Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የነዳጅ ዘይት’

What’s Going On? Massive Fires at Three Mexico Oil Facilities Including One in Texas Within 24 Hours | Nordstream Syndrome – Putino to Blame?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 25, 2023

🔥 In just one day, massive fires broke out at three different facilities in Mexico and one in the United States that are controlled by the state-owned Mexican oil company, Pemex.

On Thursday, three separate fires broke out at Petroleos Mexicanos (PEMEX) facilities, resulting in two workers’ death, at least eight people were injured, and several others missing, Bloomberg reported.

This resulted in increased scrutiny of the safety record of the Mexican state oil firm in advance of its earnings call on Monday.

The fires broke out at the Pemex crude oil storage facility in Veracruz, Mexico, in Maya unit (285,000-barrel-a-day) Minatitlan refinery in Veracruz, and in Deer Creek, Texas.

______________

Posted in Ethiopia, Infos, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኃይለኛ እሳት በግብጽ | ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 14, 2020

ዛሬ በካይሮ ከተማ አንድ የነዳጅ ዘይት ፈንድቶ ኃይለኛ እሳት ተቀሰቀሰ። ግብጽ፣ አረቢያ፣ አሜሪካ አውሮፓ ሁሉም ባቢሎን ናቸውና ተራ በተራ ይወድቃሉ!

[የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፰፥]

ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።

በብርቱም ድምፅ። ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤

አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፥ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለ ጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ።

ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ።

እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፥ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤

ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ኀዘን ስጡአት። በልብዋ። ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ኀዘንም ከቶ አላይም ስላለች፥

ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።

ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤

ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው። አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።

፲፩ የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል ያዝኑላትማል፤

፲፪ ጭነትም ወርቅና ብር የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር ቀይም ሐርም ሐምራዊም ልብስ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥

፲፫ ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።

፲፬ ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፥ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፥ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።

፲፭፲፯ እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ። በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፥

፲፰ የመቃጠልዋንም ጢስ ባዩ ጊዜ። ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች? እያሉ ጮኹ።

፲፱ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ። በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና እያሉ ጮኹ።

ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።

፳፩ አንድም ብርቱ መልአክ ትልቅን ወፍጮ የሚመስልን ድንጋይ አንስቶ ወደ ባሕር ወረወረው እንዲህ ሲል። ታላቂቱ ከተማ ባቢሎን እንዲህ ተገፍታ ትወድቃለች ከእንግዲህም ወዲህ ከቶ አትገኝም።

፳፪ በገና የሚመቱና የሚዘምሩም ድምፅ እንቢልታንና መለከትንም የሚነፉ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥ የእጅ ጥበብም ሁሉ አንድ ብልሃተኛ እንኳ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይገኝም፥ የወፍጮ ድምጽም ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፥

፳፫ የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፥ የሙሽራና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፥ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።

፳፬ በእርስዋም ውስጥ የነቢያትና የቅዱሳን ደም በምድርም የታረዱ ሁሉ ደም ተገኘባት።

_________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያ ተከብባለች – አዎን ከሁሉም አቅጣጫ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 23, 2012

P.S: Republished Post from June 2012

ያዝነው ዓመት መጀመሪያ ላይ ሳዑዲ አረቢያ በአገሯ የሚመረቱትን እህል እና አታክልት ወደ ውጭ እንዳይላኩ ከለከለች። በተለይ በሳዑዲ የሚመረት ድንች ወደ ውጭ እንዳይላክ ተከልክሏል። የተሰጠውም ምክኒያት ሳውዲ የውሃ ኃብት ይዞታዋን መንከባከብ ይገባታል የሚል ነው።

በአዲስ አበባ የተባበሩት መንግሥታት የቀድሞው የምጣኔ ኃብት አማካሪ የነበሩትና ስዊዝራንዳዊ የማሕበረሰብ አጥኚ፡ አቶ Jean Ziegler ከአንድ የስፓኝ ራዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ሳዑዲ አረቢያ ወደ ስዊዘርላንድ በኤክስፖርት መልክ አሁን የምትልካቸው ድንቾች ኢትዮጵያ ውስጥ የተመረቱ ናቸው ብለው ነበር። ከኢትዮጵያ በሳውዲ በኩል ወደ አውሮፓ ማለት ነው። የሳዑዲ ባለስልጣናትና ንጉሣን ቤተሰቦች ለህክምና ወደ ስዊዘርላንድ ይላካሉ፤ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ሆስፒታሎች የኢትዮጵያን ፍራፍሬዎች ጭማቂ ፉት እያሉ ይታከማሉ። አማካሪዎቹ እነማን ቢሆኑ ነው? የትኛውስ ጋኔን እየጠራቸው ይሆን? ከዚህ በፊት አንድ የማውቃቸው ሰውየ አዲስ አበባ መንገድ ላይ አገኘኋቸውና፤ እባክህ ልጄ ከውጭ አገር መድኃኒቱን ላክልኝአሉኝ። ደስ ይለኛል ግን መድኃኒቱ ባይፈውሰዎት እኔን እንዳይረግሙኝ፡ እዚህ እናንተ ጋር እኮ ሁሉም ነገር አለ፤ መድኃኒቱንም ቅዱሳን ተራራዎቻችን፤ አብያተክርስቲያኖቻችንና ገዳሞቻችን አጠገብ ያገኙታል፤ እስኪ ከጠበሏ ፉት ይበሉአልኳቸው። ወደጠበል እንደሄዱና ደህንነታቸውም እንደተመለሰላቸው ስሰማ በጣም ደስ አለኝ፤ እንኳን መድኃኒቱን አልላኩላቸው አልኩ። ለህክምና እያሉ ውጭ የወጡና ከፈውሱ ይልቅ በሽታ፡ ስቃይ ገዝተው የተመለሱና እድሜያቸውም ያጠረባቸው ብዙ ሰዎች አውቃለሁና። በርግጥ ዘመናዊ ህክምና አስፈላጊ የሚሆንበት ጊዜ አለ።

የነዳጅ ዘይት ለመጀመሪያ ጊዜ ከምድር በብዛት ከመውጣቱ በፊት፡ በድህነትና በኋላቀርነት ለዘመናት በበረሃ ተከብበው ይኖሩ የነበሩት አረቦች ዱሮ በገንዘብና ምግብ እጥረት የተጋለጡ ነበሩ። ከሁሉ ይበልጥ እጥረታቸው በተለይ የውሃ ጥማት ነበር። እነዚህ የበረሃ ሕዝቦች ሌት ተቀን ስለ ውሃ ነበር ሲያስቡ የሚውሉት፤ በመጀመሪያ አረቢያን ለቀው እስከ ደቡብ አውሮፓ ድረስ ለብዙ የወረራ ጦርነቶች ያደፋፈራቸው የእስልምና እምነታቸው ብቻ ሳይሆን ውሃ ለማግኘት፣ የለማ ቦታ ለማየት ከፍተኛ ፍላጎትና ናፍቆት ሰለነበራቸው ነበር። ባጠቃላይ እንደ አረብ ውሃ የሚናፍቀው ሕዝብ በዓለም ላይ የለም።

ታዲያ ይህን የውሃ ጥማታቸውን እንዴት ማርካት ይችላሉ?

የነዳጅ ዘይት ተቆፍሮ ከመውጣቱ በፊት፡ የባትሪና ኤሌክትሪክ ጥበብ በቅድሚያ ተደርሶበት ነበር። በዘመናችን በቴክኖሎጂው ቀድመው ያደጉት አገሮችና ሕዝቦች ሞተሮቻቸውን፤ መኪናዎቻቸውን ገና ከመቶ ዓመታት በፊት፡ በባትሪና በኤሌክትሪክ ሃይል የማንቀሳቀስ ችሎታው ነበራቸው። የመጀመሪያዎቹ የኤሊክትሪክ መኪና በብዛት መሠራት በጀመሩበት ወቅት አንዳንድ በነዳጅ ዘይት የሚሠሩ መኪናዎችም እንደ አማራጭ ተደርገው ይመረቱ ነበር፤ ነገር ግን የሚገማ ጭሳቸው ተዋድጅነት ስላላገኘ፡ የኤሊክትሪክ (እለቄጥሩ) መኪናዎቹ (ሠረገላዎች) ይመረጡ ፤ በሰፊውም ተቀባይነት አግኝተው ነበር።

ይህ ዓይነቱ ሁኔታ ያላስደሰተው የሉሲፈር ቡድን ግን ዓለምን በዘይት ለማስከር፤ የእግዚአብሔርን ልጆች ጤንነት ለመጉዳት እንዲሁም ተፈጥሮን ለማበላሸትና ውሃ የተጠሙትን አረብ ልጆቹን ማገልገል ስለፈለገ በነዳጅ ዘይት የሚንቀሳቀሱትን መኪናዎችና ሞተሮች እውቀቱን ባካፈላቸው አውሮፓውያን በኩል እየተመረቱ እንዲወጡ አዘዘ። ስለመጀመሪያዎቹ ኤሊክትሪክ ሠረገላዎች እዚህች ላይ ይመልከቱ

ይህን የተገነዘቡት አረቦችም እየቆዩ ነቁ ተበረታቱ (አዎፓውያን አበረታቷቸው) ፤ ውሃ የሚያገኙበትንም ጎዳና መጥረግ ጀመሩ። ቆየት ብለውም እኛ ቆሻሻውን ጥቁር ውሃ፡ ዘይትን፡ ስለምናወጣ መጀመሪያ እረፍት የሌላቸውን ምዕራባውያንን በነዳጅ እናስክር፡ ከዚያ ዶላራቸውን እየተቀበልን በ ጎተራ እያስቀመጥን እንመዝብራቸው፡ ዘይቱ ይጣፍጣቸዋል፡ ያስከራቸውማል፡ በስካራቸው ላይም እንዳሉ፡ በጠበል ውሃ ኃብት የተካነችውን ኢትዮጵያን ለረሃብና ድህነት እንዲያጋልጡልን እንቆስቁሳቸው፡ ከዚያ ኢትዮጵያውያኑ ደክመው፣ ድኽይተው በረሃብ አለንጋ ሲገረፉ፡ እኛን ለመለመን ይገደዳሉ፣ ዶላር ናፈቀን ብለው እሱን ማምለክ ይጀምራሉ፣ ከዚያ ያዘጋጀናቸውን ልጆቻችንን ለስለስ፡ ሸልሸል ብለው ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ ካደረግን በኋላ የተቀደሱትን የኢትዮጵያ የጠበል ውሃዎች መጥጠን እንጨርስባቸዋለን፤ ዱሮም ነብያችን ውሃው ሲጠማው የኢትዮጵያ አየር ሸቶት ነበር ሰላዮቹንም ወደኢትዮጵያ ተልከው እንዲሄዱ አድርጎ ነበር።ይላሉ።

የኢትዮጵያ ጠላቶች አገሪቷን ለመቆጣጠር ዳርዳር እያሉ ነው፡ የወረራውም ጊዜ እየተቃረበ ነው፤ አገራችን ከባሕር እንድትነጠል ተደርጋለች፤ በኤርትራ የሚገኙት ልጆቿም እንዲያምጹ፡ ጥላቻ እንዲገዙ ተደርገዋል፤ በዚህም ምክኒያት አደገኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በኢትዮጵያ ምድር ሰላም ጠባቂ መስሎ ሰተት ብሎ በመግባት ሥራውን እየሰራ ነው፤ ባካባቢዋ የሚገኙትም አገሮች አንድ ባንድ በጠላቶቻችን እጅ ሥር በመግባት ላይ ናቸው፤ በአየር ላይም መንኮራኩሮቻቸው በተራቀቁ ሌንሶች ታጥቀዋል ወደ አገራችንም ላይ ካነጣጠሩ ውለው አድረዋል።

በተለይ አፍጋኒስታን ልክ የኢትዮጵያ ዓይነት ተራራማ የመልክዓምድራዊ ባሕርይ ስላላት ለወታደራዊ ልምምድ አመች ነች፤ የኔቶ ወታደሮችም ለኢትዮጵያ ወረራ የሚረዳቸውን ብዙ ልምድ በአፍጋኒስታን በመቅመስ ላይ ናቸው። የአረብ ጸደይ የሚል እንቅስቃሴ እንዲደረግ በመገፋፋት ደግሞ ውጭ የሚገኙ የሰሜን አፍሪቃና የመካከለኛው ምስራቅ ተወላጆች በምን ዓይነት መልክ መንግሥታቱን መገለባበጥ እንደሚችሉ አስፈላጊውን ልምድ በመቅሰም ላይ ናቸው፤ ውጭ የሚገኙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ለዚህ ዓይነቱ ሉሲፈራዊ ዘመቻ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ በመዘጋጀት ላይ ይገኛሉ። እሽ፡ አሁን ሰሜን አፍሪቃ በነርሱ እጅ ገብታለች፣ ጅቡቲና ኬኒያ ሁልጊዜ የነርሱ ናቸው፤ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ሶማሊያና የመንም በቅርቡ ሙሉበሙሉ በነርሱ እጅ ይወድቃሉ፤ የዓለም ትኩረት በአፍጋኒስታን፣ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ፍልስጤምና ግብጽ ላይ ነው፤ ነገር ግን ትልቁ የሉሲፈር ዓይን ግን በኢትዮጵያ ላይ ነው ያረፈው።

ይህች ብዙ ምስጢር የተደበቃበት አገራችን ምን ያህል ድብቅ ኃብት እንደያዘች ለኛ ለሞኞቹ ነው እንጂ እስካሁን ያልተገለጥልን፣ ሉሲፈርማ ገና ድሮ ከአዳምና ሔዋን ጊዜ አንስቶ ነው ይህን ምስጢር ያውቅ የነበረው። አሁን የቴክኖሎጂ ነገር እጅግ እየተራቀቀ በመጣበት ዘመናችን የሉሲፈር ምርጥ ልጆች የምስጢሩ ተካፋዮች ለመሆን በቅተዋል ፤ በዓይኖቻችን ሊታዩ የማይቻሉትን አንዳንድ ረቂቅ ነገሮችንም ለማየት እየተቻላቸው ነው፤ ታይተው የማይታወቁ፡ እኛ መናፍስት የምንላቸውን ነገሮች ለመከታተል ችሎታውን እያገኙ ነው። ከዚህ ቀደም ይህን ጽሑፍ አቅርቤ ነበር፤ ይህ ቦታ የኢትዮጵያ ምስጢራት ከተደበቁባቸው ቦታዎች አይርቅም፤ እነዚህ ቦታዎች የኢትዮጵያን ብርቅ ገዳማት የሚያጠቃልል ነው። የሉሲፈር ሠራዊት ይህን ቦታ ቃኝቶ ደርሶበታል፣ የነካተሪናን አውሎ ነፋስ የሚቀሰቅሰው የእግዚአብሔር አምላክ እስትንፋሽ፣ ኃያሎቹ ቅዱሳናት ከሚገኙባቸው የኢትዮጵያ ተራራዎችና ገዳማት እንደሚፈልቅ ተገንዝበወታል።

የሉሲፈር ወገኖች ባወጡት ፕላናቸው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ በረሃብና በሽታዎች እንዲደክምና እንዲዋረድ ይደረጋል፡ በኋላም ማንነቱን ለማወቅ ስለሚሳነው ፣ አገሩን እየለቀቀ መሰደድ ይጀምራል፣ በመጨረሻም አገሩን፣ ወገኑን፣ እራሱንም አሳልፎ እስከመሸጥ ይደርሳልየሚል ሃሳብ አላቸው። ይህንንም ዕቅዳቸውን አሁን በሥራ ላይ ለማዋል በመታገል ላይ ይገኛሉ። ግማሹ የሕዝባችን ክፍል አውቆም ሆነ ሳያውቅ ለአገሪቷ ጠላቶች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ይሠራል፤ እነርሱንም በማገልገል ላይ ይገኛል፣ ገንዘብና ቁሳቁስ እንዲያፈቅር ተደርጓል፣ ሰይጣን ለ6ሺህ ዓመታት ያህል የተዋጋለትን ክቡር ነፍሡን ለሰይጣን አርበኞች አሳልፎ በመስጠት አንድ ቀን የማይቆየውን ጊዜአዊ እርካታ በመሸመት ላይ ይገኛል።

ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?” – ማር. 8 36 –

 በመጨረሻ ብዙ ተዓምር እንደምናይ፡ የኢትዮጵያ ጠላቶችም አንድ በአንድ እንደሚቀነጠሱ፡ ዓለምም ለመገረም እንደሚበቃ አንጠራጠር። አንመለስም፤ ንስሐ አንገባም ብለው የከበቡን ኃይሎች ውጊያውን የተያያዙት እጅግ በጣም ግዙፍ ከሆነውና ከማይሸነፈው ኃይል ጋር ነው።

_____________________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: