Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ዘመነ ሉቃስ’

✤ ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በበጎው ዘመን | ✤ ደብረ ሳሌም ቦሌ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ቤተ ክርስቲያን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 12, 2022

😇 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ፡ የአዲስ ዘመን ምልክት

በኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን የበዓላት ቀኖና መሰረት የአዲስ ዓመት ዘመን መለወጫ በዓል የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በዓል ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ቅዱስ ዮሐንስ የአሮጌ (ብሉይ) ዘመን ማብቃት ብስራት፣ የአዲስ ዘመን መምጣት ማሳያ ሆኖ በቅዱሳት መጻሕፍት ስለሚታወቅ ነው፡፡ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ብሉይ ኪዳንና በሐዲስ ኪዳን መካከል ከነበሩት ቅዱሳን አበው አንዱ የሆነ፣ ከነቢያት እነ ነቢዩ ኢሳይያስ፣ ከመላእክት ቅዱስ ገብርኤልና ከካህናት አባቱ ዘካርያስ ትንቢት የተናገሩለት ነቢይና ሐዋርያ ነው፡፡ ገና ከሕፃንነቱ ጀምሮ ቅኑት እንደ ገበሬ፣ ጽሙድ እንደ በሬ ሆኖ እግዚአብሔርን ያገለገለ፣ በፍጹም ልቡ ዓለምን የናቀ፣ ከተድላዋና ከደስታዋም የተለየ፣ አምላክን ለማጥመቅ የታደለ ሐዋርያ፣ መምህር፣ ሰማዕት፣ ባሕታዊ፣ ነቢይ፣ ጻድቅ ነው፡፡

😇 የቅዱስ ዮሐንስ መዓርጋት

ቅዱስ ዮሐንስ በርካታ መዓርጋት አሉት፤ የተወሰኑትን ቀጥለን እንመለከታለን፤

  • መጥምቅ /መጥምቀ መለኮት/ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በማጥመቁ
  • ነቢይ ከእኔ በፊት የነበረውና ከእኔ የሚበልጠው ይመጣል ብሎ ትንቢት በመናገሩ
  • ካህን ሕዝቡን በማጥመቁ
  • ወንጌላዊ ያስተማረው ትምህርት እንደነቢያቱ ይመጣል ይወለዳል ብቻ ሳይሆን መጥቷል፣ ተወልዷል፣ እነሆ በመካከላችሁ ቆሟል የሚል ለመሆኑ፤ እንደ ነቢያቱ ለቅጣት ምርኮን፣ ለስጦታ /ደስታ/ ምድረ ከነዓንን ሳይሆን ለቅጣት የዘለዓለም ሕይወትን፤ ለስጦታ መንግሥተ ሰማያትንና ገሃነመ እሳትን ማስተማሩ፤ የሥነ ምግባር ትምህርቱም እንደ ወንጌል ትሩፋትን የሚሰብክ በመሆኑ

ርእሰ ዓውደ ዓመት ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን መሸጋገሪያ ላይ የነበረ ነቢይ በመሆኑ የዓመቱ መጀመሪያና የዘመን መለወጫ በዓል በሆነው መስከረም አንድ ቀን የእርሱ መታሰቢያ እንዲደረግበት፣ በዓሉም «ቅዱስ ዮሐንስ» ተብሎ እንዲጠራ አባቶቻችን ወስነዋል፡፡ ቅዱስ ያሬድም በድጓው «ውስተ ርእሰ ዓውደ ዓመት ተጽሕፈ ተዝካርከ፤ ባርከኒ እንሣእ በረከተከ»፤ «መታሰቢያህ በርእሰ ዓውደ ዓመት ተጻፈ፤ በረከትህን አገኝ /እውሰድ/ ዘንድ «ባርከኝ» ብሎ ምሥጋናና ጸሎት ደርሷል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ መልክአ ዮሐንስ ደግሞ «ርእሰ ዓውደ ዓመት ዮሐንስ ወላዴ መጥቅዕ ወአበቅቴ» ይለዋል /ሠላም ለሥዕርተ ርእስከ/፡፡ «የመጥቅዕ እና የአበቅቴ ወላጅ፣ አስገኚ» ማለት ነው፡፡ ይህም ስም የተሰጠው የዓመቱ ክብረ በዓላት የሚውሉባቸው ቀናትና ዕለታትን ለማስላት የሚጠቅሙት መጥቅዕ እና አበቅቴ የሚባሉት ቁጥሮች በዚሁ በመስከረም አንድ ቀን ስለሚወጡ /ስለሚስሉ/ ነው፡፡

ሰማእት /ምስክር/ስለጌታችን አምላክነትና መድኃኒትነት እንዲሁም ስለ እውነት ስለመሰከረ፤ በመጨረሻም በአላውያን ነገሠታት እጅ ስለ ተገደለ፡፡

ከእነዚህ ሁሉ ስሞች የሚበልጠው ግን መጥምቅ /መጥምቀ መለኮት/ የሚለው ነው፡፡ ምክንያቱም ቅዱስ ዮሐንስ ካደረጋቸውና ከሆናቸው ነገሮች ሁሉ የሚበልጠው አምላክን ማጥመቁ ነው፡፡ ጌታችንም ስለ እርሱ ክብር በተነገረ ጊዜ «እውነት እላችኋለሁ፤ ሴቶች ከወለዱአቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም…» በማለት ይህንን ስያሜ አጽድቆለታል፡፡

😇 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ለእኛ

ቅዱስ ዮሐንስ በዘመኑ የነበሩ ሰዎችን ገሥጾና አስተምሮ ወደ እግዚአብሔር አቅርቧቸዋል፡፡ እኛስ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች ከእርሱ ምን እንጠቀማለን? ሁለት ነገሮችን መጥቀስ ይቻላል፡፡

  • . ያስተምረናል፡፡
  • . ያማልደናል፡፡

. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ያስተምረናል

ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በቃሉ /በስብከቱ/፣ በሕይወቱ እና በአገልግሎቱ ዛሬ ድረስ ያስተምረናል፡፡

. በስብከቱ /በቃሉ/ ያስተምረናል

አንድ ሰው የድኅነትን ጸጋ /ስጦታ/ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለመቀበል ሦስት ነገሮች ያስፈልጉታል፡፡ እነዚህም እምነት፣ ምሥጢራትን መካፈል እና ምግባር ናቸው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ በእነዚህ በሦስቱም ዙሪያ ትምህርቶችን ያስተምረናል፡፡

እምነት፡ቅዱስ ዮሐንስ «አብ ወልድን ይወዳል፤ ሁሉንም ነገር፤ በእጁ ሰጥቶታል፡፡ በወልድ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ በወልድ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቁጣ በእርሱ ላይ ይሆናል እንጂ ሕይወትን አያይም» እያለ ምሥጢረ ን ምሥጢረ ሥጋዌን ያስተምረናል፤ ካላመንም የዘለዓለም ሕይወት እንደሌለን ይነግረናል፡፡

ምስጢራትን መካፈል፡ቅዱስ ዮሐንስ «መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ፡፡»«ከእኔ በኋላ የሚመጣው በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ያጠምቃችኋል»«የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ» እያለ ምሥጢራትን /ምስጢረ ጥምቀት፣ ምስጢረ ንስሐን እና ምስጢረ ቁርባንን/ እንድንካፈል ያስተምረናል፡፡

ምግባር፡– «እናንት የእፉኝት ልጆች ለመሆኑ ከሚመጣው ቁጣ እንድታመልጡ ማን መከራችሁ፤ ለንስሐ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ … እነሆ ምሳር የዛፎችን ሥር ሊቆርጥ ተዘጋጅቷል፤ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፤ ወደ እሳትም ይጣላል፡፡» እያለ ምግባር እንድንሠራ ያስተምረናል፤ ያስጠነቅቀናል።

. በሕይወቱ ያስተምረናል

ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ በሕይወቱ እግዚአብሔርን ያስደሰተ፤ «ከሴቶች ከተወለዱ የሚያህለው የለም» የተባለለት ስለሆነ አርአያ ልናደርገው፤ ለዚህ ክብር ያበቃውን ነገር ልንመረምርና በመንገዱ ልንከተለው ይገባናል፡፡ ከሕይወቱ ብዙ ልንማራቸው የሚገቡ ነገሮች ቢኖሩም ጥቂቶቹን ለጊዜው እንመልከት፡

ትሁት ነው፡ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ጌታ «ከሴቶች ከተወለዱት ወገን የሚያህለው የለም» እያለ ቢያመሰግነውም እርሱ ግን ያሉትን መልካምና ታላላቅ ነገሮች በሙሉ ችላ ብሎ «እኔ የጫማውን ማሰሪያ ልፈታ የማይገባኝ ነኝ» ይል ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ቅዱስ ያሬድ «ዘወጠነዝ ትርሢተ ክብር ትሕትና ወፍቅር ትሕትና ወፍቅር ርእዮ እበዩ ለዮሐንስ…» እያለ የቅዱስ ዮሐንስ የክብሩ ጌጥ፣ የታላቅነቱ ምንጭ ትሕትናው እና እግዚአብሔርን ማክበሩ መሆኑን ይገልጻል፡፡ እመቤታችን በጸሎቷ «ትሁታንን ግን ከፍ ከፍ አደረጋቸው» [ሉቃ.፩፥፶፪] እንዳለችው እርሱ ትሁት ሲሆን እግዚአብሔር ከሁሉ በላይ አከበረው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ትሕትና ግን ምንጩ ምንድን ነው?

ትሕትና ማለት ምንም ነገር የሌለው መሆን ማለት አይደለም፡፡ እግዚአብሔር በባሕርይው ትሁት ነው፡፡ ጌታ «ከእኔ ተማሩ፣ እኔ ትሁት ነኝ» ይላል፡፡ የእግዚአብሔር ትሕትና ምንጩ ክቡር፣ ባዕለ ጸጋ መሆኑ ነው፡፡ የቅዱስ ዮሐንስ ትሕትና ምንጭም ይኸው ነው፤ በእምነትና በምግባር ያጌጠ ባለ ብዙ ፍሬ ባለ ጸጋ መሆኑ ማንም ትሕትናን የሚፈልጋት ቢኖርም ማድረግ ያለበት ይህንኑ ነው፤ ባለብዙ ምግባር፤ ባለ ትልቅ እምነት መሆኑ፤ ያን ጊዜ ትሕትናው አብሮ ይመጣል፡፡

ሁለተኛው የቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ትሕትና ምንጭ የእግዚአብሔርን ማንነትና ባሕርይ በሚገባ ማወቁ፤ የራሱን ማንነቱንና አቅሙንም መረዳቱ ነው፡፡ እኛም ትሕትናን ገንዘብ ልናደርግ ብንወድ የእግዚአብሔርን ማንነት፣ ባሕርይ፣ እና ክብር የተቻለንን ያህል ለማወቅ መጣር፤ ራሳችንንም ዘወትር መመርመር፣ ድካማችንን መረዳትና ይህንንም ደግመን ደጋግመን ለራሳችን መንገር አለብን፡፡

ጸጋውን ተጠቅሞ ፍሬ አፍርቷል፡ – ቅዱስ ዮሐንስ በእናቱ ማኅፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ መልቶበት ነበር፡፡ እርሱም ይህንን ጸጋውን አትርፎበታል፤ሕዝቡም ካህናቱም አመጸኞች በነበሩበት በዚያ አስከፊ ዘመን [ሐዋ.÷፴፡፴፱] ጻድቅ ሆኖ ተገኝቷል፤ ለራሱ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም በረከት ሆኖ ነበር፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዳሉት ለዚህ የበቃው «የበረሃ እና የተራሮች ልጅ» በመሆኑና በብህትውና /በብቸኝነትና/ እና በትህርምት በመኖሩ ነው፡፡

እያንዳንዳችን ከጥምቀታችን ቀጥሎ በሚፈጸምልን ምሥጢረ ሜሮን አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ያድርብናል፡፡ ይህንን ተጠቅመን ሥራ ለመሥራት እኛም እንደ መጥምቁ የራሳችን በረሃ ያስፈልገናል፤ በትህርምትና ራስን በመግዛት መኖር አለብን፡፡

ይህንን ማድረግ የሚገባቸውና የሚችሉት በገዳም ያሉ ሰዎች ብቻ አይደሉም፡፡ በዓለም የምንኖር ሰዎችም ብቻችንን የምንሆንበትና በጸሎት፣ በተመስጦ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ፣ ራሳችንን በመመርመር የምናሳልፈው ጊዜ በመመደብ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ በወጣትነት ዘመኑ እንዳደረገው መኖሪያ ቤቶቻችንን ገዳማት ማድረግ እንችላለን፡፡ ሁኔታዎችን እያመቻቸን ወደተለያዩ ገዳማት እየሄድን ጊዜ ማሳለፍም ጠቃሚ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ምግባችንን፣ መጠጣችንን እና ልብሳችንን በልክ እያደረግን መጥምቁን ባለ ብዙ ፍሬ በሆነበት ጎዳናው ልንከተለው ያገባናል፡፡

በአግልግሎቱ ያስተምረናል፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ከቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ አገልግሎት ልንማራቸው የሚገቡ በርካታ ቁም ነገሮች አሉ በማለት የሚከተሉትን ይዘረዝራሉ፡፡

ቅድስ ዮሐንስ ያገለገለው ለአጭር /ከስድስት ወራት ብዙ ላልበለጠ/ ጊዜ ብቻ ቢሆንም በርካታ ሥራዎችን ሠርቶ አልፏል፡፡ እኛም አገልግሎታችንን ልንመዝነው የሚገባን በርዝመቱ ሳይሆን በጥልቀቱ፣ በውጤታማነቱ፣ በሚያፈራው ፍሬ እና በሚያመጣው ለውጥ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል ዓላማው ሰዎችን ከእግዚአብሔር ጋር ማገናኘት እንጂ ሰዎችን በእርሱ ዙሪያ መሰብሰብና መክበር አልነበረም፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ እንደሚነግረን «ከኢየሩሳሌም፣ ከመላው ይሁዳ፣ በዮርዳኖስ ዙሪያ ባለው ነገር ሁሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይጎርፉ ነበር፡፡» [ማቴ.፫፥፭፡፮] እርሱ ግን «እኔ በውኃ ለንስሐ አጠምቃችኋለሁ፤ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፡፡» እያለ ሰዎቹ እርሱን እንዲከተሉ ሳይሆን የጌታችንን መምጣት ተስፋ እንዲያደርጉ የሚያደርግ ትምህርት ያስተምራቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዛሙርት በኋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብተዋል፡፡

የመጀመሪያዎቹ ጌታችንን የተከተሉት ደቀመዛሙርት የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ነበሩ፡፡ ስለዚህ በዚህ ዘመን መታጀብ /በሕዝብ መከበብ/ ለሚያስደስተን የእግዚአብሔርን ሳይሆን የእኛን ተከታዮች እንደ ፈሪሳውያን ለምንፈልግ አገልጋዮች ትልቅ ተግሳጽ ነው፡፡

«በማግስቱ ዮሐንስ ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር እንደገና በእዚያው ቦታ /ጌታችን በተጠመቀበት/ ቦታ ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በዚያ ሲያልፍ አይቶ «እነሆ የእግዚአብሔር በግ» አለ ሁለቱ ደቀመዛሙርትም ይህን ሲናገር ሰምተው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ተከተሉት» [ዮሐ.፩፥፴፭፡፴፯]

የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍም በርካታ የዮሐንስ ደቀመዛሙርት የነበሩና የእርሱን ጥምቀት የተጠመቁ ሰዎች በቀላሉ ወደ ክርስቲያኖች ማኅበር እንደተቀላቀሉ ይነግረናል፡፡ [ሐዋ.፲፰፥፳፬+ ፲፱፣ ፮፥፲፫፡፳፬]

ራሱም ይህንን አቋሙን እንዲህ በማለት ልብ በሚነኩ ቃላት እንዳጋለጠው ወንጌላዊው ዮሐንስ በወንጌሉ መዝግቦታል፡፡

ሰዎች ወደ ቅዱስ ዮሐንስ መጥተው «መምህር፣ በዮርዳኖስ ከአንተ ጋር የነበረው፣ ስለ እርሱም የመሰከርክለት … ሰው ሁሉ ወደ እርሱ እየሄዳ ነው» ባሉት ጊዜ እንዲህ ሲል መለሰ «ከላይ ካልተሰጠው በቀር ማንም አንዳች ሊቀበል አይችልም፡፡ «እኔ ክርስቶስ አይደለሁም፤ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ተልኬአለሁ» እንዳልሁ እናንተ ራሳችሁ ትመሰክራላችሁ፡፡ ሙሽራይቱ የሙሽራው ነች፡፡ ድምፁን ለመስማት በአጠገቡ የሚቆመው ሚዜ ግን የሙሽራውን ድምፅ ሲሰማ እጅግ ደስ ይለዋል፤ ያ ደስታ የእኔ ነው፤ እርሱም አሁን ተፈጽሟል፡፡ እርሱ ሊልቅ፤ እኔ ግን ላንስ ይገባል፡፡»

እውነት ነው፡፡ ሙሽራይቱ ቤተ ክርስቲያን የሙሽራው የክርስቶስ ነች፡፡ አገልጋዮች ሚዜ ናቸው፡፡ ሥራቸውም ሙሸራይቱን ወደ ሚዜው ማቅረብ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ሲያገለግል በድፍረት ነው፡፡ እርሱ በነበረበት ወቅት ሔሮድስ አንቲጳስ የወንድሙን ሚስት አግብቶ የሚገሥጸው ጠፍቶ ነበር፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ ግን በበረሃው ሳለ ደፋር፣ ለሰው ፊት የማያደላ፣ መሆንን ተምሮ ነበርና ገብቶ ገሠፀው፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዲህ ይላሉ «ከአገልግሎቱ ሊያዘገየው ወይም ሊያስተጓጉለው የሚችል ቢሆንም እንኳን ተገቢውን ነገር ከማድረግ ወደ ኋላ አላለም፡፡ አስተሳሰቡም እንዲህ ነው «እግዚአብሔር እንዳገለግል ፈቃድ ከሆነ አገለግላለሁ፤ ካልሆነም የእርሱ ፈቃዱ ይሁን፡፡ ዋናው ነገር እውነትን መመስከር ነው» ቅዱስ ዮሐንስ ስለእውነት ራሱን አሳልፎ ቢሰጥም ከሞተ በኋላም ቢሆን የትምህርቱ ድምፅ ሄሮድስን ሲወቅሰው ኑሯል፡፡»

እውነት ነው፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ከሞተ በኋላም ቢሆን ራሱ አስራ አምስት ዓመት ዙራ አስተምራለች፡፡ ሔሮድስም ከሞት ተነሥቶ የሚመጣ እስኪመስለው ድረስ ይፈራው እንደበር ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ ጽፏል «በዚያን ጊዜ የአራተኛው ክፍል ገዢ የነበረው ሄሮድስ /አንቲጳስ/ ስለ ኢየሱስ ዝና ሰማ፤ ባለሟሎቹንም እንዲህ ከሆነ መጥምቁ ዮሐንስ ከሞት ተነሥቶ መጥቶአል ማለት ነው፤ ይህ ሁሉ ድንቅ ተዓምራት በእርሱ የሚደረገውም ለዚህ ነው» አላቸው፡፡ [ማቴ.፲፬፥፩፡፪]፡፡

😇 ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ያማልደናል

ቅዱስ ዮሐንስ ዛሬ እኛን እግዚአብሔር ለወዳጆቹ በሰጠው ቃል ኪዳን መሠረት በጸሎቱ ከእግዚአብሔር ያማልደናል፡፡

ቤተ ክርስቲያንም ዘወትር «ሰአል ለነ ዮሐንስ» «ዮሐንስ ሆይ ለምንልን»፤ ትለዋለች፤ «በአንተ ዮሐንስ መጥምቅ መሐረነ» «ስለ ዮሐንስ ስትል ማረን» እያለችም ትጸልያለች፡፡ እኛም ገድሉንና፣ መልኩን በመጸለይ፣ መታሰቢያው በሚደረግበት ጊዜም በስሙ ዝክር በመዘከር፣ ቸርነት በማድረግ በረከትን ለማግኘት ልንተጋ ይገባናል፡፡

«ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀመዛሙርቶቼ ስም ቢያጠጣ፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋው አይጠፋበትም» [ማቴ.÷፵፪]

«የቅዱስ ዮሐንስ ጸሎቱና በረከቱ ይደርብን! አማላጅነቱ ይደረግልን»

ወስብሐት ለእግዚአብሔር

______________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መጥምቁ ዮሐንስን የምናከብረው ከስጋና ከደም ጋር ስለተጋደለ አይደለም

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 12, 2022

😇 የቅዱስ ዮሐንስ ክብር እና መዓርጋት

ቅዱስ ዮሐንስ ክብሩ በጣም ከፍ ያለ ነው፡፡ የክብሩ ምስክሮችም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እና መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ናቸው፡፡

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ሲል የመጥምቁን ክብር ተናግሯል፡፡

«ምን ልታዩ ወደ ምድረ በዳ ወጥታችኋል? ከነፋስ የተነሣ የሚወዛወዛውን ሸንበቆ ነው? ወይስ ምን ልታዩ መጥታችኋል ቀጭን ልብስ የለበሰ ሰውን ነውን? እነሆ ቀጭን ልብስ የሚለብሱማ በነገሥታት ቤት አሉ? ምን ልታዩ መጥታችኋል ነቢይ ነውን? አዎን እርሱ ከነቢያት እጅግ ይበልጣል፤ እነሆ በፊትህ መንገድህን የሚጠርግ መልእክተኛዬን እልካለሁ ተብሎ ስለ እርሱ የተጻፈለት ይህ ነውና፡፡ እውነት እውነት እላችኋለሁ ሴቶች ከወለዷቸው ወገን ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም» [ማቴ.፲፩÷፯፡፲፩]

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም እንዲህ ሲል ክብሩን ተናግሮለታል፡– «እርሱ በእግዚአብሔር ፊት ታላቅ ይሆናል» [ሉቃ.÷፲፭]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ «የቅዱስ ዮሐንስ ክብር እና ከፍ ከፍ ማለት ምንጮች ሁለት ናቸው፡፡» ይላሉ፡፡

. በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ስለሆነ

ከመጥምቁ ዮሐንስ በፊት የእግዚአብሔር መንፈስ ወደ ብዙ ሰዎች መምጣቱ ተጽፏል፡፡ ለምሳሌ ያህልም

ሳሙኤል ሳኦልን ቀብቶ ባነገሠው ጊዜ «የእግዚአብሔር መንፈስ በእርሱ ላይ ወረደ» ተብሏል [፩ኛሳሙ. ፲፥፲]፡፡

ሳሙኤል ዳዊትን በንግሥና በቀባው ጊዜ «የእግዚአብሔር መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ መጣ» ተብሏል፡፡ [፩ኛ ሳሙ. ፲፮÷፲፫]

❖ “የእግዚአብሔር መንፈስ ከሶምሶን ጋር ይሄድ ነበር» ተብሎም ተጽፏል፡፡[መሳ.፲፫÷፳፬]

ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ «ሞልቶታል» የተባለ ግን ማንም አልነበረም፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ግን በመንፈስ ቅዱስ የተሞላ ነበር፡፡ የከበረ እና ታላቅ በመሆኑ አንዱ ምክንያት ይህ ነው፡፡

በመንፈስ ቅዱስ የተሞላው ግን መቼ ነበር? በመንፈስ ቅዱስ የተሞላው ገና በማኅፀን ሳለ እናቱ ኤልሳቤጥ የእመቤታችንን የሰላምታ ድምፅ በሰማችበት ቅፅበት ነው፡፡

«ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፤ ፅንሱ በማኅፀኗ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ መላባት» [ሉቃ.÷፲፬]

መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል «ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ መንፈስ ቅዱስ ይመላበታል» ብሎ የተናገረው በዚህን ጊዜ ተፈጽሟል፡፡

. ተጋድሎው

የመንፈስ ቅዱስ ስጦታ በእኛ ሕይወት ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው እኛ በድርጊታችንና በተጋድሎአችን ስንጠብቀው፣ ስንንከባከበውና ስንሠራበት ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ይህንን በሚገባ አድርጓል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ ያደገው በበረሃ ውስጥ፣ በብሕትውና /በብቸኝነት/፣ የግመል ጠጉር እየለበሰ፣ አንበጣ እና የበረሃ ማር ብቻ እየተመገበ ነው፡፡ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ እንዲህ ብለዋል «እርሱ በበረሃው ውስጥ ጸሎትና ተመስጦን፣ ድፍረትን እና ፍርሃት አልባነትን፣ ጥንካሬን እና እምነትን ተምሯል፡፡ እግዚአብሔር እመቤታችንን አምላክን ፀንሣ ለመውለድ በቤተ መቅደስ እንዳዘጋጃት እርሱን ደግሞ ለመንገድ ጠራጊነት ተልእኮው በበረሃ አዘጋጅቶታል፤ እኛም የእነዚህ ነገሮች ባለቤት ለመሆን የብቸኝነትና የትህርምት ጊዜ የምናሳለፍበት የየራሳችን በረሃ ያስፈልገናል፡፡»

😇 መጥምቁ ዮሐንስን የምናከብረው ከስጋና ከደም ጋር ስለተጋደለ አይደለም

❖❖❖[ወደ ኤፌሶን ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፲፪]❖❖❖

መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።”

እያንዳንዳችን ከጥምቀታችን ቀጥሎ በሚፈጸምልን ምሥጢረ ሜሮን አማካኝነት መንፈስ ቅዱስ ያድርብናል፡፡ ይህንን ተጠቅመን ሥራ ለመሥራት እኛም እንደ መጥምቁ የራሳችን በረሃ ያስፈልገናል፤ በትህርምትና ራስን በመግዛት መኖር አለብን፡፡

ይህንን ማድረግ የሚገባቸውና የሚችሉት በገዳም ያሉ ሰዎች ብቻ አይደሉም፡፡ በዓለም የምንኖር ሰዎችም ብቻችንን የምንሆንበትና በጸሎት፣ በተመስጦ፣ ቅዱሳት መጻሕፍትን በማንበብ፣ ራሳችንን በመመርመር የምናሳልፈው ጊዜ በመመደብ መኖሪያ ቤቶቻችንን ገዳማት ማድረግ እንችላለን፡፡ ሁኔታዎችን እያመቻቸን ወደተለያዩ ገዳማት እየሄድን ጊዜ ማሳለፍም ጠቃሚ ነው፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ምግባችንን፣ መጠጣችንን እና ልብሳችንን በልክ እያደረግን መጥምቁን ባለ ብዙ ፍሬ በሆነበት ጎዳናው ልንከተለው ያገባናል፡፡

ሲሰርቁ፣ ሲያመነዝሩ፣ በዝሙት ሲወድቁ፣ ሲሰክሩ፣ ሲዘሉ፣ ሲያብዱና ሲያጨበጭቡ ከመሞት እግዚአብሔር ሁላችንንም ይጠብቀን!

😇 የቅዱስ ዮሐንስ ጸሎቱና በረከቱ ይደርብን! አማላጅነቱ ይደረግልን

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

እንቁጣጣሽ | ፳፻፲፭ የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር አረም የሚነቀልበት፣ ሕዝባችን የሚነሳበትና የጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ ጠላቶች የሚጠረጉበት ዓመት ይሆናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 10, 2022

❖❖❖ሕዝባችንን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም፣ በጤና እና በድል ያሻግርልን❖❖❖

በዚህ የአዲሱ ዓመት ዋዜማ እንዲህ ያለ ርዕስ ይዘን ለመምጣት መገዳደችን ያሳዝናል። ነገር ግን ጠላቶቻችን የቁስልና ሕመሙን ዘመን አራዝመውብናልን ዛሬ ከመቼውም በላይ ባገኘነው መንገድ ሁሉ፣ እግዚአብሔር በሰጠን ስጦታ፣ ኃይልና አቅም ልንዋጋቸው ግድ ይለናል።

የፊንላንዱን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር የፔካ ሃቪስቶን እና የአሜሪካዊውን የምክር ቤት አባል ብራድ ሼርማንን ምስክርነት ደጋግመን ሰምተናል። አውሮፓውያን፣ አሜሪካውያንን፣ አረቦችን፣ ቱርኮችን፣ ኢራናውያንን ብሎም አፍሪቃውያንን ጋብዞ፤ “ሰሜኑ ኢትዮጵያውያን በተለይ በትግራይ ያሉት ጽዮናውያን የእናንተም የእኛም ጠላቶች ናቸውና ተባበረን ከምድረ ገጽ እንድናጠፋቸው ከጎናችን ሁኑ!” ብሎ በግልጽ እየተናገረ ከባድ የዘር ማጥፋት ወንጀል በመፈጸም ላይ ያለ ብቸኛው የዓለማችን አገዛዝ በአረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ የሚመራው የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ነው። ስለዚህ ለሕዝባችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለልጆቻችን፣ ለሃገራችን፣ ለሃይማኖታችን፣ ለግዕዝ ቋንቋችንና ባጠቃላይም ለመንፈሳዊው ማንነታችንና ምንነታችን ስንል በመጪው ዓመት ግራኝን እና የሚከተሉትን ጭፍሮቹን ፤ ከፊሎቻችን በአባቶቻችን ጸሎትና ድግምት ከፊሎቻችን ደግሞ እያሳደድን በቆራጥነት በእሳት የምንጠርግባቸውን ቀናት ማመቻቸት ይኖርብናል። ይህ የእያንዳንዱ ጽዮናዊ ግዴታ ነው፤ በእነ ደብረ ጽዮን ተስፋ አታድርጉ፤ ከፈለጉ ለእነርሱ ቀላል ነበር፤ እነ ግራኝን መጥረግ ይችሉ ነበር፤ ግን ለሕዝብ የቆሙ ስላልሆኑና አውሬውንም እንዳይነካባቸው ስለሚፈልጉ/ እንዳይነኩት ስለታዘዙ በጭራሽ እንደማይጠርጉት ከበቂ ጊዜ በላይ አይተናል።

👉 በሚቀጥሉት ቀናት፣ ሳምንታትና ወራት በእሳት መጠረግ ያለባቸው የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ቁንጮዎችና አጋሮቻቸው በጥቂቱ፦

  • አብዮት አህመድ አሊ(ሙስሊም መናፍቅ)
  • ኢሳያስ አፈወርቂ (አማኒ)
  • ☆ ዝናሽ አቴቴ አህመድ አሊ (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ ሳህለ ወርቅ ዘውዴ (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ ደመቀ መኮንን ሀሰን(ሙስሊም)
  • ☆ ሳሞራ አሞራ ዩኑስ (ሙስሊም)
  • ☆ ሙስጠፌ መሀመድ ዑመር (ሙስሊም)
  • ☆ ብርሃኑ ጂኒ ጁላ(ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ዲና ሙፍቲ (ሙስሊም)
  • ☆ መሀመድ ተሰማ (ሙስሊም)
  • ☆ ሀሰን ኢብራሂም(ሙስሊም)
  • ☆ ሬድዋን ሁሴን (ሙሊም)
  • ☆ ሞፈርያት ካሚል (ሙስሊም)
  • ☆ ኬሪያ ኢብራሂም (ሙስሊም ፥ ለስለላ ነበር ወደ መቀሌ ተልካ የነበረችው)
  • ☆ አህመድ ሺዴ (ሙስሊም)
  • ☆ ጃዋር መሀመድ(ሙስሊም)(“የታሰረው” ለስልት እንደነበር አየን፤ አይደል?!)
  • ☆ ፊልሳን አብዱላሂ (ሙስሊም)
  • ☆ ለማ መገርሳ (ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ታከለ ኡማ (ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ሽመልስ አብዲሳ (ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ በቀለ ገርባ(ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ህዝቄል ገቢሳ(ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ዳውድ ኢብሳ(ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ አምቦ አርጌ (ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ፀጋዬ አራርሳ(ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ አደነች አቤቤ(ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ መአዛ አሸናፊ (ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ሳህለወርቅ ዘውዴ (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ ብርቱካን ሚደቅሳ (ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ታዬ ደንደአ(ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ ሌንጮ ባቲ (ዋቀፌታ-መናፍቅ)
  • ☆ አገኘው ተሻገር (ኦሮማራ -መናፍቅ)
  • ☆ ዳንኤል ክብረት (ኦሮማራ-አርዮስ)
  • ☆ ዘመድኩን በቀለ (ኦሮማራ-አርዮስ)
  • ☆ ኢሬቻ ጂኒ በላይ (ዋቀፌታ-አርዮስ)
  • ☆ አለማየሁ ገብረ ማርያም (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ ብርሀኑ ነጋ (ኦሮጉራጌ-መናፍቅ)
  • ☆ ገዱ አንዳርጋቸው (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ አንዳርጋቸው ፅጌ (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ አንዱዓለም አንዳርጌ (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ ታማኝ በየነ (ኦሮማራ-መናፍቅ)
  • ☆ አበበ ገላው (ኦሮማራ-መናፍቅ)

ወዘተ.

በተረፈ ለሌሎቻችን፤ መጭው የ ፳፻፲፭ አመት፡ የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የደስታ ዘመን ይሁንልን !!!

ጽዮናዊው ሕዝባችን ከአፈኑት፣ ካገቱት፣ ከሚያስርቡትና ከሚጨፈጭፉት አረመኔጠላቶቹ የሚድንበት፤ በሕዝባችን ላይ መከራና ግፍ ያመጡት የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር ጭፍሮች ተጠራርገው የሚወገዱበት ዓመት ይሁንልን። አሜን!

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ

ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሲፈካ

ዝናም በሙቀት ሊተካ

ብርሃን ጨለማን ሲተካ

እንቁጣጣሽ፡ እንቁጣጣሽ!!

ደህና ጊዜን ይዘሽ ደግሞ ደግሞ ያምጣሽ።

እርቅ ነው ፍቅር ነው ለኛ አዲስ ዘመን፡

የሚታረቀውን እናቀናለን፡ አረሙን እንነቅላለን።

፳፻፲፭ የጽዮናዊቷ ኢትዮጵያ ጠላቶች የሚያፍሩበት፡

ልዩ ዘመን ሕዝባችን ነቅቶ የሚታገልበት።

እንቁጣጣሽ በያመቱ ያምጣሽ!

መልካም አዲስ አመት!

🌱 መልካም አዲስ ፳፻፲፭ አመት – Happy Ethiopian New 2015 Year! 🌱

❖❖❖ ENKUTATASH ❖❖❖

Enkutatash in Ethiopia, a part of the American roster of holidays, in a way that is very similar to St. Patrick’s Day or Cinco de Mayo. Columbus Day, for example, was popularized out of Denver, CO back in the mid 19th century as a way of promoting Italian culture.

Enkutatash is the name for the Ethiopian New Year, and means “gift of jewels” in the Amharic language. The story goes back almost 3,000 years to the Queen of Sheba of ancient Ethiopia and Yemen who was returning from a trip to visit King Solomon of Israel in Jerusalem, as mentioned in the Bible in I Kings 10 and II Chronicles 9. She had gifted Solomon with 120 talents of gold (4.5 tons) as well as a large amount of unique spices and jewels. When the Queen returned to Ethiopia her chiefs welcomed her with enku or jewels to replenish her treasury.

Six events are observed every Ethiopian New Year, seven in each hundred year and eight in each thousand year. The Ethiopian calendar celebrates New Year on Meskerem first to commemorate the receding of the great storm during the time of Noah and beheading of Kidus Yohannes, (St. John the Baptist). Hence, the Ethiopian New Year is also known as Kidus Yohannes in memory of the saint and his sacrifice.

Kontakion of St. John the Baptist, Tone 5

The beheading of the glorious Forerunner was a divine dispensation that the coming of the Savior might be preached to those in hell. Lament then, Herodias, that thou didst demand a murder despising the law of God and eternal life.

Today is a little Great Friday, a second Great Friday. For today the greatest man among those born of women, John, the Holy Forerunner and Baptiser of the Lord, is murdered. On Great Friday, people murdered God, crucified God. On today’s holy great feast, people murdered the greatest of all men. It is not I who chose to use the expression “the greatest.” What are my praises of the great and glorious Forerunner of the Lord, whom the Lord praised more than anyone among men, more than any of the apostles, the Angels, the Prophets, the Righteous Ones, the Sages? For the Lord declared of him:

Among them that are born of women there hath not risen a greater than John the Baptist… (Matthew 11: 11).

Our battle is not against flesh and blood, but against principalities, against powers, against the rulers of the darkness of this world, against spiritual wickedness in the heavenly places” (Ephesians 6:12).

______________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: