Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን’

የዋልድባ መነኵሴ አባ ሀብተወልድ በ ሔሮድሳዊው ግራኝ አህመድ ነው ተገድለው የሚሆኑት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 9, 2020

እግዚአብሔር ነፍሳቸውን በምህረት ተቀብሎ ከቅዱሳን ኅብረት ይደምርልን! አሜን!

ጀግንነቱንለማሳየት የላሊበላውን ልጅ ጄነራል አሳምነውን የሠራዊቱን መለዮ በመልበስ አሳድዶ ረሸናቸው ፤ ይህ አልበቃውም፡ የሰይጣን አሻንጉሊቱ አብዮት የጄነራሉን ነፍሰጡር ባለቤት በጨለማ እስር ቤት ውስጥ በማጎር “ዐደጋው ከቁጥጥር ውጪ ይሆንብኛል ፣ አንድ ቀን ይበቀለኝ ይሆናል” በሚል ሰጋት ተተኪውን ሕፃንም ገና በጨቅላነቱ ገደለው።

ሰውዬው ሰምተናቸው አይተናቸው ለማናውቃቸው ጭካኔ የተሞላባቸው ተግባራት ብቁና ዝግጁ ነው፤ መንግስቱ ኃይለማርያም ስጋን ብቻ ነው ሲገድል የነበረው ፤ ይህኛው ግን ነፍስንም እያሸተተ ለመግደል ነው የሚሻው፤ ሰውዬው በሰሜን ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ላይ ሔሮድሳዊ የሆነና በቅናት መንፈስ የሚነዳ እጅግ በጣም ከፍተኛ ጥላቻ ነው ያለው። በዚህ አትጠራጠሩ! የኢትዮጵያዊውን ወንድ ወኔ ለመስበር ልጃገረድ ተማሪዎችን ያግታል/ይገድላል ፥ የተዋሕዶ አማኙን ቅምስ ለመስበር ደግሞ ካህናትንና መነኮሳትን ይገድላል፤ አብያተ ክርስቲያናትን ያዘጋል።

ይህ እርኩስ አውሬ በአማራ እና ትግሬ ኢትዮጵያውያን መካከል መተላለቅ የሚፈጥርለትን ክብሪት ሳይጭር እንቅልፍ የለውም። ለዚህም አስፈላጊውን ድጋፍ በራያ ኦሮሞዎች መንፈስ ውስጥ ከሚገኘው ህዋሃት እያገኘ ይመስላል። ይህ ሁሉ ግፍ ሲፈጽም ሁሉም ጸጥ ማለታቸው ብዙ የሚነግረን ነገር አለ። እውነት ጄነራል ሰዓረን የገደላቸው አብዮት አህመድ እንደሆነ የሚያጠራጥር አይደለም፤ ግን ብቻውን፤ ያለ ደብረ ጽዮን ፈቃድ ግድያውን ፈጽሞታልን? እስካሁን በምናየው የእነ ስብሀት እጅም አለበት። ምክኒያቱም አንድ እንደ ህዋሃት የታጠቀ ቡድን አንድ ከፍተኛ ጄነራሉ ሲገደልብት ዝም አይልም፤ ወዲያው ነበር የሚበቀለው፤ እነ በረከትም ታሥራው ዝም፣ ደጋፊ ጋዜጠኞቻቸውም ታግተው፤ ዝም። አብረው ባይሠሩ አብዮት ሁለት ዓመት አይደለም አንድ ወር ሥልጣን ላይ አይቆይም ነበር።

በጣም የሚያስገርመው እና የሚያሳዝነው የህዋሃቶች አልማርባይነት ነው። ኦሮሞዎች ከአማራዎች ይልቅ ትግሬዎችን በጣም ይጠላሉ፤ ይህን ማንም ሊክደው አይችልም፤ ይህ ሥር የሰደደና ደማቸው ውስጥ የተቀበረ ጥላቻ ነው። ታዲያ እንደዚህ ሆኖ ልክ ስልጣን ላይ እንደወጡ ሉሲፈራውያኑ የሰጧቸውን የኢትዮጵያ ካርታ ያለምንም ማመንታት በመቀበል ትልልቆቹን የኢትዮጵያ ግዛቶች የኢትዮጵያ ጠላቶች ለሆኑት ለኦሮሞዎችና ሶማሌዎች ሰጧቸው። ይህ አልበቃ ብሎ ለ27 ዓመታት ያህል በአላሙዲን በኩል ከሳውዲ አረቢያ የተገኘውን ገንዘብ ለኦሮሞ ባንኮች፣ ዋስትና ኩባንያዎች፣ ሰፋፊ እርሻዎች፣ ባሕል ማዕከላት ወዘተ በማስረከብ በአማራ ላይ እያሴሩ እንደ ባርያ ሲያገለግሏቸው ከቆዩ በኋላ መጨረሻ ላይ ስልጣኑን አስረክበው ፈረጠጡ። ከሁሉ ወንጀል የሚከፋው ይህ ነው! የአማራ ልሂቃኑም ተመሳሳይ ስህተት እየሠሩ ነበር፤ ዛሬም እየሠሩ ነው። ለሃገር የሚያስብ አንድ ቡድን ወይም ግለሰብ ለአንድ ሃገርወዳድ ቡድን ወይም ግለሰብ ስልጣኑን በማስረከብ በሚቀጥለው የተሻለ ሆኖ ለመቅረብ ይሞክራል። እነዚህ ግን “ከኔ የተሻለ መምጣት የለበትም” ፣ “እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል” በሚል ድንቁርና ዜጎችን አላግባብ ያሰቃያሉ። መቼ ይሆን ደገኞቹ የሰሜን ሰዎች ከአቴቴ እስር ቤት ነፃ ወጥተው ሕዝባቸውን ከጦርነት፣ ከረሃብና በሽታ የሚያድኑት?

እስኪ ሰሞኑን በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ እየታየና ኡ!! ከሚያሰኝ የዘርኝነትና የጥላቻ ዘመቻ ትንሽ ተምረው ይህን ያህል የሚጠሏቸው ሉሲፈራውያኑ ከሰጧቸው የመቶ ዓመት አጀንዳ ፎቀቅ ይበሉ። “ጎረቤትህን እንደራስህ አድርገህ ውደድ” እንጅ ቃሉ የሚለው “የጎረቤቴ ጠላት ወዳጄ ነው” አይደለምና የሚለው ዛሬውኑ የጋራ ጠላታችንን መቀለቡን ያቁሙ።። ለሉሲፈራውያኑ የጎሳ ክፍፍላችንን ተጠቅመው የሚፈልጉት ዓላማ ላይ ከደረሱ በኋላ ሁላችንም ኔግሮዎች እያሉ መጥፎ ስም በመስጠት ሊጨርሱን እንደሚፈልጉ ነው የምናየው።

በጣም ያሳዝናል፤ መላው ዓለም በኮሮና ጉዳይ ትንፋሹን ይዟል እነዚህ አልማርባይ የዲያብሎስ የግብር ልጆች ግን በጎንደር፣ በቤኒ ሻንጉል፣ በአዲስ አበባ፣ በላሊበላ እና በዋልድባ የሽብርተኝነት ዘመቻቸውን አጧጥፈዋል። በዚህ የወረርሽኝ ጊዜ አረመኔዎች የሚባሉት የአፍጋኒስታን ታሊባኖች እና አይኤስ እንኳን “ሰልጥነው” ሰይፋቸውን ለማስቀመጥ ወስነዋል። የዋቄዮአላህ ልጆች ግን መነኮሳትን ይገድላሉ፣ ወጣቶችን ያድናሉ፣ እናቶችን ያፈናቅላሉ። በናይጄሪያም ፉላኒ የተባሉት ወራሪ ወንድሞቻቸው ተመሳሳይ ድርጊት እየፈጸሙ ነው፤ ትናንት በወጣው መረጃ ሃምሳ የሚጠጉ ክርስቲያኖች በጎራዴ እየተቆራረጡ ተገድለዋል።

አባትችን አባ ዘወንጌል እንደነገሩን በአህዛብ የከፋ ጉዳት ከሚደርስባቸው ገዳማት መካከል ዋልድባ፣ ማኅበረ ሥላሴ፣ ጉንድ ተክለሃይማኖት፣ አክሱም ጽዮን፣ ደብረ ሊባኖስና አሰቦት ሥላሴ ይይገኙበታል። ገዳማውያኑ የሰማዕትነት አክሊል እየተቀበሉ እንደሆኑ ያው እያየነው ነው።

__________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በዶክተሮች ሊፈታ የማይችለው ወረርሽኝ በጻድቁ ማእጠንት ይታጠናል | የማእጠንት ፀሎት በአሜሪካ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሃብተማርያም የማእጠንት ፀሎት በተወሰኑ የቨርጂንያ መንደሮችና ጎዳናዎች

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፰፤]

ሰባተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ እኵል ሰዓት የሚያህል ዝምታ በሰማይ ሆነ

በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፥ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው

ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው

የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ

ሌላ የሚገርመው ነገር፤ ልክ እዚህ አካባቢ ነበር ባለፈው ጊዜ የሚከተለው የተከሰተው፦

_______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይኸው ሰዓቱ ደርሶ አሜሪካ በአቡነ ሃብተማርያም ማዕጠንት እየታጠነች ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፥፲፮]

እንዲሁ ኋለኞች ፊተኞች፥ ፊተኞችም ኋለኞች ይሆናሉ፤ የተጠሩ ብዙዎች፥ የተመረጡ ግን ጥቂቶች ናቸውና።

ይህን ሳይ የሚሰማኝ፤ “እግዚአብሔር እኛ ኢትዮጵያውያንን በመላው ዓለም በስደትም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ከአገራችን አውጥቶ የሚልከን በርገር እየበላን በከንቱ እንድናውደለድል ሳይሆን እንደዚህ እጣኑን እያጨስን መንፈሳዊ ውጊያውን እንድንመራለት፣ ከጠፉት ጋር አብረን እንድንጠፋ ሳይሆን፣ ሁሉም እንዲድን መድኃኒቱን እንድናሳይ ነው።” የሚለው ነው። በእውነት ነው የምለው፤ እኛ ኢትዮጵያውያን በከንቱ ሌላውን ለመምሰል ብንታገልም ምናልባት 90% መንፈሳውያን ሰዎች ነን።

እንግዲህ ያውልሽ አሜሪካ፤ ግብጻውያን አውሮፕላን አብርረው ከሰማይጠቀስ ፎቆችሽ ጋር በማላተም ሦስት ሺህ ዜጎችሽን ገደሉብሽ፣ ፕሬዝደንትሽ ለጉብኝት ወደ ግብጽ ሲመጡ በንቀት ጫማቸውን ወረወሩባቸውዛሬ የከዳሻቸው ኢትዮጵያውያን የተዋሕዶ ልጆች ግን መቅሰፍቱ ሁሉ ከምድርሽ እንዲርቅ ክቡር እጣኑን ከደመናው ጋር አዋሐዱልሽ። ይህን ውለታ አትርሺ፤ አሜሪካ!

የፃድቁ አባታችን አቡነ ሃብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን!

መምህር ዘመድኩን እንዳካፈለን፦

መፍትሄው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ጭንቅ ውስጥ በገባችው አሜሪካ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በየአደባባዩ፣ በየመንደሩ፣ እየዞረች የጻድቁ አቡነ ሀብተ ማርያምን ዕጣን እንድታጥን ተጠይቃ ይኸው ቃሏን አክብራ በጻድቁ አቡነ ኃብተ ማርያም ጸሎት ምድሪቱን እያጠነች ነው።

ዛሬ መጋቢት ፲፫ / ፲፪ /13/2012 .(Mar.22/2020)

በአሜሪካን ሀገር በሀገሩ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 5:00 PM ላይ በኸረንደን ቨርጂንያ 2472 Centreville Rd.Herndon, VA 20171 የደብረ ከርቤ ቅድስት ማርያም ወአቡነ ሀብተማርያም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ካህናቱ የጻድቁ የአቡነ ሀብተ ማርያም ሥዕላቸው ተይዞ

በኸረንደን፣

በረስተን፣

በቻንትሊን፣

በእስትርሊንግና በሌሎችም ከተሞች የሚገኙ አደባባዮችና አውራ ጎዳናዎች በማጠን ላይ ይገኛሉ።

ለዚሁ የአሜሪካን ከተሞችና መንደሮች የማዕጠንት አገልግሎት

መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን

መጋቤ ካህናት መ/ር ቀሲስ ዮናስ ፍቅረ

ሊቀ ስዩማን መ/ር ቀሲስ ኢዮብ ደመቀ

ሊቀ ልሳናት መ/ር ቀሲስ ጌቱ ተገኑ

ሊቀ ማዕምራን መ/ር ዮሐንስ ለማ

ሊቀ ትጉሀን ዲ/ን አብርሐም ቶማስ

ሊቀ ዲያቆን ገረመው ተዘጋጅተው አገልግሎቱን ጀምረዋል።

አሜሪካ ደንግጣለች። ቤተ ጸሎቶች በሙሉ ተዘግተዋል። የመኪና መንገድ አውራ ጎዳናዎች ሁሉ ጭር ብለዋል። ነገር ግን በእኒህ ሞት ባጠላባቸው የአሜሪካ ጎዳናዎች ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት አባቶቻችን ጸሎት እንዲያደርጉ የአሜሪካ መንግሥት ፈቅዶላቸዋል። በእውነት ከዚህ ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። ይሄ ምልክት ነው። ወደድንም ጠላንም መጪው ዘመን የኦርቶዶክስ ነው። ኦርቶዶክሳዊነት የዓለሙ ሁሉ ሃይማኖት ይሆናል። ሰዎች ሁሉ ወደ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት ይተምማሉ። የኢትዮጵያ ሃይማኖት የዓለም ሃይማኖት ይሆናል የሚባለው የአበው የትንቢት ቃል በቅርቡ ፍጻሜውን ያገኛል።

ከኢትዮጵያ ውጪ ብቸኛው የጻድቁ አቡነ ሃብተ ማርያም ታቦት የሚገኘውም እዚሁ ቦታ ነው። በቦታውም ብዙ ህሙማን እየተፈወሱ መካኖች መወልዳቸው ብዙዎችን ሲያስደንቅ መኖሩም ተነግሯል። በእውነት መንክር እግዚአብሔር በላዕለ ቅዱሳኒሁእግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው፤ የእስራኤል አምላክ እርሱ ኃይልን ብርታትንም ለሕዝቡ ይሰጣል “(መዝሙረ ዳዊት 68:35)

በጻድቁ ዜና ገድል (ገድለ አቡነ ሀብተማርያም ገጽ.117) ላይ ተጽፎና ተመዝግቦ እንደምናገኘው ልዑል እግዚአብሔር ለጻድቁ በሰጣቸው ቃል ኪዳን መሰረት ስማቸው፣ በተጠራበት፣ ማዕጠንታቸው በታጠነበት፣ ዜና ገድላቸው በተነበበትና ባለበት፣ ጠበላቸው በተረጨበት ሥፍራ ፭ቱ መቅሰፍታት ማለትም :-

፩ኛ.መብረቅ

፪ኛ.ቸነፈር

፫ኛ.የረኀብ ጦር

፬ኛ.ወረርሽኝና

፭ኛ.ሰደድ እሳትና የመሳሰሉት ቦታ የላቸውም። ዜና ገድላቸው እንደሚነግረን በአንድ ወቅት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ልጆቻቸው በእነዚህ ፭ቱ መቅሰፍታት እንዳይጠቁና እንዳይጎዱ ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያምን በቃል ኪዳናቸው ልጆቻቸውን እንዲጠብቁላቸው ሲማጸኑዋቸው የጻድቁ የአቡነ ሀብተማርያም መልስ የነበረው “ወዳጄ ተክለሃይማኖት ሆይ፤ በእኔ ስም ልጆችህና ወዳጆችህ በቃል ኪዳኔ የሚድኑ ከሆነ ይሁን ብለው ቃል እንደገቡላቸው ተመዝግቧል። ይህ ቃል ኪዳን ደግሞ ዘመን ተሻጋሪና ጊዜ የማይሽረው ነው። በእውነት ያለ ሀሰት። እንጠቀምበት።

በኢትዮጵያም በትናንትናው ዕለት የቃሌ አቡነ ሃብተማርያም ገዳም ካህናት አዲስ አበባ ቃሌ አከባቢ ሲያጥኑ መዋላቸው ተዘግቧል። ትናንት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የዐድዋውን ዘማች ታቦተ ጊዮርጊስን ይዛ ማዕጠንቱን ብታካሂድ ወረርሽኙ ድራሹ ይጠፋል በማለት ያሳሰብኩትም ማሳሰቢያዬም መልስ አግኝቷል። የአራዳ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መጋቢት 20 ታቦቱን ይዘው ሊወጡ ነው። የአዲስ አበባ ሃገረ ስብከትም መጋቢት 13 በአዲስ አበባም የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራትም በጋራ ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ አዲስ አበባን እንዲያጥኑ መመሪያ ተላልፏል።

በጣልያን ሊቀጳጳሱን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስን አናግሬያለሁ። የጣልያን መንግሥት ፈቃድ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ እኛ ዝግጁ ነን ብለዋል። የጀርመኑን ሊቀጳጳስ ብፁዕ ዲዮናስዮስንም እንዲሁ አግኝቼ አውርተናል። ፈቃዱ ከመንግሥት ካለ እኛ ዝግጁ ነን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እጹብ ድንቅ ነው | የአቡነ ሃብተማርያም ገዳም ካህናት አዲስ አበባ ቃሌ አከባቢ ሲያጥኑ ዋሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 23, 2020

በዚህ በጣም ተደስቼ ነው የዋልኩት፤ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን!

ትንሽ ቅር ያለኝ ነገር ግን እዚህ ድንቅ ገዳም ተራራ ጫፍ ላይ አንጋፋውን መስቀል ለማስተከል መስነፋችን ነው።

የፃድቁ አባታችን አቡነ አብተማርያም ቃል ኪዳናቸው ይጠብቀን የመጣውን መቅሰፍት ከአገራቸን ኢትዬጵያና ከመላው ዓለም ይሰውርልን!

________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አይሁዱ ተመራማሪ | ለኮሮና መድኃኒቱ እጣን መሆኑን ብሉይ ኪዳን ጠቁሞናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 21, 2020

ቫይረሱ ጋኔን መሆኑን አረጋገጠልን!

ምን እንደሆነ አላውቅም እስከ አለፈው ነሃሴ ወር ድረስ ምናልባት በወር አንዴ ብቻ ነበር እጣን የማጤሰው፤ ካለፈው ጥቅምት ወር አንስቶ ግን በቤትም በመሥሪያ ቤትም በጣም አዘውትሬ አጤሳለሁ፤ የእግዚአብሔር ሥራ ድንቅ ነው፤ ቅዱስ መንፈስ ማድረግ የሚገባንንና የሚጠቅመንን ነገር ሳናስበውና ሳንዘጋጅበት እንድናደርገው ወደ በጎው ነገር ይመራናል።

ዛሬ ወደዚህ አይሁድ ቪዲዮ እንዴት እንደገባሁ ሁሉ አላውቅም፣ ያውም እጣንን በሚመለከት የገባሁበት ገጽ አልነበረም ፤ ግን ያው! ለኮሮና ጋኔን መፍትሄ ይሆናሉ ብዬ ሳስባቸው ከነበሩት ከጸበል፣ ከጸሎት ጎን እጣን እና ከርቤ እንደሚኖሩበት አረጋገጠለን። አሁን በዚህ በጣም እርግጠኛና ደስተኛ ነኝ።

ደካሞችና ምስጋና ቢሶች ሆነን ነው እንጂ አምላካችን እኮ የሚጠቅሙንን ነገሮች ሁሉ ሰጥቶናል፤ ጸበሉንም፣ ጸሎቱንም፣ እጣኑና ከርቤውንም በነጻ ሰጥቶናል። እጣንና ከርቤ ከወርቅ በላይ የሆኑበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ለብዙ በሽታዎች ፈውስ እንደሆኑ ሳይንሱ ሳይቀር እያረጋገጠልን ነው። Seeing the Unseen of the Combination of Two Natural Resins, Frankincense and Myrrh

እጣኑን በአግባቡ እናጢስ፤ ወገኖቼ፤ ነገር ግን ከተለመደው የቡና ስነ ሥርዓት ወቅት፣ በተለይ ከኦጋዴን እና አረብ ዕጣኖች ጋር አብሮ ማጤሱን ዛሬውኑ ማቆም አለባችሁ! አባቶች ይህን አስመልክቶ አንድ ይበሉን!

አየን አይደለም?! ጠላት ዲያብሎስ ለብዙ ሳምንታት በቂ የኮሮና ቫይረስ በአውሮፕላን እንዲረጭ ካደረገ በኋላ ወሮበላው መንግስት “በረራዎችን አቁሜአለሁ ፣ ይቅርታ ቅብጥርሴአለን። ቫይረሱ ልክ እንደ አንበጣ እስኪፈለፈል የሁለት ሳምንታት ጊዜ ይወስድበታል ተብሏል። ስለዚህ አባቶች ልክ እንደ ጆርጂያ ኦርቶዶክስ አባቶች በተለይ አዲስ አበባን በመኪና እና በሄሊኮፕቶር እየዞሩ ዛሬውኑ ደጋግመው ጸበል ቢረጩና እጣን ቢያጤሱ ትልቅ ሥራ ይሆን ነበር። በተለይ ምዕመናን ለቅዳሴ የማይመጡ ከሆነ ይህ መደረግ አለበት። ቀዝቃዛዎቹ የጉንፋን ወራት ከመጀመራቸው በፊት አስቀድሞ መደረግ ያለበት አንዱ ተግባር ይህ ሊሆን ይገባል።

UPDATE

የመንፈስ ቅዱስን ሥራ እያየን ነው፡ ወገኖቼ? ዋው! የሚገርም ነው፦ ያው መምህር ጳውሎስም እንዲህ ይለናል፦

የማዕጠንት ጊዜ ነው፤ ማዕጠንት ጥሩ ነው፤ በሽታ የሚያርቅ ነው፤ እጣኑንን እያሸተታችሁካህናት በየቤቱ በመዞር ጸሎተ ማርያም እየደገሙና ማዕጠንት እያደረጉ ቢያልፉ በሽታው ያልፋል ከተማው ይታጠላንል አስፈላጊ ከሆነ”።

ወደ እዚህ እንግባና ሙሉውን እናዳምጥ፦

አስደናቂ ስብከት በሽታው የሚርቀው በማዕጠንት ነው መምህር ጳውሎስ መልካሥላሴ ክፍል፪

ቃለ ሕይወት ያሰማልን!

___________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይህ በዝምታ አይታለፍም | ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 20, 2020

[የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፯፥፮|

በእግራቸው እንዳይረግጡት ተመልሰውም እንዳይነክሱአችሁ፥ የተቀደሰውን ለውሾች አትስጡ፥ ዕንቁዎቻችሁንም በእሪያዎች ፊት አትጣሉ።

ውሀችን / ጸበላችን ከመካ እና ውሀን ከተሞች የፈለሰውን የኮሮና ጋኔን ያርቅልናል!

እስኪ ይታየን፤ ከግብጽ እና አረቦች ጠላቶቻችንን ጎን በመሰለፍ የህዳሴው ግድብ እንዳይገነባ ፊርማዋን ያስቀመጠችው ጂቡቲ ንጹህ ውሀ ከኢትዮጵያ በነፃ ተሰጥቷታል። ኢትዮጵያን ለመውረር ያቀዱትን የኤዶማውያን እና እስማኤላውያን የጦር ሠራዊቶች በግዛቷ የምታስተናግደዋ ጂቡቲ ኢትዮጵያውያን የማይጠጡትን ንጹሕ ውሀ በነፃ ትጠጣለች።

ጥንታውያን ግሪካውያን ረጅም እድሜ የሚያስገኘው የመጠጥ ውሃ የሚገኘው በኢትዮጵያ ነው በማለት ይናገሩ ነበር። ታዲያ ይህን ምስጢር ጠላቶቻችን ስለሚያውቁ ኢትዮጵያውያን ይህን እግዚአብሔር የሰጣቸውን ፀጋ አውጥተው እንዳይጠቀሙና ወደፊት እንገነባታለን ለሚሏት አዲሷ ዓለም ውሃው እንዳይነካባቸው ኢትዮጵያውያኑ ከሽንት ቤት ተጠራቅሞ የተጣራውን ውሃ ብቻ እንዲጠጡ ማድረግ አለብን ስላሉ ያው እነ ቆቃ ተገንብተዋል። እነዚህም የውሃ ማጠራቀሚያዎች ከላይም ከታችም እንደማይበከሉ የሚታወቅ ነገር የለም። የጣናው እንቦጭም ከአውሮፕላን ላይ ተረጭቶ የተተከለ የአትክልት አውሬ ነው።

በእሳቱ ለመጠረግ ችቦው ውስጥ በመግባት ላይ ያሉት የሃገራችን ጠላቶች በውሀው፣ በአየሩና በምድሩ ላይ ነው ጥቃት እየፈጸሙ ያሉት። ከሁሉም አቅጣጫ!

ለዘመናት ለኢትዮጵያውያኑ መንፈሳዊ እና ስጋዊ በጎነት፣ ጤንነትና ብልጽግና ብቸኛውን ሚና የምትጫወተው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እንደሆነች በየቦታው እየፈለቁላት ያሉት ጠበላት ምስክሮች ናቸው። ይህ ቀላል ነገር አይደለም፤ ይህን በተለይ በያዝነው ዘመን በጣም ክቡር የሆነውን የጸበል ውሃ ነው ጠላቶቻችን ሊነጥቁን የሚሹትና። አሁን ለተጀመረው የፀረቤተ ክርስቲያን ዘመቻ አንዱ ምክኒያትም ይህ ነው። ኢትዮጵያዊው ጤናማ እንዲሆን፣ የታመመውም እንዲፈወስ አይፈልጉም። “በዓለማችን በጣም ውድ የሆነው ነገር ለእኛ ብቻ የተቀደሱት ተራራዎች ውስጥ ተቀብሮ ይቆይልን” ይላሉ ፤ ውሀ ኬኛ!

በአንድ ወቅት ከግብጽ የመጡ የኮፕት ቤተ ክርስቲያን አባቶች ከእንጦጦ ኪዳነ ምህረት ጠበል ወደ ሰላሳ በርሚል የፀበል ውሃ በጭነት መኪና አስጭነው ወደ ግብጽ ሲወስዱ እና በሌላ በኩል ብዙ የእኛ ሰው ይህን በእጁ የያዘውን ወርቅ ለመጠቀም አለመፍቀዱን ሳይ በጣም ነበር ያዘንኩት። የሚጠመቁ መሀመዳውያንን እንኳን ደስ እያለኝ በየጊዜው አይቻለሁ፤ ግን አንዳንዶቹ ከተፈወሱና ከዳኑ በኋላ የፈወሰቻቸውን ቤተ ክርስቲያን ያጠቋት ዘንድ የዲያብሎስ አባታቸውን ፍላጎት ለመፈጸም ተመልሰው ይመጣሉ።

ይህ ዘመን ሃገራችን ያጠባቻቸውን ጡቷን ሊነክሱባት የሚሹ ከሃዲዎች የበዙበት ዘመን ነው።

በቤተ ክርስቲያን ላይ ጦርነቱ ተጧጥፏል፣ ጠላቶቻችን እግዚአብሔር በሰጠን ጤናማ ውሃችን ላይ ዓይናቸውን አሳርፈዋል፣ ጥምቀተ ባሕር መውረስ ጀምረዋል፣ በጠበላቱ አቅራቢያ የኬሚካል ፋብሪካዎችንና ጋራጆችን ይሠራሉ (አያት፣ ነፋስ ስልክ፣ ፉሪ፣ ለጋሃር፣ ቃሊቲ ወዘተ) ሰው አምላኩ ከሰጠው ንጹህ ምንጩ ሳይሆን “ሃይላንድ” በተሰኘው ላስቲክ ምናምኑን ቀምመው ያዘጋጁለትን ውሃ ካልቻለ በኬሚካል የተበከለውንና የደፈረሰውን ውሃ ብቻ እንዲጠጣ አማራጩን ሰጥተውታል።

ታዲያ ይህ ትልቅ፤ እጅግ በጣም ትልቅ ወንጀል አይደለምን?! በደንብ እንጅ! አዎ! አባታችን አባ ዘወንጌል ኢትዮጵያን በዚህ ወቅት እያስተዳደሯት ያሉት ጠላቶቿ ናቸው!” ሲሉ 100% ትክክል ናቸው።

_________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Health | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ይህ ተሰምቶ አይታወቅም | ጸሎት የሚያደርሱትን የተዋሕዶ ልጆች ይሸናሉ ብለው ዘረኞቹ ወነጀሏቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 23, 2018

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች፡ በጀርመኗ ሙኒክ ከተማ፡ ቤተክርስቲያናቸው አጠገብ ቆመው ጸሎት ሲያደርሱ፡ ዘረኞቹ ፎቶ በማንሳት፡ መጀመሪያ ፊስ ቡክ ላይ ለቀቁት፡ ከዚያም በይቦታው ወሬውን አሠራጭተው ብዙ ነጮች እንዲቆጡ ለማድረግ በቅተው ነበር።

ተመልከቱ! አዲስ መጤ ጥቁሮች ቤተክርስቲያናችን ላይ እየሸኑ ነው!”

በማለት ብዙ የጥላቻ እና የዛቻ ዘመቻ በኢትዮጵያውያኑ (ኤርትራ) ላይ ለመቀስቀስ ሞክረዋል።

ጸሎት እያደረሱ እንደሆነ ከጀርመን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በኩል ማስተባበያ ቢሰጥም አምነው መቀበል ስላቃታቸው/ስላልፈለጉ እጅግ የሚያሳዝን የጥላቻ መርዛቸውን መርጨቱን ቀጥለው ነበር።

በጣም አሳዛኝ ሁኔታ ነው፤ በጣም አሳዛኝ ሰዎች ናቸው። ጀርመናውያኑ እራሳቸው ከፈጠሩት ውድቀታቸው ምናልባት ኢትዮጵያውያኑ እንደ መልአክ ተልከውላቸው ሊሆን ይችላል፣ ግን ወደ ጨለማው በመግባታቸው በጎ ነገር መሻትና ጥሩውን ከመጥፎ ለመለየት ተስኗቸዋል። ለልጆቹ ወደፊት ማሰብ ያቃተው ትውልድ ምንም የሚያኮራ ነገር ሊኖረው አይችልም።

እንደ ነቀርሳ እየበዘበዟቸው፣ እየበደሏቸው፣ ህፃናቶቻቸውን እየደፈሩባቸው ብሎም እየገደሉባቸው ባሉት በሙስሊሞቹ ወራሪዎች ላይ “የለም የገነባነውን ማፍረስና ማስፈረስ የለብንም!“ በማለት እንደ መነሳሳት፣ ምንም ባላደረጓቸው፡ ምናልባትም ሊረዷቸውና ሊጠቅሟቸው በሚችሉት የኢትዮጵያ (ኤርትራ) ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ላይ ያላግባብ አካኪ ዘራፍ ይላሉ።

ዘረኞች፡

ግብዞች! ደካሞች! ተልካሾች! ውዳቂዎች!

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አባቶች ሠዐልያን ዛሬ ኖረው የእኛን ዘመን ሰው በሥዕል አሳዩ ቢባሉ ያለ ዐይን ይስሉን ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 7, 2017

የእንግሊዙ Express ጋዜጣ በትናንትናው ድኽረገጹ ላይ፤ ከዚህ ቀደም ቀርቦ የነበረውን “ኢየሱስ ክርስቶስ የፈረንጅ ገጽታ የለውም” የሚል መረጃ በማረጋገጥ በድጋሚ አቅርቦልናል። የ ፎረንሲክ ባለሙያዎች እንደደረሱበት የኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛ መልክ አሁን በየአገሩ እንደምናየው ረጅም ጸጉር ያለው የኮውኬዢያ (ነጭ ዘር) ሰው ዓይነት ያለው መልክ አይደለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ነጭ ቆዳና ሰማያዊ ዓይኖች ሳይሆን፡ ልክ እንደ ብዙው ኢትዮጵያዊ ቡናማ የቆዳ እና ጥቁርቡናማ የዓይን ቀለማት የነበረው መሢሕ ነበር።

ይህ ሥዕል ኢየሱስ ክርስቶስን በቅርበት የሚመስል ነው፡ ይሉናል የሳይንሱ ሊቃውንት።

ለእኔም ከዚህ ጋር የሚቀራረብ የጌታችን ሥዕል እንዳል ተገልጾልኝ ነበር፤ በሌላ አጋጣሚ አቀርበዋለሁ።

ከዚህ በፊት ደጋግሜ የምናገረው ነገርና አሁንም እጅግ በጣም በማዘን እንድጠይቅ የሚያስገድደኝ ነገር፡ ለምንድን ነው አንዳንድ የአሁኑ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ሠዐልያን፡ ጌታችንን፣ እመቤታችንን፣ መላዕክቱን ሳይቀር ፈረንጅ በማስመሰል የሚስሏቸው? ፈጣሪንና አባቶቻችንን ማስቀየም አይሆንምን? በግድ የለሽነት? ወይስ በክኽደት? ቤተክህነት፣ ማሕበረ ቅዱሳንና የሚመለከታቸው ድርጅቶች፡ በተለይ ውጭ ያለን ሁሉ ይህን፡ በእኔ አመለካከት፡ ለማረም ቀላል የሆነ ከባድ ወንጀል እንዴት ማስተካከል አቃተን? ዓለማዊው ወገናችን ለራሱ በፈጠረው ሰፊ መድረክ ኢትዮጵያውያንን ፈረንጅ እና እንግሊዝኛ ተናጋሪ ለማድረግ ተግቶ በመሥራት ላይ ነው፤ መንፈሳዊ የሆነ ግን፡ ለምንድን ነው አማራጭ በናፈቃት ዓለማችን ለሰው ልጅ ሁሉ የሚጠቅም ብርቀኛ ማንነታችንን እየተው ሊያጠፉን የሚታገሉትን ጸረክርስቶሳውያን ፈረንጆች ለመኮረጅ የሚሻው? በጣም ያሳዝናል፤ ያቆስላል! ይህን ጉዳይ ቶሎ ካላስተካክልን አባቶቻችን በጣም ይዝኑብናል፤ መጪውም ትውልድ ክፉኛ ይረግመናል።

የሚከተለው ጽሑፍ፡ „እመጓ” ከሚለው የ ዓለማየሁ ዋሴ እሸቴ ድንቅ መጽሐፍ የተወሰደ ነው። ከከበረ ስላምታ እና ምስጋና ጋር።

.ጉብኝታችንን የጀመርነው ከጥንታዊቷ የናዳ ማርያም ቤተክርስቲያን ሕንፃ ነው….

የጥንቱ ሊቃውንት ሥዕሎች ቤተ መቅደስን ከማስዋብ በዘለለ ትልቅ ማስተማሪያና የታሪክ መዛግብት ሆነው እንዲያገለግሉ በማሰብ ሲሳሉ ወጥ የሆነ የቦታ አቀማመጥና የአሳሳል ሥርዓት ተሠርቶላቸዋል። ሁል ጊዜ፡

  • በስተምሥራቅ በኩል ባለው የቤተ መቅደሱ ግድግዳ ላይ የሚሳሉት ሥዕሎች ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ያደረጋቸውን ተዓምራት የሚያሳዩ ሲሆኑ፤
  • በስተምዕራብ በኩል ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ በምድር ላይ ተገልጦ በተመላለሰበት ዘመን የፈጸማቸውን መጽሐፋውያንም ትውፊታውያንም ታሪኮች፡ ለምሳሌ ከብሥራት እስከ ዕርገት ያለውን፤
  • በስተደቡብ ደግሞ የድንግል ማርያምን ስደትን

የሚያመለክቱ ይሳላሉ።

ሁሉም ሥዕሎች ክብ ፊት፣ ትልልቅ ዓይኖችና ጥቁር ፀጉር አላቸው። በአንድ ወቅት የድኅረ ምረቃ ጥናቴ አማካሪ ፕሮፌሰር ከነበረ ሆላንዳዊ ወዳጄ ጋር ጣና ሃይቅና ዘጌ የሚገኙ ገዳማትን ስንጎበኝ ሥዕሎቹን በአድናቆት ሲመለከት ከቆየ በኋላ የተናገረኝም ትዝ አለኝ፦

ከሥዕሎቹ ጥንታዊነትና ውበት በላይ የአስገረመኝ ሁሉም ሥዕሎች ራሳችሁን ኢትዮጵያውያንን እንዲመስሉ ተደርገው መሳላቸው ነው። ይህም በራሳችሁ የምትተማመኑ ሕዝቦች መሆናችሁን ያስረዳል” ነበር ያለኝ።

እኔም በውስጠ ወይራ ንግግር “አዎን ነበርን” ብዬ ነበር የመለስኩለት።

አስጎብኚዬ አባ፦ “ይህን ሥዕል ተመልከተው ግማሽ ፊቱ ከአንድ ዐይኑ ጋር ብቻ ነው የተሳለው። እንደዚህ ሲሆን ባለታሪኮቹ ኃጥኣን፥ ከሃድያን፡ አረማዊያን ናቸው ማለት ነው። ምክኒያቱም በሰማዕታቱና በቅዱሳኑ ያን ሁሉ መከራ ያደረሱባቸው በተፈጥሮ የተሰጣቸውን በነጻነትና በሙሉነት የማሰቢያ ጭንቅላት ስላልተጠቀሙበትና አስተሳሰባቸውም ሆነ ድርጊታቸው ሰብአዊነትን ለቅቆ ከእንስሳም ከፍቶ አውሬነት የታየበት ስለሆነ በሙሉ ሰውነት አይሳሉም። ከዚህ በተቃራኒው የጌታ፣ የእመቤታችን፣ የቅዱሳንና የሰማዕታት ግን ሙሉ ፊታቸው ከሁለት ዐይኖቻቸው ጋር ራሳቸው አካባቢ የብርሃን ክበብ ኑሮበት ይሳላሉ” አሉ። “ምክኒያቱም ደግነታቸውና በጎነታቸው፣ አዛኝነታቸውና ርኅራኄያቸውም ለገዳዮቻቸውም ጭምር ስለሆነና በሚገደሉበት ሰዓት እንኳ በገዳዮቻቸው ላይ ቂምም ሆነ በቀል ስለሌላቸው አምላካቸውንም ስለሚመስሉት ሙሉነታቸውን፡ አድሎም የሌለባቸው መሆኑን፤ ቅድስናቸውንና ክብራቸውን ስለመግለጥ ባለሙሉ ገጽ ባለ ክብ ዐይን (ሁሉንም እኩል የሚያይ ማለት ነው) ሆነው ክብራቸውና ጸጋቸውም በራሳቸው ላይ ባለው የብርሃን ክበብ ተወክሎ ይሳላሉ” ሲሉ፡ እኔ በመገረም፦

እነዚህ ሠዐልያን ኖረው የእኛን ዘመን ሰው በሥዕል አሳዩ ቢባሉ ያለ ዐይን ይስሉን ይሆን?„ የሚል የኅሊና ጥያቄ መጣብኝ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

ጼዴንያ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 20, 2016

maryamበቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን ከሚዘከሩ በዓላት መካከል የእመቤታችን በዓል አንደኛው ሲኾን ይኸውም ጼዴንያ በምትባል አገር ከሥዕሏ ተአምር የተደረገበት ዕለት ነው፡፡ በተአምረ ማርያምና በመጽሐፈ ስንክሳር እንደ ተመዘገበው ቅዱስ ሉቃስ ከሣላት ሥጋ የለበሰች ከምትመስል የእመቤታችን የሥዕል ሠሌዳ ቅባት ይንጠፈጠፍ ነበር፡፡

እመቤታችን ድንግል ማርያምን የምትወድና በሚቻላትም ኹሉ የምታገለግላት፣ ቤቷንም ለእንግዳ ማደሪያ ያደረገች አንዲት ማርታ የምትባል ሴት ነበረች፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን አባ ቴዎድሮስ የሚባሉ መነኵሴ ከእርሷ ዘንድ በእንግድነት አድረው በማግሥቱ ከቤቷ ሲወጡ ማርታ የሚሔዱበትን አገር በጠየቀቻቸው ጊዜ እርሳቸውም ወደ ኢየሩሳሌም ሔደው ቅዱሳት መካናትን እንደሚሳለሙ ነገሯት፡፡

ማርታም ከእርሷ ገንዘብ ወስደው የእመቤታችንን ሥዕል ገዝተው ይዘውላት እንዲመጡ ለመነቻቸው፡፡ መነኵሴውም በራሳቸው ገንዘብ ሥዕሉን ገዝተው እንደሚያመጡላት ቃል ገቡላት፡፡ አባ ቴዎድሮስ ኢየሩሳሌም ደርሰው ቅዱሳት መካናትን ከተሳለሙ በኋላ ሥዕሏን ሳይገዙ ወደ አገራቸው ተመለሱ፡፡ ያን ጊዜም ‹‹ሥዕል መግዛትን ለምን ረሳህ?›› የሚል የሚያስደነግጥ ቃልን ሰምተው ወደ ገበያ ተመልሰው መልኳ ያማረና የተወደደ የእመቤታችን ማርያምን ሥዕል ገዝተው በሐርና በንጹሕ ልብስ ጠቅልለው ይዘው እየተጓዙ ሳሉ ከሚያስፈራ ዱር ውስጥ ሲደርሱ ወንበዴዎች ተነሡባቸው፡፡ ሊሸሹ ሲሉም ‹‹መንገድህን ሒድ›› የሚል ቃል ከሥዕሏ ወጣ፤ መነኵሴውም መንገዳቸውን በሰላም ተጓዙ፡፡ ሁለተኛም አንበሳ ሊበላቸው በተነሣባቸው ጊዜ ከዚያች ሥዕል የሚያሥፈራ ድምፅ ወጥቶ አንበሳውን አባረረላቸው፡፡

አባ ቴዎድሮስ ይህን ኹሉ ድንቅ ተአምር ባዩ ጊዜም ያቺን ሥዕል ለማርታ ከመስጠት ይልቅ ወደ አገራቸው ሊወስዷት ወደዱ፡፡ በመርከብ ተሳፍረው በሌላ አቅጣጫ ሲሔዱም ታላቅ ነፋስ ተነሥቶ ወደ ማርታ አገር ወደ ጼዴንያ ወሰዳቸው፡፡ ከመርከብም ወርደው ከብዙ እንግዶች ጋር ወደዚያች መበለት ቤት ደረሱ፡፡ ነገር ግን ማንነታቸውን ለማርታ አልገለጡላትም፤ እርሷም አላወቀቻቸውም ነበር፡፡

በማግሥቱም ተሠውረው ወደ አገራቸው ሊሔዱ ሲሉ የቅፅሩ ደጃፍ ጠፍቶባቸው ሲፈልጉ ዋሉ፤ በመሸባቸው ጊዜም ወደ ማደሪያቸው ተመለሱ፡፡ ማታ ማታ በሩን ያዩታል፤ ነግቶ መሔድን ሲሹ ግን የበሩ መንገድ ይሠወርባቸዋል፡፡ እንዲህም ኾነው እስከ ሦስት ቀን ድረስ ቆዩ፡፡ ማርታም ‹‹አባቴ ሆይ አእምሮህ ተነክቷልን? ስትቅበዘበዝ አይሃለሁና ምን ኾነህ ነው?›› ሰትል ጠየቀቻችው፡፡ እርሳቸውም ከእመቤታችን ሥዕል የተደረገውን ተአምር ኹሉ ነገሯት፤ ራሳቸውንም ገለጡላትና ሥዕሏን ሰጧት፡፡ እርሷም የእመቤታችንን ሥዕል ተቀብላ የተጠቀለለችበትን ልብስ በፈታችው ጊዜ ወዝ ከሥዕሊቱ ሲንጠፈጠፍ አገኘች፡፡ ከደስታዋ ብዛት የተነሣም የአባ ቴዎድሮስን እጃቸውንና እግራቸውን ሳመች፡፡

ከዚህም በኋላ ያቺን ሥዕል ወደ ጸሎት ቤቷ ወስዳ በታላቅ ክብር አኖረቻት፡፡ ማንም እንዳይዳስሳትም የነሐስ መስኮትን ሠራችላት፡፡ በቀንና በሌሊትም የሚያበሩ መቅረዞችን በፊቷ ሰቀለች፤ ከመቅረዞች ውጭም የሐር መጋረጃን ጋረደች፡፡ ከሥዕሊቱ በታችም እየተንጠፈጠፈ የሚወርደው የወዝ ቅባት የሚጠራቀምበት ከዕብነ በረድ የተሠራ ወጭት አኖረች፡፡ እኒያ መነኰስም እስከሚሞቱበት ቀን ድረስ የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ሥዕል እያገለገሉ ኖሩ፡፡

CrossOnBahirzaf4የአገሩ ሊቀ ጳጳስም የእመቤታችን ሥዕል ሥጋ የለበሰች ኹና ባገኙና ተአምሯንም በተመለከቱ ጊዜ ከዚህ አምላካዊ ግብር የተነሣ አደነቁ፡፡ ከሥዕሏ ከሚንጠባጠበው ቅባት ቀድተው ለበረከት ሲካፈሉም ወዲያውኑ በወጭቱ ውስጥ መላ፡፡ ሥዕሊቱን ወደ ሌላ ቦታም ሊወስዷት በፈለጉ ጊዜም ንውጽውጽታ ኾኖ ብዙዎች በድንጋጤ ወደቁ፡፡ ሥዕሊቱም እስከ ዛሬ ድረስ በዚያች አገር (በጼዴንያ) ትገኛለች፡፡

‹‹እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነው›› ተብሎ እንደ ተጻፈ /መዝ.፷፯፥፴፭/ እግዚአብሔር አምላካችን በልዩ ልዩ መንገድ ለሰው ልጅ ተአምራቱን ይገልጣል፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ተመዝግቦ እንደምናገኘው እግዚአብሔር ከዓለት ላይ ውኃ እያፈለቀ ሕዝቡን ያጠጣል፡፡ ከግዑዝ ዓለት ውስጥ ውኃ የሚያፈልቅ አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ፤ ከነፍሷ ነፍስ ተዋሕዶ ካከበራት ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ወዝ እንዲፈስ ቢያደርግ ምን ይሳነዋል? እንደዚሁም ቅዱሳን ሐዋርያት በቃላቸውም፣ በልብሳቸውም፣ በጥላቸውም ሙታንን በማስነሣት፤ ሕሙማንን በመፈወስ ተአምራትን ያደርጉ ነበር፡፡ ለምሳሌ ቅዱስ ጴጥሮስ በጥላው፤ ቅዱስ ጳውሎስም በልብሱ ቅዳጅ ያደርጓቸው የነበሩ ተአምራትን መጥቀስ ይቻላል፡፡

ሐዋርያት ከእግዚአብሔር ዘንድ በተሰጣቸው ጸጋ በልብሳቸውና በሰውነታቸው ጥላ ተአምራትን ማድረግ እንደ ተቻላቸው ኹሉ አምላክን በማኅፀኗ የተሸከመችው ወላዲተ አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምም በሥዕሏ ወዝ ብዙ ሕሙማንን መፈወስ ይቻላታል፡፡ ከቅዱሳን ልብስና ጥላ የእርሷ ሥዕል ይከብራልና፡፡ ስለዚህም ነው በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት የሚከበረው፡፡ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት፤ የልጇ፣ የወዳጇ የጌታችን የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቸርነት አይለየን፡፡

ምንጭ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

እንኳን ለልደት በዓሉ በሰላም አደረሰን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 6, 2015

ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚበልጥ ፀሀይ እና ብርሀን የለም

ቅዱስ ፓትርያርኩ የልደት በዓልን አስመልከቶ ያስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት

HERALDINGብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2007 .. የጌታችን የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓልን አስመልክቶ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን ታኅሣሥ 27 ቀን 2007 .. የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡

ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት:-

ቃለ በረከት ዘእምኅበ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ በዓለ ልደት ዓቢይ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!

  • በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
  • ሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
  • የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
  • በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
  • እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያት፤

የዘለዓለም አባት፤ የሰላም አለቃ፤ ስሙም ድንቅ መካርና ኃያል አምላክ የሆነው ጌታችን፤ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ2007 .. በዓለ ልደቱ በሰላም አደረሳችሁ!!

ውውእቱ ቃል ሥጋ ኮነ ወኃደረ ላዕሌነ፤ ያ ቃል ሥጋ ሆነ፤ በእኛ ላይም አደረ” (ዮሐ.114)

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

የጌታችን፤ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓል ልደት ስናከብር ከሁሉ በፊት የእርሱን ማንነት በማውሳት፤ በመረዳትና የእምነት ግብረ መልስን በመስጠት ልናከብር እንደሚገባ መገንዘቡ ተገቢ ነው፤

ከዚህ አኳያ ለመሆኑ የተወለደው ማን ነው? ለምንስ ተወለደ? በልደቱ ዕለት ለዓለም የተላለፈው አጠቃላይ መልእክትስ ምንድነው? የሚለውን ማየት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፣

ቅዱሳት መጻሕፍት በግልጽ እንደሚያስተምሩን ከሦስት አካላተ እግዚአብሔር አንዱ የሆነው እግዚአብሔር ወልድ የአብና የመንፈስ ቅዱስ ቃል ስለሆነ በተለየ ኩነቱ ቃል፣ ቃለ አብ፤ ቃለ እግዚአብሔር፣ አካላዊ ቃል ተብሎ ይጠራል፤(መዝ.326፤ ዮሐ.11-2፤ ራእ.1913) ቃል ከልብ እንደሚገኝ አካላዊ ቃልም ከአብ የተገኘ ነው፤ ይሁንና ቃል ከልብ በመገኘቱ ደኃራዊ አይባልም፤ ልብም ቃልን በማስገኘቱ ይቀድማል አይባልም፡፡ በህልውናም በተመሳሳይም አካላዊ ቃል ከአብ በመገኘቱ ደኃራዊ አይባልም፣ የአካላዊ ቃል አስገኝ በመሆኑ ከወልድ ይቀድማል አይባልም፡፡ በህልውናው (በአኗኗር) ከቃል የተለየ ወይም የቀደመ ልብ እንደማይኖር ሁሉ፣ ከአካላዊ ቃል የተለየ ወይም የቀደመ የአብ ህልውና (አኗኗር) የለም፤ ቃል የሚለው ስም እኩል የሆኑ የሦስቱ አካላተ እግዚአብሔር ቅድምና እና ህልውና በምሥጢር ያገናዘበና በትክክል የሚገልጽ በመሆኑ ወንጌላዊው ዮሐንስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በመለኮታዊና በቀዳማዊ ስሙ ቃል ብሎታል፤

ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ “በመጀመሪያው ቃል ነበረ፤ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ፤ ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፤ ሁሉ በእርሱ ሆነ፣ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም” በማለት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት በያማሻያማ መልኩ ያረጋግጣል፤ (ዮሐ.11-3)፡፡ እግዚአብሔር አብ አካላዊ በሆነ ቃሉ በእግዚአብሔር ወልድ ፍጥረታትን ሁሉ እንደፈጠረ፣ አካላዊ በሆነ እስትንፋሱ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስም ለሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ሕይወትን እንደሰጠ በቅዱስ መጽሐፍ በብዙ ቦታ በግልጽ ተቀምጦአል፤ (ዘፍ.11-3፤ መዝ.326፤ዘፍ.27፤ ሮሜ 811)፡፡

በመሆኑም ከጊዜ በኋላ ሥጋችንን በመዋሐድ ሰው ሆኖ ተወለደ እየተባለ ያለው ፍጥረታትን በሙሉ የፈጠረ፣ ከተፈጠረው ፍጥረት አንዳች ስንኳ ያለእርሱ የተፈጠረ ምንም እንደሌለ የተነገረለት አካላዊ ቃል ማለትም ቃለ እግዚአብሔር ወልድ ነው፤

አካላዊ ቃል ከዘመን መቆጠር በፊት በመለኮታዊ ርቀትና ምልአት ከፍጡራን አእምሮ በላይ በሆነ ዕሪና፣ ዋሕድና፣ ቅድምና፣ ኩነትና ህልውና እንደ አብና እንደ መንፈስ ቅዱስ የነበረ ሲሆን፤ በሞቱ የእኛን ዕዳ ኃጢአት ተቀብሎ ከሞተ ኃጢአት ሊያድነን በአምስት ሺሕ አምስት መቶ ዓመተ ዓለም መጋቢት 29 ቀን መዋች የሆነው ሥጋችንን በማኅፀነ ማርያም ተዋሕዶ ሥጋ ሆነ፤ (ዮሐ.114)፡፡

ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ሲሆነው ታሕሣሥ 29 ቀን እንደ ትንቢቱ ቃል በዳዊት ከተማ በቤተልሔም ተወለደ፤ የምሥራቹም “ዛሬ መድኅን ክርስቶስ ተወልዶላችኋል” ተብሎ በመላእክት አንደበት ተበሠረ፤ (ሉቃ.210-12፤ ማቴ.21-11)፡፡

ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን ተዋሕዶ በተወለደ ጊዜ በቃል ርስትነት ሰው እግዚአብሔር ሆነ፤ በሥጋ ርስትነት አካላዊ ቃል ሰው ሆነ፤ ዕፁብ ድንቅ የሆነ ይህንን ተዋሕዶ የተመለከቱ የሰማይ ሠራዊትም አካለ ሰብእን በተዋሕዶተ ቃል ለአምላካዊ ክብር ላበቃ ለእርሱ “ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን፤ ሰላምም በምድር ይሁን፤ በጎ ፈቃዱም ለሰው ይሁን” ብለው በደስታ ዘመሩ (ሉቃ.213-15)

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

LIDETEKRISTOS

እግዚአብሔር አምላክ ለሰው ልጅ ያደረገው በጎ ፈቃድ፣ በሰማይም ሆነ በምድር ላሉ ፍጥረታት ለማንም ያልተደረገ ነው፤ (ዕብ.11-14)፡፡

ምንም እንኳ ፍጥረታትን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብና የሚጠብቅ እርሱ ብቻ መሆኑ ቢታወቅም፣ አካሉን አካል አድርጎ በተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ያደረገው፣ በመንበረ መለኮት ያስቀመጠውና የሰማይና የምድር ገዢ ያደረገው ግን ከሰው በቀር ከፍጡር ወገን ሌላ ማንም የለም፤ (መዝ.84-6፤ዕብ 216፤ ኢሳ.96-7)፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች አብያተ ክርስቲያናት በተለየ ሁኔታ በስሟ ላይ “ተዋሕዶ” የሚለውን ቃል መጠቀሟ የድኅነታችን መሠረት፤ የቃልና ሥጋ ተዋሕዶ መሆኑን ለማሳየት ነው፤

ምክንያቱም ቃል ሥጋን ካልተዋሐደ አይሞትምና፤ ቃል በሥጋ ካልሞተ ደግሞ እኛ ከሞትና ከኃጢአት ዕዳ ነጻ መሆን አንችልምና ነው፤

የአምላክ ሰው ሆኖ መወለድ ለሰው ልጅ ያስገኘለት ክብር እስከዚህ ድረስ መሆኑን መገንዘብና ማወቅ ለሰው ልጅ በጣም አስፈላጊ ነው፤

ክርስቶስ የተዋሐደው ሥጋችን ዛሬ በመለኮት ዙፋን ተቀምጦ ዓለምን ማለትም ሰማያውያኑንና ምድራውያኑን በአጠቃላይ እየገዛ ይገኛል፤ (ዕብ. 25-8)፡፡

ይህ ታላቅና ግሩም ምሥጢር የተከናወነው በሰው ብልሃትና ጥበብ ሳይሆን በእግዚአብሔር ፍቅር ብቻ የተፈጸመ አስደናቂ ጸጋ ነው፤

በዚህ ፍጹም የተዋሕዶ ፍቅር ሰማያውያኑና ምድራውያኑ እውነተኛውን ሰላም ማለትም በጌታችን ልደት የአምላክና የሰው ውሕደት እውን ሆኖ ስላዩ “ሰላም በምድር ሆነ” አሉ፡፡ ሰማያውያኑ ፍጡራን ዛሬም ያለ ማቋረጥ ሰው ለሆነ አምላክ ይህንን የሰላም መዝሙር ይዘምራሉ፤ እኛ ምድራውያኑም የዘወትር መዝሙራችን “ሰላም በምድር ይሁን” የሚለው ሊሆን ይገባል፡፡

ምክንያቱም በሰላም ውስጥ ሃይማኖትን መስበክና ማስፋፋት አለ፤ በሰላም ውስጥ ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና አለ፤ በሰላም ውስጥ መቻቻል፣ መከባበርና መተማመን አለ፤ ሰላም ውስጥ መደማመጥና መግባባት አለ፡፡

ስለሆነም በልደተ ክርስቶስ ከተዘመረው መዝሙር የሰማነው ዓቢይ መልእክት “ሰላም በምድር ይሁን” የሚለው ነውና ከሁሉ በላይ ለእርስ በርስ መፋቀርና ለሰላም መጠበቅ ቅድሚያ መስጠት የዘወትር ግዳጃችን ሊሆን ይገባል፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት፤

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደቱን ያደረገው በትሑታኑ መኖሪያ ማለትም በእንስሳቱ በረትና በእረኞቹ ሠፈር እንደነበር ልናስታውስ ይገባል (ማቴ. 1029-31)

ስለሆነም የእርሱ ደቀመ መዛሙርት የሆን እኛም ከልደቱ መልእክት ትምህርትን ወስደን በዚህ ቀን በጤና፣ በዕውቀት፣ በሀብትና በልዩ ልዩ ምክንያት አካላዊ፣ ሥነ ልቡናዊ መንፈሳዊ ድኽነት ከተጫናቸው ወገኖች ጋር አብረን በመዋል፣ አብረን በመመገብና እነርሱን ዘመድ በማድረግ በዓሉን ልናከብር ይገባል፤ (ማቴ.2540)፡፡

በመጨረሻም፤

ልደተ ክርስቶስ መለያየትንና ጥላቻን ያስወገደ፤ በምትኩ እግዚአብሔርንና ሰውን በማዋሐድ ለሰው ልጅ አዲስ የድኅነት ምዕራፍን የከፈተ እንደሆነ ሁሉ፣ እኛ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያትም ድህነትን በአጠቃላይ ለመቀነስ የጀመርነው አዲስ የልማትና የዕድገት መርሐ ግብር ከግብ ለማድረስ አሁንም ሌት ተቀን ጠንክረን በመሥራት ሀገራችንን በልማት እንድናሳድግ አባታዊ መልእክታችንን እናስተላልፋለን፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝባችንን ይባርክ፤ይቀድስ፡፡ አሜን!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ

ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክኩስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ታኅሣሥ 29 ቀን 2007 ..

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

ምንጭ

እነሆ የጌታ ልደት ደረሰ

መስጠት

ከታምራት ፍሰሃ

እነሆ የጌታ ልደት ደረሰ ፡ የጭፈራ ጊዜም ደረሰ ፡ የዳንስና የእስክስታ የመጠጥና የዝሙት ጊዜም ደረሰ። ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የጌታዋን ልደት ድምጿን ከፍ አድርጋ ታውጃለች ፤ የዚህ አለም ገዢ ዲያቢሎስ ደግሞ ይህን ቅዱስ ጥሪ ማንም እንዳይሰማው ይህን አለም በልዩ ጩኸት በክሎታል ፤ ጭኸቱንም በሚዲያዎች በኩል ያደርጋል። “እንኳን ለጌታ ልደት አደረሳችሁ” ይሉናል። ቀጠል አድርገውም “እዚህ ክለብ ብትሄዱ ለገና ልዩ ዝግጅት ተዘጋጅቷል ፡ ጭፈራው ዘፈኑ ሌላ ነው ፡ መጠጡ ምግቡ ልዩ ነው ፡ ሆይታው ሞቅታው ልዩ ነው ፡ ኑ ና ጌታችሁን እያሳዘናችሁ የዲያቢሎስን ፈቃድ ፈፅሙ” ሲሉ በጥበብ እንሰማቸዋለን፤ በጌታችን ልደት ሰይጣን የሚከብርበት ፡ በክርስቲያኖች ልደት ዲያቢሎስ የሚደምቅበት ፡ በመድሃኒት ክርስቶስ መገለጥ ፡ የዚህ አለም ገዢ ሃሳዊው መሲህ የሚታይበት ይህ ዘመን እንደምን ክፉ ነው?

እነሆ የጌታ ልደት ደረሰ ፡ ቡና ቤቶችም ሰውን ለማስከር ተዘጋጁ። ዘማውያንም አይኖቻቸውን ተኳሉ ፡ ዘፋኞችም ፡ ዳንሰኞችም ፡ አጃቢዎችም ሁሉ ቀኗን በናፍቆት ጠበቋት ፡ ሚድያዎችም ዘፈን ሊጋብዙ ዝግጅታቸውን ጨረሱ፤ ጌታችንስ በዚህ ጨለማ ላይ ብርሃኑን ሊያበራ ተገለጠ። ዲያቢሎስ ግን ከእንስሳ በላይ ሊሆን የተጠራውን ክቡር ሰው ከብርሃኑ ይልቅ ጨለማውን መርጦ ለጨለማው እንዲተባበር ሊያደርገው ይጥራል ፤ እንግዲህ የዚህ አለም ገዥ ባለሟሎች ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ ምን ህብረት አላቸው? የዲያቢሎስ ተልእኮ አስፈፃሚወች ከጌታችን ከክርስቶስ ጋር ምን ህብረት አላቸው? በጌታ ቀን ጌታ እንዲያዝን ያደርጉታል። በክርስቲያኖች ቀን ክርስቲያኖችን ያስከፋሉ ፡ ለአለም በሚያበራው በእውነተኛ ብርሃን ምትክ የዚህን አለም ጨለማ ብርሃን አድርገው አድምቀው በሁሉ ፊት ያጎሉታል ፡፡ ለዚህ ደግሞ ከሚዲያዎች የበለጠ ታላቅ መሳሪያ ዲያቢሎስ አላገኘም፡፡

ነገር ግን በጌታ ቀን ጌታ የሚወደውን ቢያደርጉ እንደምን በጎ ነበር? ድሆችን ቢያስቡ ፡ የተራቡትን ቢያበሉ ፡ በጎወችን ቢያነቃቁ እንደምን በጎ ነበር? ድሆች እንዲረዱ ህዝቡን ሁሉ ቢያስተባብሩ ፡ የጎዳና ልጆች ምሳ እንዲያገኙ ቢደክሙ ፡ በየመንደሩ ያሉ ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች እንዴት ድሃን እየረዱ እንዳሉ ቢያሳዩ ፡ የታክሲ ሹፌሮች ተባብረው ጤፍ ፡ ስንዴ ፡ ስኳር ወዘተ እየገዙ ለድሃ እንደሚያከፋፍሉ ቢዘግቡ ፡ የሰፈር ወጣቶች ህብረት ፈጥረው ከጥቂት ገቢያቸው ላይ እየቀነሱ በየወሩ የተቸገሩትን እንደሚረዱ ቢናገሩ እንዴት መልካም ነበር? ለአድራጊወቹ አነቃቂ ፡ ለሚሰሙትም በጎ አርአያ በሆነ ነበር ፡ ዲያቢሎስም ባዘነ ፡ ክርስቶስም ደስ በተሰኝ ነበር ፡ ገናም ይህ ነበር ፡ የጌታም መምጣት ስለዚህ በጎነት ነበር፡፡ ነገር ግን በክርስቲያኖች ቀን ክርስቲያኖችን ያሳዝናሉ ፡ አንድም ክርስቲያኖችን አለማዊ ለማድረግ ይደክማሉ፡፡

እነሆ የጌታ ልደት ደረሰ ፡ አለም ግን ይህን እንዳታይ አይኗ ታውሯልና በጨለማው ዲያቢሎስ ልታጌጥ ትዘጋጃለች፡፡

እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፡፡

ለቆንጆዎቹ ምስሎች ታላቅ ምስጋና ለ አርቲስት አለማየሁ ብዙነህ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: