Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የኢትዮጵያ ሴቶች’

ጀግኖቹ እህቶቻችን ግዙፉን አውሮፕላን በ ኖርዌይ ኦስሎ ማረፊያ እንደ ርግብ አሳረፉት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 9, 2019

ንቅንቅ የማይል ድንቅ አስተራረፍ!፤ የሴቶች ቀን የኢትዮጵያ ሴቶች ቀን ተብሎ ቢሰይም ጥሩ ነው | አዎ! ባለፈው አመት ወደ አረጀንቲና ዘንድሮ ወደ ኖርዌይ፤ ሰማዩ ገደብ ነው፤ የምታኮሩ ናችሁ እህቶች።

የዛሬውን ዕለት ምዕራባውያኑ “የሴቶች ቀን” ይሉታል። ሜዲያው ሁሉ ሊያወራለት የሚገባው ሌላ ታሪካዊ ቀን ነው። እህቶቻችን በኢትዮጲያ አየር መንገድ ሙሉ በሴቶች ብቻ የተከናወነ የበረራ ጉዞ ወደ ኖርዌይ ዋና ከተማ ወደ ኦስሎ አድርገዋል። ለአራተኛ ጊዜ መሆኑ ነው በዚህ መልክ ሲበሩ።

በሴቶች ብቻ የበረረ ዓየር መንግድ የኢትዮጵያ ብቻ ነው። ለሴቶች መብት እንቆማለን የሚሉት ምዕራባውያን እንኳን ተመሳሳይ ተግባር ፈጽመው አያውቁም፤ ኖርዌይ እራሷ አንዷ ምሳሌ ናት።

ሴቶቻችን በዚህ መልክ ሲጎብዙ ደስ ይላል፤ ያኮራል፣ እሰይ ያሰኛል፣ ሊበረታታም ይገባዋል፤ በአረብ መጋረጃ የተሸፈኑ ግብዝ አስመሳዮች ግን የመከላከያ ሚንስትርና የ ”ስላም” ሚንስትር ሲሆኑ ያንገበግባል፣ ያሳዝናል፣ የኢትዮጵያን ሕዝብ ክፉኛ ያሰድባል፣ በታሪክ ያስወቅሳል፣ መቅሰፍት ያመጣል። እስኪ በቅድሚያ ሳውዲ አረቢያ ለሚገኙት የእምነት እህቶቻቸው መኪና ማሽከርከር እንዲፈቀድላቸው ጠበቃ ይቁሙ።

____________

Posted in Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | 1 Comment »

ሳውዲ ሴቶች ወደ አውሮፓ በብዛት በመሰደድ ላይ ሲሆኑ፡ ፳ሺህ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ደግሞ እንደ ከብት ለሳውዲ ሊሸጡ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 18, 2019

ይህ ወገኖቼ ካለፈው ዘመን የከፋ ዘመናዊ ባርነት ነው

የግራኝ አህመድ መንግስት በመጭው መጋቢት ወር ብቻ ሃያ ሺ ኢትዮጵያውያን ሴቶችን ለሳውዲ አረቢያ ለመሸጥ መወሰኑን የሳውዲ ሜዲያዎች ዘግበዋል።

፳፩ ኛው ክፍለ ዘመን ወገኖቻችን ወደ እስላም ሃገራት ለሥራ የሚያደርጉት ጉዞ በ ፲፰ ኛው ክፍለዘመን ጫካ ለመመንጠር በባርነት ተገደው ወደ አሜሪካ ከተወሰዱት አፍሪቃውያን ጋር ተመሳሳይነት አለው፤ በአረብ ሃገራት የሚታየው የሥራ ባሕርይ እንዲያውም ከዚያ በጣም የከፋ ነው። ከሦስት መቶ ዓመታት በፊት እንደ አሁኑ በቂ መረጃ በሌለበት የጨለማው ዘመን የተወሰነ ቁጥር ያላቸው አፍሪቃውያን ተገደው የተወሰዱ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ ሁሉ ነገር ግልጥ ብሎ በሚታይበት ዘመን የራሳችን ሰዎችና መንግስታችን የአገሪቷን ዜጎች ለጠላት ይሸጣሉ፤ ለሰላሳ አመታት ያህል ባልተቋረጠ መልክ

ነፃ ሆነው የተፈጠሩት ኢትዮጵያውያን ለዚህ ዓይነቱ ባርነት በ ፳፩ ኛው ክፍለ ዘመን መጋለጣቸው እጅግ በጣም ነው የሚያሳዝነውና የሚረብሸው። በተለይ ለታሪካዊ ጠላቶቻቸውና ለእግዚአብሔር አምላካቸው ጠላቶች መሆኑ በይብለጥ የሚያስቆጣ ነው።

ባለሥልጣናቱ በእህቶቻችን ገንዘብ መሥራቱን ቀጠሉበት ማለት ነው፤ “በቃን!” ለማለት በቂ ጊዜ ነበራቸው። ዛሬ በዚህ ጽንፈኛ ተግባር ላይ የተሠማሩትን ባለሥልጣናት እና ተቋማት እግዚአብሔር የሚገባቸውን ፍርድ ይስጣቸው!!!

____________

Posted in Ethiopia, Life | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኃይለኛ ምስል | ጀግኖቹ እህቶቻችን በሰማይ ሲበሩ፡ የሳውዲ ሴቶች ገና መሬት ላይ ዳዴ ይላሉ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 9, 2018

የትናንትናውን ቀን ምዕራባውያኑ “የሴቶች ቀን” ይሉታል። ሜዲያው ሁሉ ሊያወራለት የሚገባው ታሪካዊ ቀን ነበር። በትናንትናው ዕለት እህቶቻችን ከኢትዮጲያ አየር መንገድ ጋር ሙሉ በሴቶች የተከናወነ ጉዞ ወደ ሩቋ አርጀንቲና አካሂደው ነበር። በዋና ከተማዋ ቡዌኖስ አይሬስ የአርጀንቲና ፕሬዚደንትና ምክትል ፕሬዚደንት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸው ነበር። እህቶቻችን ለሦስተኛ ጊዜ ነው በዚህ መልክ ሲበሩ።

በሌላ በኩል ደግሞ፡ የእህቶቻችን ጠላቶች የሆኑት ሳውዲዎች ሴቶቻቸውን ለመጀመሪያ ጊዜ መኪና እንዲነዱ በትናንትናው ዕለት ፈቀደውላቸው ነበር።

ሳውዲዎች ወደታች ቁልቁል ያያሉ፤ ገና በምድር ላይ ናቸውና!

የኢትዮጵያ ሴቶች ግን ወደሰማይ ያያሉ፤ ክንፍ አውጥተውም መብረር ይችላሉ!!!

በሴቶች ብቻ የበረረ ዓየር መንግድ የኢትዮጵያ ብቻ ነው። ለሴቶች መብት እንቆማለን የሚሉት ም ዕራባውያን እንኳን ተመሳሳይ ተግባር ፈጽመው አያውቁም።

ይህ በጣም ኃይለኛ ምስልነው፤ ብዙ ነገሮችን የሚናገርና የሚያስደንቅ የንፅፅር ምስል ነው!!!

እህቶቻችን ለእነዚህ አረቦች በፍጹም፣ በጭራሽ የበታች ሆነው መኖርና መሥራት የለባቸውም!

International Women’s Day – a comparative story of symbolic nature the Medias avoid to report on:

Ethiopian Women Fly High Ethiopian Airlines honors March 8, 2018 sends all women crew to Buenos Aires, Argentina – while Saudi Women are still crabbing their way across the desert.

This is for a 3rd time that the all female Ethiopian crew is making history.

While ‘Rich’ Anti-Christian Saudi Women Still Crawl on Earth – The Sky’s The Limit for ‘Poor’ Christian Ethiopian Women

A woman from Spain, Estefania Aguirre, did a video recently mocking “International women’s day” and said that the women marching are an embarrassment to all women:

______

 

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አዲስ አበባ | ወገኔ፡ አሳሳቢና አስደንጋጭ የሆነ ውፍረት በእህቶቻችን ላይ እየታየ ነው!!!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 23, 2017

በየአብያተክርስቲያናቱ አባቶች፦“ሴቶቻችን ውስጥ የገባው ጋኔን ይውጣልን!”

እያሉ ጸሎት ማድረስ ጀምረዋል።

ዛሬ፤ እንደገና፡ ቀኑን ሙሉ ሲያሳስበኝ የዋለ ጉዳይ ነው

ጌታዬ አምላኬ፣ ፈጣሪዬ ሆይ፡ ጠላቶችህ፡ በጥቁር አሜሪካውያን ላይ የተጠቀሙትን ዓይነት ዲያብሎሳዊ ትሪክ በየዋሆቹ እህቶቼ ላይ እየተጠቀሙ ነው፤ አባቴ ሆይ፡ አንተ ታያቸዋለህና ዝም አትበል

በጣም ብዙ የሆንት እህቶቻችን የወሊድ መከላከያውን እንደ ክረሜላ ነው የሚወስዱት፤ የሚያስጠነቅቃቸው፣ የሚመክራቸውና የሚያስተምራቸው አካል የለም፤ በጣም ነው የሚያሳዝነው።

ምግብንም በሚመለክት፤ እንደ ምሳሌ አድርጌ ቪዲዮ ውስጥ “በርገር” ቤቱን አቅርቤዋለሁ፦

ቦሌ መድኃኔ ዓለም ፊት ለፊት፤ መድኃኔ ዓለም እየተባለ የሚጠራው ህንፃ ሥር፡ በእንግሊዝኛው ይጠራል፡ “InN Out Burgerየሚባል ትልቅና “ዘመናዊ/ፈረንጃዊ” የፈጣን ምግብ ቤት አለ። ዶሮና ድንች ጥብስ፣ በርገሮችና የመሳሰሉትን የፈረንጅ ምግቦች ነው የሚያቀርቡት። ባጠቃላይ፡ ቦሌና ሃያሁለት በመሳሰሉት አካባቢዎች ጣፋጩንና ጤነኛውን ኢትዮጵያኛ የእንጀራ ምግብ ማግኘት በጣም ከባድ ነው። የሚገኝ ከሆነ እንኳን ምግቡ ሁሉ በአደገኛው ዘንባባ ዘይት የተሠራ ነው።

አንን ቀን አመሻሽ ላይ፡ እስኪ ልቅመሰው ብዬ በረንዳው ላይ ቁጭ አልኩ፤ የተቆራረጡ ዶሮዎችና (ሁሉ ነገር በእንግሊዝኛ ነው„Chicken Nuggetsብለውታል)የድንች ጥብሶች አቀረቡልኝ። ለመግለጽ ያዳግተኛል፤ አንዷን ቁራጭ ዶሮና ድንቹን እንደቀመስኩ በጣም አጥወለወልኝ፣ አፈር አፈር ይላል ብል አፈርን መስደብ ይሆንብኝል፤ አፈር የተሻለ ይጣፍጣል፡ የበለጠም ጥቅም ይኖረዋል፤ ይህ ግን ዶሮውም ድንቹም፡ ከፈርንጅ አገሩ እንኳን ሲነጻጸር በጣም የተለየ ነው።

አሳላፊውን ጠርቼ ይቅርታ ስለምቸኩል አልጨረስኩትም ብዬ ሂሳቤን ከከፈልኩ በኋላ ወርጄ ሄድኩ። ምነው ብለው ደነገጡ። ትንሽም ሄደት እንዳልኩ፤ አንዲት ወጣት እህታችን መንገድ ዳር ቁጭ ብላና ጨቅላዋን አቅፋ ትለምናለች…..ኩምሽሽ ብዬ አብሪያት ቁጭ አልኩእዚያ ሬስቶራንት ለዚያ ምግብ 95 ብር ነበር የከፈልኩትሬስቶራንቱ ውስጥ እስከ መቶ የሚጠጉ ወጣቶች እየተጯጯሁ ይመገባሉ፤ በብዙ ብር የሚገመት ምግብ ያዛሉበሽተኞች የሚያደርጋቸውን/ የሚያደርገንን ምግብ ይወስዳሉ/ እንወስዳለንእዚህ ደግሞ እህታችን፡ ልክ እንደ ማርያም ልጇን አቅፋ፡ ትለምናለች….. ያው እስካሁን ልረሳው የማልችለው ገጠመኝ ነው፣ ልክ እንደ ኃይለኛ ነገር ሆኖ ነው የሚትየኝ።

እዚያ ምግብ ቤት እንዲሁ ለመታዘብ አልፎ አልፎ አለፍ እያልኩ ወደ ውስጥ አይ ነበር። ሁሌ ሙሉ ነበር። አንድ ሌላ የታዘብኩት ነገር ቢኖር፦ ባካባቢው የሚገኙት ብዙ ፈረንጆች ወደ እዚህ ቤት ገብተው ሲመገቡ አለማየቴ ነው። እለምን ይሆን? የሚያውቁት ነገር ይኖር ይሆን? ለነገሩማ ለእነርሱ የት፣ ምን መብላት እንዳለባቸው ብዙ ጊዜ አስቀድሞ ባገራቸው/በኢንባሲዎቻቸው በኩል ይነገራቸው የለ!?

ዔዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ የሳጥናኤል ልጆች በተገኘው ቀዳዳ ሁሉ ነው እየገቡብን ያሉት፣ ዓይናችን እያየ ጆሮአችን እየሰማ ዲያብሎሳዊ ድርጊታቸውን በፈርኦናዊ ትዕቢትና ድፍረት በመፈጸም ላይ ናቸው። በተለይ አሁን ትኩረቱን ያደረጉት የሕብረተሰባችን ምሶሶዎች በሆኑት ሴቶቻችን እና ህፃናቶቻን ላይ ነው፤ በቅርቡ ደግሞ የወንዱን ዘር ለማድከም የተለያዮ ኬሚካሎችን፣ ጀርሞችንና ባክቴሪያዎችን እያዘጋጁልን ነው። ይህን እያንዳንዳችን ያልቸልተኝነት ልናውቅና ልናሳውቅ ግዴታ አለብን።

ለእህቶቻችን ውፍረት፦

መንስዔ

ዲያብሎሳዊ ምግብና መጠጥ

ይህ ምግብ ፈረንጁ አገር “ጃንክ/ቆሻሻ” ምግብ ይባላል፤ የሚመገቡትም፤ ብዙ ያልተማሩና ድኾች የሚባሉት ናቸው።

በአዲስ አበባችን ደግሞ፣ ተምሯል፣ ያውቃል፣ ኃብታም ነው የሚባለው ነው በፈቃዱ ይህን ቆሻሻ የሚበላው።

+ የሚረጋ የዘንባባ(ፓልም)ዘይት(በውስጡ ፓልሚክ አሲድ የተባለ አደገኛ ኬሚካል የያዘ ነው)

+ ኦርጋኖፓስፌት በተባለ መርዝ የተቀቀለ የእርዳታ(አሜሪካ)ስንዴ

+ የፈረንጅ በርገር እና ጥብሳጥብስ

+ የ ”ፈረንጅ” ዶሮና እንቁላል

+ የ “ፈረንጅ” ወተትና እርጎ

+ ሚሪንዳና ኮካኮላ

+ የአረብ ዱቄቶች

+ የቱርክና ፓኪስታን ስኳር

+ ኤታኖል የተሽከራሪ ነዳጅ

መንስዔ ፪

ዲያብሎሳዊ የወሊድ መከላከያዎች

+ ውርጃ

+ እንክብሎች

+ ክትባቶች

+ ቅባቶች

መንስዔ ፫

ዲያብሎሳዊ የማሕበረሰብ ግኑኝነት መርዞች

+ በየጎረቤቱ ምግብና ውሃ ውስጥ የሚቀላቀሉ የአረብ ቅመሞች፣ ሽታዎች(መርዝ ጂሃድ)

+ በጎረቤት እንስሶች ላይ የሚካሄድ ጭካኔ፤ በተለይ በውሻ ላይ

+ በየትምህርት ቤቱ በህፃናት የምሳ እቃ ውስጥ በድብቅ የሚጨመሩ ጠብታዎች(መርዝ ጂሃድ)

+ የቱርክ የ”ፍቅር” ድራማዎች (የፍቅር ጂሃድ)

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹፫:

አቤቱ፥ እንደ አንተ ማን ነው? አቤቱ፥ ዝም አትበል፥ ቸልም አትበል።

እነሆ፥ ጠላቶችህ ጮኽዋልና፥ የሚጠሉህም ራሳቸውን አንሥተዋልና።

ሕዝብህን በምክር ሸነገሉአቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ።

ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ።

አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተ ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤

የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞዓብም አጋራውያንም፥

ጌባል አሞንም አማሌቅም፥ ፍልስጥኤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤

አሦርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፥ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኑአቸው።

______

Posted in Conspiracies, Faith, Health, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: