ይህ ለሩሲያው ድሕረ–ገጽ የቀረበ ሚዛናዊ የሆነ ግሩም ጽሑፍ ነው።
በእንግሊዝኛ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ፦
የሚገርም ነገር አይደለም!? አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ከመንግስቱ ኃይለማርያም ጋር እንዲገናኝ ወደ ዚምባብዌ ላኩት፤ አይደል! ወቸውጉድ!
የደርግ ስርዓት ከኮሙኒስት ሶቪየት ህብረት ጋር ወዳጅ ነበር። ደርጎች አንድ የኢትዮጽያን ትውልድ ከቀጠፉና በሚሊየን የሚቆጠሩትን ወገኖቻችንን ከገደሉ በኋላ ወደ አንግሎ–አሜሪካዊው የሩሲያ ጠላት ዓለም ኮበለሉ። አሁን በአቶ አብይ አህመድ በኩል ተመልሰው ሥልጣን ላይ ለመውጣትና ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ ለማጥፋት ይሞክራሉ። ባለፉት 27 ዓመታት ሁኔታዎች አመች በሆነ መልክ ተዘጋጅተዋቸዋልና፤ ኢሃዴጎች፡ በወስላታው ሌኒን አነጋገር፤ “Useful Idiots / ጠቃሚ ጅሎች” ነበሩ ማለት ነው።
ወገኔ ምነው ታወርክ?! ይህን እንዴት ማየት ተሳነህ?!
በኢትዮጵያ የስልጣን ለውጥ ከተካሄደ ከአምስት ወራት ገደማ በኋላ በሀገሪቷ የተለያዩ ክልሎች ውስጥ ብዙ ሕይወት የቀጠፉ የኅብረተሰብ ብጥብጦች ተከስተዋል። ግጭቱ እየጨመረ የመጣው በዚህች የአፍሪቃው ቀንድ አገር ለበርካታ ዓመታት የፖለቲካ መረጋጋት ከሰፈነ በኋላ ነው። ኢትዮጵያ ምናልባት አሁን እስከ መገነጣጠል ድረስ ሊያደርስ የሚችል ጽኑ ብጥብጥ ሊያጋጥማት እንደሚችል ይታሰባል።
ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቀቀ አለመረጋጋት በዩኤስ አሜሪካ በተደገፈ የጂኦፖሊቲካል አመራር አካል ላይ የተመሰረተው ነው። ዓላማው፡ ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ያላትን ግኑኝነት እንድታቆምና በ አረቦች እና አሜሪካ ተፅዕኖ ስር እንድትወድቅ ማድረግ ነው። ይህ በአዲሶቹ ገዢዎች ፍልስፍና ሳቢያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ አገር አቀፍ ብሔራዊ የመግባባት ሂደትን አላካሄደም። በአሜሪካና አረቦች ግፊት እርስበርስ የተመሳጠሩ ግለሰቦች ያካሄዱት የመንግስት ግልበጣ ነው።
በዚህ ዓመት በሚያዝያ ወር ላይ የኢትዮጵያ ፓርላማ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲመርጡ አድርጓል። የሽፍት ምርጫው ሂደት ብዙ ፈረስ–ነጋዴን የሚያካትት ይመስላል። ወጣቱ አብይ አህመድ (41) በአዲስ መሪነት ብቅ አለ። በተለይም በምዕራባውያኑ ሚዲያ እና ከአሜሪካ መንግስት በተለይም አዎንታዊ ተፅእኖዎችን በማስተዋወቁ ታላቅ ምስጋናዎችን አግኝቷል። ለምሣሌ በመቶዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን እንዲፈት አዝዟል። የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታውን አቁሟል፤ እናም ያለፉትን በፀጥታ ኃይሎች የደረሱትን የሰብአዊ መብት ድፍጠጣዎች አውግዟል። በእውነት ጉዳዩ አሳስቦት ሳይሆን የቀድሞውን መንግስት በ “አገር ሽብርተኝነት” ለመኮነን ስላቀደ ነው።
“አቢይ” ብቻ እየተባለ በአብዛኛው የሚጠራው አብይ አህመድ የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር (OFL) ተብሎ ከሚጠራው ተቃዋሚ ሽብረተኛ ቡድን ጋር ውስጣዊ የሰላም ሂደት እንዲካሄደት በማድረግና እና ከዩ.ኤስ እና ከሌሎች ሀገራት ውስጥ የነበሩትን ፖለቲከኞች በ “ይቅርታ” ስም በግዳጅ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።
በአለም አቀፍ ደረጃ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከአጎራባች ኤርትራ ጋር ነገሮችን በፍጥነት በማስተባበር ከሶስት ዓመታት የድንበር ጦርነት በኋላ (ከ 1998 እስከ 2001) ለ 20 ዓመታት የቆየ መረጋጋት ማስፈብ ችሏል። ሁለቱ ሀገራት ይህን ባለፈው ወር ላይ በይፋ አሳውቀዋል።
ይሁን እንጂ እነዚህ ግልጽ መሻሻል ያላቸው የሚመስሉ ለውጦች በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ የሚረብሽ መዘዝ ያላቸው ናቸው። የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይን ዴሞክራሲያዊ ለዘብተኛ አድርገው ሲገልጹ ይታያሉ፡ ነገር ግን እየተካሄደ ካለው በስተጀርባ አንድ ጨለማ የሆነ ነገር አለ።
ባለፉት ሳምንታት ላይ ዶ/ር አብይ ከሳውዲ እና ኢሚሪቲ ባሕረ ሰላጤ አገሮች ለመጡ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ሞቅ ያለ አቀባበል አድርጎላቸዋል። የሳውዲው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዴል አል–ጁቤር ቀደም ሲል ኤርትራ ውስጥ ከአምባገነኑ የኤርትራ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቅ ጋር ከተገናኘ በኋላ ነበር በዚያው ቀን ወደ ኢትዮጵያ ያመራው። የባሕረ ሰላጤው አረብ ገዥዎች የኤርትራ የረጅም ጊዜ ድጋፍ ሰጪዎች ናቸው። ታዲያ አሁን ኢትዮጵያ ከእነዚህ አስጨናቂ አረብ አምባገነኖች ጋር ድንገተኛ ግንኙነት መፍጠሯ በርካታ ኢትዮጵያውያንን በሀገሪቱ ውስጥ እጅግ አሳስቧል፤ አገሪቷ የምትጓዝበት ክፉኛ አቅጣጫ ብዙዎችን አስጨንቋቸዋል።
አሁን እየተተገበረ ያለው ነገር ኢትዮጵያን ከቻይና ተፅዕኖ ሥር አውጥቶ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ እና፡ ሳዑዲ ዓረቢያን ጨምሮ፡ የሱኒ እስላሙ መካከለኛው ምስራቅ ደንበኛ የማድረግ ጂኦፖሊቲካዊ ጨዋታን ያሳያል። ይህም ኢትዮጵያ ከቻይና ጋር ለምታደርገው የስትራቴጂያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር፡ እንዲሁም ለሀገሪቱ ውስጣዊ ውጥረት መንስኤ ይሆናል።
በቅርቡ በምስራቅ ኢትዮጵያ የተከሰተው ግጭትና ብጥብጥ በጣም የተወሳሰበ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ 100 ሚሊዮን ህዝብና 84 ብሔረሰቦችን የያዘች አገር መሆኗን ይጠቁመናል። በአብዛኛው የክርስትያን ኦርቶዶክስ ሀገርም በርካታ ሙስሊም ህዝቦችም የሚኖሩባት አገር ናት። እነዚህ ብጥብጦች አገሪቱን ወደ ሰፊ ዓመፅ ሊወስዳት ይችላል።
ባለፈው ሳምንት በአገሪቱ ምስራቃዊ ድንበር ሶማሊያ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት ተቃጥለዋል፣ በርካታ ቄሶች ተገድለዋል። ይህን መሰሉ ጥቃት በክርስቲያኑ ላይ በመከሰቱ ወደፊት ጉዳዩ ምናልባት ወደ ሃይማኖታዊ ጦርነት ሊያመራ ይችላል። አገሪቱ በአሻሚ ጫፍ ላይ እየተንከባለለች ስለሆነ ብዙ ነዋሪዎቿ ከስጋት ጋር አብረው እንዲኖሩ እየተገደዱ ነው።
በደቡባዊ፣ ምእራብ እና ምዕራባዊ ክልሎች ሌሎች ብዙ ሰዎች የተገደሉባቸው ግጭቶች ነበሩ። በተለይ የምዕራባውያን የመገናኛ ብዙሃን “ለውጥ አምጭው” አቢይ አህመድን የማይመለከታቸው እንደሆነ አድርገው ነገሮችን ለመሸፋፈን ቢሞክሩም፡ ይሁን እንጂ እንደታየው ከሆነ በእርግጠኝነት ድርጊቱ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ተጠያቂ ያደርገዋል።
በምስራቁ የሶማሌ ክልል የተፈጸመው ግድያ መንስኤ አሁንም ግልጽ አይደለም። በዋና ከተማዋ በአዲስ አበባ ቁጥጥር ስር የሚገኘው ባለሥልጣን የሶማሌ አካባቢ የሕዝባዊ ወታደሮች በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ጥቃቶችን እንደፈጸሙ አድርጎ ተናግሮ ነበር፤ የምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙሃንም ይህንን ተቀብለው የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ ሲነዙ ተሰምተዋል፥ ነገር ግን በአዲስ አበባ ባለስልጣናት ይህን ግጭት በማነሳሳትና በክልሉ ላይ ማዕከላዊ ቁጥጥር በማካሄድ የግድያ ድርጊቶች ሊፈጸሙ እንደሚችሉ ጥርጣሬ አለ።
ጥርጣሬን የሚያስነሳው በዚያ ቦታ ላይ በ ክርስቲያኖች ላይ እንዲህ ያለ ጥቃት መፈጸሙ ነው። የሶማሌ ክልል አገረ ገዢ አብዲ ኢልሊ በአሁኑ ጊዜ በአዲስ አበባ ማዕከላዊ መንግስት ቁጥጥር ሥር እንደሆነ ይታመናል። ይሁን እንጂ አብዲ ኢሌል እራሱ ሙስሊም ቢሆንም ለዓመታት በርካታ አብያተ ክርስቲያናትን አሠርቶ ነበር፤ በአካባቢያቸው ካሉ ክርስቲያኖችም ጋር መልካም ግንኙነት ነበረው። ምናልባትም ይህ የወቅቱ ገዢ የቀድሞው ገዥው ፓርቲ መንግስት ደጋፊ ስለሆነ ይሆናል። ምናልባትም አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር በሚያዝያ ወር ከተመረጠ በኋላ ፀረ–ቀድሞ መስተዳደር አቋም እንዳለው ያሳይ ነበር።
በአዲስ አበባ የሚገኙት ማዕከላዊ ባለስልጣናት በትግራይ ህዝቦች ነጻነት ግንባር (ወያኔ) ቁጥጥር ሥር ነበሩ። በኤርትራ ድንበር ላይ ከሚገኘው ሰሜናዊው የኢትዮጵያ ክፍል በመነሳት በ 1990-91 ያለውን አስከፊውን የደርግ አገዛዝ ለመገልበጥ ዋና ሚና የተጫወቱ ወያኔዎች ነበሩ። በአዲስ አበባ ያለው አዲሱ አመራር አሁን የተያያዘው የደርግ ስርዓትን መልሶ ማቋቋም ነው። በያዝነው ወር ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዩኤስ ወር ላይ አንድ ሳምንት የፈጀ ረዥም ጉብኝት ሲያደርጉ፡ ከደርግ አባላት ጋር በአንድ መድረክ ላይ ሆነው በግልጽ ታይተዋል። እነዚህን የደርግ ርዥራዦች ይዘው ወደ አገራቸው ስለተመለሱ፡ የምዕራቡ ዓለም የመገናኛ ብዙኃን እንደሚገልጹት ሳይሆን ብዙ ኢትዮጵያውያኖች እንደታዘቡት ይህ “የለውጥ ማሻሻያ” እንደሆነ ተደርጎ እንደማይቆጠር፤ እንዲያውም አገሪቷን ወደቀድሞው አስከፊ ሁኔታ በመመለስ እንደገና ሊበጠብጣት እንደሚችል ይናገራሉ።
ኢትዮጵያውያን በተለይም በሰሜናዊ ትግራይ ክልል ውስጥ አቢይ የክፍፍል ሁኔታዎችን በመፍጠር ለኦሮሞ ብሔረሰብ የበላይነት ቅድሚያ የመስጠት አጀንዳ ይኖረዋል ብለው ይፈራሉ። የሙስሊም ዝርያ ያለው አቢይ ከአረቦች ጋር እየፈጠረ ባለው ጥብቅ የወዳጅነት ግኑኝነት በክርስቲያኖች ላይ የዓመፅ ብጥብጦችን ልያስነሳ ይችላል። ነገሮችን በደንብ ለማየት የሚረዳን ቁልፍ ሁኔታ፡ ሳውዲዎች እና ኤምራቶች በኢትዮጵያ እጅግ ጽንፈኛ የሆኑትን መስጊዶቻቸውን መገንባት ሲጀምሩ ነው።
እንደ ኢትዮጲያ የፖለቲካ ምንጭ ዘጋቢዎች እንደሚሉት ከሆነ የአቢይ ሥልጣን ላይ መውጣት ከረጅም ጊዜ በፊት በአሜሪካ እና አረብ ወዳጆቿ አስቀድሞ የታቀደ ነው። የአፍሪካ ቀንድን ከቻይና ኢኮኖሚ ጫና የማራቁ ፍላጎት የረጅም ጊዜ ዕቅድ አካል እንደሆነ ይታመናል። ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ቻይና የኢትዮጵያን ልማት ለመላው አፍሪቃ እንደ ሞዴል አድርጋ ወስዳዋለች። በወያኔ የሚተዳደረው መንግስት ከቻይና ጋር ከፍተኛ አጋርነት ነበረው። ይህ አሰላለፍ አሁን በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ በመሸርሸር ላይ የሆነ ይመስላል። ለምሳሌ ያህል፡ ቻይና ቁልፍ ሚና የተጫወተችበትን የወያኔን እና አንዳንድ የአገሪቱን ታላላቅ የልማት ፕሮጀክቶች በመውቀስ አንዳንድ አስተያየቶችን ሲሰጥ ተሰምቷል።
የኤምራት አረቦች በዚህ ወር መጀመሪያ በኤርትራ ቀይ ባህር በኩል ከአሰብ ወደ አዲስ አበባ ለመዘርጋት ያቀዱትን የነዳጅ ባንቧ ዕቅድ አስመልክተው መናገራቸው ትልቅ ግምት የሚሰጠው ነው። በቅርቡ ኢትዮጵያ በምስራቃዊው ክልል ውስጥ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ክምችቶችን አግኝታለች።
በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል የተደረገው “ድንገተኛ” የሰላም ግኑኝነት በሳውዲዎች፣ ኤምራቶችን እና አሜሪካ ግፊት ነው። ሁሉም ነገር የተደረገው አቶ አቢይ ቢሮ ከወሰደ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ መሆኑ ነው።
ኢትዮጵያን ከቻይና ስልታዊ አጋርነት ለማራቅ፣ የቻይናን ልማታዊ ካፒታል ያገኘውን የኢሃዴግን መንግስት ለሚቃወሙት ኦሮሞዎች ሲባል፡ አንድ ኦሮሞ የፖለቲካ መሪ አድርጎ መሾም አስፈላጊ ነበር። የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ኢትዮጵያን በሚወጋበት ወቅት ኤርትራ ከጎናቸው ተሰልፋ ነበር። ይህም የኦነግ አመራሮች ከኢትዮጵያ እንዲወጡ፣ እንዲሰደዱና አንዳንድ መሪዎቻቸውም እንዲታሠሩ ካደረጓቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ነበር። የጦረኛው ቡድን ቀደም ሲል በወያኔ–አመራር አስተዳደር የ “አሸባሪ ድርጅት” ተብሎ ይጠራ ነበር። የኦነግ ማዕከል አሁንም በ ኤርትራ ዋና ከተማ፡ በአስመራ ውስጥ ይገኛል። እንግዲህ እነዚህን ነው አቶ አቢይ ወደ አዲሱ የኢትዮጵያ የፖለቲካ መዋቅር በወንድማማችነትን ስልት “ይቅርታ” ብሎ በመደመር ላይ ያለው።
በዚህም ምክንያት ኢትዮጵያን ከቻይና አላቅቆ ወደ አሜሪካ እና አረብ ተፅዕኖ በማዘዋወር – እግረመንገዱን ለአሜሪካ የካፒታል ትርፋማነት ያመጣላታል – የኦሮሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን በዘር እና በሃይማኖት ዙሪያ ረብሻና ብጥብጥ ለመቀስቀስ አስተዋፅኦ ያበረክታል።
የክርስቲያን እና የሙስሊም ግጭት ሊፈጠር ወይም በኦሮሞና ትግራይ ጎሳዎች መካከል የእርስ በርስ ጦርነት ሊቀሰስ እንደሚችል ፍርሃት አለ። አቢይ አህመድ ከአሜሪካ ጉብኝት ሲመልስ ይዟቸው የመጣው አንዳንድ የኦሮሞ ተቃዋሚዎች በትግሬዎች ላይ የበቀል እርምጃ እንዲወስዱ በይፋ በመቀስቀስ የሚታወቁ የጥላቻ ጥሩምባዎ ናቸው። በሳዑዲ እና በኤሚራቲ ዋሃቢ ገዢዎች ድጋፍ የሚያገኙ ክብሪት ጫሪዎችም አጋጣሚውን ተጠቅመው የጅሃድ እሳት ይቀሰቅሱ ይሆናል።
ኢትዮጵያ ወደ አደገኛ ሁኔታ በሚያመራው ቢላዋ ጫፍ ላይ ናት። አንድ ነገር ግን በእርግጠኝነት የምዕራቡ ዓለም፡ በአዲሱ የኢትዮጵያ አመራር ዲሞክራሲን እያመጣ ነው በማለት የሚያሞካሹት አቶ አቢይ አህመድ በተቃራኒው አደገኛ ሁኔታ በመፈጠር ላይ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ጥቅሞች ወይም የፖለቲካ ፍላጎቶች ለማስተናግድ ሳይሆን የአሜሪካ እና አረብ ደንበኞቿን ጥቅም ለማስከበር ነው ስልጣን ላይ ያወጡት፤ እንዲያውም የሃገሩን መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥል “ትሮጃን ፈረስ” ይመስላል።
በአጠቃላይ የምዕራቡ ዓለም መገናኛ ብዙሃን ያለአግባብ እንደሚናገረው አዲሱ መንግስት በኢትዮጵያ “ዴሞክራሲ” እና “እድገት” እየሰፈነ ሳይሆን ያለው፤ የኢትዮጵያን አለም አቀፋዊ ነፃነት እና ማንነቷን ለማጥፋት፡ በመፈንቅለ መንግስት፡ ወንበሩን የያዘ መንግስት ነው።
______
Like this:
Like Loading...