Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 14, 2020
ባለፈው ሳምንት ሐምራዊቷን የፋሲካ ጨረቃ አይተናታል…አሁን ደግሞ እየመጣ ያለውን እንከታተል…”ምስጋና ለኮሮና ፥ አንበጣ ይምጣ!” የምንልበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ከጠላቶቻችን ውድቀት ይልቅ የፍትሕ አምላክ እግዚአብሔር የሚሰጠው መልስ በይበልጥ ያስደስታል።
- ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን አግተህ ያንተ ልጆች ብቻ ሊማሩ?
- ኢትዮጵያውያንን አስርበህ ያንተ ልጆች ብቻ ሊመገቡ?
ፋሲካን ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመሩት የእስራኤል ልጆች ናቸው ። በዓሉንም ማክበር የጀመሩት ከግብጽ ነው።
ኦሪት ዘጸአት ምዕራፍ ፲፪
እግዚአብሔር በግብጻዊን ምክንያት በእስራኤላዊያን ላይ ሲደርሱ የነበሩ በርካታ ችግሮችን :- ጡብ መስራት ግርፋት መጨረሻ ላይም የእስራኤል ሴቶች የሚወልዷቸው ህጻናት ወንዶች ከሆኑ እንዲገደሉ ልምድ አዋላጆችን አሰልጥኖ ማሰማራት…ይህ ሁሉ ግፍ ሲደርስባቸው እስራኤል ወደ እግዚአብሔር ጮሁ እግዚአብሔርም ጩኸታቸውን ሰምቶ ሙሴንና አሮንን “ያመልከኝ ዘንድ ህዝቤን ልቀቅ” የሚል መልዕክት አስይዞ ወደ ንጉሥ ፈርኦን ላካቸው። ፈርኦን ግን ልቡ ደንዳና ስለነበረ እግዚአብሔር ማነው? ህዝቡንም አልለቅቅም አለ ይልቁንስ በእስራኤል ላይ የባሰ ጫና መፍጠር ጀመረ :-ትናንት ጡብ እንዲሰሩ ገለባ ይሰጣቸው ነበር አሁን ግን ገለባውን ራሳቸው ከየትም እንዲያመጡ የጡቡ ቁጥር ግን ከትናንቱ እንዳያንስ ተወሰነባቸው ። ከዚህም የተነሳ እስራኤል አሁንም ይጮሃሉ ።
በዚህም ምክኒያት እግዚአብሔር በግብጽ ላይ መቅሰፍት ማውረድ ጀመረ።
መቅሰፍቶችም:-
- ፩.የሙሴ በትር እባብ መሆን ዘጸአት ፯፥፰፡፲፫
- ፪.የደም መቅሰፍት (የግብጽ ወሃ ሁሉ ወደ ደም መቀየር) ዘጸአት ፯፥፳፡፳፰
- ፫.የጓጉንቸር መቅሰፍት ዘጸአት ፰፥፩፡፲፭
- ፬.የተባይ (የቅማል)መቅሰፍት ዘጸአት ፰፥፲፮፡፲፱
- ፭.የዝንብ መቅሰፍት ዘጸአት ፰፥፳፡፴፪
- ፮.የእንስሳት እልቂት ዘጸአት ፱፥፩፡፯
- ፯.የእባጭ(ቁስል) መቅሰፍት በሰውና በእንስሳት ላይ ዘጸአት ፱፥፰፡፲፪
- ፰.የበረዶ መቅሰፍት ዘጸአት ፱፥፲፫፡፴፭
- ፱.የአንበጣ መንጋ መቅሰፍት ዘጸአት ፲፥፩፡፳
- ፲. የጨለማ መቅሰፍት ዘጸአት ፲፥፳፩፡፳፱
ይህ ሁሉ ሲሆን ፈርኦን እስራኤልን አልለቅቅም አለ። ስለዚህ አሁን የቀረውና የመጨረሻው የፋሲካን በዓል ማክበር ነው።
ላይ እንደተጠቀሰው የእስራኤል ልጆች ፋሲካን የጀመሩት በግብጽ ሳሉ ነው።
በእነሱ የዘመን አቆጣጠር በመጀመሪያ ወር ወሩም በገባ በ10ኛ ቀን ጸሐይ ስትጠልቅ በግ ወይም ፍየል እንዲያርዱ የሚታረደው በግ ወይም ፍየል ምንም አይነት ነውር የሌለበት ሆኖ ከታረደ በኋላ ደሙ ከስጋው የሚበሉትን ሰዎች ቤት ጉበኑንና መቃኑን እንዲቀቡት ከዚያም የበጉ ወይም የፍየሉ ስጋ ተጠብሶ በዚያች ሌሊት ከመራራ ቅጠልና ካልቦካ ቂጣ ጋር እንዲበሉት ሲበሉም በአጭር ታጥቀው ጫማቸውን አድርገው በትራቸውን ይዘው በጥድፊያ እንዲበሉ ምክኒያቱም አሁን በግብጽ ላይ የሚመጣው መቅሰፍት እጅግ ከባድ (የበጉ ወይም የፍየሉ ደም በቤታቸው ጉበንና መቃን ላይ የቀቡ እስራእል ብቻ ስለሆኑ ቢያች ሌሊት እግዚአብሔር በከተማ ውስጥ እያለፈ ደሙን በጉበኑና በመቃኑ ላይ ያልተቀባ ቤት ሲያገኝ በእያንዳንዱ ቤት ከሰው እስከ እንስሳ በኩር የተባለውን በሙሉ ስለሚገድል) ግብጾች በራሳቸው ጊዜ ወጡልን ስለሚሏቸው ነው ።
ከዚህ በኋላ ለእስራኤል ፋሲካን ማክበር የዘላለም ስርዓት እንዲሆን ተደነገገ። በመጀመሪያ እርሾ የተባለ ከቤታቸው ያወጣሉ ለሰባት ቀን ያልቦካ ቂጣ ይበላሉ።
ሰሞኑን በመላው ዓለም እርሾ ከገበያ መጥፋቱን ልብ ብለናል?! ለምን እርሾ?
__________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: መቅሰፍት, መንጋ, ምስራቅ አፍሪቃ, ሰብል, አብይ አህመድ, አንበጣ, ኢትዮጵያ, እህል, እስራኤላውያን, ኦሮሚያ, የታገቱት ተማሪዎች, የእግዚአብሔር መልስ, የግብጽ መቅሰፍቶች, ፈርዖን, ፋሲካ, ፍርድ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 7, 2020
እስኪ ተመልከቱ ወገኖቹ፤ የድምቢዲሎን ህፃናት ተማሪዎች ግራኞቹ አህመድና ለማ መገርሳ ገድለዋቸዋል። ሕዝቡ በውስጡ ይህን ባወቀበትና ነቅቶ መነሳሳት በጀመረበት ወቅት ተመልሶ ለማስተኛት በበዓላት፣ በአብይ ጾምንና በአባይ ጉዳይ ሕዝቡን በድጋሚ ነደፉት። እነዚህ እባቦች የኢትዮጵያን ሕዝብ ትርታ የሚያዳምጥ ፀረ–ኢትዮጵያ ጆሮ አላቸው፤ እንቁላሎቻቸውን በየቦታው ጥለዋል። መስተዳደራቸውን የሚቃወም ኃይል ብቅ ማለት ሲጀምር ሰርገው በመግባትና እንቅስቃሴዎቹንም በመምራት ኃይሉን ያዳክሙታል፣ ያጠፉታል። ለመስከረም ፬ እና ለታገቱት ተማሪዎች የተጠሩት ሰላማዊ ሰልፎች እንዲሁም በአባይ ጉዳይ ዋሽንግተን ላይ ተካሄዶ የነበር የተቃውሞ ሰልፍ ለዚህ ምስክሮች ናቸው።
ልክ በዚህ ወቅት ከሁለት ዓመታት በፊት የአብይ ጾም ዋዜማ ላይ ማንም የማያውቀው አብይ አህመድ የድጋፍ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ ጠርቶ ከኦዳ ዛፍ የተሠራውን ቦምብ በማፍነዳትና ንጹሐንንም ለዋቄዮ–አላህ የመጀመሪያውን ደም እንዲገብሩ በማድረግ እራሱን ለመላው ዓለም አስተዋወቀ። የፈረንሳይ ፕሬዚደንቶች ልክ ስልጣን ላይ ሲወጡ የኑክሌር ቦምብ ሙከራ በደቡብ ፓሲፊቅ ውቂያኖስ ያደርጉት እንደነበረው።
____________________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: ለማ መገርሳ, አብይ አህመድ, ኢትዮጵያ, ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን, ኦሮሞዎች, ዘረኝነት, የታገቱት ተማሪዎች, ደምቢዲሎ, ግራኝ አህመድ, ፀረ-ተዋሕዶ ዘመቻ, ፀረ-ኢትዮጵያ | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 30, 2020
እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ እረፍት (አስተርዮ ማርያም) አደረሰን!
ከምድር ሰዎች ሁሉ ጥበበኛ የሆነው ሰሎሞን እንዲህ አለ፡– “ወዳጄ ሆይ ተነሽ፤ ውበቴ ሆይ ነይ፡፡ እነሆ ክረምት አለፈ፥ ዝናሙም አልፎ ሄደ አበቦች በምድር ላይ ተገለጡ፥ የዜማም ጊዜ ደረሰ፥ የቁርዬም ቃል በምድር ላይ ተሰማ”፡፡ /መኃ.፪፥፲–፲፬/2፥10-14/ ይህ ትንቢት የዚህ ዓለም ድካሟ ሁሉ መፈጸሙን ያስረዳል፡፡ ልጇን ይዛ ከሀገር ሀገር በረሀብና ጥም የተንከራተተችበት ጊዜ አሁን አለፈ፡፡ ታናሽ ብላቴና ሳለች ልጇን አዝላ በግብጽ በረሃ የተቀበለችው መከራ ሁሉ ፍጻሜ አገኘ፡፡ ከእግረ መስቀል ሥር ወድቃ የልጇን የቆሰለ ገላ እየተመለከተች የደረሰባት ልብ የሚሰነጥቅ ኀዘን ወደ ደስታ ተለወጠ፡፡ በነፍሷ ሰይፍ ያልፋል ተብሎ የተነገረው ልብ የሚሰነጥቅ መከራ እንደ ነቢዩ ቃል ትንቢት የሚቀጥልበት ጊዜ ተፈጸመ፡፡ እርሷ ባለችበት ሥፍራ የሕይወት ትንሣኤ ያላቸው ሰዎች ይሆኑ ዘንድ አስቀድማ ከሙታን ተለይታ በመነሣት የተጠበቀልን ተስፋ ማሳያ ሆነችን፡፡ በእግዚአብሔር መንግሥት ስደት መከራ ኃዘን ሰቆቃ የለም፤ መገፋት መግፋትም የለም፡፡
የእመቤታችን ልመናዋ ክብሯ ፍቅሯ አማላጅነቷ የልጇም ቸርነት በሁላችንም ላይ አድሮ ይኑር፡፡
እባቡ አብዮት አህመድ የወጣት ተማሪዎቹን ቤተሰቦች ወደ አዲስ አበባ ሲጠራ ሁለት ሃላፊነት የማራቂያ/ የማላከኪያ ዲያብሎስዊ ተንኮሎችን በማሰብ ነው።
1ኛ. እኔ የምፈራውና የሚሰማኝ እህቶቻችን ገና ከወር በፊት አስከፊ የሆነ ነገር ደርሶባቸዋል፤ ሰለዚህ ወይ በስጋም በመንፈስም አስከፊ ሁኔታ ላይ ናቸው፤ ወይ ደግሞ በሕይወት የሉም። የተመረጡትን ወላጆች በመጥራት “ልጆቹ በሕይወት አሉ፡ ደህና ናቸው” ብለው እንዲያምኑ እና ለሜዲያው እንዲዋሹ ይደረጋሉ። በዚህም በአዲስ አበባ ለቅዳሜ የታቀደውን ሰላማዊ ሰልፍ እንዳይካሄድ ያደርጋል።
2ኛ. ምናልባት ወላጆቹ ነፃ ከሆኑ ሜዲያዎች ጋር ተገናኝተው አብዮት አህመድን የሚያስወቅስ ነገሮች ከተናገሩና ሰላማዊ ሰልፉም እንደታቀደው የሚካሄድ ከሆነ፤ ተማሪዎቹ በሕይወት ካሉ በይበልጥ እንዲጎዱና እንዲገደሉ ያደርጓቸዋል፤ ወይም ደግሞ ከወር በፊት ተገድለው ከሆነ “አሁን በወላጆቹና በሰላማዊ ሰልፈኞቹ ጥፋት በመጭው እሁድ ወይም ሰኞ ተጎዱ/ ተገደሉ” በማለት ወላጆቹንና ሰልፈኞቹን ለመኮነን የታቀደ ይመስላል።
ይህን አሳፋሪ ቅሌት በማስመልከት፡ ካላቃጠሏቸው በቀር፡ ምርመራ ሊያካሂዱ የሚችሉ፣ ለእውነትና ለሀገር የቆሙ የፎሬንሲክ ህክምና ሳይንስ ባለሙያዎች መዘጋጀት ይኖርባቸዋል።
+____________________________+
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: መንፈሳዊ ውጊያ, መከራ, ቅድስት ማርያም, ቤተክርስቲያን, አስተርዮ ማርያም, ኢትዮጵያ, ክርስትና, የታገቱት ተማሪዎች, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, ደምቢዶሎ, ፈተና, ፪ሺ፲፪, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith | Leave a Comment »