Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 29, 2020
ከጥቂት ቀናት በፊት ዝነኛው የድሬስደን ከተማ የኦፔራ ቤት የቅዱስ ጊዮርጊስ ሽልማትን ለግብጹ ፕሬዚደንት አብዱል–ፋታህ አል–ሲሲ ለመስጠት ወሰነ፤ ይህም ብዙ ተቃውሞዎችን ቀሰቀሰበት። በተለይ ፕሬዚደንቱን እንዲሸልሙት የተጋበዙት ታዋቂ የጀርመን ሜዲያ ሰዎች “አምባገነኑን አል–ሲሲን በፍጹም አንሸልምም” ብለው በሽልማት ስነ ሥርዓቱ ላይ ለመገኘት ፈቃደኞች አልነበሩም።
እባብ አብዮትን የሰላም ሽልማት፤ ዘንዶ አል–ሲሲን የቅዱስ ጊዮርጊስ የሰላም ሽልማት ሰጧቸው። ዋው! እንግዲህ ይህ ሽልማት ግብጽ የባንዲራዋን ቀለማት ያዋሰቻቸውን ቅጥረኞቿን ኦሮሞዎችን እየደገፈች እንዳቀዱት ኢትዮጵያን ስላወከችላቸው መሆኑ ነው። አውሬው ኢትዮጵያን በእጁ ለማስገባት አመቺ ይሆንለት ዘንድ ከእንቁላሉ የፈለፈላቸውን ልጆቹን በየወሩ ይሸልማቸዋል። አላጋጮቹ ሉሲፈራውያን እንዲህ ነው እርስበርስ የሚሸላለሙት።
ከሐዲውና ጣዖት አምላኪው ዱድያኖስ በአምልኮ ጣዖት የፀና፣ እውነተኛውን አምላክ እግዚአብሔርንም የካደ ከመሆኑ የተነሣ የክቡር ጊዮርጊስን ራስ በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ፡፡ ድል አድራጊ ጊዮርጊስም እጅግ ደስ አለው፡፡ እሳት ከሰማይ አውርዶ ሰባውን ነገሥት ያቃጥላቸው ዘንድ መከራውም ከክርስቲያን ወገን ጸጥ ይል ዘንድ ጌታችንን ለመነው፡፡ ወዲያው እሳት ወርዶ ከሠራዊታቸው ጋር ሰባውን ነገሥታት አቃጠላቸው፡፡
የኢትዮጵያ ጠባቂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ! ሀገራችንን በማተራመስ ላይ ያሉት ጣዖት–አምላኪ የዘመኑ ዱድያኖሶች ከያዙት እርኩስ ዓላማ ኢትዮጵያን ጠብቅልን ፣ እኛን ልጆቿንም በበረከት ጎብኘን አትለየን አሜን!
___________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: ቅዱስ ጊዮርጊስ, አል-ሲሲ, አብይ አህመድ, አድዋ, ኦሮሞዎች, ክህደት, ዘር ማጥፋት, የሰላም ሽልማት, የኢትዮጵያ ጠላት, ድሬስደን, ጀርመን, ግብጽ, ጣልያን, ፀረ-ኢትዮጵያ, ፋሺዝም | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2019
አብዮት አህመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ለመቀበል በሚቀጥለው ሳምንት ኦስሎ ከተማ በሚገኝበት ወቅት የዜና ማሰራጫዎችን ለማነጋገር ፈቃደኛ አይደለም። ይህም ነፃ እና ገለልተኛ ፕሬስ በጣም አስፈላጊ ነው ከሚለው የሽልማት ኮሚቴው መርሆ ጋር ስለሚጻረር ትችት እየተሰነዘረበት ነው።
የኖቤል የሰላም ሽልማት በተለምዶ ዲሴምበር 10 ቀን ከመካሄዱ አንድ ቀን በፊት የኖቤል የሰላም ሽልማት የዜና ስብሰባ ያካሂዳል ፡፡
አብይ አህመድ ከኖርዌይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሶልበርግ ጋር ከተገናኘ በኋላ ከጋዜጠኞች ለሚቀርብለት ጥያቄዎች ለመጠየቅ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ከመግለጹ ሌላ በየዓመቱ በኖብል የሰላም ማእከል በሙዚየሙ ውስጥ በሚከበረው የልደት በዓል ላይና ከህፃናት ጋር በሚደረገው ዝግጅት ላይም አይሳተፍም፡፡
አብይ አህመድ የኖርዌይ ፖለቲከኞች እና ምሁራን ከሚሳተፉበት ሚስጥራዊ ሽልማት ኮሚቴው በኩል ያልተለመደ ትችትና ወቀሳ አግኝቷል ፡፡ “ሀሳብን የመግለጽ ነፃነት እና ነጻ ፕሬስ የሰላም ወሳኝ አካላት ናቸው ብለን እናምናለን። አብይ አህመድ የዜና ጉባኤ አለመያዙ ችግር እንዳለበትና በኦስሎ በሚቆይበት ጊዜ ከሜዲያ ጋር እንዲነጋገር በጣም ፈልገን ነበር።” ብለዋል ፡፡
ከዚህ በፊት ከሚዴያ ጋር ለመነጋገር ተመሳሳይ ፍራቻን አሳይቶ የነበረው ምንም ሳይሰራ በ2009 ዓ.ም ይህን ሽልማት የተረከበው የአብይ ሞግዚት ባራክ ሁሴን ኦባማ ነበር።፡ ተመሳሳይ ላባ ያላቸው ወፎች አንድ ላይ ይበራሉ!
አሁንስ ምን ዓይነት ድራማ አዘጋጅተውልን ይሆን? ምንስ አስደንግጧቸው ይሆን? የኖበል ኮሜቴው ለገዳይ አብይ ሽልማቱን በመስጠቱ ተጸጽቶ ይሆን? ወይንስ ዲዜምበር 10 አብዮትን ሊጠብቀው የሚችለው ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አስደነገጠው። ብዙ የሚደብቀው ጉዳይ ስላለ በነፃ ከጋዜጠኞች ጋር ነፃ ቃለ መጠይቅ ማድረግ አይችልም፤ በደንብ የተዘጋጀበትና እራሱ ካዘጋጃቸው ጋዜጠኞች ውጭ በገለልተኛ ወይም ተቃዋሚ በግልጽ ሲጠየቅ ታይቶ አይታውቅም። ለምን? ብላችሁ እራሳችሁ ጠይቁ! ለማንኛውም ኖርዌይ ለዚህ ገዳይ ይህን ሽልማት በመስጠቷ ጽንፈኛ ኦሮሞዎች እየፈጸሙት ላሉት የዘር ማጥፋት ድርጊት ከተጠያቄዎቹ መካከል አንዷ ናት።
________________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: ሜዲያ, ሰላም, ቃለ መጠይቅ, ተሳትፎ, ኖርዌይ, አብይ አህመድ, አብዮት አህመድ, ኢትዮጵያ, ኦስሎ, የሰላም ሽልማት, ግራኝ አህመድ, ፍራቻ, Genocide | Leave a Comment »