Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የኔቢጤዎች’

ወደ ኢትዮጵያ በመጉረፍ ላይ ያሉት ሶሪያውያን ከልመና ታገዱ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 25, 2019

በተለይ በአዲስ አበባ መንገዶች ላይ፣ ሆቴሎች እና መስጊዶች አካባቢ እየበዙ የመጦቱ ሶሪያውያን ለማኞች (የኔ ቢጤ አይደሉምና የኔ ቢጤ አልላቸውም) አሁን ከልመና እንዲቆጠቡ መታዘዛቸውን አሶሲየትድ ፕሬስ አስታውቋል።

እስካሁን 560 ሶሪያውያን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል ተብሏል። ባጠቃላይ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ስደተኞች በኢትዮጵያ አሉ።

ወገኖች፤ ሦስተኛው ሂጂራ ጀምሯል፦ እንደ ግብጽ፣ ሱዳን እና ሳውዲ አረቢያ የመሳሰሉትን ያካባቢ አገራት ተሻግረው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት አገራችንን ለመውረር ወስነዋል። አዎ! ይህ መረጃ እንደሚጠቁመን ስደተኞቹን ቀስቅሶ ወደ ኢትዮጵያ እንዲጓዙ ያደረጋቸው የሉሲፈራውያኑ ድርጅት የተባበሩት መንግስታት ነው። በመላው ዓለም እንደሚታየው ተልዕኮው የብሔራዊ ስሜት ያሏቸውን ሕዝቦችና ነዋሪዎች ከየአገሩ ማፈናቀል ነው፤ በሶሪያና ኢራቅ ክርስቲያኖችን ጨፍጭፈው ጨርሰዋቸዋል፤ በግብጽም ተመሳሳይ ድርጊት እየተካሄደ ነው።

በኢትዮጵያችን ደግሞ ተቸግረናል በማለት የአዞ እንባ እያነቡ እንዲገቡ በመደረግ ላይ ናቸው። በኤርትራ አቶ ኢሳያስን አስቀምጠው አንድ የተዋሕዶ ክርስቲያን ትውልድ በስደት እንዲያልቅ ተደረገ፣ በሶማሊያ እና በደቡብ ሱዳን ጦርነት ጀምረው ብዙ ስደተኞች ኢትዮጵያን እንዲወሩ ተደረጉ፤ አሁን ደግሞ በሱዳን ጦርነት በመለኮስ ላይ ናቸው፤ አንጠራጠር፤ የቱርክ እጅ አለበት፤ ሌላ “መህዲ” ተነስቷል፤ መተተኞቹ ሱዳኖች ከየመናውያን ጋር ወደ ኢትዮጵያ ገና ይጎርፋሉ፤ በዚህም የተዋሕዶ ልጆች አገራቸውን ለጠላቶቻቸው አስረክበው እንዲወጡና በዔሳውያን እና እስማኤላውይን በርሃ ላይ እንዲያልቁ ይደረጋሉ።

ሱዳኖች ደጎች ናቸው፤ ኢትዮጵያውያን ደግሞ በይበልጥ ደጎች ናቸው” አሉ ሶሪያውያኑ?! እንደው፡ ንጹሑ የክርስትና ስንዴ ከእንክርዳዱ፣ በጉ ከፍየሎች በሚለይበት በዚህ ዘመን የሚታለል ወገን (ከመሀመዳውያን ሌላ) ይኖራልን?

ለመሆኑ የሚጨቆኑት ክርስቲያን ሶሪያውያን ለምን ወደ ኢትዮጵያ አይመጡም? በዱሮ ጊዜ ለኢትዮጵያ አገራችን ብዙ ውድ ነገር ያበረከቱ ቅዱሳን ሶሪያውያን ክርስቲያኖች ወደ አገራችን መጥተው ነበር፥ አሁን ግን ወራሪ መሀመዳውያን በሦስተኛው ሂጂራቸው ለማኝ ሆነው በመግባት ላይ ናቸው። አይይይይ!


Ethiopia Bans Street Begging By Syrians In Growing Numbers


Ethiopia is banning street begging by Syrian nationals who have startled people by showing up in growing numbers in recent months in major cities around hotels and mosques.

“We are now coordinating our security services to effectively ban Syrian citizens from begging. We have tolerated them for some time but we have now decided to ban the illegal practice. … They are becoming a burden,” the deputy head of Ethiopia’s immigration office told The Associated Press on Friday.

Some 560 Syrians entered between mid-August and mid-December and the majority leave when their tourist visas expire, said the deputy, Yemane Gebremeskel. While street begging is not illegal in Ethiopia – there is a large presence of children – the act of entering the country as a tourist and begging is, he said.

Nearly 120 other Syrians have applied for refugee status in the East African nation that hosts one of the world’s largest refugee populations, and they were provided with support equaling around $73.

“We gave them what we could afford but they are still begging,” Yemane said.

Many Ethiopians were baffled when the Syrians began appearing on the streets of the capital, Addis Ababa, displaying signs written in the local Amharic language appealing for help.

One Syrian told the AP his family fled the war at home and has moved from place to place as life in other countries became too expensive.

Khalid Youssef said he, his wife and three children first sought refuge in Lebanon then a year ago moved to Sudan, which neighbors Ethiopia, with the help of the United Nations. They finally moved to Ethiopia.

“We don’t have any money,” he said. “Besides, there was no work in Sudan even though people were generous. Here, people are even more generous and they help us a lot.”

To survive, he said, the family asks for charity during the day. “At night we go to sleep at the mosque.”

The U.N. refugee agency told the AP in December it was supporting Ethiopia’s government in caring for close to 80 “Syrian refugees and asylum seekers” whom it said started arriving in the country in 2014.

After several interviews the Syrians on the streets, the agency “was able to establish that these were new arrivals,” it said. Over the previous month three Syrian families composed of 20 people had applied for asylum, it added.

Ethiopia currently hosts 900,000 refugees mainly from neighboring Somalia, South Sudan, Eritrea and Sudan. Earlier this month the U.N. praised the government for a new law that will allow refugees to obtain work permits, go to primary schools, open bank accounts and more.

Ethiopia’s refugee law is now “one of the most progressive refugee policies in Africa,” the agency said.

Source

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሶሪያዊያን ስደተኞች በአዲስ አበባ | አረቦች ለማኝ ሆነው ወደ አገራችን በመግባት ላይ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 7, 2018

እርግጥ ነው የአዲስ አበባ ጎዳናዎች ነዳያን አያጣቸውም። ሶሪያውያንን ማየት ግን እንግዳ ነው።

በተረጂነት እምብዛም የማይታወቁ አረቦች በየጥጋጥጉ ምጽዋት ሲጠይቁ ማየት ለበርካታ አዲስ አበቤ ጥያቄ ቢያጭርበት አይደንቅም። የሶሪያውያን ነገር መነጋገሪያ የኾነውም ለዚሁ ይመስላል።

በዚህ ዘመን ከዕልቂቶች ሁሉ የከፋው እልቂት የደረሰው በሶሪያ ምድር ነው። ግማሽ ሚሊዮን ሕዝቧ በእርስ በርስ ጦርነት አልቋል። ከጠቅላላው የሶሪያ ሕዝብ ገሚሱ ተፈናቅሏል።

በየዓለማቱ እየተንከራተቱ ካሉት ሶሪያውያን ጥቂቶቹ ከቅርብ ወራት ወዲህ የኢትዮጵያን ምድር መርገጥ ጀምረዋል።

እንዴት ኢትዮጵያን መረጡ?

ኢትዮጵያ እንግዳ ተቀባይ አገር ናት ሲባል በመንግሥት ደረጃም የሚገለጽ፣ በአሐዝም የሚደገፍ ሐቅ ነው። ምንም እንኳ በድህነት ተርታ ያለች ቢሆንም ኢትዮጵያ በዓለም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ስደተኞችን በማስጠለል ከቀዳሚ አገራት ተርታ ትመደባለች።

አያሌ ሶማሊያውያን፣ ኤርትራውያንና ደቡብ ሱዳናውያን በመጠለያ ጣቢያዎችና በዋና ዋና ከተሞች ጭምር ይገኛሉ።

ሶሪያዊያኑ ግን የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ናቸው።

ስምንት ዓመታትን ካስቆጠረው የሶሪያ ጦርነት የሸሹ ስምንት ሚሊዮን ዜጎች በጎረቤት አገራትና በአውሮፓ ተጠልለዋል። ጥቂቶች ወደ አፍሪካ አቅንተዋል።

ግብጽ ከአፍሪካ አገራት በርካታ የሶሪያ ስደተኞች የሚገኙባት ናት። ከግብጽ ሌላ ሊቢያ፣ አልጄሪያና ሱዳን ወደ 33ሺህ የሚጠጉ ስደተኞችን ያስተናግዳሉ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰሜን አፍሪካ የሚገኙት የሶሪያ ስደተኞች በአየርም በምድርም አቆራርጠው ወደ ምሥራቅ አፍሪካ ማማተር ጀምረዋል። ከእነዚህ መሐልም የተወሰኑት ኢትዮጵያን መርጠዋል።

የምንማጸነው እንደትረዱን ነው

አናስ መሐማት ወደ ኢትዮጵያ የመጣው ከአንድ ወር በፊት ነው። ቤተሰቡን ይዞ ከንጋት እስከ ምሽት ለምጽዋት እጁን ይዘረጋል፤ በአዲስ አበባ ጎዳና።

ከአረብኛ ሌላ አይናገርም። በአንድ እጁ ሮጦ ያልጠገበ ልጅ ይዞ በሌላ እጁ በነጭ ወረቀት ላይ በአማርኛ የተጻፈለትን የድረሱልኝ ጥሪ ከፍ አድርጎ ለወጪ ወራጁ ያሳያል። አትላስ አካባቢ።

ያነገበው ጽሑፍ፣ እኛ ወንድሞቻችሁ ከሶሪያ ተሰደን የመጣን ሲሆን አሁን በችግር ላይ ስለሆንንን ያላችሁን እንድትረዱን በፈጣሪ ስም እንለምናችኋለን። አላህ ይስጥልንየሚል ነው።

አናስ አትላስ አካባቢ በልመና ላይ ሳለ የቢቢሲ የአዲስ አበባ ወኪል አግኝቶት ነበር።

“…በሕይወት ለመቆየት እየታገልን ነው። መንገድ ላይ፣ ትራፊክ መብራት አካባቢ እና በየመስጊዶች እንለምናለን። ባንለምን ደስ ይለን ነበር። ኾኖም በሕይወት ለመቆየት ሌላ አማራጭ የለንም። ፈጣሪ ይርዳን….” ብሎታል።

ሕሊናዬ ሊያርፍ አልቻለም

ያለፉት ጥቂት ወራት በርከት ያሉ ሶሪያዊያን በኢትዮጵያ ጥገኝነት እየጠየቁ ነው። ስደተኞቹ የነበራቸውን ጥሪት ኢትዮጵያ ለመድረስ በጉዞ ወጪዎች አሟጠውታል።

በቁጥር ምን ያህል ሶሪያዊያን ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል የሚለው በይፋ ባይታወቅም መንግሥት ግን የስደተኞች ምዝገባ እያካሄደ እንደሆነ ይገልጻል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ በየጎዳናው ጥጋጥግ የሚተኙ በርካታ ሶሪያዊያን እየተታዩ ነው። በጎ ፈቃደኞች አይተው ማለፍ አልቻሉም፤ አይሻ መሐመድ ከነዚህ አንዷ ናት።

የሚያሳዝኑ ሕዝቦች ናቸው። እዚህ ከደረሱ ጀምሮ እያገዝናቸው ነው። የምንችለውን ሁሉ እየለገስን ነው። ብርድልብስ፣ ምግብ፣ አልባሳት። ሰዎችም በተቻላቸው መጠን እንዲረዷቸው እየጠየቅን ነው። ትንንሽ ልጆችን ይዘዋል። በዚያ ላይ ቋንቋ አይችሉም።

የአዲስ አበባ ነዋሪ የኾነው ቢኒያም ታምሩ በበኩሉ ከሁሉም በላይ ሕጻናትን ይዘው የሚንከራተቱ ሶሪያዊ እናቶች ስሜቱን የሚረብሹት ይመስላል።

ሴቶችና ሕጻናት በዚህ መልኩ ሲንገላቱ ሕሊናዬ እያየ ዝም ሊል አልቻለም። ያለኝን ሁሉ ለማካፈል አልሳሳም። ምንም ትንሽ ቢሆን። 20 ብር ካለኝ 10 ብሩን እሰጣቸዋለሁ።

ሩሲያና የአሳድ መንግሥት ግጭቶች ስለረገቡ ስደተኞች ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እየጠየቁ ነው። ነገር ግን ከ5 ሚሊዮን የሚልቁት ስደተኞች ለመመለስ እያመነቱ ነው። በአገሪቱ ዘላቂ ሰላም ሳይሰፍን መመለሱ ስጋት ጥሎባቸው በሰው አገር ይንከራተታሉ።

መቼስ ምን ይደረጋል። እንደዚህ አልነበርንም። አሁን ያለንበት እውነታ ግን ይኸው ነው። ኢትዮጵያዊያን የሚቻላቸውን እንዲያደርጉልን ነው የምንማጸነውይላል አናስ።

ለአናስና ቤተሰቡም ሶሪያ የምትባለው እናት አገራቸው የሩቅ ትዝታ ሆናባቸዋለች።

ምንጭBBC https://www.bbc.com/amharic/news-46453324


ለመሆኑ፤

ሶርያውያኑ እንዴት መጡ? ማን አመጣቸው? ለምን መጡ? በሶሪያ የሚበደሉትና የሚጨፈጨፉት ክርስቲያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን አይደሉም ወደ አገራችን እየገቡ ያሉት!

ኢትዮጵያውያን ለአረቦች እየተሸጡ ሲሆን፤ አረቦች ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው። ለኤርትራ ከእናት ኢትዮጵያ መገንጠል ቁልፍ ሚና የተጫወቱት ሶርያና ኢራቅ ነበሩ። የአሳድ አባት እና ሳዳም ሁሴን ነበሩ “ጀብሃ” የሚባለውን የጂሃዲስቶች ቡድን በመርዳት የእርስበርስ ጦርነቱን እና የመገንጠል እንቅስቃሴውን የደገፉት፤ ልክ አሁን ኦሮሞ ነን ለሚሉት ጂሃዲስቶች እርዳታ እንደሚያደርጉት። ግን ሁሉን የሚያየው መድኃኔ ዓለም እነዚህን አገራት ፍርክስክሳቸውን አወጣላቸው። ምናልባት አሁን አምላክ እነዚህን አረቦች እንዲዋረዱ ለማኝ አድርጎ ወደ ኢትዮጵያ እየላካቸው ይሆን? ወይስ ፫ኛው የወረራ ሂጂራ ወደ ኢትዮጵያ?

ለማንኛውም “አረብ አገር ያላችሁ እህቶች፡ “ማዳሞቻችሁን” እንዲህ የምታሳድዱበት ቀን ደርሷል”


ሚያዝያ ፪ሺ፲ ዓ.ም የቀረበ ቪዲዮ፦

እርኩስ አረብ ኢትዮጵያውያን ሕፃናትን በእናት አገራቸው እየደፈራቸው ነው

የብርሃነ ጥምቀት ዕለት፡ ጥር ፲፩ ፡ ፪ሺ፱ ዓ..

በአዲስ አበባ ቦሌ ቅድስት መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን ከአክስቴ ልጅ ጋር ደስ በሚል ሁኔታ ቅዱስ ታቦቱን በክብር ካስገባን በኋላ፡ ከቤተክርስቲያኗ ፊትለፊት ወደሚገኘው የካልዲስ ቡናቤት አምርተን በረንዳው ላይ ቁጭ አለን። ቡናቤቷ በቱርኮች እና አረቦች ተሞልታለች። ወቸውጉድ! እያልን ቡና እና አምቦ ውሃ ካዘዝን በኋላ፡ ህፃናት የኔቢጤዎች በረንዳው ላይ ጠልጠል እያሉ መለመን ጀመሩ። እኛም ትንሽ ገንዘብ አካፈልናቸው። ልጆቹም ቀጥለው ባጠገባችን ወደነበሩ አረቦች አመሩ፤ እነዚህ በጣም እየጮሁ ሲነጋገሩ የነበሩት አራት አረቦች ልጆቹን ሲያዩ ጩኽታቸውና ቁጣቸው ዓየለ፤ ከዚያም በጣም እያመናጨኩ አባረሯቸው። እኛም በእንግሊዝኛው ቆጣ ብለን፡ “ለምንድን ነው ይህን ያህል የምትጮኹባቸው፡ መስጠት ካልፈለጋቸሁ የለንም! አንስጠም! በሉ” አልናቸውና፡ ሂሳባችንን ከፍለን እያጉረመረምን ወደ ኤድና ሞል አካባቢ አመራን። እዚያም፡ ሌሎች የኔ ቢጤ ህፃናት ያው የኛን ከተቀበሉ በኋላ አልፈውን የሚሄዱትን ሁለት አረቦች እየተከተሉ፤ “አባብዬ! አባብዬ” እያሉ ሲለምኗቸው፤ አንድኛው “የላላ፤ ታዓዓል!„ እያለ በመጮህ፡ ልክ ቪዲዮው መግቢያ ላይ የምትታየውን ቆንጅዬ የመሰለች ልጃችንን ወርውሮ ጣላት (በነርሱ የተለመደ ነው፤ ልክ ቪድዮው መጨረሻ ላይ እንደሚታየው)። እኛም አላስቻለንም፡ “እንዴ!„ ብለን ወደ አረቦች መሮጥ ስንጀምር አፍትልከው አመለጡን። እኔ እምባ በእንባ ሆኑኩ፡ አይይይ! አልኩ፤ በጣም አዘንኩ። እስካሁን አረብ በገጠመኝ ቁጥር ያ ስዕል ነው ብልጭ የሚልብኝ። በኢትዮጵያ ቆይታዬ እጅግ በጣም ካሳዘኑኝ ሁኔታዎች አንዱ እና ፈጽሞ ልረሳው የማልችለው ክስተት ነው። ማነው ይህን ያህል ያጠገባቸው?! በአገራቸው ያው እንደ ውሻ ያሳድዱናል፤ በአገራችን ግን በጭራሽ ይህን ዓይነት ድርጊት በእነዚህ እርጉሞች ሊከስትብን አይገባም። ያውም በብርሃነ ጥምቀቱ?! ማነው ለዚህ አቻ ለሌለው ድፍረት እንዲበቁና እንዲደፍሩን የሚረዳቸው??!!

____________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos, Life | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: