያኑ አንገት በመበጠሳቸው ሕፃኗ ከነማህተቧ ተወለደች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 10, 2019

በእውነት በጣም የሚገርም ነው፤ ያውም በመድኃኔ ዓለም ዕለት ነው ሕፃኗ የተወለደችው። የአብ ሥራ እፁብ ድንቅ ነው! እግዚአብሔር በጥበቡ ያሳድግልን!

[ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፩፥፭]

በሆድ ሳልሠራህ አውቄሃለሁ፥ ከማኅፀንም ሳትወጣ ቀድሼሃለሁ፥ ለአሕዛብም ነቢይ አድርጌሃለሁ።

በአንገቷ ልዩ ምልክት ያሰረች ሕፃን ተወለደች::

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዳንግላ ወረዳ በአባድራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ በአንገቷ ላይ ልዩ ምልክት ያሰረች ህፃን መወለዷ ተገለጸ፡፡

የአባድራ ጤና አጠባበቅ ጣቢያ አዋላጅ ነርስ እውነቱ አብየ እንደገለፁት ጥቅምት 27 ቀን 212.ም ከሌሊቱ 8፡ዐዐ አካባቢ በውፍታ ዳጢ ቀበሌ ነዋሪ ወይዘሮ ጥሩወርቅ አብነት በአንገቷ ላይ የክርስትና እምነት ተከታዮች የሚያደርጉትን የማተብ ምልክት በአንገቷ ያሰረች ሕፃን መውለዳቸውን ተናግረዋል።

ሕፃኗ ስትወለድ 3 ኪሎ ግራም የምትመዝን ስትሆን አሁን ላይ ሕፃኗም ሆነ እናቷ በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የሕፃኗ እናት ወይዘሮ ጥሩወርቅ አብነት ስትወለድ ክስተቱ አስደንግጦኝ ነበር፤ አሁን ግን ልዩ ማተብ አድርጋ የተወለደች ሕፃን ልጅ እናት ስለሆንኩ ደስተኛ ነኝብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ዳንግሌላ ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የተዋሕዶ ልጆች ተቃውሞ ሰልፍ በበርሊን | “ፕሮቴስታንቶችና ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች ላይ እጃችሁን አንሱ!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2019

ዋው! ጽሙድ እንደበሬ ትጉህ እንደ ገበሬ እንዲሉ በጾም በጸሎት የተጠምዱት የአቡነ ሀብተማርያም ልጆች በበርሊን ጎዳናዎችያውም በፐርጋሞን ኃውልት ዙሪያብዙ አንጮኽም፡ ግን ለሚመለከተው ክፍል ይህ ታላቅ የማስጠንቀቂያ ምልክት ነው።

ይህ ትልቅ እርምጃ ነውይህን ሰልፍ በበርሊን ማካሄዳቸው በጣም አስፈላጊ ነውምክኒያቱም በኢትዮጵያ ውስጥ በመካሄድ ላይ ያለው የዘርና የሃይማኖት ጭፍጨፋ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መልክ ከፕሬቴስታንት ጀርመን ጋር የተያያዘ ነው። በቁስጥንጥንያ ለኦርቶዶክስ ክርስትና መውደቅና ቱርክ የምትባል የክርስቶስ ተቃዋሚ ሃገር እንድትመሠረት ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረከተችው የማርቲን ሉተር ጀርመን ናት፣ በሃገራችንም ኢትዮጵያን በማመስ ላይ ያለውን አመጸኛ የኦሮሞ እንቅስቃሴ የጀመሩት እንደ ዮኻን ክራፕፍ ያሉት ፕሮቲስታንት ጀርመናውያን ነበሩ።

..አ ከ 1837 እስከ 1843 .ም ባለው ጊዜ ፕሮቴስታንቱ ጀርመናዊ ዮኻን ክራፕፍ ኦሮሚያ የተባለውን ግዛት ለመመሥረት የተነሳሳው ክርስትናን ለማስፋፋት ሳይሆን፡ እንደ አንድ ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ቀጥተኛ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመዋጋት ነው። ለዚህም በወራሪነት ባሕርይ ከጀርመኖች ጋር ይስማማሉ በሚል ሃሳብ “ጋላ” ተብለው ሲጠሩ የነበሩትን ጎሳዎች ለማደራጀት የተነሳሳው። ተልዕኮው የክርስቶስ ተቃዋሚ ተልዕኮ ነው።

በርሊን የክርስቶስ ተቃዋሚው መቀመጫ ከሆኑት ዋና ከተሞች መካከል አንዷ ናት።

 • + የፖለቲካ መናኸሪያ በርሊን፣
 • + የኤኮኖሚ ለንድን እና ኒው ዮርክ፣
 • + የመንፈሳዊ ቫቲካን እና መካ ናቸው።

የራዕይ ዮሐንስ ላይ ከተጠቀሱት ሰባት ዓብያተ ክርስቲያናት(ሁሉም ያሁኗ ቱርክ ውስጥ ነው የሚገኙት) መካከል አንዷ፤ ፐርጋሞን ናት፤ ይህችም የሰይጣን ዙፋን የሚገኝባት ቦታ እንደሆነች ቅዱስ ዮሐንስ ጠቁሞናል።

ታዲያ ከ ፐርጋሞን የተወሰደው የሰይጣን ኃውልት አሁን የሚገኘው በበርሊን ከተማ ነው። እነ ሂትለር፣ ቡሽ፣ ኦባማና ሂላሪ ክሊንተን ሁሉም ይህን ኃውልት ለመሳለም ወደ በርሊን ጎራ ብለው ነበር። ሚሊየን ሙስሊም ወራሪዎችን ወደ ጀርመን አገር ያስገባችው ወይዘሮ አንጌላ ሜርከልም ከዚሁ ኃውልት ፊት ለፊት ነው የምትኖረው፤ ለዚህም ይመስላል ሰላማዊ እና ንጹህ በሆነቸው ጀርመን ላለፉት ጥቂት አመታት ታይቶ የማይታወቅ ቅሌታማ ተግባር ተከላካይ በሌላቸው ጀርመናውያን ህፃናትና ሴቶች ላይ እየተፈጸመ ያለው።

በየዕለቱ አሰቃቂ ድርጊቶች ይከሰታሉ፣ ሁሉም ውረጅ፡ አንፈልግሽም ይላታል፡ ሆኖም ሴትየዋ ያው 15 ዓመት ሞላት ሥልጣን ላይ ከወጣች፤ ከሥልጣን ለመውረድ ፈቃደኛ አይደለችም፤ በኢትዮጵያ ላይ ተንኮል በመሥራት ላይ ያለቸውን ጀርመን ታጠፋ ዘንድ የተቀመጠች የዘመኑ ኤሊዛቤል ነችና።

... 1871 .ም የተዋሀደችው የጽንፈኛው ማርቲን ሉተሯ ጀርመን (ሁሉም ጀርመን አንድ አይደለም) የፐርጋሞንን የሰይጣን ኃውልት ወደ አገሯ በማስገባት ኢትዮጵያን መተናኮል ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በየጊዜው ስትቀጣ ቆይታለች። ጀርመን ቅኝ ግዛቶቿን አጣች፣ የአንደኛውንና ሁለተኛውን የዓለም ጦርነቶች በመቀስቀስ ዜጎቿ ብዙ ተሰቃዩ፣ ለመሰደድ ተገደዱ፤ የመሰማማት ህልም ነበራት ግን የራሷ ግዛቶች ተቆራረሰው በጎረቤት ሃገራት ተወሰዱ። አሁን ከምስራቁ የጀርመን ክፍል ጋር ከተዋህደችበት ጊዜ አንስቶ እንደገና የወራሪነትና የመስፋፋት መንፈሷ ተቀስቅሷል፤ በዚህም ምናልባት ለሦስተኛው የዓለም ጦርነት እንደገና መንስኤ ልትሆን ትችላለች። እኔ እንኳን በአቅሜ፡ “ከቀውስ መዳን የምትሹ ከሆነ ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ፐርጋሞንን ወደ ቱርክ መልሱ” የሚሉ ቃላትን የያዘ ደብዳቤ ለአንጌላ ሜርከል ሳይቀር ጽፌ ነበር።

________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: