Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • June 2023
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  2627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘የቀለም አብዮት’

የኢትዮጵያን ቀለማት በመረጠችው ቦሊቪያ በአ’ማራ ዜጎች ላይ የዘር ጭፍጨፋ እየተካሄደ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 20, 2019

ቦሊቪያ እንደ ጋና የሉሲፈራውያኑ ኮከብ ያረፈበትን አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ባንዲራ ስላልመረጠች ጥንታውያኑ አማራ ነዋሪዎቿ የኢትዮጵያን ሕዝቦች ስቃይ በመጋራት ላይ ናቸው።

በጥንታዊው ክርስትና፣ በጥንታውያን ሕዝቦች እና በኢትዮጵያ የማርያም መቀነት ቀለማት ላይ የሚካሄድ የቀለም አብዮት

በጣም የሚያስገርም ዘመን ላይ እንገኛለን ፥ በርግጥ ዓለማችን ትንሽ ሆናለች።

የኢትዮጵያን ቀለማት የያዙት ቦሊቪያውያን የሉሲፈራውያኑ ተቋም ሲ.አይ.ኤ ያካሄደውን መንፈቅለ መንግሥት በጥብቅ በመቃወም ላይ ይገኛሉ። ሆን ተብሎ በርዕዮተ ዓለም እንድትከፋፈል የተደረገችው ደቡብ አሜሪካዋ ቦሊቪያ ልክ እንደ ቺሌና ቬኔዝዌላ ታይቶ በማይታወቅ የእርስበርስ ጦርነት ተናውጣለች። ብዙዎች ተገድለዋል። ሉሲፈራውያኑም በአጭር ጊዜ ውስጥ እራሳቸው ያስቀመጡትን አብዮታዊ ዲሚክራሲያዊፕሬዚደንት ኢቮ ሞራሌስን ከስልጣን እንዲወገድና እራሳቸው በመረጧት ሴት እንዲተካም አድርገዋል።

ተመሳሳይ ሁኔታም በአረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱ ባለቤት በሃገረ ኢትዮጵያ በመታየት ላይ ነው።

ከሰባት ዓመታት በፊት(መለስ ዜናዊን ሲገድሉት) በኢትዮጵያ ሃገራችንም ተመሳሳይ መፈንቅለ መንግስት(መፈንቅለ ሥርዓት) በሉሲፈራውያኑ ተካሄዶ ነበር። 666ቱ ገዳይ አብዮትም የዚህ መፈንቅለ ሥርዓት ልጅ ነው። የሁለቱ መፈንቅለ ሥርዓታት ዓላማም ሃገራዊ፣ ብሔራዊ፣ ክርስቲያናዊ እና የጥንት የሆነውን ነገር ሁሉ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ ነው። በኢትዮጵያ አማራ እና ትግሬየተባሉትን ጥንታውያን ኢትዮጵያውያንን ፥ በቦሊቪያ ደግሞ ጥንታዊ የሆነውን የአማራ ነገድ ከእናት ሃገራቸው ማጥፋት ነው። ልክ መለስ ዜናዊን እና አብዮት አህመድን በኢትዮጵያ እንዳዘጋጇቸው ፥ በቦሊቪያም ከአማራ ነገድ የሆነውን የቀድሞ ፕሬዚደንትን ኢቮ ሞራሌስን ሤረኛ በሆነ መልክ አዘጋጅተውታል።

በደቡብ አሜሪካዎቹ ቦሊቪያ፣ ቺሌ እና ፔሩ የሚገኙትና “Pueblos Indiginas / ፑዌብሎስ ኢንዲኺናስበመባል የሚታወቁት ጥንታውያኑ የአገሬው ሕዝቦች መጠሪያቸው አይማራነው። 11 ሚሊየን ነዋሪዎች ባሏት ቦሊቪያ የአይማራ ሕዝብ ቁጥር 1.5 ሚሊየን ወይም 20% ይጠጋል። አብዛኛው የቦሊቪያ ነዋሪ ከአውሮፓውያን ጋር የተካለሰ ሲሆን ለረጅም ጊዜ ስልጣኑንም የያዘው እነዚህ ሜስቲዞስ / ክልሶችየሚባሉት ናቸው። ቦሊቪያን እንደ አይማራ ከመሳሰሉት ያገሬው ጥንታውያን ነዋሪዎች ለማጽዳት ዘር ከመከለስ እስከ ምግብና ውሃ መበከል ያልተሞከረ የዘር ማጥፋት ዘመቻ አልነበረም።

ከአሥር ዓመታት በፊት ሉሲፈራውያኑ የዓለማችን ፈላጭ ቆራጮች ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚሁ የአይማራ ነገድ የወጣውን የአገሪቷን መሪ ኢቮ ሞራሌስንሥልጣን ላይ አወጡት። ምንም እንኳን ኢቮ ሞራሌስ የአይማራ ነገድ ይሁን እንጅ ተጠሪነቱ ግን ለሉሲፈራውያኑ ነው። የአሜሪካ ተቀናቃኝ እንዲሆን (የሚቆጣጠሩት ተቀናቃኝ / Controlled Opposition) ብሎም የሶሺያሊስታዊ ሥርዓት አራማጅ እንዲሆን አዘዙት። አሁን ልክ ጊዜው ሲደርስ ከስልጣን አስወገዱት፤ በከፊሉ የቦሊቪያ ሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነትንም እንዲያተርፍ ስላደረጉት አሁን እየታየ ያለው ህውከት ሊፈጠር ቻለ።

በሃገራችንም ከዚህ የከፋ ህውከት ከመጪው ግንቦት ምርጫበኋላ ሊፈጠር እንደሚችል ለማወቅ ሊቅ መሆን አይጠበቅብንም።

ከሃያ ዓመታት በፊት በኦርቶዶክስ ክርስቲያኗ ሰርቢያ (የቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ) የጀመረው የሉሲፈራውያኑ የቀለም አብዮትጥንታውያን እና ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ሕዝቦች ዘንድ እንዲቀጣጠል ነው እየተደረገ ያለው። ከኦርቶዶክስ ሰርቢያ ወደ ኦርቶዶክስ ጆርጂያ፣ ዩክሬይን እና ሩሲያ እንዲቀጥል ተደርጓል።

አዎ! የሳጥናኤል ግብ ኢትዮጵያ ነው። ዲያብሎስ ተዋሕዶ ክርስትናን እና ሰንደቅ ዓላማችን በጣም ይጠላቸዋል፣ ይፈራቸዋል። ይህን በሃገራችን እያየን አይደለም?! የክርስቶስ ተቃዋሚዋ ቱርክ እንኳን የኩርድ ሕዝብን በመጨፍጨፍ ላይ ያለቸው ኩርዶች የኢትዮጵያን ቀለማት በመያዛቸው ነው።

የአንድን ሕዝብን ዘር ሙልጭ አድርጎ በማጥፋት የሺህ ዓመታት ልምዱ ያላቸው ቱርኮች እና አረቦች ወደ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ወደ ቦሊቪያ እና ቬኔዝዌላም ርቀው በመጓዝ እየሠፈሩ ነው። እነዚህ የመጥፎ ዜና እና ጥፋት መልዕክተኞች ከምዕራባውያኑ ረዳቶቻቸው ጋር በማበር የኢትዮጵያን ክርስቲያኖች ደም አፍስሰው ለዋቄዮአላሃቸው እንደሚገብሩት በቦሊቪያም ማራ የተሰኘውን ጥንታዊ ሕዝብ ለዚሁ ሰይጣናዊ ተግባር መፈጸሚያ ለማድረግ በመዘጋጀት ላይ ናቸው።

ኢቮ ሞራሊሰ ከስድስት ወራት በፊት ቱርክን በመጎብኘት የመጀመሪያው የቦሊቪያ ፕሬዚደንት ለመሆን በቅቶ ነበር።

የሚገርም ነው፤ በሃገራችን አማራ፤ በቦሊቪያ አማራ። ሁለቱም በአሁኑ ሰዓት የተዳከሙ ሕዝቦች ናቸው። ልዩነቱ ግን የኢትዮጵያ አማራ የደከመው ኢትዮጵያዊነቱ ስላልጠነከረ/ በኢትዮጵያዊነት ስላልተጠናከረ፣ የአባቶቹን ነፍጠኛነት በመርሳቱ ሲሆን የቦሊቪያዎቹ አማራዎች ግን በአማራነታቸው ስላልጠነከሩ/ስላልተጠናከሩ ነው። ከአማራ በፊት ኢትዮጵያ ስትቀድም ከቦሊቪያ በፊት ግን አማራ ይቀድማል።

በኢትዮጵያ በአማራ ላይ እየተካሄደ ያለው ጥቃት ነዋሪዎቹ አማራበመሆናቸው ሳይሆን አማርኛ በመናገራቸው፣ ተዋሕዶ ክርስቲያን በመሆናቸው፣ አረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቅ ዓላማ በማውለብለባቸው፤ ባጠቃላይ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው። ትግሬየሚባለውም በትግሬነቱ ሳይሆን ጥቃት የሚፈጸምበት በጥንታዊው ኢትዮጵያዊነቱ እንጂ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ከዚህ ኢትዮጵያዊነታቸው እስካልተላቀቁ ድረስ ጥቃቱ ይቀጥላል። ስለዚህ በተቻለ መጠን አማራነት ኢትዮጵያዊ ባልሆነ አማራነት፣ ትግሬነት ኢትዮጵያዊ ባልሆነ ትግሬነት እንዲቀየሩና እንዲዳብሩ ይደረጋሉ። ትናንትና ኤርትራ ዛሬ ደግሞ ትግራይ እና ኦሮሞ በተባሉት የኢትዮጵያ ክፍለሃገራት የተደረገው ነገር ይህ ነው።

አብንየተባለው ፓርቲ ገና ሲቋቋም ! ! ዋይ! ዋይ!” ብዬ ነበር። በዘውግ የተደራጀ አማራየተሰኘው ሕዝብ በአማራነት ከኢትዮጵያ የሚነጥል ሤር መጠንሰሱን ከውዲሁ ይታየኝ ነበር። የደከመው አማራ ላይ ቶሎ ጥቃት የፈጸሙት፣ መሪዎችየሚሏቸውን ልሂቃን የገደሉትን እና የአብን አመራራትን ወደ እስር ቤት የከተቱት አማራ የሚሉት ነዋሪ ተቆጭቶና ተነሳስቶ ኢትዮጵያዊነቱን እንዲተውና ኢትዮጵያን የከዳ የአማራ ሃገር እንዲገነባ ነው።

አብንየተሰኘው ፓርቲ ሰሞኑን ከኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ከሆኑ ኦነጎች ጋር በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መቀመጡ ይህን የፀረኢትዮጵያ የሆነ አካሄድ ነው የሚጠቁመን። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች ሁሉም በፀረኢትዮጵያ ኃይሎች የተደራጁና በጠላቶቻችን ባትሪ የሚሞሉ ሃገር አጥፊዎች ናቸው። አሁን በአብን እና በኦነጎች መካከል የተፈጠረው ግኑኝነት ከሰላሳ ዓመታት በፊት በህዋሃት እና ኦነግ መካከል ተካሂዶ የነበረውን ጋብቻ ያስታውሰኛል። ያኔም የጥፋት ኦርኬስትራውን ሲመሩ የነበሩት ምዕራባውያኑ ሉሲፈራውያን ነበሩ ፥ ዛሬም እየመሩ ያሉት እነርሱው ናቸው።

በሠላሳ ዓመት ውስጥ ኦሮሞው እና ትግሬው ከኢትዮጵያዊነት እንዲርቅ ተደርጓል ፥ በመጭዎቹ ሰላሳ ዓመታት ደግሞ አማራው ኢትዮጵያዊነቱን እርግፍ አድርጎ እንዲተው ይደረጋል፤ ያኔ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እትኖርም፣ ተዋሕዶ ትጠፋለች፣ አረንጓዴ፣ ቢጫ እና ቀይ ቀለማቱም ወደ ጥቁርነት ይቀየራሉየሚል ነው እቅዳቸው። ግን ብዙ መስዋዕት ያስከፍለናል እንጂ ይህ እቅዳቸው አይሳካላቸውም።

ስቃዩና ዕልቂቱ እንዲቀነሱ ግን ባፋጣኝ አማራእና ትግሬየተባሉት ነገዶች ልሂቃቃናቶቻቸው ለዘመናት ለፈጸሙባቸው በደሎች ብድር ከመመላለስ በመቆጠብና እርስበርስ ይቅር በመባባል ባፋጣኝ መተባበር ይኖርባቸዋል። ይህ በአማሮችና ትግሬዎች ላይ የመጣ የህልውና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፤ ከምጽዋ እስከ ሞያሌ ያሉትን ሌሎቹን ደካማኢትዮጵያውያን ነገዶችን አንስፍስፎ ከመጣው የዋቂዮአላህ ሠራዊት መከላከል ብሎም ኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ከዚህ አውሬ ኃይል ማዳን መቻል ስለሚኖርባቸው ነው።

በሃገራችን፣ በቤተክርስቲያናችን እና በሰንደቅ ዓላማችን ቀለማት ላይ የተነሱትን የዲያብሎስ ቡችሎች ቅዱስ ሚካኤል በሰይፉ ቆራርጦ ከእግራችን ስር ይጣልልን!

ኢትዮጵያውያንን በተበከለ የፈረንጅ ዶሮየሚመርዙት አላሙዲን እና ቢል ጌትስ በቦሊቪያም ተመሳሳይ ፕሮጀክት ለመፈጸም አቅደው እንደነበርና ቦሊቪያም ከልክላቸው እንደነበር ከሚከተለው ቪዲዮ ጋር በተያያዘ አውስቼ ነበር፦

________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: