ፕሪያንካ ቾፕራ በህንድ አገር/ በቦሊውድ ትኩስ፣ ታዋቂና ኃብታም ከሆኑት ተዋናይቶች መካከል አንዷ ናት። ከሃያ ዓመታት በፊት የአለም የቁንጅና ውድድር አሸናፊ የሆነችዋ ፕሪያንካ በአሜሪካዋ ሆሊውድ በፊልም ተዋናይነት ስኬታማ ከሆኑት ጥቂት የህንድ ተዋናይቶች መካከል አንዷ ናት። ዶ/ር አብዮትን የ2019 ዓመት ከ100 ተጽእኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ያደረገው የኢሉሚናቲዎቹ “ታይም መጽሔት” ፕሪያንካ ቾፕራንም በ2016 ዓ.ም ላይ መርጧት ነበር።
ከትናንት ወዲያ ኢቫንካ ትራምፕ፣ ትናንትና የኔዘርላንድሷ ማክሲማ፣ ዛሬ ደግሞ የህንዷ ፕሪያንካ፤ ተልዕኳቸው ብቻ ሳይሆን ስማቸውም ሳይቀር ተመሳሳይ ድምጽ አለው። የማሕበረሰባዊነቱን ካርድ መዝዘው በቡና እና በእስክስታ በኩል እየገቡብን ነው!