Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • December 2022
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  262728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘የነነዌ ጾም’

ትንኮሳ በመምህር ምህረተአብ ላይ | አይደለም መፈረም ሞት ተዘጋጅቷል ቢባል ለመታረድ ዝግጁ ነን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2020

ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ፥ ማክሰኞ የካቲት ፫ / ፪ሺ፲፪ ዓ./ በዓታ

አሁን ሁላችንም እንዘጋጅ፣ ሁላችንም እንቁረጥ፣ እንጨክን! እኔ ብታሠር ወንጌል አይታሠር፣ ካህናቱ ሁሉ ቢገደሉ ክህነቱ አይሞት፣ ቤተ ክርስቲያን አትጠፋ.…

እምንሞትም እኛ ፥ እምንበዛም እኛ ፥ እሚገሉም እነሱ ፥ እሚያለቅሱም እነሱ ፥ እሚገፉም እነሱ ፥ እሚወድቁም እነሱ ፥ እሚነቅሉም እነሱ ፥ እሚነቀሉም እነሱ ፤ ግን ማድረግ ያለብንን ድርሻችንን ማድረግ አለብን።

____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ኦሮሞ ፖሊሶች በመምህር ምህረተአብ ላይ ፀያፍ ተግባር ሞከሩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 11, 2020

በመስቀል አደባባይ ለተቃውሞ ሰልፍ እንዳትወጡ አሉን፣ ከዚያም ቦታውን ለማርከስ ሰይጣናዊውን ኢሬቻን አከበሩበት፤ አሁን የልብ ልብ ብሏቸው ቤተክርስቲያን ውስጥ እየገቡ መተናኮስና መግደል ጀምረዋል። አዎ! ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቍ!

ነጠብጣቦቹንእናገናኝ፦

+++ ዕለተ መስቀል ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ግቢ ፥ በሬው ተጋድሞ ክፉኛ ይንቀጠቀጣል+++

መምህር ዘመድኩን በቀለ እንዳካፈለን፦

ትናንት ምሽት በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በሚገኘው በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የተደረገውን ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ደፋሩ የኦሮሚያ ፖሊስ በጉባኤው መምህር በመ/ር ምህረተ አብ ላይና በደብሩ አስተዳደር ላይ ያደረገውን ትንኮሳ እንደ ቀላል፣ እንደዋዛ አትመለከተው። ትናንት ፎሊስ ነፍሴ በአንድ ድንጋይ 100 ወፍ ለመምታት ነበር አቅዶ መጥቶ የነበረው። ፎሊስ ነፍሴ ከድንጋዩ ሌላም የሙቀት፣ የስሜት መለኪያ ቴርሞ ሜትርም ይዞ ነበር የመጣው። የ75 ሚልየን ኦርቶዶክሳዊያንን የልብ ትርታና ስሜት፣ የመምህሩንና የቤተክርስቲያኒቱንም አስተዳደር አቋምና ሙቀት ለመለካትም ነበር ዊኒጥዊኒጥ እያለ ዘው ብሎ መጥቶ የነበረው።

ፎሊስ ነፍሴ አስቀድሞ የጉባኤውን አዘጋጆች መረመሩ፣ ስሜታቸውንም ኮርኩረው በማስፈራራት መምህር ምህረተአብ እንዳይመጣና በጉባኤው ላይ ሳያስተምር እንዲመለስ እንዲያደርጉ ወተወቱአቸው፣ ቃታ ስበው አስፈራሩዋቸው። አዘጋጆቹ፣ የጉባኤው አስተባባሪዎችም መለሱላቸው አፍጥኑት፣ ሰማእትነት ብርቃችን ነው እንዴ? በማለት ቴርሞ ሜትሩን አከሸፉት።

ፎሊስ ነፍሴ በአስተናጋጆቹና በጉባኤው አስተባባሪዎች ላይ የዘረጋው የሙቀት መለኪያ እንደከሸፈ ሲያውቅ በቀጥታ ወደ ደብሩ አስተዳደር ቢሮ ገብቶ አለቃውን ከቤተ ክርስቲያን ውጪ አንድ ጊዜ እንዲያናግሩን ብለው በመጥራት ሌላ ዕድል ሞከሩ። አስተዳዳሪውም ከቢሮዬ አልወጣም። የሚፈልገኝ ቢሮዬ ይምጣ፣ ጉባኤውም በሰዓቱ ይካሄዳል። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የምናዘጋጀውን ጉባኤ የሚከለክለን አንዳችም ምድራዊ ሕግ የለም ብለው በአቋማቸው ጸኑ። ፎሊስ ነፍሴም ይሄኛው ሁለተኛው ቴርሞ ሜትሩም ዐይኑ እያየ እጁ ላይ ቋ ብሎ ተሰበረ።

ፎሊስ የመጨረሻ ሙከራውን በምእመናኑ ላይ ለማድረግ ሞከረ። ግርግር፣ የፖሊስ መዓት በአካባቢው እንዲተራመስ፣ ቤተ ክርስቲያኑ መግቢያ በሮች ላይ የታጠቀ ሠራዊት በማፍሰስ፣ የህዝቡን ሀሞት ለማፍሰስ፣ በዚያውም የሙቀት መጠናቸውን ለመለካት በእጅጉ ጣረ። ጭራሽ ህዝቡ እንኳን ሊፈራ ፎሊስ የመጣው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ስላለ ለዚያ ጥበቃ እንጂ ጉባኤውን ለማጨናገፍ ነው ሳይል ወደ ጉባኤው ነጠላውን መስቀለኛ አጣፍቶ ተመመ። ፎሊስ ነፍሴ ቴርሞ ሜትሩን ይዞ ዊኒጥ ዊኒጥ ቢል ሰሚ አጣ። በሰጨው። ይሄም ከሸፈ።

የመጨረሻ ሙከራው ምህረተ አብን መተናኮል ነው። እኛ ፈቃድ ሳንጠየቅ፣ እኛ ሳናውቅ ይሄ ሁላ ሺ ህዝብ እንዴት ይሰበሰባል? ብሎ ኮማንደር ፍጹም ወበራ፣ በምህረተ አብ ላይ መንገድ ተዘጋ። ወደ ጉባኤው እንዳይመጣ ከመጣ ለሚፈጠረው ትርምስ ኃላፊነቱን እንዲወስድ በገደምዳሜ፣ በሾሬኔ ተነገረው። ይሄ የመጨረሻው የፎሊስ የሙቀት መለኪያ ዘዴው ነበር። “ እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” የሚለውን መመሪያ መጠቀሙ ነበር ፎሊስ ነፍሴ።

ዑራኤል በነበረው ጉባኤ መምህር ምህረተ አብ አሠፋ ስለ ሰማእታት ክብር አስተምሮ ነበር። በጉባኤው ላይ የነበሩ የ24 ቀበሌ ወጣቶች የዚያኑ ዕለት በታከለ ኡማ የፎሊስ ሠራዊት ተረሽነው የሰማእትነት አክሊልን ተቀብለዋል። ምህረተአብ ልቡ በጣም ተነክቷል፣ አልቅሷል፣ አዝኗል። የሰማእታቱ የቀብር ሥነሥርዓት ላይም ይሄው ስሜቱ በግልጽ ይነበብበት ነበር።

መመህር ምህረተ አብ በዘመነ ህወሓት በብቸኝነት ለአክራሪ እስላሞች መልስ በመስጠት የተጋፈጠ ወንድሜም መምህሬም ነው። ለጥያቄ ፎሊስ ጣቢያ በተጠራ ቁጥር በደስታ ሲሄድ አውቀዋለሁ። መምህር ምህረተ አብ ፓስተር ዳዊት በግልጽ ለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የይቅርታ ደብዳቤ እንዲጽፍ ያስደረገም ጀግና ነው። ሲኖዶሱ ዝም ባለ ጊዜ ሁሉ ለቤተክርስቲያን አንደበት የሆነ የስስት ልጇ ነው። አይደክመውም፣ ታምሞ እንኳ ጉባኤ የቀረበትን ዘመን አላስታውስም።

እነ ዛኪር ፣ እነ አህመዲን ዲዳት አክራሪ የወሀቢይ እስላሞቹ በቤተ ክርስቲያን ላይ በተነሱ ጊዜ ብቻውን በሲዲም በቪሲዲም መልስ በመስጠት አንገታቸውንም የሰበረም መምህር ነው። ማስፈራሪያ፣ የእንገልሃለን ዛቻን ከቁብም ሳይቆጥር በፅንአት ቤተ ክርስቲያንን ያገለገለም ነው ምህረተ አብ።

ለእኔ ደግሞ ሲበዛ ወንድሜ ነው። በቅርብ አሳምሬ አውቀዋለሁ። ከመጀመሪያ የዐውደ ምህረት ላይ አገልግሎት ዘመኑ ጀምሮ አሳምሬ አውቀዋለሁ። “አለን” የሚለውን ዝማሬ በአንድ ላይ በእኔዋ “ ጌልገላ መንፈሳዊ መዝሙር ቤት” አማካኝነት በሠራንበት ወቅት ከስብከት ውጪ ያለውን ዕምቅ የግጥምና ዜማ ፀጋውንም በሚገባ አይቻለሁ። በስደት ዘመኔ ወቅት ለልጆቼ በቅርብ እንደ አባት እኔን ተክቶ በጉድለታቸው ሁሉ ይሞላ የነበረም ወንድሜ ነው። ሁሉ በከዳኝ ወቅት ከአጠገቤ የቆመ ያልተለየኝም ነው መምህር ምህረተ አብ። በእነ በጋሻው ደሳለኝ ክስ ስታሰርም ጠያቂዬ ነበር። ልጆቼ እንዳይርባቸው፣ ቤተሰቤ እንዳይበተን፣ እንዳይራብ እንዳይበተንም ያደረገም ወንድሜ ነው ምህረተ አብ። ሲበዛ ሃይማኖተኛ ነው።

በቅርቡ ወላይታ በነበረ ጉባኤ ላይ በ3 ቀን ጉባኤ የእነ ኢዩ ጩፋ መጫወቻ የነበሩና ከበረቱ፣ ከጋጣው ወጥተው የነበሩ የወላይታን ልጆች የተዋሕ በጎችን መመለሱ በፕሮቴስታንቶቹ ዘንድ ብዙም አልተወደደለትም። የማንቂያ ደወል ብሎ ይሄን ፍራሽ ጎዝጉዞ ጫትና ሺሻ ላይ የተወዘፈውን፣ የተዘፈዘፈውን የከተማ ወጣት የግዱን በእግዚአብሔር ቃል እየገረፈ ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲመለስ ማድረጉንም ሰይጣን ዲያብሎስም አልወደደለትም። ምሮኮ ነጣቂ ነው ምህረተ አብ።

በንግሥ ቀን እንኳ ሰው የማይሞላባቸው፣ ሚልዮኖችን ውጠው ቅም የማይላቸው እነ ቦሌ መድኃኔዓለም። ጉርድ ሾላ ሲኤምሲ ሰዓሊተ ምህረት፣ አዲሱ ሚካኤል መርካቶ አውቶቡስ ተራ ከቅፅረ ቤተ ክርስቲያን አልፎ ዋናው መጋቢ መንገዱ እስኪዘጋጋ ድረስ ጉባኤ ማድረጉ ለሌሎች አሁን ፕሮጀክት ዘርግተው ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ለሚፈልጉ አካላት ፈጽሞ አልተመቻቸውም። ምቾት አልሰጣቸውም። ይበሰጫሉ። ኢትዮጵያን መውደዱ፣ ሰንደቋን ከፍአድርጎ ለብሶ መድመቁም ቋቅ የሚላቸው የትየለሌ ናቸው።

ምህረተ አብ እንደሌሎቹ አገልጋዮች አሜሪካና አውሮጳ ብቻ እየዞረ ኮሚሽኑን እየለቀመ ዘና ብሎ እንዲኖር የመንግሥትም የሰይጣንም ፍላጎት ነው። ምህረተ አብ ግን የአውሮጳም የአማሪካም ኑሮን አልፈለገውም። ልጁንና ሚስቱን አውሮጳ ለንደን ትቶ ከህዝቤ ጋር መከራን መቀበሉ ይሻለኛል ብሎ የተሻለውንና ከሁሉ የሚበልጠውን መርጦ ከወገኑ ጋር ከገጠር እስከ ከተማ መከራም ሆነ ደስታ ለመካፈል የቆረጠና ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ላቡን ወዙን ለተዋሕዶ እያፈሰሰ ያለ ጀግና የተዋሕዶ ልጅ ነው። እስከአሁን በተቻለው ሁሉ እናት ቤተክርስቲያንን ሳይከዳ ከፊት መስመር ተሰልፎም ፍልሚያውን እየመራ ያለም ጀግና ሐዋርያ ነው።

በአሁን ሰዓት ከመምህር ምህረተ አብ በቀር ዐውደምህረቱ ላይ ሌላ ማን አለ? አንዳንዴ መምህር ጳውሎስ መልክአ ሥላሴን፣ ሌላ ጊዜ መምህር ዘላለም ወንድሙን እንደ መስቀል ወፍ ብቅ ብለው ከምናይ በቀር ማን አለ? ምህረተ አብ ነው አሁን ከፊት መስመር እየተጋፈጠ ያለው። ፌስቡክን እየተጠቀመ፣ መረጃ እያስተላለፈ፣ ለህዝብ በቅርብ ተፈልጎ የሚገኘው ምህረተ አብ ብቻ ነው። እናም ይሄን በሰገነት ላይ ያለ መብራት ለማጥፈት ነው የኦሮሚያ ፖሊስ ትናንትና ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ድረስ በድፍረት ቴርሞ ሜትሩን ይዞ የመጣው።

እግዚአብሔር ያሳያችሁ፣ መድኃኔዓለም ያመልክታችሁ። በዚህ በየፌርማታው፣ በየገበያው፣ በየአውራጎዳናው፣ በየአውቶቡስና ታክሲ መያዣው፣ “ ኢየሱስን ካልተቀበላችሁ ሞተን እንገኛለን ” ብለው የፍንዳታ መዓት፣ የወጠጤ መዓት፣ በአነስተኛና ጥቃቅን የተደራጁ የፕሮቴስታንትና የወሀቢይ እስላሞች ሳይቀር የጆሮአችን ታምቡር እስኪበጠስ ድረስ እዬዬዬዬ እሪሪሪሪ ቋቀምበጭ እያሉ መከራ በሚያበሉን ዘመን በራሷ ዐውደምህረት ላይ ለምታደረግው ዘወትር የተለመደ ጉባኤ ፍቃድ አምጡ ማለት የጤና አይመስልም። ይሄ ከባድ ንቀት ነው። እጅግ ከባድ ንቀት ነው።

የመጨረሻውንም የሙቀት መለኪያ ልኬቷ ቋ እንቀጭ አድርጎ ፎሊስ እጅ ላይ ከሽ አድርጎ ምህረተአብ በታላቅ ክብርና ሞገስ ወጥመዱን ሰባብሮ፣ መረቡን በጣጥሶ የተለመደ አገልግሎቱን ሰጥቶ ጉባኤውን በሰላም ፈጽሟል። ዛሬስ እሺ ነገ ምን ሊኮን ነው? ዘንዶው ደፋር ነው ቱ ምን አለበሉኝ ቅድስተ ማርያም ሄዶ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያላወከ እንደሆን? ዛሬ ለስብከት ፍቃድ የጠየቀ ፎሊስ ነገ ለቅዳሴ አስፈቅዱኝ ያላለ እንደሆን ምን አለ በሉኝ። እነማን ናቸው የሚቀድሱት፣ ሰሞነኞቹስ እነማን ናቸው ያላለ እንደሆን ጠብቁ። በዚህ ድፍረቱ ገና ብዙ ታሪክ ያሳየናል።

ለማንኛውም አሁን ሁላችንም እንንቃ። ጎበዝ ጫትህን ትፋ። ሲጋራህን ጣል። ሀሺሽ ሺሻህን አስወግድ፣ አንቡላ ካቲካላህን አረቄ ድራፍትህን ድፋ። በየጋለሞታ ጭን ስር አትርመጥመጥ። ጹም፣ ጸልይ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያን ተመለስ። በዕድሜ እኩያህ በፀጋ አባትህ ከሆነው ከመምህር ምህረተ አብ ጎን ቁም። ንስሀ ግባ፣ ሥጋወደሙ ተቀበል። ተዘጋጅተህም ሁሉን ነገር ጠብቅ። አንተ የተኛህ በቶሎ ንቃ።

የፌስቡክ ላይ ፉከራ ብዙም አያዋጣም። ፍከራው ይቅርና መሬት ላይ ቁምነገር ለመሥራት ወስን። በዘወትር ጉባኤያት ላይ በአካል ተገኝ። ተማር፣ ዘምር፣ መስክር። አስቀድስ፣ ተቀደስ። ፀበል ጠጣ፣ ተጠመቅ፣ እምነት ተቀባ፣ በመስቀል ተዳሰስ፣ አንገትህ ላይ ማዕተብህን አጥብቀህ እሰር። በደንብ አጥብቅ እሰረው። በየሰፈሩ፣ በየቤትህ፣ ተሰባሰብ፣ ተመካከር። ተወያይ፣ ተነጋገር። እንደጤዛ ጠዋት ደምቀህ ረፋድ ላይ አትርገፍ። ጽና!!!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Russia: US Becoming a Godless Nation

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 10, 2014

NenAt the height of the Cold War, it was common for American conservatives to label the officially atheist Soviet Union a “godless nation.”

More than two decades on, history has come full circle, as the Kremlin and its allies in the Russian Orthodox Church hurl the same allegation at the West.

Many Euro-Atlantic countries have moved away from their roots, including Christian values,” Russian President Vladimir Putin said in a recent keynote speech. “Policies are being pursued that place on the same level a multi-child family and a same-sex partnership, a faith in God and a belief in Satan. This is the path to degradation.”

In his state of the nation address in mid-December, Mr. Putin also portrayed Russia as a staunch defender of “traditional values” against what he depicted as the morally bankrupt West. Social and religious conservatism, the former KGB officer insisted, is the only way to prevent the world from slipping into “chaotic darkness.”

As part of this defense of “Christian values,” Russia has adopted a law banning “homosexual propaganda” and another that makes it a criminal offense to “insult” the religious sensibilities of believers.

The law on religious sensibilities was adopted in the wake of a protest in Moscow’s largest cathedral by a female punk rock group against the Orthodox Church’s support of Mr. Putin. Kremlin-run television said the group’s “demonic” protest was funded by “some Americans.”

Mr. Putin’s views of the West were echoed this month by Patriarch Kirill I of Moscow, the leader of the Orthodox Church, who accused Western countries of engaging in the “spiritual disarmament” of their people.

In particular, Patriarch Kirill criticized laws in several European countries that prevent believers from displaying religious symbols, including crosses on necklaces, at work.

The general political direction of the [Western political] elite bears, without doubt, an anti-Christian and anti-religious character,” the patriarch said in comments aired on state-controlled television.

We have been through an epoch of atheism, and we know what it is to live without God,” Patriarch Kirill said. “We want to shout to the whole world, ‘Stop!’”

Although Mr. Putin has never made a secret of what he says is his deep Christian faith, his first decade in power was largely free of overtly religious rhetoric. Little or no attempt was made to impose a set of values on Russians or lecture to the West on morals.

However, since his inauguration for a third presidential term in May 2012, the increasingly authoritarian leader has sought to reach out to Russia’s conservative, xenophobic heartland for support.

It has proved a rich hunting ground.

Western values, from liberalism to the recognition of the rights of sexual minorities, from Catholicism and Protestantism to comfortable jails for murderers, provoke in us suspicion, astonishment and alienation,” Yevgeny Bazhanov, rector of the Russian Foreign Ministry’s diplomatic academy, wrote in a recent essay.

Analysts suggest that Mr. Putin’s shift to ultraconservatism and anti-West rhetoric was triggered by mass protests against his rule that rocked Russia in 2011 and 2012. The unprecedented show of dissent was led mainly by educated, urban Muscovites — many with undisguised pro-Western sympathies.

Some 70 percent of Russians define themselves as Orthodox Christians in opinion polls, and opposition figures in the past have called on the church to play a mediating role between the Kremlin and protesters.

Source

የተገለባበጠች ዓለም

horseinalandscap2የክረምትኦሎምፒክ ጨዋታዎች በሩሲያዋ የሶቺ ከተማ እየተካሄዱ ናቸው። እነዚህን ጨዋታዎች ለማጨናገፍ በሉሲፈራውያን የሚደገፉት ሽብር ፈጣሪዎች በመቁነጥነጥ ላይ ይገኛሉ። በሚያስገርም ፍጥነት በሰዶማውያን እጅ በመግባት ላይ የሚገኙት የምእራባውያን መገናኛ ብዙኃን በጣም ኋላቀር፣ ቅሌታማና አሰልቺ የሆነውን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳቸውን በሞኙ ኦርቶዶክስ ሩሲያ ሕዝብ ላይ በመንዛት ላይ ይገኛሉ። ሁሉም እርስበርስ የጥላቻ ውድድር የሚያካሂዱ ነው የሚመስሉት። ዓለምን በማመስ ላይ የሚገኙት እና ሁልጊዜ አቱኩሮት ፈላጊዎቹ እስላማውያንና ሰዶማውያን መድረኩን ለጽንፈኛ ጩኽታቸው ሲጠቀሙበት ይታያሉ። እንደ እነ ኦባማ የመሳሰሉትም የሉሲፈራውያን መሣሪያዎች ወደ ሶቺ መሄዱን አልፈለጉም፡ ነገር ግን ሰዶማውያን ቱጃሮቻቸውን ወደዚያ በመላክ ሩሳውያኑን ይተናኮላሉ። እነዚህ አውሬዎች ዒላማቸውን ያነጣጠሩት በኦርቶዶክስ ክርስቲያናውያን እና በአፍሪቃውያን ላይ ነው። ኡጋንዳና ናይጀሪያ ፀረሰዶማዊ የሆነ ህግ ባረቀቁበት ባለፈው ሰሞን፡ ሕንድም ተመሳሳይ ህግ አውጥታለች፣ ነገር ግን የምእራቡ ዜና ማሠራጫዎች የወቀሳ ዘመቻ ያተኮረው በአፍሪቃውያኑ ላይ ብቻ ነው።

ለ ቢቢስ የሚሠሩ ሁለት አፍሪቃውያን ጋዜጠኞች በቅርቡ አርፈዋል። በበሽታ ምክኒያት እንዳረፉ ነው በይፋ የተነገረው። ሁለቱ ጋዜጠኞች የጋና እና የኬኒያ ተወላጆች ነበሩ። አዎ! የሚገርም ነው፡ ጋናውያን እና ኬኒያውያን፡ (ከዚህ በፊት ገልጬ ነበር) ከሁሉ አፍሪቃውያን ለፈረንጅ በጣም ማጎብደድ የሚወዱ ሕዝቦች ናቸው፤ መቼም ሰው ካረፈ በኋላ መፍረድ በጎ አይሆንም፡ አምላኬ ይቅር በለኝ፡ ግን፡ እነዚህ ሁለት ጋዜጠኞች በቢቢሲ ቆይታቸው አፍሪቃውያንን በበጎ መልክ ሲያቀርቡና ለአፍሪቃ በስሜት ሲከራከሩ የነበሩ ጋዜጠኞች አልነበሩም፡ ሆኖም፡ እንደ አብዛኛው አፍሪቃውያን ፀረ=ሰዶማዊ የሆነ አቋም ነበራቸው፤ ቢቢሲ ደግሞ በተበቃዮቹ ሰዶማውያን እጅ የገባ ተቋም ስለሆነ፡ እንደ ባሪያያስጠጋው ሰው ሲያጉረመርምበት ያስቆጣዋል። በአፍሪቃውያን ጋዜጠኞች ዘንድ እከሌ በልብ በሽታ ሞተተብሎ ስሰማ ምናልባት ይህ 10ኛ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም። ታዲያ እነዚህም ጋዜጠኞች ለሕፃናትደፋሪዎቹ የቢቢሲ ሠሪዎች ተንኮል ተጋልጠው ይሆን? ለማንኛውም ቢቢሲ እስያውያንን እንጂ አፍሪቃውያንን በብዛት አይቀጥርም/አያቀርብም፤ ሬዲዮና ቴሊቪዥኑን የሞሉት እስያውያን ብቻ ናቸው!

ለኢትዮጵያውያን የምድር ሲዖል የሆነችውንና እስክ ሁለት መቶ ሺህ የሚጠጉ ወገኖቻችንን ባጭር ጊዜ ውስጥ ከአገሯ ሙልጭ ብለው እንዲወጡ ያደረገችውን ሳዑዲ አረቢያን ፕሬዚደንት ኦባማ በመጪው ወር ለመጎብኘት አቅደዋል። ቀደም ሲል፡ የውጭ ጉዳይ ሚንስትራቸው፡ ጆን ኬሪ፡ ሪያድ ከተማ በገቡበት ዕለት ነበር ኢትዮጵያውያን እንደ እንስሳ ሲታደኑ የነበሩት። በመጭው ወር ደግሞ ፕሬዚደንት ኦባማ ለዚህ ጀብደኛ‘” ተግባር ለሳዑዲው ንጉሥ ምስጋናቸውን እንደተለመደው ጎንበስ ብለው ያቀርባሉ። የአፍሪቃው ህብረት 50ኛ ዓመቱን በሚያከብሩበት ዓመት ወደ አዲስ አበባ መሄድ አሻፈረኝ ያሉት አፍሪቃአሜሪካዊውኦባማ በሰው ልጆች ላይ ተወዳዳሪ የሌለው በደልን በምትፈጽመው ሳዑዲን ለሦስተኛ ጊዜ ይጎበኛሉ።

ሰኞ የ ነነዌጾምይገባል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በዚህ ጊዜ ነበር ሉሲፈራውያኑ የኢትዮጽያ አየር መንገድን ቤይሩት/ሌባኖን ሰማይ ላይ መትተው በመጣል ብዙ ወገኖቻችንን ለመግደል የበቁት። በአሁኗ ሰሜን ኢራቅ የምትገኘዋ ነነዌ አሁን እራሷን እንድታስተዳደር እና ብሔራዊ ቋንቋዋም ጥንታዊው ሶሪያኛ ቋንቋ (አራሜይክ) እንዲሆን ሰሞኑን ታወጆ ነበር። ይህ አዋጅ ቢዘገይም፣ ደህና፡ ይሁን! እንበል። ለማንኛውም የክርስቶስ ጠላቶች ሙሉ በሙሉ እስካልተምበረከኩ ይህን መሰሉ የቀዶጥገና ተግባር ዋጋ አይኖረውም። መጪዎቹ ቀናት ብዙ አስገራሚ ነገሮችን የምናይባቸው ይሆናሉ!

መልካም ጾመ ነነዌ!

__

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መገሰጽና ለእነርሱ መጸለይም ይገባናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2013

ዳኛው ፈራጁ ሁሉን ነገር የሚያየው እርሱ ንጉሡ ክርስቶስ ብቻ ነው!

በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።”[ትንቢተ ሶፎንያስ.118]

ባዕዳውያኑ የአገራችን ጠYonasNAsaላቶች ምንም ሳናደርጋቸው፤ ሳንደርስባቸው በሕዝባችን ላይ ያደረሱት በደል በዓይነቱ በጣም አስከፊ በመጠኑም እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡ ለሃሳብ እንኳ የሚያንገፈግፍ ነው። አንመኝላቸውም፡ ግን የፍትህ አምላክ፡ ኅያሉ ፈጣሪያችን መቅሰፍቱን ያወርድባቸዋል፤ ሌላ አማራጭም ያለ አይመስልም።

በመጪዎቹ የጾምና የጸሎት ቀናት እንድንድንና እንዲድኑ ልዩውን ጸሉት ልናደርስ ይገባናል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅም በክህደታዊ መንገድ ከጠላቶች ጋር በመመሳጠርና በመተባበር ወንድሞቹን፣ እህቶቹን እንዲሁም ልጆቹን ለአውሬው አሳልፎ ለሚሰጠው ኢትዮጵያዊጊዜው ሳይረፍድ እንጸልይላቸው፤

ማንነታቸውን ክደው የክርስቶስ አምላክን ልብ ለሚያቆስሉት፡

 • ለተታለሉት የባዕዳውያን እምነት ተከታዮች ሁሉ እንዲድኑ ፀሎት እናድርስላቸው

 • የክርስቶስን ደናግልት ህፃናት ለባእዳዊ ሰዶማውያን ለሚያስረክቡት እንዲድኑ እንጸልይላቸው

 • የክርስቶስ ልጆች እንዳይበዙ የእህቶቻችንን ማሕፀን ለሚመርዙት ጨካኝ ውገኖች እንዲድኑ እንጸልይላቸው

 • በክርስቶስ ስም የተጠመቁትን እህቶቻችንን ለአረማውያኑ ጣኦትአምላኪ ባዕዳን አሳልፈው ለሚሰጡት የዘመኑ ጂፋሮች እንዲድኑ እንጸልይላቸው

 • የክርስቶስን ገናናነትና ክብር ለመቀነስ የናዝሬትን፣ የደብረ ዘይትንና የመሳሰሉትን የኢትዮጵያ ቦታዎች ስም በዘፈቃድ ለሚቀይሩት ምስጋናቢሶች እንዲድኑ እንጸልይላቸው

 • ውጩ አገር ሆነው፡ ቸሩ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ ቸል በማለት እራሳቸውን በስንፍና የስድብና ጥላቻ ማዕበል ውስጥ ለከተቱና ወገናቸውንና ቅድስት ቤተክርስቲያናቸውን በድፍረትና በትዕቢት ለሚያዋርዱት እንዲድኑ ጸሎቱን እናድርስላቸው።

ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ[ሉቃስ 21:16]

ኒፈሌያዊ የደመና መጋረጃዎች ባገራችን ሰማያት ላይ ተዘርግተዋል፡ ነገር ግን የጽዮን ልጆች በእግዚአብሔር ብርኃን የተከበቡ፡ በፍቅሩ የታጠሩ ናቸውና የእርሱ ኃይል ይጠብቃቸዋል፡ የሚያሸነፋቸውም ኅይል የለም። የቃልኪዳኑ ልጆች ያሉበት ቦታ ሁሉ አምላካችን ስላለ ሁሉ ነገር ጥሩ ነው፡ ቸር ነው፤ በቤቱ ለዘላለም ለመኖር ተመርጠዋልና።

የቅዱሳን አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን፡ ልክ እንደ ክርስቶስ፡ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት በአሣ ሆድ አሳድሮ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቆ እንዳዳነው እኛንም ከመጥፎ ነገር ይከላከለን ከመቅሰፍት ይጠብቀን። አሜን!

ትንቢተ ዮናስ

ምዕራፍ አራት

የተናገረው ቃል ስላልተፈጸመ

ዮናስ ተቆጥቶ እያጕረመረመ

እንደዚህ እያለ ጸለየ ወደ አምላክ

እኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክ

አስበህ ብታዘኝ ይህንኑ ዐውቄ

ወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄ

ምሕረትህ የበዛ መሓሪና ታጋሽ

በደል የምትረሳ ከቍጣ ተመላሽ

የቍጣህን ያህል ምሕረትህ የጠና

መሆንክን ጥንቱንም እኔ ዐውቃለሁና

እኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበር

ሐሰት ተናግሬ የማይሆን ነገር

አልፈልግምና ቆሜ ለመኖር

ክከተማ ወጥቶ በምሥራቅ በኩል

ከወደ ዳር ሆኖ ነነነዌን ሊያስተውል

ምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስ

ሠርቶ ተቀመጠ አንድ ትንሽ ዳስ

እግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎ

ቅሉም አደገና ከፍ ከፍ ብሎ

የዮናስ ራሱ እንዲያገኝ ጥላ

ለፀሓዩ ንዳድ ሆነለት ከለላ

በዚህ በቅል አገር ዮናስን ደስ አለው

እንዲህ ቶሎ ደርሶ ስላገለገለው

እግዜር በማግሥቱ ጧት በማለዳ

ቅል የሚበላ ትል ፈጣሪ አሰናዳ

ትሉ ቅሉን በልቶ በፍጥነት ደረቀ

ፀሓይ ወጣችና ግዜው በጣም ሞቀ

እግዜር አዘዘና ትኩስ ነፋስ መጣ

የሚከለልበት መጠጊያ ስላጣ

ቅሉ ደረቀና ንዳድ ቢያቃጥለው

ዮናስ ተበሳጭቶ ላምላክ እንዲህ አለው

እንደዚህስ ሆኜ ቆሜ ከምኖር

እባክህ ግደለኝ ልሙት ለቀበር

ደረቀብኝ ብለህ ይህን ቅል ለማጣት

እውን ይገባል ወይ ያንተ አሁን መቆጣት?

ብሎ እግዜር ቢጠይቅ መለሰ ዮናስ

በንዴቴ ብዛት እስክሞት ድረስ

አዎን ይገባኛል መናደድ መጤስ

እግዜርም መለሰ ለምን ጠፋ ስትል

ይህ ያልለፋህበት ያልደከምህበት ቅል

አንተ ስትናደድ ፈጥሬአት እኔማ ሳጠፋት ሳፈርሳት ነነዌን ከተማ

መቶ ሓያ ሺህ ነው የሕዝብዋ ብዛት

ለምን ትቆጣለህ እኔ ባዝንለት

ብሎ በምሳሌ ሲያስተምር ይቅርታ

ለዮናስ ነገረው የምሕረቱ ጌታ

ለእግዚአብሔር ቸርነት ምስጋና ይድረስ

ከክቡር አቶ ከበደ ሚካኤል የቅኔ አዝመራ ከሚለው የተወሰደ (1956)

ከምዕራፍ 1-3 PDF እዚህ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: