የተጠመቅኩት፣ በመሰቅል የተሰቀልኩትና የተሰዋኹት ለአመኑኝና ቃሌን ለተቀበሉኝ ሁሉ ለስጋቸው በረከት ለነፍሳቸው ድኽነት ለመስጠት ነው!
ለእያንዳንዱ ለተጠመቀው ክርስቲያን፣ ስጋው ለተቆረሠለት፣ ደሙ ለፈሰሰለትና እግዚአብሔር ሰው ለሆነለት ክርስቲያን ጠባቂ መላእክት አሉት።
ሊቀ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቅን!
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 19, 2020
የተጠመቅኩት፣ በመሰቅል የተሰቀልኩትና የተሰዋኹት ለአመኑኝና ቃሌን ለተቀበሉኝ ሁሉ ለስጋቸው በረከት ለነፍሳቸው ድኽነት ለመስጠት ነው!
ለእያንዳንዱ ለተጠመቀው ክርስቲያን፣ ስጋው ለተቆረሠለት፣ ደሙ ለፈሰሰለትና እግዚአብሔር ሰው ለሆነለት ክርስቲያን ጠባቂ መላእክት አሉት።
ሊቀ መላእክ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቅን!
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሊቀ መልአክ, ቅዱስ ሚካኤል, አዲስ አበባ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን, ፀበል | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 28, 2020
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ሰዓሊተ ምሕረት, ቅድስት ማርያም, አዲስ አበባ, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን, ደብር / ካቴድራል, ግንቦት ማርያም | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 25, 2018
ክብረ መስቀል በኢትዮጵያ
መስቀል ስንል ሦስት መሠረታዊ ቁም ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል፤ የመጀመሪያው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጅ ከሞተ ነፍስ ለማዳን ሲል የተቀበለው መከራና የከፈለው መሥዋዕትነት መስቀል ይባላል፡፡ ሁለተኛው በክርስእንትና ውስጥ የሚያጋጥም ልዩ ልዩ ዓይነት መከራም መስቀል ነው፡፡ ጌታችን ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ቢኖር ራሱን ይካድ፤ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› /ማቴ.፲፮፥፳፬/ በማለት መናገሩም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚደርሰውን ይህንኑ መከራ መታገሥ ተገቢ መኾኑን ሲያመለክተን ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ጌታችን የተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው፡፡ በሦስቱም ቁም ነገሮች ነገረ መስቀል (የመስቀሉ ነገር) ከክርስትና ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ ስለ ክርስትና ሕይወት ሲነሣ ነገረ መስቀልም አብሮ ይታወሳል፡፡ ስለ ክርስትና ሲነገር ክርስቶስ የተቀበለው መከራ፣ የተሰቃየበትና ነፍሱን በፈቃዱ አሳልፎ የሰጠበት ዕፀ መስቀል፣ በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠት ፈተና አብረው የሚነሡ ጉዳዮች ናቸው፡፡
ስለ መስቀል ሲነገር ክርስቶስ ሰውን ለማዳን ሲል በሥጋው የተቀበለው ስቃይ፤ ሰማዕታት በሃይማኖታቸው ምክንያት የሚደርስባቸው ስደት፣ መከራና ሞት፤ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በየዘመኑ በአረማውያንም በውስጥ ጠላቶችም የሚያጋጥማት የዘረፋና የቃጠሎ፣ እንደዚሁም የሰላም እጦትና የመልካም አስተዳደር እጥረት፤ በተጨማሪም በክርስትና ሕይወት ውስጥ የሚከሠቱ የኑሮ ውጣ ውረዶች መስቀልና ክርስትና የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ለመኾናቸው ማስረጃዎች ናቸው፡፡ ከዚሁ ኹሉ ጋርም መስቀል ሲባል ክርስቶስ መከራ የተቀበለበት፣ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው የለየበት፣ ድንቅ ተአምራትን ያደረገበት፣ ከኹሉም በላይ ለአዳምና ለልጆቹ ነጻነትን ያወጀበት ዕፀ መስቀልም አንዱ የክርስትናችን አካል ነው፡፡
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በጉልላቷና በሌሎችም ንዋያተ ቅድሳቷ መስቀልን እንደ ምልክት ትጠቀመዋለች፡፡ መሠረቷ፣ የልጆቿ መድኀኒት ክርስቶስ በመስቀል ላይ የከፈለው ዋጋ ነውና ሰንደቅ ዓላማዋ መስቀል ነው፡፡ አባቶች ካህናት ጸሎት ሲያደርጉ ‹‹ከመስቀሉ ዓላማ፣ ከወንጌሉ ከተማ አያውጣን›› እያሉ የሚመርቁትም ስለዚህ ነው፡፡ በእጃቸው ይዘውት የሚንቀሳቀሱት፣ እኛንም የሚባርኩትም በመስቀል ነው፡፡ መስቀል የጠላት ሰይጣን ተንኮል የከሸፈበት፣ የክርስቶስ ቤዛነት የተረጋገጠበት የድኅነት ኃይል ነውና፡፡ በየገዳማቱና በየአብነት ት/ቤቱ፤ እንደዚሁም በክርስቲያኖች መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በሚከናወኑ ተግባራት መስቀል ሰፊ ድርሻ አለው፡፡ በቅዳሴ ጊዜ፣ በጠበል ቦታ፣ በጸሎት ጊዜያት፣ ወዘተ ቡራኬ የሚፈጸመው በመስቀል በማማተብ ነው፡፡ የመስቀሉን ምልክት ባዩ ጊዜ አጋንንት ይንቀጠቀጣሉ፤ ካደሩበት ሰው ላይም በፍጥነት ይወጣሉ፡፡ ምእመናን በመስቀሉ ስንዳሰስ ከልዩ ልዩ ደዌ እንፈወሳለን፡፡
ወደ አገራችን ክርስቲያዊ ባህል ስንመለስ በኢትዮጵያ የመድኀኒታችን የክርስቶስ መስቀል በብዙ ተግባራት ላይ በምልክትነት ጥቅም ላይ ሲውል ይታያል፡፡ ለምሳሌ በቡልኮ፣ ጋቢ፣ ነጠላ፣ ቀሚስ ወዘተ የመሳሰሉ የሸማ ልብሶች፤ እንደዚሁም በጆሮ፣ በአንገት፣ በእጅና ሌሎችም ጌጣጌጦች ላይ የመስቀል ምልክት አለ፡፡ ክርስቲያን ልጃገረዶች (በተለይ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል) በግንባራቸው፣ በጉንጫቸው፣ በአንገታቸው፣ በደረታቸውና በእጃቸው ላይ በመስቀል ቅርፅ እየተነቀሱ ያጌጡበታል፡፡ ክርስቲያኖች ከዚህ ዓለም በሞት ስንለይም በመቃብር ሣጥናችን ወይም በሐውልቶቻችን ላይ የመስቀል ምልክት ይቀመጣል፡፡ በቤት ውስጥም ስንተኛና ከእንቅልፋችን ስንነቃ ፊታችንንና መላ ሰውነታችንን በትእምርተ መስቀል እናማትባለን፤ አባቶችና እናቶችም ውሃ ሲቀዱ፣ ሊጥ ሲያቦኩ፣ እንጀራ ሲጋግሩ፣ ምግብ ሲቈርሱ፣ ወዘተ በመስቀል አማትበው ነው፡፡ በአጠቃላይ መስቀል ብዙ ነገር ነው፤ መስቀል በክርስትና ሕይወት ውስጥ በሚደረጉ ተግባራት ኹሉ ያለው ድርሻ ጕልህ ነው፡፡ /ለተጨማሪ መረጃ ግሸን ደብረ ከርቤ የቃል ኪዳን አምባ፣ መስከረም ፲፱፻፺፮ ዓ.ም፤ ገጽ ፺፮–፻፪ ይመልከቱ/፡፡
በክርስቶስ ደም የተቀደሰው ይህ ክቡር መስቀል ለበርካታ ዓመታት በአይሁድ ምቀኝነት በጎልጎታ ተቀብሮ ከኖረ በኋላ በንግሥት ዕሌኒና በልጇ ቈስጠንጢኖስ ጥረት ከተቀበረበት ወጥቶ ከፀሐይ ብርሃን በላይ አብርቷል፤ ሙት በማስነሣት፣ ሕሙማንን በመፈወስ ብዙ ተአምራትን አሳይቷል፡፡ በመላው ዓለም በሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት ደመራ ተደምሮ በዓሉ የሚከበረውም ንግሥት ዕሌኒ መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ ለማግኘት ከእግዚአብሔር መልአክ በተሰጣት አቅጣጫ መሠረት ያነደደችውን ዕጣንና የመስቀሉን መገኛ የጠቆማትን ጢስ ለማስታዎስ ነው፡፡ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይኹን! በንጉሥ ዳዊት በልጃቸው በዘርዐ ያዕቆብ አማካይነት ወደ አገራችን የመጣው የጌታችን መስቀል ቀኝ ክፍል በአገራችን ኢትዮጵያ በደቡብ ወሎ ሀገረ ስብከት በግሸን ደብረ ከርቤ ይገኛል፡፡ ከቅዱስ መስቀሉና ከገዳሙ በረከት ለመሳተፍ ብዙ ምእመናን በየዓመቱ ቦታው ድረስ በመሔድ በዓለ መስቀልን ያከብራሉ፡፡
በዓለ መስቀል በቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይኾን በየመንደሩና በየቤቱም ምእመናን ደመራ በመደመር፣ ጸበል ጸሪቅ በማዘጋጀት በድምቀት ያከብሩታል፡፡ በተለይ በደቡቡ የአገራችን ክፍል በዓለ መስቀል በደማቅ ሥርዓት ይከበራል፡፡ ይህም የቀደሙ አባቶቻችን ስለ በዓለ መስቀል ይሰጡት የነበረው ትምህርት ቁም ነገር ላይ መዋሉን የሚያስረዳ መንፈሳዊ ትውፊት ነው፡፡ የአከባበሩ ባህል ከቦታ ቦታ ይለያይ እንጂ በዓለ መስቀል በየዓመቱ በመስከረም አጋማሽ በመላው ኢትዮጵያ በልዩ ድምቀትና በመንፈሳዊ ሥርዓት ይከበራል፡፡ በአገራችን መስቀልና ክርስትና እንዲህ ሳይነጣጠሉ ተሳስረው ይኖራሉ፡፡ እኛም አባቶቻችን እንዳስተማሩን ይህንን በክርስቶስ ደም የተቀደሰውን መስቀል በዘወትር ጸሎታችን ‹‹… መስቀል ኃይልነ መስቀል ጽንዕነ መስቀል ቤዛነ መስቀል መድኃኒተ ነፍስነ አይሁድ ክህዱ ንሕነሰ አመነ ወእለ አመነ በኃይለ መስቀሉ ድኅነ፤ … መስቀል ኀይላችን፣ ጽንዓችን፣ ቤዛችን፣ የነፍሳችን መዳኛ ነው፡፡ አይሁድ ይክዱታል፤ እኛ ግን እናምንበታለን፡፡ ያመነውም እኛ በመስቀሉ ኀይል እንድናለን፤ ድነናልም›› እያልን ለመስቀሉ ያለንን ክብር እንገልጻለን፤ በክርስቶስ መስቀል ኀይል መዳናችንንም ስንመሰክር እንኖራለን፡፡ ልዑል እግዚአብሔር በመስቀሉ ኃይል ኹላችንንም ከልዩ ልዩ ዓይነት መከራ ይጠብቀን፡፡
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: መስቀል, ክርስትና, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን, ደመራ, Ethiopian Orthdox Tewahedo Faith, Meskel, The Cross | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 13, 2018
በኢየሩሳሌም ከተማ፡ የኢትዮጰያውያን ርስት ወደ ሆነውና፡ የእስራኤል ሬድዮ ጣብያ ተከራይቶ ይሠራበት ወደነበረው ከ110ዓመት በላይ ያስቆጠረ ህንፃ የእስራኤል መከላክያ ሰራዊት በራሱ ፈቃድ ገብቶ አባቶችን በኃይል ማስወጣቱ፣ ማንገላታቱና ማሠሩ አንድ ተንኮል ከበስተጀርባው አለ ያስብላል።
የግብጽ እጅ፡ ወይስ ኢትዮጵያ በኢየሩሳሌም ጉዳይ ከጥቂት ወራት በፊት ባልተባበሩት መንግሥታት ከመሀመዳውያኑ ጋር በመሰለፏ?
ያም ሆነ ይህ፡ በአባይ ወንዝ ሳቢያ፡ እስራኤልም ሆነች አውሮፓ፡ ሁሉም ከግብጽ ጋር ማበሩን ይመርጣሉ።100 ሚሊየን ቁንጥንጥ ግብጻውያን ከሚጠሙና ከሚራቡ 100 ሚሊየን ሰላማዊ ኢትዮጵያውያን መቸገራቸውን ይመርጣሉ። 100 ሚሊየን የተራቡ ግብጻውያን እስራኤልንም ሆነ አውሮፓን በስደትና በሽብር ያተረማምሷቸዋልና።
ስለዚህ፡ ዓለማዊው የእስራኤል መንግስት ኢትዮጵያን ወደ አረቦቹ በይበልጥ እንድትጠጋ መግፋት፣ ከእስራኤል ጋር ያላትንም ቅርርብ በጣም እንዳታጠብቅና በረከቱንም እንድታጣ ይሻሉ። የአባቶቻችንም መንገላታት የሚነግረን፡ ኢትዮጵያ ኤምባሲዋን ወደ ኢየሩሳሌም አዙራ፡ በእስራኢል ዘንድ መልካም ግምት እንዳይሰጣት ለማድረግ በማሰብ ሊሆን ይችላል። Problem – Reaction – Solution.
ለማንኛውም፡ እስራኤል ዕብራይስጥ ቋንቋን እንደ አረብኛ ከቀኝ ወደ ግራ መጻፉን ማቆም አለባት፤ ኢትዮጵያም ከአረቦች ጋር ጢብጢብ መጫዋቱን መተው ይኖርባታል።
[ትንቢተ አሞጽ ፱፥፯]
“የእስራኤል ልጆች ሆይ እናንተ ለእኔ እንደኢትዮጵያ ልጆች አይደላችሁምን? ይላል እግዚአብሔር”
Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: ኢትዮጵያ, ኢየሩሳሌም, እስራኤል, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክርስቲያን, የኢትዮጵያ ገዳማት, Ethiopian Monastery, Israeli Police, Jerusalem | Leave a Comment »