Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን’

የሩሲያው መሪ ጥምቀትን በኦርቶዶክሷ ሰርቢያ ሲያከብሩ፡ የኛዎቹ ደግሞ ‘፫ኛውን ሂጂራ’ ወደ ኢትዮጵያን በማመቻቸት ላይ ናቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2019

መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፫]

ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።

ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።

ኦርቶዶክሱ ፕሬዚደንት ፑቲን ለጉብኝት እህት አገር ወደ ሆነችው ወደ ሰርቢያ አምርተዋል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዝነኛው የቅዱስ ሳቫ (የሰርቢያ ቅዱስ) ቤተክርስቲያን የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በሉሲፈራዊያኑ የቱርክ፣ የናዚዎች እና በቅርቡም የኔቶ ሠራዊት በታሪኳ ብዙ ጥቃት የደረሰባት ኦርቶዶክስ ሰርቢያ መጀመሪያ በእርሷ እርዳታ ኃያል ለመሆን የበቃችውን ዩጎዛላቪያን በታትነው አደከሟት፤ ከዚያም፡ በቅርቡ፡ የክርስትና ስልጣኔዋ ታሪካዊ ቦታ የሆነችውን ኮሶቮን ገንጥለው ወሰዱባት።

..አ በ1999 .ም እሑድ በትንሳኤ በዓል ወቅት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ዋና ከተማዋን ቤዖግራድን በከፋ መልክ በቦምብ ማስደብደቡን አንረሳም፤ በኦርቶዶክስ ትንሳኤ ዕለት! እዚህ ያንብቡ

ያው እንግዲህ፤ ሉሲፈራውያኑ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጦርነቱን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ሰርቢያ፣ ማኬዶኒያ፣ አርሜኒያ፣ ጆርጂያ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬይን ቆጵሮስ፣ ሶሪያ፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ላይ በማጧጧፍ ላይ ናቸው።

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሩሲያ መሪዎች በቤተክርስቲያን | አንድ የአገራችን መሪ ግን ለመጨረሻ ጊዜ ቤተክርስቲያን የሄደው ከ፵፭/ 45 ዓመታት በፊት ነበር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 13, 2019

እስኪ አስቡበትአብረን እናስብበትአንድ የኢትዮጵያ መሪ የክርስቶስ የሆነችውን እናት ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። ዋው!

የኮሙኒዝምን ሥርዓት ሲያገለግሉ የነበሩት የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የሉሲፈራውያኑን ርዕዮተ ዓለም እርግፍ አድርገው በመተው ወደ ክርስቶስ መጥተዋል። በሶቪየት ኮሙኒዝም ጊዜ የቭላዲሚር ፑቲን እናት በቅዱስ ፒተርስቡርግ ከተማ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን በድብቅ ቭላዲሚር ፑቲንን አምጥተዋቸው አስጠምቀዋቸው ነበር። (ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሩሲያውያን ክትትልና አድሎ ይደረግባቸው ነበርና)

በአንድ ወቅት፤ “አንገቴ ላይ ያደርግኳት ይህች መስቀል ሕይወቴን አድናታለች” በማለት መስክረው የነበሩት ፕሬዚደንት ፑቲን በዚሁ በተጠመቁበት ቤተክርስቲያን ነበር ባለፈው እሑድ የገና በዓልን ተመስጠው ሲያከብሩ የሚታዩት። ጠቅላይ ሚንስትር ሚድቪዴም ለፀሎት ሦስት ጊዜ ሲያማትቡ ይታያሉ።

ወደ አገራችን ስንመጣ፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው፡ አንድ የአገራችን መሪ ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊቷን ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። እንዴት ነውይህ ክስተት እርርይ! ! ! አያሰኘንምን። ምን ዓይነት ኃጢዓት ብንሠራ ነው ኢትዮጵያን እና አምላኳን የሚጠሉ መሪዎች የተሰጡን?! እንደ መስቀል፣ ገና እና ጥምቀት በመሳሰሉት አንጋፋ የኢትዮጵያውያን ክብረ በዓላት (ሰባ ሚሊዬን ኢትዮጵያውያን የሚያከብሯቸው) ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ መሪዎች እንኳን የሉንም። በመስከረሙ የመስቀል ደመራ በዓል ወቅት ዶ/ር አብይ በመስቀል አደባባይ ይገኙ ይሆናል የሚል ጭምጭምታ ነበር፤ ነገር ግን እርሳቸውም ያው ከ666ቱ ስለሆኑ ሳይሳተፉ ቀሩ።

ባለፈው ጊዜ፡ በዚምባብዌ፡ ለገዳዩ መንግስቱ ኃይለማርያም የሰገዱት የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ከመውረዳቸው በፊት በኢየሩሳሌም የምትገኘውን የኢትዮጵያ ቤትከርስቲያን በእስራኤል መንግስት ግፊት ለመጎብኘት ሲገደዱ ጫማቸውን እንኳን ሳያወልቁ ነበር የገቡት፤ አቤት ድፍረት! አቤት ትዕቢት አቤት ቅሌት!

! ለሉሲፈራውያኑ ወኪሎች፤ ሕዝባችንን ኋለኞች ለማድረግ ተግተው ለሚሠሩት፤ ዋ!

እኛ የተዋሕዶ ልጆች ግን በገዢዎች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረጉን እንመርጣለን፦

[ ፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፩፡፲]

አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው። አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።”

__________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሩሲያ ፓትርያርክ፡ “ዘመናዊ ስልኮች ለፀረ-ክርስቶሱ መምጣት መንገድ ይከፍታሉ” በማለት በጥብቅ ያስጠነቅቃሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 11, 2019

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ኪሪል የግና በዓልን በማስመልከት ከሩሲያ ቴሌቪዥን ጋር በተደረገ አንድ ቃለ ምልልስ ላይ የሚከተለውን ተናግረዋል፦

የክርስቶስ ተቃዋሚ፡ አሁን የተስፋፉትን ዘመናዊ ስልኮችን ወይም ስማርት ስልኮችን ለመጥለፍ የሚያስችለው ኤሌክትሮኒክ መሣሪያ አጠቃቀም ስልት በጣም ሰፊ ነው

ቤተክርስቲያኗ የቴክኖሎጂ ዕድገትን አትቃወምም፥ ነገር ግን በኢንተርኔት የተገናኙ መሳሪያዎች ለሰው ዘር ሁሉ ዓለም አቀፍ ቁጥጥርማድረግ የሚችሉበትን ሁኔታ ፈጥረዋል

ሰዎች በትክክል የት እንዳሉ ምን እንደሚፈልጉ፣ ምን እንደሚፈሩ ተከታያቾቻቸው እንዲያውቁ ያስችላቸዋል

እንዲህ ያለው መቆጣጠሪያ መንገድ፡ ፀረክርስቶሱ ከአንድ ቦታ ሆኖ አስቀድሞ እንዲመለከት ይረዳዋል።

ፀረክርስቶሱ የሰው ዘር ሁሉ የሚቆጣጠር ዓለም አቀፋዊ መሪ ይሆናል ይህም ማለት ይህን መሰሉ የቴክኖሎጂ መዋቅ እራሱ አደጋን ያመጣል ማለት ነው

የአለም ፍጻሜን ቶሎ ለማድረስ ካልፈለግን በቀር ነገሮች በአንድ ማዕከላዊ በሆነ ቦታ ቁጥጥር ሥር መውደቅ የለባቸውም፤ ማዕከላዊ ሆኖ የሚንቀሳቀስ ነገር መጥፋት አለበት።” ብለዋል።

ፓትርያርክ ኪሪል ብልህ የሆነ እና በጣም ጠቃሚ የሆነ መልዕክት ነው ያስተላለፉልን። በተለይ ሕፃናት ከስማርት ስልኮች መራቅ ይኖርባቸዋል። አሁን እንኳን ምዕራባውያኑ ሕፃናት በስማርት ስልክ ሳቢያ ዓይኖቻቸው ክፉኛ እየተጎዱ ነውእዚህ እና እዚህ ያንብቡ።

ከጥቂት ዓመታት በፊት እነ ቢል ጌትስ ከወስላታው ኮፊ አናን ጋር በማበር ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሕፃን አንድ ላፕቶፕ እንሰጣልን( One Laptop Per Child) ሲሉ፡ “ኡ! ! አውሬው ሕፃናቶቻችንን ሊቆጣጠር ይሻል!” በማለት ስጋቴን ገልጬ ነበር።

ስለ ፀረክርስቶሱ፡ ብዙ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስጠንቀቂያዎች ፩ኛ የዮሐንስን ጨምሮ በሌሎችም መጻሕፍት ውስጥ እናገኛለን፦

፩ኛ የዮሐንስ መልእክት ምዕራፍ ፪ ፲፰ እንዲህ ይላል

ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።

ውድ ልጆች ሆይ, ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው; የክርስቶስ ተቃዋሚ እንደሚመጣ እንደ ሰማችሁ መጠን አሁንም ብዙዎቹ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል

ኢትዮጵያ አገራችንንም በጥቂቱ ላለፉት 50 ዓመታት እየመሩ ያሉት ፀረክርስቶሶቹ ናቸው። ለመሆኑ ዶ/ር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ መንግስት የኢንተርኔት መቆጣጠሪያ ባለሥልጣንን የገነቡ ግለሰብ መሆናቸውን እናውቅ ነበርን? ታዋቂው የስዊዘርላንድ ጋዜጣ NZZ ይህን በማስመልከት ከሁለት ወራት በፊት በሰፊው አትቶ ነበር።

በሌላ በኩል የ ጉግል ተቋምና የአሜሪካ ኤምባሲ፡ በልማት እና ስራ ፈጠራ ስም፡ ወንጀላዊ የኢንተርኔት ጠለፋና ፕሮፓጋንዳን የተመለከተ ሥልጠና በአሜሪካ ኢምባሲ በኩል ለኢትዮጵያውያን እንደሚሰጡ ባለፈው ኅዳር ላይ ተገልጾ ነበር።

በአገራችን ላይ እየተካሄደ ያለው ፀረክርስቶሳዊ ድራማ በቅደም ተከተል ነው በደንብ የተቀነባበረው። ነገሮች ሁሉ ወዴት እያመሩ እንደሆነ እያየን ነው።

______

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አስገራሚ ዘመን | የሩሲያ ቀሳውስት ፕሬዝደንቱንና ጠፈርተኞችን ሲባርኩ፡ እነ ኃይሌ ገ. የባረከቻቸውን እናታቸውን ይኮንናሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 6, 2018

የሩሲያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አገልጋዮች ዛሬ ወደ ጠፈር ባመጠቀችው ሶዩዝ ሮኬት ላይ ጠበል ከረጩ በኋላ፡ ሦስቱን ጠፈርተኞችንም በጠበል እና በመስቀል ባርከዋቸዋል። ጨረቃዋም በመስቀሉ ኃይል ተገምሳለች!

የሕክምና ዶክተር የሆነችው አሜሪካዊቷ ጠፈርተኛ ፊቷን ሦስት ጊዜ ስታማትብ ይታያል።

ኃይለኛ ምልክት፤ ትልቅ መልዕክት!!!

ፊተኞቹ ኋለኞች እንዳንሆን መጠንቀቅ ይኖርብናል!

______

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: