Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • March 2023
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728293031  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘የሉሲፈራውያን ሤራ’

አፈወርቂ & አህመድ እንደገና ተገናኙ | ሉሲፈራውያኑ ሌላ የሩዋንዳ እልቂት በተዋሕዶ ትግሬዎች ላይ አቅደዋልን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 10, 2018

ሉሲፈራውያኑ ላለፉት 50 ዓመታት ከፍተኛ ትኩረት ያደረጉት የተዋሕዶ ክርስትና ማዕከል በሆነችው በትግራይ ግዛት ላይ ነው። ለዚህም በተደጋጋሚ ሲታዩ የነበሩት፤ ረሃቡ፣ በሽታው፣ ጦርነቱ፣ አስገድዶ ማፈናቀሉ፤ ይመሰክራሉ። ከሌሎች የኢትዮጵያ ግዛቶች የበለጠ እዚህ ይፈጸም ነበርና።

በለንደኑ ስምምነት መሠረት፡ ላለፉት 27 ዓመታት መንግስታዊ ሥልጣኑን በከፊልም ቢሆን ለትውልደ ትግራዮች ከሰጡ በኋላ፡ የደቡቡ ኢትዮጵያ ግዛቶች ተወላጆችን (ኦሮሞ፣ ወላሞ፣ ሶማሌ፣ ጉራጌ) በፖለቲካው፣ በተለይ ደግሞ በምጣኔ ኃብትና ሃይማኖት ዘርፍ አገሪቷን እንዲቆጣጠሩና አሁን ለደረስንበት ዘመን እንዲያዘጋጇቸው አደረጓቸው፤ አንድ አዲስ ትውልድ ፈጠሩ ማለት ነው።

ይህ አዲስ ትውልድ በትግሬዎች ላይ ጥላቻ እንዲኖረው ከፍተኛ ቅስቀሳ ከማድረጋቸውም ሌላ የመረጧቸውን ቡድኖች ወደ ኤርትራ በመላክ አሁን እየተካሄደ ላለው ድራማ አሰለጠኗቸው። ለዶ/ር አብይና የትግል ዘመዶቹ በዚህ መልክ ሥልጠና ካደረጉ በኋላ አመቺ ጊዜ በመጠበቅ (የሰው በትግሬ ላይ ያለው ጥላቻ ከፍተኛ ደረጃ እስኪደርስ ድረስ) ሥልጣን ላይ አወጧቸው። የዶ/ር አብይ በሞኙ ሕዝባችን ተወዳጅነት ማትረፍ ሰው ሁሉ በትግሬ ላይ ምን ያህል ጥላቻ እንዳለው ነው የሚያንጸባርቀው፤ ሌላ ለዚህ ዓይነት ተወዳጅነት የሚያበቃ ምክኒያት ሊኖር አይችልም፤ ዜሮ።

ምንም እንኳን ኢአማንያኑ ትውልደ ትግራይ ኢሀዴጎች ፀረተዋሕዶ የሆነ አቋም ያላቸው ኮሙኒስቶች መሆናቸው ቢታወቅም፤ ግን፡ “ምናልባት ልክ እንደ መለስ ዜናዊ ወደ ተዋሕዶ ሊመለሱ ይችላሉ፥ ነበር ዥንጉርጉርነቱን ሊለውጥ አይችልም”፥ በሚል ስጋት ሊቆጣጠሯቸው የሚችሏቸውን የደቡብ ሰዎች (ጴንጤዎችና ሙስሊሞችን) ሥልጣን ላይ ማውጣቱን መርጠዋል። ትግሬ አይሁን እንጅ ሌላው የፈለገው ሰው ሥልጣኑን ቢይዝ የሚደሰት ትውልድ የፈራበት ዘመን ላይ ደርሰናልና።

የሉሲፈራውያኑ ሤራ ዒላማውን እየመታ ነው፤ ዋናው ዒላማቸውም ተዋሕዶ ክርስትና ናት፤ የተዋሕዶ ክርስትና መሠረት ደግሞ ትግራይ ናት። ትግራይን ካጠፉ ለብዙ ዕቅዶቻቸው እንቅፋት የሆነችውን ተዋሕዶን አጠፉ ማለት ነው። አሁን ትግራይን በመክበብ፥ ልክ አረቦችና ፀረሴማውያን የሆኑት ኍ በአይሁዶች ላይ እንደሚያሳዩት ጥላቻ፤ ትግሬዎችንም እንዲሁ መጥፎ ስም እየሰጡ በመኮነን እና በመተናኮል ላይ መሆናቸውን ሁላችንም የምናየው ነው።

ብዙ ጊዜ የሕዝቦች እልቂት ከመጀመሩ በፊት አንዱ የሕዝብ ክፍል ይለይና መጥፎ ስም እንዲሰጠው ይደረጋል፣ ይንቋሸሻል (ውሻውን መጥፎ ስም ሰጥተህ ገደለው!) እንዲሉ። ከዚያም የራሴ ነው፣ እወደዋለሁ፤ “በውስጤ ነው” የምንለውን ሰው እንድናጣው እንደረጋለን። ብዙ ጊዜ በደንብ በተቀነባበሩ ስሜታዊና አስደናቂ የአውሮፕላን ላይ ግድያዎች።

/ር አብይን ተወዳጅ እንዲሆን ለማድረግ ከሁሉም አቅጣጫ ተሞክሯል፤ የእኛን በጎ መሆን የማይመኙት ምዕራባውያን እና አረቦች እንኳን ያጨበጭቡለታል። ቀጣፊው የእንግሊዝ መንፍስት ቱልቱላ፡ ቢቢስ እንኳን በትናንትናው ዕለት ይህን አቅርቧል፡ “Abiy-mania: Ethiopia Transformed

/ር አብይን የአውሮፕላን በረራዎች እንዲያበዛ፥ በተለይ ደግሞ ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ቶሎ ቶሎ እንዲገናኝ ወይም አብሮ እንዲበር አዘውታል።

ይህ ሁኔታ ምንን ነው የሚያስታውሰን? አዎ! ... ሚያዝያ 6 ቀን 1994 .ም ምሽት የሩዋንዳን እና የቡሩንዲን ፕሬዚደንቶች ይዛ ትበር የነበረች አውሮፕላን በሚሳኤል ተመታ ፕሬዚደንት ጁቨን ሀቤራማና እና ሲፕሪንኔታሪማ ተገድለዋል። የሁለቱ ፕሬዚደንቶች መገደለም ለሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል መንስኤ ነበር።

የፕሬዚደንቶቹን አውሮፕላን ለመምታት ተጠያቂዎቹ ምዕራባውያን እንደሆኑ አንዳንድ መረጃዎች ይናገራሉ። በጊዜው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሐፊ የነበሩት ግብጻዊው ቦትሮስ ቦትሮስ ጋሊ በአንድ ወቅት፡ “ለሁሉቱ ፕሬዚደንቶች መገደል የአሜሪካው የስለላ ተቋም፡ ሲ አይ ኤ ተጠያቂ ነው” ብለው ነበር።

በኢትዮጵያችንስ ተመሳሳይ ፅንፈኛ የሆነ ተግባር ለመፈጸም ታቅዶ ይሆን?

እስኪ እናስበው፡ ሞኙ ሕዝባችን አሁን በሚገኝበት ስሜታዊ ቅዠት ላይ ጠ/ሚንስትር አብይ አህመድን እና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቅን የያዘቸው አውሮፕላን ተመታ ሕይወታቸውን ቢያጡ ምን ሊከተል እንደሚችል። ትግሬዎች ናቸው አውሮፕላኑን የመቱት በማለት፤ በትግራይ እና ትግሬዎች ላይ የሩዋንዳ ዓይነት እልቂት ይመጣል ማለት ነው። አዎ! በቂ የጦር መሣሪያ ከሱዳን በጎንደር በኩል፣ ከሶማሊያ በጅጅጋ በኩል በማስገባት ላይ ናቸው።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ግእዝ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ሌላ አገር ሐይማኖታዊ/ መንፈሳዊ ቋንቋ ነው። የዓለም ህዝብ ተቀብሎታል፤ ከኢትዮጵያውያን በስተቀር”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 7, 2017

ዛሬ: ..አ: 07/07/2017 ነው። ምስሉ ኩራታችን የሆነው አየር መንገዳችን ቦይንግ 777 ን ሲያበር ያሳያል።

በእግዚአብሔር አምላካችን ዘንድ አንድ ሐቅ ነው ያለችው፤ ወደድንም ጠላንም፡ አንድ ሐቅ ብቻ! ግዜ በእጃችን አይደለም ያለው፤ ለእኛ የተባለውን ነገር ሁሉ፣ የተሰጠነን ህልውና፣ የተረከብነውን ቅዱስ መንፈስ በመጠቀም ዛሬውኑ፣ አሁኑኑ ነው በሥራ ላይ ማወል የሚገባን። “ቆዩ፤ አሁን ሁኔታው አይፈቅድም ቀስ እንበል!„ እያሉ ከመቀመጫቸው መነሳት የማይሹትን አታላዮችና ሌላውንም እንዲያንቀላፋ የሚያደርጉት፣ በሌላው ላይ ብቻ ሳይሆን በራሳቸውም ላይ ነው ከባድ መዘዝ በማምጣት ላይ የሚገኙት። የራሳቸውን ቆሻሻ የቤት ሥራ ለመጪው ትውልድ አሳልፎ በመተው፡ በአሁኖቹ ህፃናት ላይ ሊሰረዝ የማይችሉ በደልና ኃጢአት ነው የሚፈጽሙት።

“ኢትዮጵያ አገራችን ተከባልች፣ ጠላቶቿ እራሳቸው በዘረጉት የጊዜ ጎዳና ላይ በመጓዝ አመቺ የሚሆነላቸውን አጋጣሚ በመጠበቅ ላይ ናቸው!፡” እያልኩ ላለፉት 15 ዓመታት ባቅሜ ያለማቋረጥ እጠቁም ዘንድ እግዚአብሔር ይገፋፋኝ ነበር። ሉሲፈራውያኑ ችግኞቻቸውን በየአገራቱ ተክለዋል፣ በተለይ በአገራችን፤ የክርስቶስንም ልጆች በግልጽ ለመዋጋት ቆርጠው ከተነሱ ውለው አድረዋል። ባሁኑ ሰዓትም ኢአማናያን ሰዶማውያኑን እና መሀመዳውያኑን እንደ መሳሪያ አድርገው በመጠቀም ላይ ይገኛሉ። አሁን ሁላችንም አካሄዳቸውን መከተል የምንችልበት ጊዜ ላይ ደርሰናል፤ ዓይን ያለው ፈጥኖ ይመልከት።

ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ ምን እንደሚሰሩ፡ ብሎም ማን እንደሆኑ ለመላው ዓለም በግልጽ ደፍረው ብዙውን ነገር እያሳዩን ነው። ካሳዩንም ሁኔታዎች መካከል የሚከተሉትን እንመልከት፤ ይህ ሁሉ ባጭር ጊዜ ውስጥ ነው የተከሰተው፦

 1. ታላቋ ብሪታኒያ ከአውሮፓው ህብረት ትወጣለች ብለው በፍጹም አልጠበቁም። brexitሬፈረንደም ውጤቱን ለመከለስ ያው እስካሁን በመታገል ላይ ናቸው

 2. የዶናልድ ትራምፕን ለፕሬዚደንትነት መብቃት ፈጽሞ አልጠበቁትም ነበር። ከተመረጡበት ቀን ጀምሮ በሳቸው እና ደጋፊዎቻቸው ላይ እየተካሄደ ያለው የጥቃት ዘመቻ በታሪክ ተወዳዳሪ አይኖረውም

 3. ኢትዮጵያውያን በአገር ቤትም በውጩም እርስበራሳቸው እንዲበጣበጡ፣ በህንድ ውቂያኖስ፣ በቀይ ባሕር፣ በሜዲተራንያን ባሕር፣ በቆሼበለንደን እና በካሌ ለሉሲፈር መስዋእት እንዲሆኑ ተደረጉ

 4. ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተመረጡ። አንድ ኢትዮጵያዊ እንደዚህ ዓለማቀፋዊ ተጽዕኖ ማድረግ በሚችል ድርጅት ውስጥ “ሰርጎ” መግባቱ፣ ከኢትዮጵያዊነት አንፃር፡ እሰይ! ትልቅ ነገር ነው! ለአገራችን የሚበጅ ነው! የሚያሰኝ ነው። ከስልጣን፣ ከታዋቂነት እና ከንዋይ ኃብት የበለጠ፡ በተለይ ለኢትዮጵያውያን፡ ሌላ እጅግ ትልቅ ነገር አለ። ዶ/ር ቴዎድሮስ ኢትዮጵያን የሚጠቅም እና እግዚአብሔር አምላኳን የሚያስደስት ሥራ ለመሥራት ይበቃሉን? ወደፊት የምናየው ነው። ለማንኛውም እንጸልይላቸው።

 5. ሊሲፈራውያኑ በአሜሪካ የሠሩትን ዓይነት ስህተት ላለመስራት፣ በፈረንሳይ ሰዶማዊውን ማክሮንን ፕሬዚደንት ለማድረግ በቁ

 6. በአየርላንድም ሰዶማዊውን የህንድ ስደተኛ በጠቅላይ ምኒስቴርነት አስቀመጡ

 7. በጀርመንም አንድ ሳምንት ብቻ በፈጀው ያልተጠበቀ ስብሰባ የሰዶማውያን “ጋብቻ” ሕጋዊ እንዲሆን በጥድፊያ አጸደቁት። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

 8. በኢትዮጵያም መንፈሳዊውን ኢትዮጵያኛ የግእዝ/አማርኛ ቋንቋ ለማጥፋት እንዲሁ በተጣደፈ መልክ ምክር ቤቱ ህግ እንዲያጸድቀ ተደረገ። ይህን መሰሉን ጉዳይ ሕዝቡ በሬፈረንደም መወስን ነበረበት።

 9. G20 አገራቱ መሪዎች ስብሰባ ከመጀመሩ ከሁለት ቀናት በፊት የአፍሪቃው ህብረት መሪዎች በአዲስ አበባ ተሰባሰቡ

እነዚህ እና ሌሎች ተመሳሳይ ጉዳዮችም በዚህ የሀምበርጉ የመሪዎች ስብሰባ ላ በሪፖርት መልክ ለውይይት እንደሚቀርቡ የሚያጠራጥር አይደለም። በነገራችን ላይ፡ ሀምበርግ ከተማ በተቃዋሚ ኃይሎች ብጥብጥ እየታወከችና እየነደደች ነው! እሳት! እሳት! እሳት!

አፍሪቃ ዋና የመወያያ ርዕስ እንደሆነች ቀደም ሲል ተጠቁሟል። ብዙ የአፍሪቃ አገሮች መሪዎች በስብሰባው እንዲሳተፉ ቢደረግም፤ አፍሪቃን በዋናነት የሚወክሉት ግን ደቡብ አፍሪቃዊውና ባለ አራት ሚስቱ (ሰዶማዊ) ያዕቆብ ዙማ ናቸው።

የሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ

በእኛ አቆጣጠር በ 2007 .ላይ ታታሪው ወንድማችን ፍስሐ ያዜ ካሳ ሳጥናኤል ጎል ኢትዮጵያ” የሚለውን ድንቅ መፅሐፍ ጽፎልናል።የዚህ መፅሐፍ ትኩረት ስለ አዲሱ የምድር መንግስት ምስረታ ብቻ ሳይሆን፤ የፍፃሜው ጦርነት ምን እንደሚመስል፣ኢትዮጵያም ከፍፃሜው ጦርነት ጋ በተያያዘ የተለየ ትኩረት እንደተደረገባት፣ ዘንዶውን በኒውክሌር እናግዛለን፤ እግዚአብሔርንና መላዕክቱንም እናሸንፋለን!ብለው የኃያላን አገራት መሪዎችና የቫቲካን ቤተክርስቲያን የሚዝቱበትና የሚዘጋጁበት፤ ጦርነቱም በዋናነት ኢትዮጵያ ላይ እንደሚሆን፤ጎላቸውም ኢትዮጵያ እንደሆነች ይገልፃል። የዓለማችን ታላላቅ የሚባሉ ገለባ አገራትና መሪዎች ከዚህ በኋላ ትልቁ የቤት ስራቸው ኢትዮጵያ ላይ እንደሆነ በማስረጃ እያስደገፈ ተንትኖታል፡፡

ለዛሬው የሚከተለውን ከመጽሐፉ ጠቅሼ አቅርቤዋለሁ፦

በቅርቡ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የታሪክ ዲፓርትመንትን ሊዘጋ ነው ሲባል ሰማሁና በጣም ተገረምኩ። እንዴት? ታሪክ ከታጠፈ ጂኦግራፊም ቀረ ማለት ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው። እሱ ቀረ ማለት ደግሞ አገር አገርነቷ የሚታወቀው በምን ሊሆን ነው? ብዬ ራሴን ጠየቅሁ። የዲፓርትመንቱ ሃላፊዎች ለምን አደጋ እንዳንዣበበበት ሲጠየቁ “በዘርፉ የሚመረቁ ተእማሪዎች ስራ እያጡ ተቸገርን፣ 70/30 ፕሮግራም፣ ወዘተ…„ የሚል የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ ዓይነት ምክንያት ሲሰጡ ሰማሁና ግርም እንዳለኝ ተውኩት። የታሪክ ትምህርትን ያጠፋች አገር ካለች ብየ ኢንተርኔት ላይ አጣራሁ። ይኖራል ብዬ ማሰቤ ራሱ የሚገርም ነው። የለም! ስራ ስላለ ስለሌለ ነው እንዴ ታሪክ ማወቅና መማር ማስተማር ያስፈለገው? ምን ማለት ይሆን? እያልኩ ሳይገባኝ አለሁ። ጭራሽ ኢትዮጵያ ታሪክን ማስቀረት? አሜሪካ እንኳ የሶስት መቶ ዓመት ታሪክ ይዛ ልዩ ትኩረት የሰጠችው ዲፓርትመንት ነው። ጭራሽ ኢትዮጵያ? ታሪክን ማስቀረት ማለት ምን ማለት መሰለህቀጣዩን ትውልድ አገርም ታሪክም ንብረትም ማንነትም ምንም ምንም የለህም ማለት ነው። መነሻም መድረሻም የሌላቸው ከንቱ ትውልዶች ናችሁ! ማለት ነው! ቀጥተኛ ትርጉሙ ይሄ ነው። ቀጣዩን ትውል ምን እያሉት መሰለህየግዛታችሁ ስፋት አይታወቅም። አባቶቻችሁም አልተናገሩም እንደማለት ነው! ደግነቱ ቀጣይ ትውልድ የሚባል ነገር…„

አሁንማ ግልጽ ሆነ! ለምን እንደዚያ እንደተደረገም አውቅነ! ይሄ ብቻ ሳይሆን ይህ በተባለ ማግስት በታሪካዊው ቤተ መፃህፍት የነበሩትን ታሪካዊ ሰነዶች በሙሉ ቦታ ጠበበ በሚል ተልካሻና አስቂኝ ምክንያት ለሲቅ እቃ መጠቅለያነት ይውሉ ዘንድ ጠርገው አወጡና አጫርተው ሸጧቸው። ግራ ገብቶኝ ነበር። ግን ግልፅ ሆነ። ለካስትልቅ የዛፍ ግንድን ሲገዘግዙ ሲገዘግዙ ቆይተው፤ ግዝገዛው ሲያልቅ ግንድስ ብሎ መውደቁ ነው። ገዝጋዡም ስራውን አጠናቆ ላቡን እየጠራረገ እፎይ ብሎ አረፈ። ተገንድሶ የወደቀውን ግንድ ገዝጋዡ ተሸክሞ የመሄድ ግዴታ የለበትም። ለሸክም የተዘጋጁ ሊሎች ሰራተኞች ይኖራሉ። የቀረውን ግፋፎና ቅጠላ ቅጠል የሚጋፋና አካባቢውን የሚያፀዱም ተዘጋጅተዋል፤ ስራው ግን ተጠናቋል!„

በጣም ያሳዝናል! ግዝገዛውን አውቅ ነበር። ይሄኛውን ግን አልሰማሁም፤ አዝናለሁ”

አሁን ነው እንዲያ የሆነው። አንድ ተማሪ አልተቀበሉም። በማግስቱ ግን አዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የቻይንኛን ቋንቋ በመደበኛ ፕሮግራም በዲግሪ መርሀ ግብር ማስተማር ጀመረ። የራሳችንን ትተን ቻይንኛ እየተማርን ነው። ቻይና ደግሞ በተመሳሳይ አማርኛ ቋንቋን ሶስተኛ ቋንቋዋ አድርጋ አገሯ ላይ እያስተማረች ነው። ሌሎች የG20 አገራትም እንደ ቻይና አማርኛንና ግእዝን ሶስተኛ ቋንቁ አድርገው በዲግሪ እያስተማሩ ነው። እስከ ፒ...ዲ ድረስ እያስተማሩ ነው። ይህን ነገር በዜና ሳይ ያው ከልማቱ ጋር በተገናኘ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር። አሁን ነው ጅልነቴ የገባኝ። ለካስ ታዘው ነው። ስለዚህ እኛ የነሱን መማር ጀመርንእውነት ለንግዱ፣ ለልማቱ፣ ለምናምኑ ቻይንኛን መልመድ እዚህ ድረስ አስፈልጎ ነው? ከዚህ ወዲያ ውድቀት አለ? ከዚህ ወዲያ ሴራ አለ? ሌቦች ናቸው! እኛም እልል ብለን እንቀበላቸዋለን!

አንድ ተረት ልናገር፦ ሰሜን ሸዋ አካባቢ አንዲት እብድ ነበረች አሉ። ይቺ ታዋቂ እብድ በአንድ ቅዳሜ ማለዳ ላይ ትነሳና፣ “ዛሬ ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። ገበያ እንዳትሄዱ ቤት ይቃጠላል። እያለች ስትለፍፍ አረፈደች። የቀዬው ሰዎች ግን፤ “ዛሬ ደግሞ ይቺ እብድ በጠዋት ተነሳባት” እያሉ አሽሟጠጧት። ቀኑ የገባያ ቀን ነውና የእብዷን ልፍለፋ ከምንም ሳይቆጥሩ ልብ ብለውም ሳይሰሙ ጎጆ ቤታቸውን ዘጋግተው ወደ ገበያ ሄዱ። አጅሪት ደግሞ ቀዬው ጭር ማለቱን ስታይ፤ እሳት በችቦ ትለኩስና ያንን ሁሉ ጎጆ ቤት ታቃጥለዋለች። ሁሉንም ቤት አንድዳ ዞር ትላለች። ያገሬው ህዝብ ገበያ ውሉ ሲመጣ መንደሩ እንዳለ ተቃጥሏል። በዚህ ጊዜ ያች እብድ ተመልሳ መጣችና፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል፤ ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያለች ትናገር ጀመር። አሁንም ከዚህ ቀደም ጥቂት ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያ ታሪክ እየተዘረፈ ነው፤ ታሪኩም አፈ ታሪክ አይደለም፤ ከ3ሺ ዓመትም ይበልጣል፤ ነጮችንም አትመኑ እያሉ ስድብ ቢጤም እያካተቱ ለመግለፅ ሞክረው ነበር። ይገሬው ጎሳ መሪዎች ግን ፈፈፋውን ልብ አላሉም፤ ወደ ጎን ሊሉት ሞከሩ። አሁን እኔ እነሱን ብሆን ኖሮ እንደዚያች እብድ፤ “ነግረናል ቤት ይቃጠላል ብለናል” እያልኩ በየአደባባዩ እለፍፍ ነበር”

የሚያሳዝን ነው!“

አለም (ዲያብሎስ) “ማየት ማመን ነው” ይለናል | እግዚአብሔር ደግሞ “ማመን ማየት ነው” ብሎ ያስተምረናል

It’s 07/07/17 | G20 Summit Embarrassment: Germany’s Merkel Bows To Saudi Arabian State Minister


______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

በሉሲፈራውያኑ ዘንድ ረመዳን የሽብር እና የግድያ ወር ነው | Gunmen Massacre Coptic Christians in Egypt, Killing at Least 26

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 26, 2017

ክርስቲያን ወገኖቻችንን እየጨፈጨፏቸው ነው | በሉሲፈራውያኑ ዘንድ ረመዳን የሽብር እና የግድያ ወር ነው

እኛ ደግሞ ቅዱስ የሆኑትን የእግዚአብሔር በዓላትን፤ የክርስቶስ እርገትን እና ጰራቅሊጦስ (መንፈስ ቅዱስ) ወይም ጴንጤቆስጤን (በዓለ ሃምሳ) የምናከብርበት ዕለታት ናቸው። ሰይጣን በዚህ ደስ አይለውም፡ ልጆቹም ይከፋሉ፣ ክፉ የስጋ ገዳዮች ይሆናሉ፣ ዓይናችን እያየም ወደ ገሃነም እሳት አብረው ይገባሉ። ከየትኛው ወገን ነን?!

On May 22, Satan murdered 22 kids, today, on May 26, it massacred 26 Children of The Lord Egziabher

Satan’s month of blood sacrifice (Ramadan) has begun. Yesterday, it was Manchester and the Philippines, Today Cairo, and tomorrow all over Africa, Europe and Asia. Take note: the father of the Manchester bomber, Salman Abedi is named Ramadan Abedi.

Was Satan Jealous of President Trump that He Didn’t Come to Pegamon and Bow Down Before His Altar?

President Trump is in Europe, after visiting the seat of Satan in Saudi Barbaria, and the former President Obama is trolling Mr. Trump by traveling to Berlin and taking the idea of a shadow government to a new level. Imagine the uproar if the then President Obama was followed by ex-President Bush to meet European leaders in Europe. Of course, Mr. Obama was there at the Brandenburg Gate, near the Pergamon Museum – where ‘Satan’s Altar’ is on display – and at the very same spot where he was ‘anointed’ to become the president of the US, back in 2008.

In these days, we Christians celebrate two of the nine great feasts of the Church: yesterday, The Feast of the Ascension of our Lord God and Savior Jesus Christ, and on Sunday, The Feast of Pentecost or Parakletos.

Satan – which is always not far away from Holy People, Holy Places and Holy Days – doesn’t like that – therefore it trolls Christians wherever they go — it wants blood.

Gunmen Ramadan -a Month of Death and Terror | Gunmen Massacre Coptic Christians in Egypt, Killing at Least 26

The fate of the Coptic Christians of Egypt should serve as a warning to all those of other faiths who live alongside Muslims!!!

__

Posted in Conspiracies, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | 1 Comment »

የG20 ሉሲፈራውያን በኢትዮጵያውያን ላይ ሲዝቱና ሲያፌዙ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 24, 2016

ለእነርሱ ቴአትር እና ድራማ ነው፤ የ ‘REALITY SHOW’ ነው። አሁን የመጨረሻው ደረጃ ላይ ስለደረሱ አይደብቁልንም፡ በቀልድ፣ በፌዝና ቧልታ መልክ መልዕክቶቻቸውን ያስተላልፋሉ፤ ማዬት የሚችል ይመልከት!

/ ሚንስትር መለስ ዜናዊን ያለ ዓላማና ያለ ምክኒያት አልነበረም ከአንድ የG20G8፡ የ UN, EU ስብሰባ ወደ ሌላው እየጋበዙ ሲያሳትፏቸው የነበረው። ምንም እንኳን ጠ/ሚንስትር መለስ አንዳንድ መከሰት ያልነበረባቸውን ስህተቶች እንዲሠሩ በሉሲፈራውያኑ ቢገደዱም፡ የኢትዮጵያዊ መልካቸውንና ማንነታቸውን በመመርመር ከስህተታቸው ለመመለስ ብሎም ኢትዮጵያዊነታቸውን እንደገና ለመቀበል ሲጀምሩ ነበር በሉሲፈራውያኑ የኢትዮጵያ ጠላቶች የተገደሉት። ከስህተቱ የሚማረውን ኢትዮጵያዊ በጣም ይፈሩታልና! ነፍሳቸውን ይማርላቸው!

የእግዚአብሔር እስትንፋስ፡ የአቡነ ተክለሃይማኖት ፈጣን ሮኬት ጠላቶቻችንን ያቃጥልልን! አሜን!!

__

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | 1 Comment »

በ ቅ/ገብርኤል ስም ባካችሁ ተውን!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 29, 2014

 

ደመ-መስዋዕትን የለመዱት የሉሲፈር / ሳጥናኤል ኃይሎች ሕዝባችንን ሊያናክሱት ቀናቀና በማለት ላይ ናቸው። የእስኮትላንድን መገንጠል እንደ ትልቅ ውድቀት አድርጋ የወሰደችውና እያነሰች የመጣችው ታላቋ ብሪታኒያ‘ ‘ታዛቢበሌለበት የተጭበረበረ ሬፈረንድም ግዛቶቿን ለማስከበር በቅታለች። ዱሮም 10-ሺህ ኪሎሜትር ያህል በመጓዝ ለማይረቡት የማልቪናስ/ፎክላንድስ ደሴቶች ስትል ከአርጀንቲና ጋር ጦርነት ከፍታ የነበረችው እንግሊዝ ጎረቤቷ የሆነችውን ስኮትላንድን ትለቅቃለች ተብሎ የማይታሰብ ነበር።

ከሬፈረንደሙ በኋላ፡ እንግሊዛውያኑ ተረጋግተዋል፤ የልብልብ ብሏቸዋል፤ ግን ከዚህ ቀደም ሲከተሉት የነበረውን ድብቅና ግልጽ የትንኮላ መንገድ በአፍሪቃ፡ በተለይም በኢትዮጵያ ላይ ለመዘርጋት ሲቁነጠነጡ ይታያሉ። እነርሱ ሊያጠፉን የጥላቻ መርዛቸውን ሲረጩብን እኛ ግን ማንቸስተር!” “አርሰናል!” እያልን ተወዳዳሪ በሌለው ፍቅረባዕድ ወገናችንን እናደነዝዛለን፣ ከተሞቻችንን እናውካለን። የእግርኳስ ጠላት መሆኔ አይደለም፤ ግን የእንግሊዝ እግር ኳስ አፍቃሪም ይህን ያህል መስዋዕት ለፕሬምየር ሊግ ስለማይከፍል የኛ እንደዚህ መሆን በይበለጥ ስለሚያሳዝነኝ ነው። ጠላትህን ውደድ!” የሚለውን ምክር ያላግባብ ነው የምንጠቀመው።

7ቁጥር ባለፉት የአገራችን የታሪክ ሂደቶች ውስጥ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፤ 19671970197719871997 ብዙ ነገሮች የታዩባቸው ዓመታት ነበሩ። 2007 ዓመተምህረትስ ምን ይዞልን ይመጣ ይሆን? ይህ ዓመት ምርጫ የሚካሄድበት ዓመት ነው። ታዲያ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በእንግሊዝ ቡልዶጎችየሚመራው የሉሲፈራውያኑ ኃይል አገራችንን ከመንከስ ወደኋላ አይልም። ሰሞኑን እንደምንታዘበው ኢትዮጵያውያኑን እንዲሁም ዓለምአቀፋዊውን ማሕበረስብ ከሁኔታዎች ጋር ለማለማመድ (conditioning) ይህ ኃይል በመሞከር ላይ ነው።

ለምሳሌ፦

 • በትውልድ አገሩ ላይ ሤራ ለመጠንሰስ ሲንቀሳቀስ የነበረውና ከየመን ወደ ኢትዮጵያ የተጠረፈው ግለሰብ፡ የእንግሊዝ ዜግነትን የያዘ ነው። አሁን ይህ ግለሰብ በኢትዮጵያ ያላግባብ ታስሯልየሚል የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በመንዛት፡ እንግሊዛውያን ኢትዮጵያን በቁራኛ እንዲመለከቱ ይደረጋል። ምናልባት እራሳቸው ሆን ብለው ልከውት ይሆን? (አፄ ቴዎድሮስን እንደተተናኮሉት)እዚህ ይመልከቱ።
 • የመካከለኛውን ባሕር እያቋረጡ በጣሊያን አድርገው ወደ ፈረንሳይዋ ካሌ በመግባት፡ ወደ እንግሊዝ መጓዝ ይፈልጋሉየሚባሉትንና በብዙህ ሺህ የሚቆጠሩትን የኤርትራ/የኢትዮጵያ/ የሱዳን ዜጎችን ከረሃብ አምልጠው የመጡ ወራሪዎች ናቸውእያሉ በሕዝባቸው ዘንድ የማስፈራሪያና ጥላቻ ቅስቀሳ ያካሂዳሉ። አብዛኛው ስደተኛ ከአረብ አገር ነው የሚመጣው፡ ሰለነሱ ግን ብዙም አይተነፍሱም። የእንግሊዛዊውን አንባቢ የጥላቻ ሀተታ እናንብብ። እዚህእዚህእዚህ ይመልከቱ።
 • የኦሮሞ ብሔረሰብ በኢትዮጵያ ተበድሏልበሚል ዲያብሎሳዊ ወቀሳ የአገራችንን ሕዝብ እርስበርስ ሊያባሉት አስበዋል። ልክ በቀደም በሩዋንዳ ጀነሳይድ ተጠያቂዎቹ ቱሲዎች (ኢትዮጵያውያን ናቸው) ናቸውበማለት ሌላ እልቂት መፈለጋቸውን እንደጠቆሙት። እዚህእዚህ ይመልከቱ።
 • ኢትዮጵያ ከ30 ዓመት በፊት ከተከሰተው ረሃብ በኋላበሚል ርዕስ ደግሞ ኢትዮጵያ የሚለው ስም ሁልጊዜ ከረሃብ ጋር የተያያዘ ይሆን ዘንድ እንደገና ለማስታወስ ይቃጣሉ። አንዳንዶቻችን ይህ ጽሑፍ የአኹኒቷን ኢትዮጵያ መለወጥና መሻሻል ካለፈው ጋር እያወዳደረ የሚያቀርብ ጽሑፍ መስሎ ይነበበን ይሆናል። አንታለል! ይህ ጽሑፍ በቅድሚያ ለእንግሊዛውያኑ ነው የቀረበው፤ እንግሊዛውያኑ ደግሞ በዝርዝር የቀረበውን ጽሑፍ ሙሉ በሙሉ ለማንበብ ሰነፎች ናቸው፤ ርዕሱን ካዩት በቂያቸው ነው፤ በተለይ ኢትዮጵያ = ረሃብየሚሉት ቃላት። እዚህእዚህ ይመልከቱ።

አብዛኛው የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ቅጥፈት የተሞላበት እንደሆነ ግን እራሳቸው ይመሰክራሉ፤ እዚህ ይመልከቱ።

ያዘኑትን የምታረጋጋ፣ ጻድቃንን የምትጐበኛቸውና ደስታን የምታበሥረው ቅዱስ ገብር ኤል ሆይ ይህ የ 2007 ዓመት የሰላም፣ የፍቅርና የጤና ዓመት እንዲሆንልን የደስታውን ወይን አጠጣን

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: