Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የኢትዮጵያ ቀጥተኛ ተዋሕዶ እምነት’

ኪዳነ ምህረት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2016

ኪዳነ ምህረት ማለት የምህረት መሐላ ማለት ነው፡፡ ከ33ቱ በዓላተ እግዝእትነ ድንግል ማርያም አንዱ ነው፡፡ እመቤታችንም ከጌታችን መቃብር እየሄደች በምትለምንበት ጊዜ አይሁድ ለምቀኝነት አያርፉምና ምን ልታመጣብን ነው በማለት ሊጣሏት ሲመጡ ጌታችንም ከዓይናቸው ሰውሯታል አይሁድም ጠባቂ ቢያቆሙ እመቤታችን ዕለት ዕለት መሄዷን አላቋረጠችን እመቤታችንም እንዲህ ብላ ስትጸልይ ልጄ ወዳጄ ሆይ ከስጋዬ ስጋ ከነፍሴ ነፍስ ነስተህ ሰው በመሆንህ ዘጠኝ ወር ከ5 ቀን በቻለችህ ማሕጸኔ ከአንተ ጋር ሀገር ለሀገር ስለ መሰደዴ መትተህ ልምናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ አለች በዚህ ጊዜ ንውጽውጽውታ ሆነ መቃብራት ተሰነጣጠቀ ጌታችንም እልፍ ከእልፍ መላዕክቱ ጋር መጥቶ ሰላም ለኪ ማርያም ምን እንዳደርግልሽ ትለሚኚኛለሽ አላት፡፡ እርሷም መታሰቢያዬን ያደረገውን ስለ ስሜ ለችግረኛ የሚራራውን በስሜ ቤተ ክርስቲያን ያነጻውን መባዕ የሰጠውን ከሃይማኖት ከፍቅር ጽናት ልጁን በስሜ የጠራውን ሁሉ ማርልኝ ከሞተ ስጋ ከሞተ ነፍስ አድንልኝ አለችው፡፡ ጌታችንም ይህን ሁለ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበ አቡየ ሕያው ወበመንፈስ ቅዱስ ብሎ ቃል ገብቶላት አርጓል፡፡

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | 1 Comment »

ተዋናይ ንብረት ገላው፡ “አዲስ ኢየሱስ የለም”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 14, 2015

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

ብሩክ ቡሄ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 19, 2015

ደብረ ታቦርና ቡሄ

 

በ መ/ር ሳሙኤል ተስፋዬ

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከምታከብራቸው ዘጠኝ ዓበይት በዓላት አንዱ የደብረ ታቦር በዓል ነው። በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን የሚከበረው ይህ በዓል መሠረቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ደብረ ታቦር ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ፀሐይ የበራበት፣ ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት፣ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።

ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።

ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና፡ ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ማቴ. ፲፯፡፩፭ በቤተ ክርስቲያን ደብረታቦር ከቤተክርስቲያን ውጭ አከባበሩ ቡሄ እየተባለ የሚከበረው በዓል በሀገራችን በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል፡፡ ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚዘለቅበት ወገግታ ፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመሆኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ በዚህ መሰረት የክረምቱ አፈና ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየውም በዚህ በዓል አካባቢ ስለሆነ ይቺ ዕለት ቡሄየሚለውን ስያሜ አገኘ። ቡሄ ማለት ገላጣ፣ የተገለጠ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብረሃን የታየበት ድምጸ መለኮት የተሰማበት ስለሆነ፤ ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓልም ይባላል፡፡

በገጠርም ሆነ በየከተማው ልጆች ጅራፋቸውን ገምደው ሲያጮሁ ይሰነብታሉ። እናቶችም ለበዓሉ ዝግጅት ስንዴ ሲለቅሙ፣ ሲፈትጉ፣ ሲፈጩ ይሰነብታሉ። መነሻ የሆናቸው ትውፊት ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ዕለት ጊዜው ምሽት ነበር፡፡ እረኞችም ከብርሃኑ የተነሣ እየተገረሙና እየተደነቁ ወደ ቤት አልተመለሱም ነበር፡፡ የልጆቹን መዘግየት ያዩ ወላጆች ችቦ አብርተውና ዳቦ ይዘው ፍለጋ ወጥተዋል ፡፡ያንን ለማስታወስ «ቡሄ» ለሚሉ ልጆች ሙልሙል ዳቦ የሚሰጠውና ችቦ በማብራት በዓሉን የሚከበረው ከዚህ በመነሣት ነው፡፡ የንጋት ወጋገን ሲፈናጠቅ ልጆች በከባድ ድምጽና በጅራፍ ጩኸት የሚታጀብ፣ በገደላገደል ስር እንዲያስተጋባ ተደርጎ ብዛት ባላቸው ህጻናት በከፍተኛ ድምጽ የሚዘመር ነው ቡሄ ። የጅራፉ ጩኸትም እግዚአብሔር አብ “€œየምወደው ልጄ ይህ ነው እርሱን ስሙት”€ ሲል ሐዋርያት ራሳቸውን ስተው የወደቁበትን የመለኮት ድምፅ ለማስታወስ ነው፡፡

ደብረታቦር ወይም ቡሄ በአብነት ተማሪዎች ስለ ደብረ ታቦርእያሉ እህል፣ ፣ ጌሾ ለምነው ጠላውን ጠምቀው፣ ዳቦውን ጋግረው፣ ቆሎውን ቆልተው ለደብረ ታቦር ዕለት ሊያስቀድሱ የመጡትን ምዕመናን በመጋበዝ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡ ይህ ትውፊት መምህረ ሐዋርያት የነበረው ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስቱን ተማሪዎቹን ጴጥሮስን፣ ያዕቆብንና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ደብረ ታቦር ይዞ ሄዶ የተገለጠ ምስጢር ስለሆነ ከመምህራቸው ጋር በመሆን በዓለ ደብረ ታቦርን /ቡሄን ያከብራሉ፡፡ ስሙን ይጠራሉ፡፡

የደብረ ታቦር ወይም የቡሄ ግጥም

ድምጽህን ሰማና

በብሩህ ደመና

የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣና

ያዕቆብ ዮሐንስ ሆ! እንዲሁም ጴጥሮስ

አምላክን አዩት ሆ! ሙሴ ኤልያስ

አባቱም አለ ሆ! ልጄን ስሙት

ቃሌ ነውና ሆ! የወለድኩት

ድምጽህን ሰማና

በብሩህ ደመና

የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣና።

መጣና መጣና ደጅ ልንጥና

መጣና ባመቱ እንዴት ሰነበቱ፣

ክፈት በለዉ በሩን የጌታዪን

ክፈት በለዉ ተነሳ ያንን አንበሳ፣

ምንጭ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | 2 Comments »

በስልጤ ዞን ክርስቲያኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው፤ ‹‹ወረዳው ሊቢያ ኾኖብናል፤ ለእኛም አልቅሱልን›› እያሉ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 13, 2015


ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ተመርረው እና ተሠቃይተው ወረዳውን እንዲለቁ ከሥራ ማባረርን ጨምሮ እስራት፣ ያለበቂ ምክንያት የደመወዝ ቅጣት፣ ያልተገባ የሥራ ምደባ እና ዝውውር እንዲኹም ‹‹እናርዳችኋለን›› በሚል የግድያ ዛቻ ይደረግባቸዋል፤

የሚያስቀድሱበት እና የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ያገኙት በብዙ ውጣ ውረድ ነው፤ የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንን ለመሥራት በኮሚቴ የተሰባሰቡ ምእመናን በአንድነት ባሉበት ቤት በምሽት ቤንዚን በማርከፍከፍ እሳት ተለቆባቸዋል፤

እየተሠራ ባለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ላይ ‹‹ጉልላት ለምን አስቀመጣችኹ›› ሦስት ጊዜ የማቃጠል ሙከራ ተደርጓል በዞኑ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ የሚወቀሱት የወረዳው አስተዳደርና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጉዳዩን በውይይት ስም እያድበሰበሱ ክርስቲያኖችን በማይመለከታቸው ጉዳይ በደመወዝ ከመቅጣት፣ ከሥራ ከማባረር እና ከመኖርያቸው ከማሳደድ ውጭ መፍትሔ ሰጭ የእርምት ርምጃ እየወሰዱ አይደለም፤

የሚደርስባቸውን በደል ለዞኑ ያሳወቁ እና በጠንካራ ሠራተኝነታቸው ከዐይን ያውጣችኹ የተባሉ የወረዳው ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች ‹‹አስወቅሳችኹን›› ባሉ የወረዳው አስተዳደር እና የድርጅት ጉዳይ ሓላፊዎች፥ ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ተባርረዋል፤ የትምህርት ዝግጅታቸውን እና የሞያ ልምዳቸውን በማይመጥን ቦታ በማዛወር ሞራላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፤ ‹‹ሀገራችኹ ሥራ ቢኖር እዚኽ አትመጡም ነበር›› በሚል ተዘብቶባቸዋል፤

በዛሬው ዕለት ለሦስተኛ ጊዜ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምስጉኑ የቂልጦ ኹለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤት መምህር የማርያም ወርቅ ተሻገር በፖሊስ ጣቢያ እንግልት እና ድብደባ እየተፈጸመበት እንዳለ ተዘግቧል፡፡ የዋስ መብቱ ተጠብቆ ሊፈታ እንደማይችልም ከወረዳው ኢንስፔክተር መገለጹን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ይህ መልእክት የደረሳችኹ ወገኖቻችን፤ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት አመራሮች እና መሥሪያ ቤቶች፣ ጋዜጠኞች፣ ለሊቢያ ወንድሞቻችን ብቻ አይደለም ለእኛም አልቅሱ፤ እነርሱ ከአገር ወጥተው ነው፤ እኛ ግን በአገራችን ከአዲስ አበባ 220 .. ርቀት ላይ ነው የምንገኘው፡፡ ፍጹም መሮናል፤ ተሠቃይተናል፤ በጭንቀት እና በስጋት ላይ ነን፤ መቼ ምን እንደምንኾን አናውቅምና ድረሱልን ! ! !

ሙሉ መልዕክቱ እዚህ ይገኛል

__

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: