Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • June 2023
  M T W T F S S
   1234
  567891011
  12131415161718
  19202122232425
  2627282930  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘የረር ሥላሴ’

ቀጣፊው የእንግሊዝ ጋዜጣ | “ኢትዮጵያውያን ‘ጋኔን ለማስወጣት’ የወር ደሞዛቸውን ለመምህር ግርማ ይከፍላሉ”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 6, 2018

ዲያብሎስ በቅናት ሲያሽሟጥጥብን ደስ ሊለን ይገባል፤ ምክኒያቱም የእግዚአብሔር ልጆች መሆናችንን ለማወቅ እንችላለንና።

ይህን ቪዲዮ የሠራሁት የእንግሊዙ “ደይሊ ሜይል” በድህረ ገጹ ላይ ትናንትና ካወጣቸው ፎቶዎች ነው።

እነዚህን የመሳሰሉት ፎቶዎችና ቪዲዮዎች ለእኛ የተለመዱ ናቸው፤ መንፍሳዊ ውጊያ ምን እንደሚመስል በግልጽ የሚታይባቸው ፎቶዎች ናቸው። ለዲያብሎስ አሽሟጣጩና ተከታዮቹ ግን በተቃራኒው ከንቱ ነገር ነው። ዓይኖቻችን የተለያዩ ናቸው!

ይህ ታዋቂ የእንግሊዝ ጋዜጣ አንድ ዳዊት Tesinsky የተባለ ወስላታ የቼክ ሪፓብሊክ ፎቶ አንሺን ወደ መምህር ግርማ ልኮ ምስሎቹን ካገኘ በኋላ በድህረ ገጹ ላይ በጣም ቅጥፍት በተሞላበትና እጅግ በጣም አንቋሻሽ በሆነ መልክ ረጅም ዘገባ አቅርቧል። ኢትዮጵያውያንን፣ ተዋሕዶ ክርስትናን እና መምህር ግርማን እያንቋሸሸ፡ ማለት ነው። እንዴት ፈቀዱለት?!

ዲያብሎስ ቀናተኛው ከጻፋቸው ዓረፍተ ነገሮች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፤ ለማሽሟጠጥ ሲሻ ቃላቶቹን በቅንፍ ውስጥ አስቀምጧቸዋል፣ ምንም እንኳን በእንግሊዝኛው በ አንተእና በ አንቱልዩነት ባይኖርም፤ ግን ስለ መምህር ግርማ አንተበሚል መንፈስ ነው የተጻፈው፦

ርዕሱ፦ “በአንድ የጅምላ የጥምቀት ሥርዓት 150 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን “ጋኔን ለማስወጣት” የወር ደሞዛቸውን ለአንድ ቄስ ይከፍላሉ” የሚል ነው።

 • + ተወዳጅ የጊዜ ማሳለፊያ፦ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሚገኝ መንደር (የረር ሥላሴ) መቶ አምሳ የሚሆኑ ሰዎች “ጋኔን አውጭውን” ዝነኛ ፈዋሽ ቄስ ለማየት መጥተዋል
 • + የምዕመናኑ ግንባር ላይ መስቀሉን በማሳረፍ ተቀደሰ ውኃ‘/ ጸበል ያርከፈክፍባቸዋል።
 • + ፎቶው፡ በሁሉም የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎች በህውከት ሲያለቅሱ፣ ሲጮኹና ሲፈራገጡ ያሳያል።
 • +የአምላክ ሥራ፦ ጋኔን አውጭው ፈዋሽ ቄስ መምህር ግርማ ወንድሙ የሰውየው ግንባር ላይ መስቀሉን ሲያሳርፉበት በእብደት ሲጮኽ ፎቶው ያሳያል
 • + ሌላው ፎቶ ላይ፡ አንዲት ሴት እየጮኸች ወደ መምህር ግርማ ስትመጣ እና ጎልማሶች ጸበል እየተረጩ ሲያለቅሱ ይታያል።
 • + ብዙ ዝናብ፦ ከ እርኩሳን መናፍስት ነጻለመሆን የመጣችው ሴት ላይ የጸበል ፉፏቴ ተለቀቀባት።
 • + የነፃነት ዋጋ፦ እንደሚባለው ከሆነ መምህር ግርማ ጋኔን የሚያወጡትተፈዋሾቹ የአንድ ወር ደሞዛቸውን ሲከፍሏቸው ነው።
 • + የዘመናዊ መድኃኒትን መቀበል የማይችሉት ኢትዮጵያውያን የወር ደሞዛቸውን ከፍለው “ጋኔን ያስወጣሉ”።

ቀጣፊው ቼክ ፎቶ አንሺ ይህን ብሏል፦

መምህር ግርማ በእዚህ ቦታ የበለጠ ገንዘብ ስለሚያገኝ በሌሎች ዓብያተክርስቲያናት ለማገልገል አሻፈረኝ ብሏል፤ እንዲያውም የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከምታገኘው ገንዘብ በላይ ያገኛል።”

አቤት ቅጥፈት! አቤት ተንኮል! አቤት ጥላቻ! ያሰኛል። ግን በድጋሚ ደስ ይበለን። እግዚአብሔር በራሱ መንገድ የራሱን ፎቶዎች ያነሳል።

[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፰፥ ፵፬]

እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።

እኔ እስከማውቀው ድረስ፡ መምህር ግርማ በየረር ሥላሴ የሚሰጡትን ታታሪ የሆነ መንፈሳዊ አገልግሎት ካቆሙ ቆይተዋል፤ ታዲያ ይህ የእንግሊዝ ጋዜጣ ስለ እርሳቸው አሁን ለመናገር የወሰነው ከምን የተነሳ ነው? ከማንስ ጋር በመተባበር? ኃይሌ ገ/ሥላሴ (የረር ሥላሴ) ይኖርበት ይሆን? እነ አንዳርጋቸውስ?

የእንግሊዝ ሜዲያ ይህን የመሰለ ተንኮልና ጥላቻ በእንግሊዝ፣ በደካማው የአንግሊካን ቸርቻቸው እና በጨካኙ የንጉሣውያን ቤተሰብ ላይ ተንፍሶ አያውቅም፤ ፀረክርስትና ዘመቻው ግን ያው በመጧጧፍ ላይ ነው። ከሃዲዎች!

ሊሲፈራውያኑ የአንግሎአሜሪካውያኑ ስውር የዓለማችን መሪዎች የመፍንቅለ መንግስት በኢትዮጵያ አደረጉ፤ ያዘጋጇቸውን ሰዎች ሥልጣን ላይ አስቀመጡ፣ ቢቢሲ በኢትዮጵያ ቋንቋዎች አገልግሎት ጀመረ፣ እነ አንዳርጋቸውን እንዲለቀቁ ወተወቱ፣ ክትባት እየወጉ ያሳደጓቸውን እነ ኃይሌ ገ/ሥላሴን ፀረተዋሕዶ የሆነ ነገር እንዲናገሩ አዘዟቸው፣ የኦጋዴን ነዳጅ እንዲወጣ ተፈቀደ፣ የኢትዮጵያ ግድብ ኬኒያ ልጃቸውን እንደሚጎዳ ተዘገበ፣ ደቡብ ኢትዮጵያውያን የብጥብጥ እሳት እንዲፈጥሩ ተቆሰቆሱ፣ 666ቷ ሮቦት ሶፊያ ወደ ኢትዮጵያ ተላከች።

እኅተ ማርያም ትክክል ናት “አቤት እንግሊዝ ጉዷ” ስትለን። በትናንትናው ዕለትም ሰሬ ወረዳ እና ጋትዊክ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተሰምቶ ነበርታይቶ የማይታወቅ ኃይለኛ የአየር ሙቀት በመላው አውሮፓ አለ፣ የድርቅ ዘመን እየመጣባቸው ነው ፣ የእስልምና እና የግብረሰዶም መቅሰፍት ያመጣባቸው መዓትማ ተዘርዝሮ አያልቅም።


The Exorcist: Priest performs mass exorcism on hundreds of people who paid up to a month’s wages to rid themselves of demons at Ethiopian ceremony


 • Hundreds queue up to meet with a priest and ‘exorcist‘ at a rural church outside Addis Ababa, Ethiopia

 • Exorcism rituals to ‘rid the body of demons‘ sometimes take place in the Ethiopian Orthodox church

 • This instance saw 150 line up to see a priest charging up to one-month’s wages for an ‘exorcism

 • Images show the priest touch believers on the forehead with a cross and spraying them with ‘holy water

A mass exorcism ritual involving hundreds of Ethiopian Christians, who paid up to a month’s wages to be punched by a priest and doused in ‘holy water‘, has been captured in a fascinating photo series.

Some 150 people had been queuing up at a church outside the Ethiopian capital Addis Ababa in order to meet a local celebrity healer whom they believe would be able to free them from ‘demons‘.

The photos show people of all ages crying hysterically as a cross touches their forehead, or being held down by relatives as they try to avoid being ‘exorcised‘, kicking and screaming.

Set me free: A woman is being held in place by two men as she screams while being sprayed with holy water

God’s work‘: A man is seen crying hysterically as priest and healer Memehir Girma Wedimu touches him with a cross

Other striking shots show a woman seemingly screaming with all her might as she is brought up to the priest, grown men in tears, and dozens of people being hosed down with holy water.

They were taken by Czech photographer David Tesinsky who had ventured to Ethiopia specifically to capture exorcism rituals.

After two weeks of trying to convince locals to let in photograph the religious events, he found the Yerer Selassie church, not far from Addis Ababa, where locals were lining up to meet Ethiopian Orthodox priest Memehir Girma Wedimu.

‘People were crying, screaming and Memehir was punching them,’ said Tesinsky. ‘Memehir, I learned, had rejected all other churches, because he earned more money than the church itself.

He kept asking for money – I saw one very old woman give him a $100 (£76) bill to ‘expel’ her of demons and he still wanted more, even though that $100 was most likely all she could earn in one month.’

Popular past-time: Some 150 people had lined up at the church outside Addis Ababa to meet with the priest

Rain in abundance: A young woman who had lined up to be ‘freed‘ from evil spirits is doused in water

Fear and faith: A man needs to be held in place and struggles as Memehir Girma Wedimu performs a ritual

Price for freedom: Memehir Girma Wedimu reportedly charged those who turned up for an exorcism up to one-month’s wages for a ‘spirit cleanser‘ ritual

Strong beliefs: Nearly three quarters of Christians in Ethiopia claim to have experienced or witnessed an exorcism

‘These exorcism rituals are usually performed if someone is not responding to modern medicine or if they are misbehaving.

‘Their families think they are possessed by a “demon spirit” or “buda” – the power of the evil eye. They must be performed by a local priest.’

Ethiopia has had a significant Christian population for centuries, and the Ethiopian Church is the largest pre-colonial Christian church in Africa.

The belief in demons and the devil found across the religious spectrum is strong, in particularly in rural areas, and according to a 2010 survey, nearly three quarters of Christians in Ethiopia claim to have experienced or witnessed an exorcism.

Source

‘People were crying, screaming and Memehir was punching them,’ said Tesinsky. ‘Memehir, I learned, had rejected all other churches, because he earned more money than the church itself. „

My Note:

What a load of crap, pack of lies, woow! Now they send a wicked Czech Photographer to mess up with Ethiopians, huh!

[John 8:44]

You are of your father the devil, and you want to do the desires of your father He was a murderer from the beginning, and does not stand in the truth because there is no truth in him Whenever he speaks a lie, he speaks from his own nature, for he is a liar and the father of lies.

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የረር ጽርሃ ሥላሴ ተዓምርና ምስጢር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 16, 2012


 

 

ሰሞኑን ወደ የረር በር ሥላሴ ገዳም ጎራ ብየ ነበር። እንደሚታወቀው ይህ ገዳም የተሰራው ከ6 ዓመታት በፊት፤ ሁለት ግለሰቦች የተለያዩ ራዕዮች ከታዩአቸው ጊዜ በኋላ ነበር።

የመጀመሪያውን ራዕይ ያዩት አንዲት ሴትዮ ነበሩ። እኚህ ክርስቲያን ኢትዮጵያዊት አሁን ገዳሙ የሚገኝበትን ቦታ በወቅቱ በመግዛት አነስተኛ የሆነ ቤት ሠርተው መኖር ጀመሩ። ነገር ግን ይህን ቦታ ለቀው እንዲሄዱ የሚጠቁም ራዕይ በተደጋጋሚ ይታያቸው ነበር። ሴትዮዋም ይህን ራዕይ ቸል በማለታቸውና ኑሮአቸውንም እዚያው ቦታ ላይ ለመግፋት በመወሰናቸው እያበዱ መጡ። በዚህም ምክኒያት ከዓመት በኋላ ግቢውን ለቅው ለመውጣት ተገደዱ።

ቀጥሎም ራዕይ ለማየት የበቁት ግለሰብ አሁን ገዳም የሚገኝበት አካባቢ ላይ መሬት ገዝተው ከባለቤታቸው ጋር የሚኖሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዊ፡ አቶ ቃሲም ናቸው። በራዕይ ተገለጠለት፡ ይመልከቱ

አካባቢው፡ በጣም ልዩ የሆነ፡ ባለታሪክ እና የተቀደሰ እንደሆነ ለእኝህ ሰው በራዕይ ይታያቸው ነበር። እዚህ ቦታ ላይ መሬት ሥር ተደብቆ የሚገኝ አንድ የጥንት ቤተክርስቲያን ሕንፃ እንዳለ እመቤታችን ድንግል ማርያም ለኚህ ግለሰብ በራዕይ ደጋግማ ትገልጽላቸዋለች።

ራዕያቸውንም ለሚያውቋቸውና ለሚመለከታቸው ወገኖች ሁሉ ለማጫወት ከበቁ በኋላ መጨረሻ ላይ ቤተ ክርስቲያኗ አለችበት ወደተባለው ቦታ ሁሉም አምርተው ቁፏሮ ይጀምራሉ። ግለሰቡ በራዕይ የታዩዋቸው ነገሮች ሁሉ መሬት ውስጥ ተቀብረው ይገኛሉ፡ ከነዚህም ውስጥ ጥንታዊ አጽሞች፡ መስቀላት እና ቅርሳቅርሶች ይገኙበታል።

4ኛው ምዕተ ዓመት ላይ በኢትዮጵያና አካባቢዋ ነግሥው ሲያስተዳድሩ የነበሩት አብርሃወአጽበሃ በሥላሴ ስም ይህችን ቤተከርስቲያን አሰርተዋት እንደነበር አሁን በደንብ ለማወቅ ተችሏል። ባካባቢው ገና ብዙ ምስጢራዊ የሆኑ ነገሮች እንደሚገኙ ይታመናል። ሣርና ዛፎች በሚገኙበት ቦታ ላይ ከየት እንደሚመጣ የማይታወቀው የሚጤስ ዕጣን ሽታ አልፎ አልፎ እንደሚሸታቸው ሰዎች ይናገራሉ። በጣም ቅዱስ የሆነ ጽላትም አሁን ቤተክርስቲያን የተሰራበት ቦታ አካባቢ ጥልቅ መሬት ውስጥ ተደብቆ እንደሚገኝ ነገር ግን እሱን እስካሁን ለማውጣት እንዳልተቻለ የኃይማኖት መሪዎች አውስተውኛል።

አሁን ቤተክርስቲያኗ በነበርችበት ቦታ ላይ የረር ጽርሃ ሥላሴ ገዳምበቆንጆ መልክ ተሰርቷል።

ቀደም ሲል የጠቀስኳት ሴትዮ መጀመሪያ ትኖርበት በነበረው ቦታ ላይ አንድ አነስተኛ ቤተመቅደስ ተሠርታለች።

ሴትዮዋም ሥላሴ ገዳም አጠገብ አንድ ቤት ተሠርቶላት ከልጅዋ ጋር እየኖረች እንዳልች ባለፈው መስከረም 2004፡ ልክ በሥላሴ ዕለት ፡ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታናለች። (እግዚአብሔር አምልክ ቀበላት!)

አቶ ቃሲም ከገዳሙ አጠገብ ከቤተሰባቸው ጋር አንድ አነስተኛ ሱቅ ከፍተው ይኖራሉ። አቶ ቃሲም ከቤተክርስቲያን ሰዎች ጋር በየጊዜው ይገናኛሉ፡ ነገር ግን ተባብሮ ለመስራት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ እሳቸው እና ያነጋገርኳቸው የቤ/ክርስቲያን አገልጋዮች አውስተውኛል።

በቤተክርስቲያን በኩል አቶ ቃሲምን ለማስጠመቅ የተሞከረው ሙከራ ሁሉ ከሽፏል። አቶ ቃሲም ለመጠምቅ እና ክርስትናን ለመቀበል ፈቃደኛ አይደሉምና። እንዲያውም፡ እሳቸው፡ በድፍረት የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን እንደሚሳደቡ፡ “ቄሶቹ የገንዘብ አፍቃሪዎች ናቸውእያሉ ስማቸውን እንደሚያጠፉ ነው የተነገረኝ።

አቶ ቃሲም፡ እኔ አሁን ለመጠመቅ ዝግጁ አይደለሁም!” “አባቶች በሚባሉትታሪክ አምናለሁ፡ ነገር ግን እኔን ለማጥመቅ ብቃት ያላቸው ቄሶች የሉም፡ ሁሉም የገንዘብ አፍቃሪዎች ናቸው…. በነገራችን ላይ ሙስሊም ራዕይ አይታየውምእየተባለ አይደለም አዲስ አበባ በየመንገዱ የሚወራው!?” እያሉ በማፌዝ አጫወቱኝ ነበር።

ይህም ሁኔታ በጣም ስላሳዘነኝ ነገሮችን ጠለቅ ብዬ ለመመርመር ሞከርኩ፤ ሁሉም የተወሳሰበ ስለሆነ ጉዳዩ ብዙዎቻችን ልናስብ እንደምንችለው ሆኖ መቀመጥ እንደማይኖርበት አሁን ተረዳሁ።

ይህ ቦታ ብዙ ታላላቅ ምስጢሮች የተደበቁበት እና መንፈሳዊ የሆኑ ጉዳዮች የሚገኙበት ቦታ ስለሆነ ከፍተኛ መንፈሳዊ ትግል ይካሄድበታል። ሰይጣን ከቅዱሳን ቦታዎች አይርቅምና ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተንኮልን እየፈጠረ ቅዱስ መንፈስን (ሥላሴን) ለመፈታተን ይሞክራል።

አቶ ቃሲም ከጥሩ የኢትዮጵያ ክርስቲያን ቤተሰብ የወጡ፡ አባት እና እናታቸው ታማኝ የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እንደነበሩ፡ ባለቤታቸውም ክርስቲያን የሰሜን ሴት እንደሆኑ ተነግሮኛል።

50 ዓመት ዕድሜ የሚሆናቸው አቶ ቃሲም በወጣትነት እድሜአቸው ወደ አረብ አገር ሄደውና ሰልመው ከተመለሱ በኋላ ነበር ለዚህ የራዕይ ጸጋ ለመታደል የበቁት። የአባቶቻቸውን እና የእናቶቻቸውን እምነት የከዱት አቶ ቃሲም እስልምናን በመቀበል የኢትዮጵያን አምላክ ጨምረው ነበር የከዱት፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ቻይ፡ መሐሪ እና ሩህሩህ ነውና ለአባቶቻቸው፡ ለእናቶቻቸውና ለባለቤታቸው ሲል አንድ ሌላ እድል ሰጣቸው። እሱም፡ ፈጣሪአችን የኢትዮጵያ አምላክ እና ሥላሴ መሆኑን በእመቤታችን አማካይነት ገለጸላቸው፡ የተገለጸላቸውም ሁሉ ከነማስረጃው ፊታቸው ላይ ቀረበ፡ አቶ ቃሲም ግን ጥመቅትን የመሰለ ታላቅ ስጦታ ለመቀበል ወይም ለመጠመቅ ፈቃደኛ አይደሉም። እንዲያውም ሳዑዲ ዓረቢያ ሄጄ ሸሆችን ማማከር አለብኝ እያሉ በማቅማማት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ሕዝብ እንደ አምላኩ ታጋሽ፡ መሐሪ እና ሩህሩህ ስለሆነ፡ ተጠምቀህ ብትድን ጥሩ ነው፡ መዳን ትፈልጋለህን?” ብሎ ከመጠየቅ ሌላ ማንንም አስገድዶ ወደ እግዚአብሔር ኃይማኖት የመቀየር ፍላጎቱም የለውም። አቶ ቃሲም ያው ሥላሴ ቤተክርስቲያን አጠገብ ቤት ሠርተው ይኖራሉ። እዚያም ሆነው የቤተክርስቲያን አገልጋዮችን መሳደብና መገለማመጥ ችለዋል፡ ሆኖም ክርስቲያኑ ተገርሞ ራሱን ከመነቅነቅ በቀር ማንም ትንፍሽ ብሎ ሊነካቸው የቃጣ የለም።

ክርስቲያኖች እስላም በሆኑ አገሮች የሚደርሱባቸውን በደሎች ዓለም ሁሉ የሚያውቀው ነው። አረብ አገር የሚገኝ አንድ ክርስቲያን፡ እንኳን ሸሆችን እና ኢማሞችን እንዲህ በግልጽ ሊሳደብ እና መስጊድ አጠገብ ቤት ሰርቶ ሊኖር፡ መጽሐፍ ቅዱስን ይዞ፡ መስቀል አንጠልጥሎ ወደ አገራቸው ከገባ እንኳ ለእስራት፡ ለስቃይና ለግድያ ይበቃል።

ከዕለታት አንድ ቀን በግብጽ አገር ያሉ አንድ ሙስሊም ሸህ ፡ ታዋቂ የነበረውን ግብጻዊ ክርስቲያን መሀንዲስ መስጊድ እንዲሰራላቸው ይጠይቁታል። እርሱም በደስታ ፈቃደኝነቱን ይገልጽ እና መስጊዱን በደንብ አሳምሮ ይሰራላቸዋል። በዚህም ሥራው በጣም የተደሰቱት ሸህ ወደ መሀንዲሱ ዘወር ይሉና አሁን እስልምናን ተቀበል!” ብለው ይጠይቁታል፤ መሀንዲሱ ግን አይ አይሆንም እልምናን አልቀበለዐም በማለቱ አስገደሉት።

ክርስቶስ አምላክ፤ ስለ አየኸኝ አምነሃል፤ሳያዩየሚያምኑ ብፁዓን ናቸውብሎ አስተምሮናል። ስለዚህ አሁን አቶ ቃሲም ታላቅ ፈተና ላይ ነው የሚገኙትክርስቶስን ወይም ሥላሴን የሚቀበሉት ቄሶቹን ወይም ሌላውን ለማስደሰት ብለው መሆን የለበትም፡ እግዚአብሔርን እንጂ። መዳን መፈለግ አለመፈለግ የራሳቸው መብት ነው፤ ግን ለጠፉት ሙስሊም ወገኖቻቸው አርአያ በመሆን ወደ ክርስቶስ መንግሥት እንዲመጡ ቀጥተኛውን መንገድ መምረጥ ነበረባቸው። በስድስት ዓመታት ውስጥ ስንት ሙስሊም መዳን በቻለ ነበር! የቤተክርስቲያን አገልጋዮች ጥፋት ወይም ድክመት የለባቸውም ማለት አይደልም፡ ሁላችንም ድክመት አለብን፡ ኃጢአተኞችም ነን፡ ነገር ግን እንኳን ከውጭ ሆነው ለሚታዘቡት አቶ ቃሲም ቀርቶ ክርስቲያኖችም እንኳ ቢንሆን በቤተክርስቲያን አገልጋዮች ላይ ምንም ዓይነት ስድብና ዘለፋ እንዲሁም ተቃውሟዊ ኃይለ ቃል የመሠንዘር መብት ሊኖረን አይገባም። የስድብና ፌዝ መንፈስ ከእግዚአብሔር አይደለምና!

አንድ ሌላ የታዘብኩት አሳዛኝና በጣም አደገኛ የሆነ ነገር የሚከተለው ነው፤

የሥላሴ ገዳምን አድራሻ ፈልጌ ለማግኘት በሞከርኩበት ወቅት የረር ሠፈር አንዳንድ ሰዎችን እጠይቅ ነበር። በአንድ ወቅት እስላማዊ አለባበስ የነበራቸው አንዲት ሲትዮ ወደኔ ጠጋ ብለው መጡና፡ “ “ቃሲም ሥላሴን” ነው እየፈልግክ ያለኽው? በዚህ በኩል ስትሄድ ታገኘዋለህ” ብለውኝ አለፉ። “ቃሲም ሥላሴ?” ፤ ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ብዬ እጅግ በጣም ተቆጣሁ። ወደ 20 የሚጠጉ የአካባቢውን ነዋሪዎችና ጎብኝዎች፤ “የዚህ ቦታ ስም መጠሪያ ምን ይባላል?” ብዬ መጠያየቅ ጀመርኩ። “ሥላሴ” “የረር ሥላሴ” “ሠፈራ ሥላሴ” ተብሎ እንደሚጠራ ነው በብዛት የተነገረኝ። “ቃሲም ሥላሴ” በማለት አንዳንዴ ለመጥራት እንደሚሞከርም ግለሰቦቹ በሃዘንና በንዴት ገልጸውልኛል። በርግጥም ገዳሙን በዚህ ዓይነት መልክ ለመጥራት መሞከሩ በጣም መጥፎ ብቻ ሳይሆን እጅግ ኃይለኛ መቅሰፍት አምጪም ነው።

ከዚህ በተረፈ ሦስት ዓብያተክርስቲያናት በነዋሪው ብርታት በሥላሴ ዙሪያ፡ ትንሽ ራቅ ራቅ ብለው ተሠርተዋል። ብዛት ያላቸው ሙስሊሞችም በቤ/ክርስቲያን አገልጋዮች ጥረት በየረር ጽርሃ ሥላሴ ተገኝተው በመጠመቀ እየዳኑና ክርስቶስንም እየተቀበሉ እንደሆነ ለማወቅ ችያለሁ።

ሥላሴ የተመሰገኑ ይሁኑ!

__________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: