Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2023
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘የኢትዮጵያ አምላክ’

ኃይለኛ አዎሎ ነፋስ | “ኃያሏ” አሜሪካ ኢትዮጵያን ታምሳለች፤ ኃያሉ እግዚአብሔር አሜሪካን ያስጠነቅቃል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 30, 2019

ቃጠሎ በአውሮፓ፣ ድርቅ በአረቢያ፣ አውሎ ነፋስ በአሜሪካእራሳቸው የመረጧቸውን የኢትዮጵያ ቀለማት ተመልከቱ

ብዙ ሚሊየን አሜሪካውያን በሚቀጥሉት ቀናት ፍሎሪዳ ዙሪያ ባሉት ግዛቶች ከዚህ በፊት ያልገጠማቸውንና “ዶሪያን” የተባለ ቅጽል ስም የተሰጠውን ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተሸብረው በመጠባበቅ ላይ ናቸው። ፕሬዚደንት ዶላንድ ትራምፕ፦ “ኃይለኛ አውሎ ንፋስ እየመጣብን ነውና ተዘጋጁ፣ እነዘጋጅ!” በማለት ዜጎችን አስጠንቅቀዋል። እነዚህ አዎል ነፋሶች አሜሪካውያንን በየጊዜው ስለሚያሸብሩ፡ የአውሎ ነፋሶቹን ሰፌድ በኑክሌር ቦንብ ለመምታት እስከ ማሰብ ድረስ ፕሬዚደንት ትራምፕ ደርሰዋል።

ለነዋሪዎቹ ሰላሙን ያምጣላቸው፤ ግን ከእናንተ የበለጠ የኃያሎች ኃያል አለ፡ የሚነፍሰውን እስትንፋሱን አትችሉትምና ኢትዮጵያን ባትነኳት ይሻላችኋል!!!

______________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሊበሏት ያሰቧትን ቆቅ፡ ዥግራ (ዶሮ) ነች ይሏታል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2011

የሚገርም ነው፡ ይህን ጽሑፍ ልክ ስጨርስ፡ ፎቶው ላይ ያለው ክቡር ሰንደቅ ዓላማ ከፊቴ ተደቅኖ ይታየኝ ነበር…

መብራት ከብትማ የተባለች እህታችን ባለፈው ሣምንት ላይ በቤይሩት፡ ሊባኖስ ሕይወቷን አጥታለች። ገዳዮቹ: የመብራትን አንገት ብዙ ጊዜ በጭካኔ  ደጋግመው በመውጋት ነበር ለዚህ ሰይጣናዊ ተግባር የበቁት(እግዚአብሔር ነፍሷን ይማርላት!)

እንደ ሌባኖስ፡ ሳውዲ ዓረቢያ፡ ዱባይ እና የመሳሰሉት የአረብ አገሮች የሚገኙት እህቶቻችን በመንፈሳቸው፡ በነፍሳቸውና በአካላቸው ላይ አሰቃቂ የሆነ ጥቃት ያለማቋረጥ እየደረሰባቸው ነው።

በሰሜናዊው አፍሪቃ በኩል የመካከለኛውን ባሕር ተሻግረው በመሄድ የተሻለኑሮ በአውሮፓ ለማየት የሚሹት፡ በግብጽ በኩል የሲናይ በረሃን በማቋረጥ ነፃነትን በእስራኤል ለመቅመስ የሚመኙት ወገኖቻችን ሁሉ የባሕር ሞገዶች ላይ ጠውልገው እንዲቀሩ፡ በየበረሃው ለጨካኝ የአረብ ድንበር ጠባቂዎች የተኩስ መለማመጃ ለመሆን እየበቁ ነው።

ለዚህ ሁሉ አሳፋሪ ሁኔታ በመጀመሪያ ደረጃ ተጠያቂዎች የምንሆነው እኛው ኢትዮጵያውያን ነን። ማንነታችንን አጠንቅቀን ለማወቅ ባለመቻላችን ወይም እንዳንችል ለጠላት በራችንን በመክፈታችን፡ ከፈጣሪያችን ያገኘነውን ውድ ስጦታ በምስጋና ተቀብለን በሥራ ላይ ለማዋል አልፈቀድንምና። እራሳችንንም እየተንከባከብን እስከመጨረሻው ለመጽናት ዝግጁ በመሆን የጠላቶቻችንን ትሪክ ለማጥናት ስለሰነፍን፡ የደንቆሮውና የእውሩ፡ የተንኮለኛውና የጨካኙ ኃይል ሁላ መጫወቻዎች ሆነናል፡ ለዲያብሎስ ጥቃት በቀላሉ ለመጋለጥ በቅተናል።

ሆኖም ፈጣሪያችን አዛኝ፡ ቸር እና መሐሪ ነው፡ ለንስሐም የሚያበቃን አንድ አምላክ ነው፡፡ ስለሆነም፡ በተለይ በውጩ ዓለም በምንገኘው ኢትዮጵያውያን አማካይነት፡ በየቦታው በሚጠነሰሱት ሰይጣናዊ ሤራዎች ላይ ፍልሚያውን እንድንያያዝ ጥሪውን አቅርቦልናል። በዚህም፡ ቀደም ሲል ከፈጸምናቸው ስህቶቻችን እየተማርን ከበደሎቻችን ሁሉ ነፃ እንድንወጣ ሌላ ትልቅ እድል ሰጥቶናል።

አገራችንን በመልቀቅ በመላው ዓለም ለመበታተን የተገደድንበት ምክኒያት እንደምናስበውና እንደምንመኘው ዓለማዊ የሆኑ ፍላጎቶቻችንን ለማሟላት፡ ወይም እኔ እበልጣለሁ/እሻላላሁ፡ አንተ ታንሳለህ/አትሻለም እየተባባልን የኩራት ደም ሥራችንን ለመወጠር ሳይሆን፥ ለዓለሙ ሁሉ መፈራጃ ለመሆን እንድንበቃ፥ በአባቶቻችንና እናቶቻችን፡ በወንድሞቻችንና እህቶቻችን ላይ የተጋረደውን የሰይጣን ግድብ ከውጭ ሆነን ለመቦርቦር ብሎም ለማፍረስ እንችል ዘንድ እውቀቱንና መረጃውን የመሰብሰብ ዕድሉ እንዲኖረን ነው። ይህን ዕድል ያልተጠቀመ፡ ተረገመ!

የሊቢያው ጦርነት፡ በየዜና ማሰራጫው ሁሉ እንደሚወራው፡ የነዳጅ ዘይትን ወይም የተቀናጣውን የኮሎኔል ጋዳፊ መንግሥትን የተመለከት መስሎ ሊታየን ይችል ይሆናል፡ ነገር ግን ይህ እንደ አንድ ሰበብ እንጂ እንደ ዋና ምክኒያት ተደርጎ መወሰድ የለበትም። የዚህ ጦርነት ዓላማ ሌሎች ብዙ የተወሳሰቡ ነገሮችን ያካተተ ነውና።

እግዚአብሔር አምላካችን፤ በልጆቼ ላይ በደል የሚፈጽሙ ሰዎች፡ ዕምነት የሌላቸው ወይም እግዚአብሔርን ያልተቀበሉት ኃይሎች ለጥፋት ይላኩባቸዋልብሎ እንዳስተማረን፡ ኮሎኔል ጋዳፊ እና ከርሱ ጋር ለዘመናት አብረው ሲንደላቀቁ የቆዩት ሊቢያውያንም ለዚህ ክፉ ጊዜ በመድረስ፡ ጨነቀኝ ጠበበኝለማለት የበቁት፡ በተለይ፡ ኮሎኔሉ በክርስቲያኖች አምላክና በመንፈስ ቅዱስ ላይ ደግሞ ደጋግሞ ትዕቢት የተሞላባቸውን ስድቦች ለመሠንዘር በመቃጣቱ፡ እንዲሁም የሊቢያው ሕብረተሰብ፡ በተለይ በሃገረ ኢትዮጵያ እና በኢትዮጵያ ስደተኞች ላይ ለዘመናት ሲፈጽመው ከነበረው ዲያብሎሳዊ አድራጎቱ የተነሳ ነው።

የኢትዮጵያና እስራኤል ግኑኝነት እንዲሻክርና ቀዳማዊ ኃይለሥላሴም እ... 1973 .ም ከእስራኤል እንዲርቁና ወደ አረቦች ጠጋ ጠጋ በማለት የመውደቂያ ጉድጓዳቸውን ለመቆፈር የበቁት የጋዳፊዋ ሊቢያ በ አፍሪቃ አንድነት ድርጅት በኩል ኢትዮጵያ ፀረእስራኤል የሆነ አቋም እንድትይዝ በርሷ ላይ ተጽእኖ ለማድረግ በመቻሏ ነበር። ልክ ከዚህ ጊዜ በኋላ ነበር በአገራችን ላይ ያ ሁሉ ታሪክ የማይረሳው መዓት ሊደርስባት የቻለው።

ከጥቂት ዓመታት በፊት ከአውሮፓውያን መሪዎች (ቶኒ ብሌር፡ ኒኮላስ ሳርኮዚ፡ ሲሊቪዮ ቤርሉስኮኒ) ጋር ጥብቅ ግኑኝነት መሥርቶ የነበረው እባቡ ጋዳፊ፡ ከኢትዮጵያ፡ ከኢርትራ ወይም ከሶማሊያ የሚመጡትን ስደተኞች በሊቢያው የሳሓራ በርሃ አፍኖ ለመያዝ እና አውሮፓን ከጥቁር ሕዝቦች ለመከላከል እንድትችሉ ለመርዳት ዝግጁ ነኝበማለት ፈቃደኝነቱን አሳየ፡ ለዚህም ተልዕኮው በቢሊየን ዩሮ የሚቆጠር የገንዘብ ስጦታ ከአውሮፓው አንድነት ሊሰጠው እንደሚገባው ገለጠ።

... 1988 .. በስኮትላንዷ ሎከርቢ ላይ የአሜሪካን አየር መንገድ በማፈንዳት270 መንገደኞች ሕይወት ማጣት ተጠየቂ የነበረውና በስኮትላንድ ፍርድ ቤት የዕድሜ ልክ እስራት ፍርድ የተሰጠው ሊቢያዊ የጋዳፊ የግድያ ወኪል፡ አብደልባሰት አልመግራሂ፡ ከ 8 ዓመት እስራት በኋላ እ... 2009 .. ከስኮትላንድ እሥር ቤት ወጥቶ ወደ ሊቢያ እንዲመለስ ተደርጓል። ይህ ሊቢያዊ ገዳይ የነቀርሳ በሽታ አለበት፡ ለመኖርም በጣም ጥቂት ቀናት ነው የቀሩትበሚል ሳቢያ ከእሥር ቤት እንዲወጣ ቢደረገም፡ በተለይ ከአሜሪካ በኩል ትልቅ ተቃውሞ መቅረቡ የሚታወስ ነው። ይህ ገዳይ እንደተባለው በጥቂት ቀናት አልሞተም፡ ያው እስካሁን በሕይወት እንዳለ ይነገራል።

ነገር ግን አንድ መጠየቅ የሚኖርብን ነገር፡ የሊቢያው ጦርነት በእውነት ከዓመታት በፊት ታቅዶ የቆየ ጦርነት ከሆነ የዚህ ሊቢያዊ ገዳይ ሚና ምን ይመስል ይሆን? እንደ አንድ የ ማንቹሪያ እጩየሮቦት ዓይነት ሥራ ተሰጥቶት፡ የጋዳፊን ዓለም ለመሰለል እና ለመጭው የሊቢያ ወረራ በእንግሊዛውያኑ ተዘጋጅቶ የተላከ ሰው ይሆን?

በመካከለኛው ባሕር ላይ የጦር መርከቦች እንቅስቃሴ፡ ገና ኖቬምበር 2010 ላይ ነው መታየት የጀመረው። በያዝነው ዓመት መግቢያ ላይ፡ መጀመሪያ በቱኒዚያ፡ ከዚያም በግብጽ የታየው የሕዝቦች እንቅስቃሴ፡ ምናልባት ሆን ተብሎ በውጭ ኃይሎች የተዘጋጀ፡ በተለይ በሁለቱ አገሮች መካከል በምትገኘው ሊቢያ ላይ ዋና ትኩረት ያደረገ እንቅስቃሴ መሆኑ አሁን አያጠራጥርም፡ ለዚህም በሊቢያ ላይ በ ፈረንጅ ሕዝቦች ክበብበሆነው በNATO መሪነት እየተካሄደ ያለው የውትድርና ጥቃት ያሳየናል።

መቼም የፈረንጁ ዓለም የኢትዮጵያንና የአፍሪቃን ስም መጥፎና አስቀያሚ ከሆኑ ድርጊቶች ጋር በማያያዝ ብቻ መጥራቱን እንደሚወዱ አሁን ሁላችንም እናውቃለን። የአፍሪቃው አንድነትም በግርግሩ ምንም ሚና እንዳይጫወት፡ “ለምንም የማይበቃ ድርጅት ነው” በሚል፡ ስም አጥፊ የሆነ አሮጌ ፕሮፓጋንዳ የዓለምን ማሕበረሰብ ለማታለል እየሞከሩ ነው። 

ሊበሏት ያሰቧትን ቆቅ፡ ዥግራ(ዶሮ)ነች ይሏታልእንዲሉ፡ የፈረንጁ ዓለም፡ በወዳጅ ጠላቱ፡ በኮሎኔል ጋዳፊ ላይ ጥቃት ከጀመረበት ዕለት አንስቶ፡ ጋዳፊ በጥቁር አፍሪቃውያን ቅጥረኞች ይደገፋልሲባል ነበር። እነ ቢቢሲና አልጀዚራም ለምንድን ነው አፍሪቃውያን ብቻ ኮሎኔል ጋዳፊን የሚደግፉት?” የሚሉ የፈጠራ ወሬዎችን በመንዛት፡ በጋዳፊ ላይ ተቃውሞ የነበራቸው ሊቢያውያን ጥቁር በሆኑ አፍሪቃውያን ላይ የጥላቻ መርዝ እንዲረጩ ተደረገ። ከዚያ፡ ነፃ አውጪዎች ተብለው በቢንጋዚ ከተማ መሠረት የያዙት ተዋጊዎች (ግማሹ የአልቄይዳ ወኪል ነው) በጥቁር ሰዎች ላይ (በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጭምር) ጥቃት እንዲፈጽሙ ተደረገ፥ አሁን የጋዳፊ ቅጥረኞችበሚል መጠሪያ ስማቸው የጠፋው እነዚህ ጥቁር ስደተኞች ባካባቢው በሚገኙት ቱኒዚያና ግብጽ በኩል አልፈው በጀልባ ወደ አውሮፓ ለማለፍ እንዳይችሉ በቱኒዚያናውያንና ግብጻውያን ተመነጠሩ፡ ተለይተው በአንድ ላይ እንዲሰበሰቡ ተደረጉ። (በየበረሃው ወድቆ ለሞት የበቃው ቁጥር ምን ያህል እንደሆነ እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያውቀው)

እንደምንም ብለው ቱኒዚያና ግብጽ የደረሱት ከዚያም ለአውሮፓ የጀልባ ጉዞ የበቁት ወገኖቻችን ደግሞ ልዩየሆነ ጀልባ እየተመደበላቸው የአሣ ነባሪ ቀለብ እንዲሆኑ ተደርገዋል።

ይህን እጅግ የሚያሳዝንና የሚያስቆጣ ተግባር በ21ኛው ምዕተ ዓመት ዓይናችን እያየ፡ ጆሮአችን እየሰማ ዕለት ተዕለት ይከሰታል።

እስቲ እግዚአብሔር ይይላቸው፡ በጣሊያን ደሴቶች በኩሉ አሁን በመላው አውሮፓ እንዲሠፍሩ የተደረጉት ከ 30 እስከ 50 ሺህ የሚጠጉ ስደተኞች ከቱኒዚያ ያመለጡ አረቦች ናቸው። (ከዚህም ግማሹ የአልቄይዳ ወኪል እንደሆነ ይነገራል)

በሌላ በኩል ግን፡ ኢትዮጵያውያኑና ኤርትራውያኑ የበሰበሰ ጀልባ ላይ እየተመነጠሩ ተለይተው እንዲወጡ ከተደረጉ በኋላ ተቀባይ አጥተው በኢንዱስትሪ ቆሻሻ በተበከለው በመካከለኛው ባሕር ወስጥ ለሚገኙት ዓሣዎች ምግብ ለመሆን ይበቃሉ።

ከሃያ ዓመታት በፊት በቀድሞው የደርግ መንግሥት ሰራዊቶች እና በተቃዋሚ ኃይሎች መካከል አባይ ወንዝ አካባቢ ከፍተኛ ዕልቂት የጠየቀ ጦርነት መካሄዱን በወቅቱ ባካባቢው ከነበሩት ወገኖች ለመረዳት ችየ ነበር። እኔን በጣም ያሳዘነኝ፡ የረበሸኝ፡ የዘገነነኝ እና ያናደደኝ፤ የወገኖቻችንን ሬሳ ወደ አባይ ወንዝ እየተጣለ የወንዙ ቀለም በደም ቀይ ሆኖ ባካባቢው የነበሩት እናቶች፡ እህቶችና ሕፃናት ለሣምንታት ያህል ዋይዋይዋይ!” እያሉ ሃዘናቸውን በጩኸት ሲገልጹ የነበረበት ሁኔታ ነው። ይሄም ሁኔታ ፊቴ ላይ እንደ አንድ መሳጭ የፊልም ስዕል እስካሁን ድረስ ይታየኛል።

የተባረከው የወንዛችን ውሃ፡ በብዙ ውድ ማዕድናት የተካነውን አፈራችንን ይዞ በመጓዝ የጠላቶቻችንን መቅኒ ለዘመናት ማዳበሩ እንዳይበቃ፡ አሁን ደግሞ ይህ ውሃ በኢትዮጵያውያን ደም ተቀምሞ እንዲፈስስላቸው እናደርጋለን!

ዓየር መንገዳችን መካከለኛው ባሕር ላይ እንዲወድቅ ይደረጋል፡ እናት ዓባያችን መሬታችንን እየሸረሸረ ወስዶ የተበከለውን የመካከለኛውን ባሕር ውሃ ይቀልባል፡ ይህ አልበቃም ስላለ ደግሞ በረሃ ለበረሃ ተንከራትተን በስቃይና በመከራ ወደዚያው ተጉዘን ከደረስን በኋላ፡ ትኩስ ሥጋችንን፡ ንጹሕ ደማችንን በነጭ ሳሕን ለባሕሩ መናፍስት እንኩ ብለን በቦታው እናቀርብላቸዋለን።

በቅርቡ ከሊቢያ ወደ ጣልያን ለመግባት ከቻሉት ጥቂት ኢትዮጵያውያን (ኤርትራውያን) መካከል TIME magazine ካቀረበው ዘገባ የተወሰደ ጥቅስ፡

Desperate Tsegay: “Whatever abuse a normal person gets, you get twice as much if you’re Christian”

Pregnant Helen: “We’re so happy, it’s like we’ve been born for the second time.”

Sensational TIME: “Italy should listen to its better angels.


ቅኑ እና ንቁ መንፈስ ይስጠን!

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: