Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ዓምባ’

ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው ፥ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 20, 2022

💭 በኤዶማውያኑ ምዕራባውያንና በእስማኤላውያኑ ምስራቃውያን ፍላጎትና ትዕዛዝ በኦሮማራ ቃኤላውያን ክሃዲዎች አማካኝነት ከዋልድባ ገዳም የተባረሩትን ፩ ሺህ አባቶቻችንን የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያጽናናቸው የእግዚአብሔር መላእክት ይጠብቋቸው፤ ይንከባከቧቸው!

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፯፥፭፡፮]✞✞✞

“እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው። እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፤ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።”

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፯፥፴፡፴፩]✞✞✞

“በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፤ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው። መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው። እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፤ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።”

✞✞✞ጻድቁ አባታችን አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ✞✞✞

✞✞✞በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!✞✞✞

አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፤ አባታችን ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በረከታችውና ረድኤታቸው ይደርብንና በሰሜኑ የሀገራችን የኢትዮጵያ ክፍል በ ፬ /4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ እንደ ተመሰረተ በሚነገርለት በደብረ ዋሊ ወይም ዋልድባ ገዳም የተነሱ ስመጥር መነኩሴ መናኝና የጽድቅ መምህር ናቸው።

የገዳማዊ ሕይወት እጅግ ተስፋፍቶ በነበረበት በ፲፫/13ኛው እና በ፲፬/14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩት ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እነ አባ ኢየሱስ ሞዓ፣ ብፁዕ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ የእነዚህም የቆብ ልጅ በሆኑት በገዳመ በንኮል በአባ መድኃኒነ እግዚእ እጅ ምንኩስናን ተቀብለው ቤተ ክርስቲያንን በተሰጣቸው መንፈሳዊ ጸጋ አገልግለዋል።

ትውልዳቸውና ቤተሰቦቻቸው፤ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የተወለዱት በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ አክሱም በ፲፪፻፺፭/1295 ሲሆን አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባሉ። እነርሱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ የተመሰገኑ ክርስቲያኖች እንደነበሩና በኋላም በምንኩስና ህይወት እንዳለፉ በአባታችን የገድል መጽሐፍና በስንክሳር ላይ በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል።

መንፈሳዊ ትምህርታቸውና ገዳማዊ ህይወታቸው እንዲሁም የተማሩበት ቦታ፤ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ አባታቸው ለአክሱም ቄሰ ገበዝ እንደሰጧቸውና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከፊደል ጀምረው የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አጠናቀው ለአገልግሎትም ዲቁናን ተቀብለው በንቃትና በልባምነትም ቤተ ክርስቲያንን ለሰባት ዓመት ካገለገሉ በኋላ ጌታችን በወንጌል “ፍጹም ልትሆን ብትወድ…”ማቴ.፲፱፣፳፩፡፳፪ ያለዉን ለመተግበር ለአክሱም ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ወደ ሚገኘው ደብረ በንኮል ገዳም ገብተው ከገዳሙ ሊቃዉንት የብሉያትንና የሐዲሳትን ትርጓሜ እንዲሁም ስርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል። ከዚያም ብፁዕነታቸው አባ ሳሙእል ዘዋልድባ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ቅዱስ ሄኖክ የመረጠውን ምናኔ፤ አባ እንጦንስና መቃርስ የተከተሉትን የምንኩስና ሕይወት በሰፊው ተጓዘበት።

ነፍሱን ነፍሴ ሆይ እነሆ ለክርስቶስ ታጨሽ የቅዱሳንን ቀንበር እነሆ ተሸከምሽ የመላእክትን ንጽህና ትጠብቂ ዘንድ ዛሬ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ፊት ቃል ኪዳን ገባሽ ቃልኪዳንሽን ብትጥብቂ እግዚአብሔር ይደሰትብሻል ባትጠብቂ ግን አጋንንት ይዘብቱብሻል በማለት መከራን በራሱ ላይ ያበዛ ነበር የጣመ የላመም አይመገብም ነበር ይልቁንም ከገዳሙ የሚሰጠዉን መቁኑን ተቀብሎ ለሌሎች

ሰጥቶ የዱር ቅጠል ይመገብ ነበር። ትጋቱንና የምናኔ ሕይወቱን ያዩ መናንያን አበው መነኮሳት የእነሱን የምንኩስና አክሊል እንዲቀበል ፈልገው የገዳሙን አበ ምኔት /ኃላፊ/ አባ መድኃኒነ እግዚእን ይመክሩና ይለምኑ ነበር አባ መድኃኒነ እግዚእም የሚያየዉንና ከመነኮሳቱም የሰማዉን ተቀብሎ በጊዜው ለምንኩስና ከተዘጋጁት አስራ ሁለት ከዋክብት ደቀ መዛሙርት ዉስጥ አንደኛው እንዲሆን ወስኗል።

ከምንኩስና ሥርዓቱም በኋላ እነዚህ አስራ ሁለት ከዋክብት ለሁለት ተከፍለው አምስቱን ከዋክብት በወሎ፣ ትግራይ እና ኤርትራ ሲመድቧቸው ሰባቱን ከዋክብት ደግሞ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በበዛዉም በጎጃም በጎንደር እንዲሁም በጣና አካባቢ እንዲያገለግሉ እንዲያስተምሩ አሰማርተዋል። አባታችን አባ ሳሙኤል በገድላቸው እንደምንመለከተው “ፀሐይ ሳሙኤል ዘዋሊ” ይላል ‘ዋሊ’ የዋልድባ ገዳም የቀድሞ መጠሪያ ስሙ ነው ዋልድባ ገዳም በጣም ተዳክሞ በነበረበት ዘመን ተነስተው ዋልድባን ከጥፋት የታደጉ መናንያንን በማሰባሰብ እንደገና ያስፋፉ በመሆናቸው ዘዋሊ ይሏቸዋል፤ ሳሙኤል ዘደብረ ዓባይም ይሏቸዋል የደብረ ዓባይን ገዳም የመሰረቱት እሳቸው ስለሆኑ።

አባታችን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ከዚህ ዓለም በምናኔ ተለይተው ግርማ ሌሊቱን ድምፀ አራዊቱን ፀብዓ አጋንትን የሌሊት ቁር የቀን ሐሩርን ታግሰው የጽድቅን ጎዳና ተከትለው ብዙ የብዙ ብዙ ገድል በመሥራት ልዩ ልዩ ተአምራትን አድርገዋል ይህም በገድልና በተአምራት መጽሐፋቸው በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል። ከነዚሁም ጥቂቶቹን ብንጠቅስ አባታችን አቡነ ሳሙኤል፤ ባሕርን የከፈለበት ጊዜ አለ፣በጌታ መንበር ፊት እየቀረበ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋርም የሚያጥንበት ጊዜ አለ፣

በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ሆኖ ከእነ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ከሁሉ ቅዱሳን ጋር አንድ ላይ ማዕድ የሚቀርብበት ጊዜ አለ፣ በእጆቹ የያዛቸው መጻሕፍትም ሳይርሱ ወንዝ የሚሻገርበት ጊዜ አለ፣ በተለይ በጸሎቱ ሰዓት የእምቤታችንን ምስጋና ሲጀምር ከምድር አንድ ክንድ ከፍ የሚልበት ጊዜ አለ፣ በቤትም ሆኖ ምስጋናዋን ሲጀምር የቤቱ መሰረት እየተናወጠ ዝናብ እንደያዘ ደመና፤ ቤቱ ከምድር ከፍ ብሎ የሚቆምበት ጊዜ አለ፣ መንፈስ ቅዱስም በብርሃን ሰረገላ እየወሰደው ወደ ተለያዩ ገዳማት ያደርሰዉና የጌታን ሥጋ እና ደም እንዲቀበልና እንዲያቀብል ያደርገው ነበር።

ብፁእ አባታችን ዉዳሴዋን ቅዳሴዋን ሲያደርስ እመቤታችን የፍቅሯ ምልክት ይሆነው ዘንድ ነጭ እጣንና የሚያበራ እንቁ ሰጥታቸዋለች። አባታችንም እነዚህን ስጦታዋች የምትሰጭኝ ምን ስላደረግሁ ነው? ብለው በጠየቋት ጊዜ እጣኑ የምኡዝ ክህነትህ ዕንቁው የንጽህናህ የድንግልናህ የቅድስናህ ናቸው ብላ ተርጉማላቸዋለች።

መራሄ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም የሁል ጊዜ ጠባቂው ነዉና በሁሉም ነገር ይረዳዉና እንደ ጓደኛም ያማክረው ነበር።

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባን የዱር አራዊት ሁሉ ይገዙለትና ይታዘዙለት እንደነበረ በዚሁ በገድል መጽሃፋቸው በሰፊዉ ተተንትኗል ይልቁንም ሁለት አናብስት የሁል ጊዜ አገልጋዮቹ ነበሩ። ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ እሳቸው በአንዱ አንበሳ ተቀምጠው ጻሕፍቶቻቸውን በሌላው አንበሳ ላይ ጭነው እንደሚጓዙ ገድላቸው ያስረዳል። ሌሎቹም አራዊት አባታችንን ሲያዩአቸው እናቱን እንዳየ እንቦሳ በደስታ ይፈነጩ ነበር።

በመግቢያችን እንደገለጽነው የዋልድባ ገዳም የተመሰረተው በጥንታውያን አበው ቢሆንም አባታችን አባ ሳሙኤል ሲገቡ ገዳሙ ምድረ በዳ ሆኖ እስከ መጥፋት ደርሶ ቋያ በቅሎበት የወባ ትንኝ መፈልፈያ ሆኖ እንደ ነበረና ቅዱስነታቸው ሲገቡ ግን የተበተኑትን መነኮሳት ሰብስበው ዋልድባን እንደገና አደራጅተዉና አድሰው አቀኑት የተባህትዎ ኑሮንም አጠናክረው የመናንያን መነኮሳት አበው መሰባሰቢያና መፍለቂያ ከማድረጋቸውም በላይ ዋልድባን እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል።

ጻድቁ አባታችን ወንጌልን ለማስፋፋት በየሀገሩ ዞረው አስተምረዋል ብዙ የትሩፋትንም ሥራ ሠርተዋል ጣና ውስጥ በሚገኙ ገዳማትና ማን እንደአባ ያሳይ እንዲሁም ገሊላ ቦታዎች በምድር ዉስጥ ጉድጓድ ቆፍረው እየገቡ ከእህልና ዉሀ ተለይተው ሁለትና ሦስት ሱባኤ ይፈጽሙ ነበረ።

ከሁለት ቅዱሳን ወንድሞቻቸው ከአባ ሳሙኤል ዘወገግና ከአባ ብንያም ዘታህታይ በጌምድር ጋር በመሆን ምድረ ከብድና ዝቋላ በመሄድ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር በተገናኙ ጊዜ ብዙ ተአምራት እንደተደረገላቸው መጽሐፈ ገድላቸው ያስረዳል እንዲሁም ደግሞ በኤርትራ የሚገኘዉን ገዳም ከመሰረቱት ከአቡነ ፊልጶስ ጋር እንደተገናኙና የእግዚአብሔርን ክብር ይጨዋወቱ እንደነበር በገድላቸው ተጽፏል።

ጻድቁ አባታችን በሰኔ ፳፩/21 በእመቤታችን የእረፍት ቀን በመካነ ጸሎታቸው ላይ እያሉ ጌታችን መድኃኒታችን ተገለጸላቸው። ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ። የሚል ድምጽ ሰሙና ደንግጠው ቆሙ። ጌታችን ቀረብ ብሎ የእናቴ የድንግል ማርያም በዓል ነውና እንድትቀድስ ብሎ አዘዛቸው። አባታችንም እኔ ኃጢአተኛ ነኝ ለመቀደስ አልበቃሁም በማለት ነው ከቤተ መቅደስ አገልግሎት የተለየሁት ብለው መለሱለት። ጌታችንም ስለዚህ ትህትናህ ነው እንድትቀድስ የመረጥኩህ አላቸው። ወዲያዉኑ አባታችን ከፈጣሪያችን ሥርየትና ቡራኬ ተቀብለው ቅዳሴ ገቡ። ሥርዓተ ቅዳሴዉን አድርሰው ከፍሬ ቅዳሴው ደርሰው ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ፣ ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ፣ ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ ባሉ ጊዜ የሚቀድሱበት ቤተ ክርስቲያን አንድ ክንድ ከስንዝር ከምድር ለቅቆ እንደ ደመና በአየር ላይ ቆመ። ቅዳሴው ተፈጽሞ እትው እስኪባልም ድረስ እንደቆመ ቆይቷል። ከቅዳሴው በኋላም ጌታችን ከሰው ልጆች የተወለዱትን ሁሉ ወደፊትም እስከ ምጽዓት ድረስ የሚወለዱትንም እልፍ አእላፋት መናንያን መነኮሳት ሰብስቦ በአምላካዊ ሥራው ሕያዋን አድርጎ አሳያቸው።አቡነ ሳሙኤልም በመገረም አምላኬ ፈጣሪየ ሆይ ይህንን ያህል ግዛት ያለው ሰው ከምን የመጣ ነው? ብለው ጠየቁት። እነዚህ እስከ እለተ ምጽዓት ድረስ የሚወለዱ ልጆችህ ናቸው።በአንተ እጅ እንዲባረኩም አምጥቻቸዋለሁ ባርካቸው በማለት ነግሯቸዋል። የአቡነ ሳሙኤልን ስም የሚጠራ መታሰቢያቸዉን የሚያደርግ በአማላጅነታቸው የሚያምን ሁሉ ተባርኳል።

የአባታችን በረከት ከሁላችን ጋር ይደር። የአባ ሳሙኤል ቃል ኪዳናቸው፣ እረፍታቸውና ዓመታዊ ክብረ በዓላቸው የአባታችን የእረፍት ጊዜ ሲደርስም በተወለዱ በአንድ መቶ ዓመት በምናኔ በተባህትዎ እና በምንኩስና ከዚህ ዓለም ተለይተው ግርማ ሌሊትን ድምፀ አራዊትን ፀብአ አጋንንትን የቀን ሐሩር የሌሊት ቁሩን ታግሰው ራቡን ጥሙን ችለው መላ ዘመናቸውን የተቀበሉትን ፀዋትወ መከራ አይቶ ገነት መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸው ዘንድ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችን ካሉበት በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃንና ሰማእታትን አስከትሎ መጥቶ በህይወት ሳሉ የሰጣቸዉን ቃል ኪዳን በእረፍታቸዉም

ደግሞ ስምህን የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በጸሎትህ በአማላጅነትህ ያመነ፣ በመቃብርህ በመካነ አፅምህ የተማፀነ የአንተ ቤተሰብ ሆኖ አንተ የገባህበት አገባዋለሁ። ርስት መንግሥተ ሰማይን አወርሰዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ንጽሕት ጽዕድት ነፍሳቸው በእደ መላእክት በመዓዛ ገነት ከሥጋዋ ተለየች። ቅዱሳን መላእክትም በነብዩ በዳዊት ቃል መዝ.፻፲፮፥፲፭ “ክቡር ሞቱ ለጻድቅ

በቅድመ እግዚአብሔር” እያሉ በታላቅ ዝማሬ፣ በይባቤ፣ በእልልታና በሕይወት ወደ ዘለዓለም የእረፍት ቦታ አስገቧት። ጻድቁ አባታችን በተወለዱ በመቶ ዓመታቸው ታህሳስ ፲፪/12 ቀን ማክሰኞ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ዋልድባ አብረንታንት አርፈዋል።

ስለ አባታችን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ይህንን አጭር ጽሁፍ ስናቀርብ አቅጣጫ ለማመላከት ያህል ሲሆን መላዉን በገድል መጽሐፋቸውና በስንክሳር ያገኙታል።

በመስከረም ፮/6 ፍልሰተ አጽማቸው ነው፤ ይህም ከአብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ የፈለሰበት ነው፣ ታህሳስ ፲፪/12 እረፍታቸው ነው እንዲሁም ወር በገባ ፲፪/12 ደግሞ ወርኃዊ በዓላቸው ነው።

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከት አማላጅነት አይለየን!!!

👉 ሙሉውን ለማንበብ

_______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 26, 2021

💭 በቅድስቲቷ አክሱም የሉሲፈር/ቻይና/ቱርክ ባንዲራ በጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ መሰቀሉ ትልቅ ድፍረት፣ ንቀት እና ጽዮን እናታችንን የሚያስቆጣ እኩይ ተግባር ነው። ጽዮናውያን ሆይ፤ “ቻይና እና ቱርክ ሕዝባችንን በድሮን እየጨፈጨፉት እንዴት የእነርሱን ባንዲራ እንኳን በአክሱም በሌላ ቦታስ እናውለበልባለን?” በማለት ባፋጣኝ ባንዲራው እንዲነሳ መወትወት አለብን። ይህ በቀላሉና በግድየለሽነት የሚታይ ጉዳይ አይደለም!

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹]✞✞✞

፲፫ ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፤

፲፬ ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤

፲፭ የእግዚአብሔር ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘላለም በሆነ ነበር፤

፲፮ ከስንዴም ስብ ባበላቸው ነበር፥ ከዓለቱም ማር ባጠገባቸው ነበር።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፱]✞✞✞

፩ አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት።

፪ የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤

፫ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ።

፬ ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት።

፭ አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል?

፮ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁህም አሕዛብ ላይ መዓትህን አፍስስ፤

፯ ያዕቆብን በልተውታልና፥ ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና።

፰ የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና።

፱ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።

፲ አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ፤

፲፩ የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።

፲፪ አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።

፲፫ እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥ ለዘላለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።

_________________

Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሆሣእና ለዳዊት ልጅ | አቤቱ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁህም አሕዛብ ላይ መዓትህን አፍስስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 25, 2021

በተለይ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ትውልድ ጆሮውን ወደ እግዚአብሔር አፍ ቃል ማዘንበል ይኖርበታል

ከዚህ ቀደም እንዳወሳሁት እንደ አፄ ካሌብና እንደ አፄ ዮሐንስ ያሉ ክርስቲያናዊ ነገሥታት የሚመሩት ሙሉ በሙሉ ክርስቲያናዊ የሆነ ሠራዊት ዛሬ አክሱም ጽዮን/ትግራይ ቢኖራት 1000% እርግጠኛ ነኝ በሦስት ቀናት ውስጥ አስመራን፣ ጎንደርን፣ አዲስ አበባን፣ ጅማን፣ ሐረርን፣ ካርቱምን፣ ጁባንና ሞቃዲሾን (ሁሉም የታላቋ ኢትዮጵያ አካል ናቸው) መቆጣጠር ችሎ፤ ለወደፊት እንኳን የግራኝ ልቅምቃሚ ሰአራዊት፤ እነ አሜሪካ፣ ሩሲያና ቻይና እንኳን የማይደፈሯት ንጉሥ ካሌብ የመሠረቷት አዲሲቷንና የጥንቷን ኢትዮጵያን ተመልሳ ለማየት እንበቃ ነበር።

❖❖❖ዘመነ ሰማዕታት❖❖❖

አክሱም ጽዮንን/ጽላተ ሙሴን ሲከላከሉ ፩ሺህ/1000 ምዕመናን በአህዛብ ሰአራዊት መገደላቸውን እግዚአብሔር በደንብ አይቶታል፤ የሰማዕትነትንም አክሊል እንዲጎናጸፉ አድርጓቸዋል፤ እነዚህና ሌሎችም ያላግባብ የተገደሉት መቶ ሃምሳ ሺህ የሚሆኑት የአክሱም ጽዮን አሁን መቶ ሃምሳ ሚሊየን ሆነው በመመለስ እዚህ ከቀሩት የጽዮን ልጆች ጋር በጽዮን ላይ የዘመቱትን ሰማኒያ ሚሊየን ከሃዲዎች መቆጣጠር፣ መዋጋት፣ ማዋረድና ማርበድበድ ይጀምራሉ።

የአሜሪካ ሆሊውድ ፊልም ሰሪዎችን አባባል ልጥቀስና፤ “ጽላተ ሙሴን የያዘ የአንድ ሃገር ሠራዊት በዓለም ኃያሉ ሠራዊት ነው!!!”

☆ Raiders of the Lost Ark (CIA Meeting)

An Army That Carries The Ark Before it… is Invincible„

❖Soldier of Zion | የጽዮን ወታደር

👉 ፈሪሃ እግዚአብሔር ያለው ክርስቲያን ሠራዊት ሁሌ ያሸንፋል!

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፯]✞✞✞

፩ ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፤ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።

፪ አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ፥ ያለውንም ተምሳሊት እናገራለሁ።

፫ የሰማነውንና ያውቅነውን፥ አባቶቻችንም የነገሩንን፥ ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም።

፬ የእግዚአብሔርን ምስጋናና ኃይሉን ያደረገውንም ተኣምራት ተናገሩ።

፭ ለልጆቻቸው ያስታውቅ ዘንድ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ምስክር በያዕቆብ አቆመ፥ በእስራኤልም ሕግን ሠራ፤

፮ የሚመጣ፥ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ፤

፯ ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ፤

፰ እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ጠማማና የምታስመርር ትውልድ፥ ልብዋን ያላቀናች ትውልድ፥ ነፍስዋ በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነች።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፹]✞✞✞

፲፫ ሕዝቤስ ሰምቶኝ ቢሆን፥ እስራኤልም በመንገዴ ሄደው ቢሆን፤

፲፬ ጠላቶቻቸውን ፈጥኜ ባዋረድኋቸው ነበር፥ በሚያስጨንቋቸውም ላይ እጄን በጣልሁ ነበር፤

፲፭ የእግዚአብሔር ጠላቶችም በተገዙለት ነበር፥ ዘመናቸውም ለዘላለም በሆነ ነበር፤

፲፮ ከስንዴም ስብ ባበላቸው ነበር፥ ከዓለቱም ማር ባጠገባቸው ነበር።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፯]✞✞✞

፩ ሕዝቤ ሆይ፥ ሕጌን አድምጡ፤ ጆሮአችሁንም ወደ አፌ ቃል አዘንብሉ።

፪ አፌን በምሳሌ እከፍታለሁ፤ ከቀድሞ ጀምሮ፥ ያለውንም ተምሳሊት እናገራለሁ።

፫ የሰማነውንና ያውቅነውን፥ አባቶቻችንም የነገሩንን፥ ለሚመጣ ትውልድ ከልጆቻቸው አልሰወሩም።

፬ የእግዚአብሔርን ምስጋናና ኃይሉን ያደረገውንም ተኣምራት ተናገሩ።

፭ ለልጆቻቸው ያስታውቅ ዘንድ ለአባቶቻችን ያዘዘውን ምስክር በያዕቆብ አቆመ፥ በእስራኤልም ሕግን ሠራ፤

፮ የሚመጣ፥ ትውልድ የሚወለዱም ልጆች ያውቁ ዘንድ፥ ተነሥተው ለልጆቻቸው ይነግራሉ፤

፯ ተስፋቸውን በእግዚአብሔር እንዲያደርጉ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ እንዳይረሱ፥ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ፤

፰ እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ጠማማና የምታስመርር ትውልድ፥ ልብዋን ያላቀናች ትውልድ፥ ነፍስዋ በእግዚአብሔር ዘንድ ያልታመነች።

፱ የኤፍሬም ልጆች ለሰልፍ ታጥቀው ቀስትንም ገትረው በሰልፍ ቀን ወደ ኋላ ተመለሱ።

፲ የእግዚአብሔርን ኪዳን አልጠበቁም፥ በሕጉም ለመመላለስ እንቢ አሉ፤

፲፩ መልካም ሥራውንና ያሳያቸውን ተኣምራቱን ረሱ፥

፲፪ በግብጽ አገርና በጣኔዎስ በረሃ በአባቶቻቸው ፊት የሠራውን ተኣምራት።

፲፫ ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፤ ውኆችን እንደ ክምር አቆመ።

፲፬ ቀን በደመና መራቸው፥ ሌሊቱንም ሁሉ በእሳት ብርሃን።

፲፭ ዓለቱን በምድረ በዳ ሰነጠቀ፤ ከጥልቅ እንደሚገኝ ያህል በብዙ አጠጣቸው።

፲፮ ውኃን ከጭንጫ አወጣ፥ ውኃንም እንደ ወንዞች አፈሰሰ።

፲፯ ነገር ግን ይበድሉት ዘንድ እንደ ገና ደገሙ፥ ልዑልንም በምድረ በዳ አስቈጡት።

፲፰ ለነፍሳቸው መብልን ይፈልጉ ዘንድ፥ እግዚአብሔርን በልባቸው ፈተኑት።

፲፱ እግዚአብሔርን እንዲህ ብለው አሙት። እግዚአብሔር በምድረ በዳ ማዕድን ያሰናዳ ዘንድ ይችላልን?

፳ ዓለቱን መታ፤ ውኆችም ወጡ፥ ወንዞችም ጐረፉ፤ እንጀራን መስጠትስ ይችላልን? ለሕዝቡስ ማዕድን ያዘጋጃልን?

፳፩ እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፤ በያዕቆብም ላይ እሳት ነደደ፥ መዓትም በእስራኤል ላይ መጣ፤

፳፪ በእግዚአብሔር አላመኑምና፥ በመድኃኒቱም አልተማመኑምና።

፳፫ ደመናውንም ከላይ አዘዘ፥ የሰማይንም ደጆች ከፈተ፤

፳፬ ይበሉም ዘንድ መናን አዘነበላቸው፥ የሰማይንም እንጀራ ሰጣቸው።

፳፭ የመላክትንም እንጀራ ሰው በላ ስንቅንም እስኪተርፋቸው ላከላቸው።

፳፮ ከሰማይ የምሥራቅን ነፋስ አስነሣ፥ በኃይሉም የደቡብን ነፋስ አመጣ፤

፳፯ ሥጋን እንደ አፈር፥ የሚበርሩትንም ወፎች እንደ ባሕር አሸዋ አዘነበላቸው፤

፳፰ በሰፈራቸው መካከል፥ በድንኳናቸውም ዙሪያ ወደቀ።

፳፱ በሉ እጅግም ጠገቡ፤ ምኞታቸውንም ሰጣቸው።

፴ ከወደዱትም አላሳጣቸውም፤ መብላቸውም ገና በአፋቸው ሳለ፥

፴፩ የእግዚአብሔር ቍጣ በላያቸው መጣ፥ ከእነርሱም ከፍ ያሉትን ገደለ፥ የእስራኤልንም ምርጦች አሰናከለ።

፴፪ ከዚህም ሁሉ ጋር እንደ ገና በደሉ፥ ተኣምራቱንም አላመኑም፤

፴፫ ቀኖቻቸውም በከንቱ አለቁ፥ ዓመቶቻቸውም በችኰላ።

፴፬ በገደላቸውም ጊዜ ወዲያው ፈለጉት፤ ተመለሱ ወደ እግዚአብሔርም ገሠገሡ፤

፴፭ ረዳታቸውም እግዚአብሔር፥ መድኃኒታቸውም ልዑል አምላክ እንደ ሆነ አሰቡ።

፴፮ በአፋቸው ብቻ ወደዱት፤ በአንደበታቸውም ዋሹበት፤

፴፰ እርሱ ግን መሓሪ ነው፥ ኃጢአታቸውንም ይቅር አላቸው፥ አላጠፋቸውምም፤ ቍጣውንም መመለስ አበዛ፥ መዓቱንም ሁሉ አላቃጠለም።

፴፱ ወጥቶ የማይመለስ መንፈስ፥ ሥጋም እንደ ሆኑ አሰበ።

፵ በምድረ በዳ ምን ያህል አስቈጡት፥ በበረሃም አሳዘኑት።

፵፩ ተመለሱ፥ እግዚአብሔርንም ፈተኑት፥ የእስራኤልንም ቅዱስ አሳዘኑት።

፵፪ እነርሱም እጁን አላሰቡም፥ ከጠላቶቻቸው እጅ ያዳነበትን ቀን፥

፵፫ በግብጽ ያደረገውን ተኣምራቱን፥ በጣኔዎስም በረሃ ያደረገውን ድንቁን።

፵፬ ወንዞቻቸውንም ወደ ደም ለወጠ፥ ምንጮቻቸውን ደግሞ እንዳይጠጡ።

፵፭ ዝንቦችንም በላያቸው ሰደደባቸው፥ በሉአቸውም፤ በጓጉንቸርም አጠፋቸው።

፵፮ ፍሬያቸውን ለኩብኩባ፥ ሥራቸውንም ለአንበጣ ሰጠ።

፵፯ ወይናቸውን በበረዶ፥ በለሳቸውንም በአመዳይ አጠፋ።

፵፰ እንስሶቻቸውን ለበረዶ፥ ሀብታቸውንም ለእሳት ሰጠ።

፵፱ የመዓቱን መቅሠፍት በላያቸው ሰደደ፤ መቅሠፍትን መዓትንም መከራንም በክፉዎች መላእክት ሰደደ።

፶ ለቍጣው መንገድን ጠረገ፤ ነፍሳቸውንም ከሞት አላዳናትም፥ እንስሶቻቸውንም በሞት ውስጥ ዘጋ፤

፶፩ በኵሮቻቸውን ሁሉ በግብጽ፥ የድካማቸውንም መጀመሪያ በካም ድንኳኖች ገደለ።

፶፪ ሕዝቡን ግን እንደ በጎች አሰማራቸው፥ እንደ መንጋም በምድረ በዳ መራቸው።

፶፫ በተስፋም መራቸው አልፈሩምም፥ ጠላቶቻቸውንም ባሕር ደፈናቸው።

፶፬ ወደ መቅደሱም ተራራ አገባቸው፥ ቀኙ ወደ ፈጠረችው ወደዚህች ተራራ፤

፶፭ ከፊታቸውም አሕዛብን አባረረ፥ ርስቱንም በገመድ አካፈላቸው፥ የእስራኤልንም ወገኖች በቤታቸው አኖረ።

፶፮ ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔርን ፈተኑት አስቈጡትም፥ ምስክሩንም አልጠበቁም፤

፶፯ ተመለሱም እንደ አባቶቻቸውም ከዱ፤ እንደ ጠማማ ቀስትም ተገለበጡ፤

፶፰ በኰረብታ መስገጃዎቻቸውም አስቈጡት፥ በተቀረጹ ምስሎቻቸውም አስቀኑት።

፶፱ እግዚአብሔርም ይህን ሰምቶ ተቈጣ፥ እስራኤልንም እጅግ ናቀ፤

፷ የሴሎምን ማደሪያ ተዋት በሰዎች መካከል ያደረገባትን ድንኳኑን፤

፷፩ ኃይላቸውን ለምርኮ፥ ሽልማቱንም በጠላት እጅ ሰጠ።

፷፪ ሕዝቡንም በጦር ውስጥ ዘጋቸው፥ ርስቱንም ቸል አላቸው።

፷፫ ጕልማሶቻቸውን እሳት በላቸው፥ ቈነጃጅቶቻቸውም አላዘኑም፤

፷፬ ካህናቶቻቸውም በሰይፍ ወደቁ፥ ባልቴቶቻቸውም አላለቀሱላቸውም።

፷፭ እግዚአብሔርም ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ፥ የወይን ስካር እንደ ተወው እንደ ኃያልም ሰው፤

፷፮ ጠላቶቹንም በኋላቸው መታ፤ የዘላለምን ኀሣር ሰጣቸው።

፷፯ የዮሴፍንም ድንኳን ተዋት፥ የኤፍሬምንም ወገን አልመረጠውም፤

፷፰ የይሁዳን ወገን ግን መረጠ፥ የወደደውን የጽዮንን ተራራ።

፷፱ መቅደሱን እንደ አርያም ሠራ፥ ለዘላለምም በምድር ውስጥ መሠረታት።

፸ ዳዊትንም ባሪያውን መረጠው፥ ከበጎቹም መንጋ ውስጥ ወሰደው፤

፸፩ ከሚያጠቡ በጎችም በኋላ፥ ባሪያውን ያዕቆብን ርስቱንም እስራኤልን ይጠብቅ ዘንድ ወሰደው።

፸፪ በልቡ ቅንነት ጠበቃቸው፥ በእጁም ብልሃት መራቸው።

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፱]✞✞✞

፩ አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት።

፪ የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤

፫ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ።

፬ ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት።

፭ አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል?

፮ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁህም አሕዛብ ላይ መዓትህን አፍስስ፤

፯ ያዕቆብን በልተውታልና፥ ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና።

፰ የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና።

፱ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን።

፲ አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ፤

፲፩ የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን።

፲፪ አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።

፲፫ እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥ ለዘላለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 18, 2021

የሚከተሉትን ፭ ድንቅ ምዕራፎች ያለማቋረጥ ደግሜ ደጋግሜ ሳነባቸውና ስሰማቸው ነበር ያነጋሁት።

በኢትዮጵያ እየተካሄዱ ያሉትን ነገሮች ሁሉ ግልጥ አድርገው የሚያሳዩ ሆኖ ነው የተሰማኝ። ድንቅ፣ ድንቅ፣ ድንቅ ነው! አዎ! ሰማይና ምድር ያልፋሉ የእግዚአብሔር ቃል ግን አያልፍም!

👉 ለምሳሌ፦ [መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፪] በትግራይ አክሱም ጽዮን ላይ ከባድ ወንጀል እየሰሩ ስላሉትና “እግዚአብሔር አያይም፤ እንዴትስ ያውቃል?” እያሉ በአመጽና በትዕቢት የሚኩራሩት ኦሮሞ፣ አማራ፣ ኢ-አማንያን፣ አህዛብና መናፍቃን የዋቄዮ-አላህ ኃጢአተኞች፦

፫ የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።

፬ ለሞታቸው መጣጣር የለውምና፤ ኃይላቸውም ጠንካራ ነውና።

፭ እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም።

፮ ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው፤ ኃጢአትንና በደልን ተጐናጸፉአት።

፯ ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፤ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ።

፰ አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ። ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።

፱ አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።

፲ ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤

፲፩ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለ? ይላሉ።

፲፪ እነሆ፥ እነዚህ ኃጢአተኞች ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ።

፲፰ በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥ ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።

፲፱ እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ ስለ ኃጢአታቸውም ጠፉ።

፳ ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለህ።

👉 በ[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፫] ደግሞ፤

በአክሱም ጽዮን ላይ፣

በዋልድባ ላይ፣

በደብረ አባይ ላይ፣

በደንገላት ቅድስት ማርያም ላይ፣

በደብረ ዳሞ አቡነ አረጋዊ ላይ፣

በውቅሮ አማኑኤል ላይ፣

በዛላምበሳ ጨርቆስ ላይ፣

በሌሎች ባልተወራላቸው የትግራይ ዓብያተ ክርስቲያናት እና ገዳማት ላይ በከንቱውና በሰይጣናዊው “የብሔር ብሔረሰብ ርዕዮተ ዓለም” የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትናን ማዕከል የሆነችውን ትግራይን ከትክክለኛው እና ጽኑ የክርስትና እምነት ተከታይ ከሆነው ሕዝቧ በረሃብ፣ በበሽታና በጥይት ለማጽዳት፣ ዓብያተ ክርስቲያናቱን፣ ገዳማቱንና ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ያደረጓትን ቅርሶቿን ለማጥፋት የሉሲፈር ኮከብ ያረፉባቸውን “የማያውቁትን ምልክት” የብሔራዊ እና የክልል ባንዲራዎችን ምልክታቸው አድርገው በመያዝ ዓብያተ ክርስቲያናቱንና ገዳማቱን በፈንጂና በመዶሻ፣ በመጥረቢያ አፈራረሷቸው፣ ቤተ መቅደሶቻቸውን ከረጋገጧቸው በኋላ በእሳት አቃጠሏቸው።

እንግዲህ ይህን በእግዚአብሔር ዘንድ እጅግ በጣም ከባድ የሆነ ወንጀል እየሰሩ ስላሉትና “እግዚአብሔር አያይም፤ እንዴትስ ያውቃል?” የሚሉት ኦሮሞ፣ አማራ፣ ኢአማንያን፣ አህዛብና መናፍቃን የዋቄዮአላህ ኃጢአተኞችን በግልጽ ያሳየናል። ላለፉት ሦስት ዓመታት “አስቀድሞ ያቆማትን አክሱም ጽዮንንና የቅዱሳን ተራሮቹን ነዋሪዎች ለማርከስና ለማጥፋት ሁሉም ተናብበው በህበረት እየሠሩ ነው” ስል የነበረውን እነዚህ ኃይለኛ የእግዚአብሔር ቃላት አረጋግጠውልኛል። በክፉውም በበጎውም ጊዜ ተመስገን ጌታዬ!

፩ አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ስለ ምን ተቈጣህ?

፪ አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።

፫ ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።

፬ ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።

፭ እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ።

፮ እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።

፯ መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።

፰ አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ።

፱ ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።”

👉 ከምዕራፍ ፸፩ እስከ ፸፭ ድረስ ሙሉውን እናንብበው/እናዳምጠው! በእውነት ድንቅ ነውና!

❖❖❖ ስብሐት ለአብ ፡ ስብሐት ለወልድ ፡ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ፤ አሜን! (፫) ❖❖❖

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፩]

፩ አቤቱ፥ ፍርድህን ለንጉሥ ስጥ፥ ጽድቅህንም ለንጉሥ ልጅ፥

፪ ሕዝብህን በጽድቅ፥ ችግረኞችህንም በፍርድ ይዳኝ ዘንድ።

፫ ተራሮችና ኰረብቶች ለሕዝብህ ሰላምን ይቀበሉ።

፬ ለችግረኞች ሕዝብ በጽድቅ ትፈርዳለህ የድሆችንም ልጆች ታድናለህ፤ ክፉውንም ታዋርደዋለህ።

፭ ፀሐይ በሚኖርበት ዘመን ሁሉ፥ በጨረቃም ፊት ለፊት ለልጅ ልጅ ይኖራል።

፮ እንደ ዝናብ በታጨደ መስክ ላይ፥ በምድርም ላይ እንደሚንጠባጠብ ጠብታ ይወርዳል።

፯ በዘመኑም ጽድቅ ያብባል፥ ጨረቃም እስኪያልፍ ድረስ ሰላም ብዙ ነው።

፰ ከባሕር እስከ ባሕር ድረስ፥ ከወንዝም እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይገዛል።

፱ በፊቱም ኢትዮጵያ ይሰግዳሉ፥ ጠላቶቹም አፈር ይልሳሉ።

፲ የተርሴስና የደሴቶች ነገሥታት ስጦታን ያመጣሉ፤ የዓረብና የሳባ ነገሥታት እጅ መንሻን ያቀርባሉ።

፲፩ ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል። አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።

፲፪ ችግረኛውን ከቀማኛው እጅ፥ ረዳት የሌለውንም ምስኪን ያድነዋልና።

፲፫ ለችግረኛና ለምስኪን ይራራል፥ የችግረኞችንም ነፍስ ያድናል።

፲፬ ከግፍና ከጭንቀት ነፍሳቸውን ያድናል፤ ስማቸው በፊቱ ክቡር ነው።

፲፭ እርሱ ይኖራል ከዓረብም ወርቅ ይሰጡታል፤ ሁልጊዜም ወደ እርሱ ይጸልያሉ፥ ዘወትርም ይባርኩታል።

፲፮ በምድር ውስጥ በተራሮች ላይ መጠጊያ ይሆናል፤ ፍሬውም ከሊባኖስ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፤ እንደ ምድር ሣር በከተማ ይበቅላል።

፲፯ ስሙ ለዘላለም ቡሩክ ይሆናል፥ ከፀሐይም አስቀድሞ ስሙ ይኖራል፤ የምድር አሕዛብ ሁሉ በእርሱ ይባረካሉም አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑታል።

፲፰ ብቻውን ተአምራትን የሚያደርግ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ይባረክ።

፲፱ የምስጋናው ስም ለዓለምና ለዘላለም ይባረክ፤ ምስጋናውም ምድርን ሁሉ ይምላ። ይሁን፤ ይሁን።

፳ የእሴይ ልጅ የዳዊት መዝሙር ተፈጸመ።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፪]

፩ ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው።

፪ እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ አረማመዴም ሊወድቅ ትንሽ ቀረ።

፫ የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።

፬ ለሞታቸው መጣጣር የለውምና፤ ኃይላቸውም ጠንካራ ነውና።

፭ እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም።

፮ ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው፤ ኃጢአትንና በደልን ተጐናጸፉአት።

፯ ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፤ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ።

፰ አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ። ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ።

፱ አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ።

፲ ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤

፲፩ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለ? ይላሉ።

፲፪ እነሆ፥ እነዚህ ኃጢአተኞች ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ።

፲፫ እንዲህም አልሁ። በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ።

፲፬ ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው።

፲፭ እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር።

፲፮ አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ።

፲፯ ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ።

፲፰ በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥ ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው።

፲፱ እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ ስለ ኃጢአታቸውም ጠፉ።

፳ ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለህ።

፳፩ ልቤ ነድዶአልና፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና፤

፳፪ እኔ የተናቅሁ ነኝ አላውቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ።

፳፫ እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ።

፳፬ በአንተ ምክር መራኸኝ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ።

፳፭ በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ?

፳፮ የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው።

፳፯ እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው።

፳፰ ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፫]

፩ አቤቱ፥ ስለ ምን ለዘወትር ጣልኸኝ? በማሰማርያህ በጎች ላይስ ቍጣህን ስለ ምን ተቈጣህ?

፪ አስቀድመህ የፈጠርሃትን ማኅበርህን፥ የተቤዤሃትንም የርስትህን በትር፥ በእርስዋ ያደርህባትን የጽዮንን ተራራ አስብ።

፫ ጠላት በቅዱሳንህ ላይ እንደ ከፋ መጠን፥ ሁልጊዜም በትዕቢታቸው ላይ እጅህን አንሣ።

፬ ጠላቶችህ በበዓል መካከል ተመኩ፤ የማያውቁትንም ምልክት ምልክታቸው አደረጉ።

፭ እንደ ላይኛው መግቢያ ውስጥ በዱር እንዳሉም እንጨቶች፥ በመጥረቢያ በሮችዋን ሰበሩ።

፮ እንዲሁ በመጥረቢያና በመዶሻ ሰበሩአት።

፯ መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፤ የስምህንም ማደሪያ በምድር ውስጥ አረከሱ።

፰ አንድ ሆነው በልባቸው በየሕዝባቸው። ኑ፥ የእግዚአብሔርን በዓሎች ከምድር እንሻር አሉ።

፱ ምልክታችንን አናይም ከእንግዲህ ወዲህም ነቢይ የለም፤ እስከ መቼ እንዲኖር የሚያውቅ በኛ ዘንድ የለም።

፲ አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ሁልጊዜ ያቃልላልን?

፲፩ ቀኝህንም በብብትህ መካከል፥ እጅህንም ፈጽመህ ለምን ትመልሳለህ?

፲፪ እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው፥ በምድርም መካከል መድኃኒትን አደረገ።

፲፫ አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፤ አንተ የእባቦችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።

፲፬ አንተም የዘንዶውን ራሶች ቀጠቀጥህ፤ ለኢትዮጵያ ሰዎችም ምግባቸውን ሰጠሃቸው።

፲፭ አንተ ምንጮቹንና ፈሳሾቹን ሰነጠቅህ፤ አንተ ሁልጊዜ የሚፈስሱትን ወንዞች አደረቅህ።

፲፮ ቀኑ የአንተ ነው ሌሊቱም የአንተ ነው፤ አንተ ፀሓዩንና ጨረቃውን አዘጋጀህ።

፲፯ አንተ የምድርን ዳርቻ ሁሉ ሠራህ፤ በጋንም ክረምትንም አንተ አደረግህ።

፲፰ ይህን ፍጥረትህን አስብ። ጠላት እግዚአብሔርን ተላገደ፥ ሰነፍ ሕዝብም ስሙን አስቈጣ።

፲፱ የምትገዛልህን ነፍስ ለአራዊት አትስጣት፤ የችግረኞችህን ነፍስ ለዘወትር አትርሳ።

፳ ወደ ኪዳንህ ተመልከት፥ የምድር የጨለማ ስፍራዎች በኅጥኣን ቤቶች ተሞልተዋልና።

፳፩ ችግረኛ አፍሮ አይመለስ፤ ችግረኛና ምስኪን ስምህን ያመሰግናሉ።

፳፪ አቤቱ፥ ተነሥ በቀልህንም ተበቀል፤ ሰነፎች ሁልጊዜም የተላገዱህን አስብ።

፳፫ የባሪያዎችህን ቃል አትርሳ፤ የጠላቶችህ ኵራት ሁልጊዜ ወደ አንተ ይወጣል።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፭]

አቤቱ፥ እናመሰግንሃለን እናመሰግንሃለን ስምህንም እንጠራለን፤ ተኣምራትህን ሁሉ እናገራለሁ።

ጊዜውን ስቀበል እኔ በቅን እፈርዳለሁ።

ምድርና በእርስዋ ውስጥ የሚኖሩት ሁሉ ቀለጡ፥ እኔም ምሰሶችዋን አጠናሁ።

ዓመፀኞችን። አትበድሉ አልኋቸው፥ ኃጢአተኞችንም። ቀንዳችሁን አታንሡ፤

ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ፥ በእግዚአብሔርም ላይ ዓመፅን አትናገሩ።

ክብር ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ ወይም ከምድረ በዳ የለምና፤

እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና ይህን ያዋርዳል ይህንም ያከብራል።

ጽዋ በእግዚአብሔር እጅ ነውና፤ ያልተቀላቀለ የወይን ጠጅ ሞላበት፤ ከዚህ ወደዚያ አገላበጠው፥ ነገር ግን አተላው አልፈሰሰም፤ የምድር ኃጢአተኞች ሁሉ ይጠጡታል።

እኔ ግን ለዘላለም ደስ ይለኛል፥ ለያዕቆብም አምላክ ዝማሬን አቀርባለሁ።

የኅጥኣንን ቀንዶች ሁሉ እሰብራለሁ፤ የጻድቃን ቀንዶች ግን ከፍ ከፍ ይላሉ።

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፭]

፩ እግዚአብሔር በይሁዳ ታወቀ፥ ስሙም በእስራኤል ታላቅ ነው።

፪ ስፍራው በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው።

፫ በዚያም የቀስትን ኃይል፥ ጋሻን ሰይፍን ሰልፍንም ሰበረ፤ በዚያም ቀንዶችን ሰበረ።

፬ አንተ በዘላለም ተራሮች ሆነህ በድንቅ ታበራለህ።

፭ ልበ ሰነፎች ሁሉ ደነገጡ፥ እንቅልፋቸውንም አንቀላፉ፤ ባለጠጎች ሁሉ በእነርሱ እጅ ምንም አላገኙም።

፮ የያዕቆብ አምላክ ሆይ፥ ከተግሣጽህ የተነሣ ፈረሰኞች ሁሉ አንቀላፉ።

፯ አንተ ግን፥ አንተ ግሩም ነህ፤ ቍጣህን ማን ይቃወማል?

፰ ፍርድን ከሰማይ አሰማህ፤ ምድር ፈራች ዝምም አለች፥

፱ ልበ የዋሃን ያድን ዘንድ እግዚአብሔር ለፍርድ በተነሣ ጊዜ።

፲ ሰው በፈቃዱ ያመሰግንሃልና፥ ከሕሊናቸው ትርፍም በዓልህን ያደርጋሉ።

፲፩ ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስእለትን ክፈሉ፤ በዙሪያው ያሉ ሁሉ እጅ መንሻን ለሚያስፈራው ያገባሉ።

፲፪ የመኳንንትን ነፍስ ያወጣል፤ በምድርም ነገሥታት ዘንድ ያስፈራል።

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው ፥ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 11, 2021

✞✞✞“ዋልድባ ሐጢአት አይሻገርብሽ እህል እንዳይበላብሽ”✞✞✞

✞✞✞ደብረ ዋሊ ወይም ዋልድባ ገዳም በ ፬ /4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ተመሰረተ✞✞✞

✞✞✞ ስለ ዋልድባ ገዳም ታሪክ (አቀማመጥና ስያሜ)✞✞✞

ዋልድባ ገዳም በሰሜን ጎንደር በምዕራብ ትግራይ በተከዜ ወንዝ በዛሬማ ወንዝ በእንስያ ወንዝ በወልቃይት በጠለምት በፅንብላ በስሜን ጃናሞራ በአርማጭሆ በነዚህ ቦታዎችና ወንዞች ተከቦ ተከብሮና ታጥሮ በአስደናቂ የመሬት ተፎጥራዊ አቀማመጥ ልዩ በሆነ የምድር ካርታ በወንዞች ብቻ የታጠረ ነው ዋልድባ አብረንታንት ገዳም በኢየሱስ ክርስቶስ የተገደመ ነው።

ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ ፬ /4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ከተገደሙት ገዳማት አንዱ የሆነው ይህ ገዳም፤ምድር ስትፈጠር ጌታ ባወቀ ያዘጋጀው ቅዱስ ቦታ ነው፡፡ የትንቢቱ ቃል የተነገረለት ዋልድባ ወይም ዋሊ ማለት ምን ማለት ነው? እመቤታችን ዋሊ የሚባል ገዳም ደረስን ብላ ተናገረችው በውስጡ ባለችው ዕፅ ምክንያት ሲሆን፤ ይቺ ዋሊ የተሰኝች ዕፅ በገነት የምተገኝ ናት፡፡

የርሷም ቅጠሎች ሰፋፊና ቅርንጫፎቿ የበዙ፣ ሁል ጊዜ ጠዋት አብባ በ፱ ሰዓት የምታፈራ ዕፅ ናት፡፡ ዋሊ ዱባ የሚያክል ፍሬ በመያዟ በተለምዶ ዋሊዱባ በማለት ስትጠራ ቆይታ በኋላ ዋልድባ ለመባል በቅታለች፡፡ ዛሬም ቢሆን የቅዱሳን ምግብ ሆና የምታገለግለውን ዕፅ ከሥጋ ህፀፅ የራቀ ሁሉ በዓይነ ኅሊናው የብቃት መጽሔት ሊያያት ይችላል፡፡

በዚች ዕፅ ስያሜ የተጠራው የዋልድባ ገዳም የቆዳ ስፋት ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ከ፴ እስከ ፵ ኪሎሜትር ርቀት ስኖረው ከሰሜን ወደ ደቡብ ከ፹—፺ ኪሎ ሜትር ስፋት አለው፡፡ ገዳሙን እንደ ገነት ዙሪያውን በአራት አፍላጋት(ወንዞች) የተከበበ ሲሆን በምስራቅ የእንስያ፣በምእራብ የዛሬማ፣በደቡብ የማይወባ፣በሰሜን የተከዜ ወንዞች አጥር ቅጥር ሆነው ገዳሙን ይከልሉታል፡፡አዋሳኝ ቦታዎቹም በምስራቅ የፀለምት ወረዳ፣ በምዕራብ ወልቃይት፣በደቡብ የዛሬማ ወረዳ፣በሰሜን ፅምብላ ናቸው፡፡

በዚህ ስፋት ወስጥ እህል አይበላም፣ጠላና የመሳሰሉት መጠጣት አይፈቀድም፣የሞቀ ደመቀ አይለበስም፡፡ይህ ገዳም ብዙ ዋሻዎች፣ፍርክታዎችና ገደላማ ስፍራዎች ያሉበት ሲሆን፤በየውኃ ምንጮችም ጭምር የጥንት የአበው ቅሪት ምልክቶች እስከ ዛሬ ድረስ ይታዩበታል፡፡

የታተሙ ህንፃዎች፣የምድር ውስጥ ቤቶች፣የታሸጉ ዋሻዎች፣ዝጉሃን የሚኖሩባቸው ጉድጓዶችና የድንጋይ ስር ቤቶች ይገኛሉ፡፡እልፍ አእላፈት ስውራን ይኖሩበታል፡፡እነዚህም ለብቁአን፣ ለእረኞች ይከሰታሉ፣በአብዛኛው ደግሞ ከእይታ ውጭ በድምፅ ብቻ ጽንሐ ደውልና ይሰማል የእጣን ሽታ ይሸታል፡፡

ቀድሞ የነበረው የሁል ጊዜ ምግባቸው፤ ለእመቤታችን ቆፍሮ የሰጣት ባለ ሶስት መቶ አስራ ስምንት ሥር ያለው ገመሎ፣ሣዳ፣ፃሌብ፣አጽግቢት ሲሆኑ፣ከቅጠላ ቅጠሎች ሓምለ አበው የተባለ፣ክረምት ብቻ የሚበቅል፣ጎመንን የሚተካ የፀጋይቶ የሚባል እጅግ መራራ ቅጠል፣ሰብኣ የሚባል ቅጠል ሌሎችም ናቸው፡፡ ፀጋይቶ ቅጠል ሁለቴና ሶስቴ ተቀቅሎ ምሬቱና መርዙ ሲቀንስ ሚበላ ነው፡፡ እስከመጨረሻው ቢቀቀል ምሬቱ አይጠፋም፡፡ ከመሬት ተቆፍሮ ከሚወጡት ውስጥ ፃብሌ የድንች መልክ የያዘ ሆኖ ለጊዜው ቀቅለው ቢበሉት ልብን ያጠፋል፣አምሮን ያናውዛል፣ለእብደት ያደርሳል፡፡ይህ ተቆፍሮ ከወጣ በኋላ ከሳምንት ያለነሰ ጊዜ በውኃ ውስጥ እየተዘፈዘፈና እየታጠበ ተቀቅሎ ከቆየ በኋላ በፀሀይ ደርቆ በማጠራቀሚያ ጎተራ ይቀመጣል፡፡ ከዚህ በኋላ ነው ለምግብነት የሚጠቀሙበት፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሥራ ሥሮች ዛሬም ቢሆን በመነኮሳቱ እየተዘጋጁ ከሚበላው ቋርፍ በተጨማሪ ለመጠባበቂያ ለእለታዊ ምግብ ይጠቀማሉ፡፡

✞ ከዱር አራዊትና እንስሳት ወገን፤

አጋዘን፣ድኩላ፣ወደምቢ፣ተኩላ፣ዘንዶ፣ጊንጥ፣ቀበሮ፣ጅብ፣ጉሬዛ፣ዝንጀሮ፣ጦጣ፣ሰስ፣ሚዳቋ፣የመሳሰሉት ሲኖሩ፤ አንበሶች(ከስውራኖቹ በስተቀር) እና ዝሆኖች፤በአድን ገዳሙን በየአመቱ ጥርግ አድርጎ በሚበላው ሰድድ እሳትና በአደን ምክንያት ተሰቅቀው በወልቃይት አደርገው ወደ መተማና ሱዳን ተሰደዋል፡፡

✞ ከእጽዋትም ወገን፤

ሰርኪን፣ደማቅ፣እንኮይ፣የእጣን ዛፍ(መቀር)፣ሐሴን፣ሑመር፣ዋንዛ፣ሳላና፣ልዩ ልዩ አበቦች፣የሌሎችም እፅዋት ዝርያ ያለበት ገዳም ነው፡፡ በገዳሙ አንድ ክፍል በሆነው በአምርሓ ደጋ /አብርሃ ደጋ/ በተባለው ተራራማ ስፍራ ቁስቋም ማርያም ተብሎ የሚጠራ ስውር ቤተ-ክርስቲያን እንዳለ ይታወቃል፡፡

በአሁኑ ሰአት እጅግ ብዙ ሊሒቃን ሙሁራን መናንያን መነኮሳት ያሉበት ቦታ ነው ዋልድባ እህል አይበላም በገዳሙ ቛርፍ የሚባል ከሙዝ የሚዘጋጅ ምግብ ይመገባሉ በተጨማሪም ግመሎ ሳዳ ጫብሌ ፃብሌ የሚባሉ ስራ ስሮች ከመሬት ከጫካው በመቆፈር መነኮሳቱ የሚመገቡት ምግብ ነው። ሌላ ስኳር ጨው በርበሬ ተልባ ኑግ ማር ብቻ በገዳሙ የሚፈቀዱ ናቸው ሌላ የእህል አይነት ፈፅሞ አይገባም ክልክል ነው።

ዋልድባ በዓለማችን ካሉ ገዳማት በስርአተ ገዳም በመነኮሳት ስምሪት እና በስርአተ ቤተ ክርስቲያን መሰረት የዋልድባ ገዳም ግንባር ቀደም ነው። ዋልድባ ገዳም በሶስት ታላላቅ ቦታዎች በአራት የአንድነት ማህበር ተከፍሎ የሚገኝ ብቸኛው በኢትዮጵያ የምናኔ ቦታ ነው። ዋልድባ በስሩ ብዙ ቅርጫፎች አነስተኛ ገዳማት ያሉት ሲሆን የእርሻ ቤቶች ሞፈር ቤቶች የአትክልት ቦታዎች የንብ ቤቶችና ወፍጮ ቤቶች በመባል የሚታወቁ ብዙ ቦታዎች ይገኛሉ። በአንዱ ሞፈር ቤት ከሁለት መቶ በላይ መነኮሳት ይኖሩበታል። ለምሳሌ በዶንዶሮቛ ሁለት መቶ ሐምሳ መነኮሳት በመዘጋ እጣኖ ማርያም መቶ ሰላሳ፣ በማይ ሐርገፅ መቶ ስድሳ፣ አባነፃ ሰማንያ ቤት ሙሉ በአሁኑ ማይገባ አምሳ በማይለበጣ ሁለት መቶ የሚኖሩ መናንያን አሉ።

በነዚህ ገዳማት የሚኖሩ መነኮሳት ሁሉ ተጠሪነታቸው ለዋናው አብረንታንት ነው። ዋልድባ አንድ አይነት ልብስ ነው የሚለበሰው፤ ስሙ ወይባ ይባላል። ዋልድቦች በምናኔ በመንፈሳዊ አስተዳደር ሊሒቃን ናቸው። ገዳሙ ፍፁም የመናኞች ቦታ ነው። እጅግ ፀሎተኞች ናቸው በስራም ቢሆን ዋልድቦች እጅግ አስደናቂ ተአምር ሰሪ ናቸው የዋልድባ መነኩሴ ሰውነታቸው ቀጫጭን ለፀሎት የሚተጉ አዕምሮአቸው በመንፈስ ሙጡቃን ናቸው። ዋልድባ ስርአተ ዐበው በሚባለው መፅሐፍ እንደተፃፈው “ዋልድባ ሐጢአት አይሻገርብሽ እህል እንዳይበላብሽ” የሚል ትዕዛዝ እስካሁን ገዳሙ ውስጥ እህል አይበላም እርሻም አይታረስም ያረሰ ካለ ራሱ ቀድሞ ይጠፋል።

በጋላማራ ቃኤላውያን ከዋልድባ ገዳም የተባረሩት አባቶቻችንን የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያጽናናቸው የእግዚአብሔር መላእክት ይጠብቋቸው፤ ይንከባከቧቸው!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ፤ አባታችን ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በረከታችውና ረድኤታቸው ይደርብንና በሰሜኑ የሀገራችን የኢትዮጵያ ክፍል በ ፬ /4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ እንደ ተመሰረተ በሚነገርለት በደብረ ዋሊ ወይም ዋልድባ ገዳም የተነሱ ስመጥር መነኩሴ መናኝና የጽድቅ መምህር ናቸው።

የገዳማዊ ሕይወት እጅግ ተስፋፍቶ በነበረበት በ፲፫/13ኛው እና በ፲፬/14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ከነበሩት ታላላቅ የቤተ ክርስቲያን አባቶች እነ አባ ኢየሱስ ሞዓ፣ ብፁዕ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሲሆኑ የእነዚህም የቆብ ልጅ በሆኑት በገዳመ በንኮል በአባ መድኃኒነ እግዚእ እጅ ምንኩስናን

ተቀብለው ቤተ ክርስቲያንን በተሰጣቸው መንፈሳዊ ጸጋ አገልግለዋል።

ትውልዳቸውና ቤተሰቦቻቸው፤ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ የተወለዱት በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ አክሱም በ፲፪፻፺፭/1295 ሲሆን አባታቸው እስጢፋኖስ እናታቸው አመተ ማርያም ይባሉ። እነርሱም እግዚአብሔርን የሚፈሩ የተመሰገኑ ክርስቲያኖች እንደነበሩና በኋላም በምንኩስና ህይወት እንዳለፉ በአባታችን የገድል መጽሐፍና በስንክሳር ላይ በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል።

መንፈሳዊ ትምህርታቸውና ገዳማዊ ህይወታቸው እንዲሁም የተማሩበት ቦታ፤ እድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ አባታቸው ለአክሱም ቄሰ ገበዝ እንደሰጧቸውና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከፊደል ጀምረው የቅዱስ ያሬድን ጸዋትወ ዜማና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን አጠናቀው ለአገልግሎትም ዲቁናን ተቀብለው በንቃትና በልባምነትም ቤተ ክርስቲያንን ለሰባት ዓመት ካገለገሉ በኋላ ጌታችን በወንጌል “ፍጹም ልትሆን ብትወድ…”ማቴ.፲፱፣፳፩፡፳፪ ያለዉን ለመተግበር

ለአክሱም ከተማ ሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ ወደ ሚገኘው ደብረ በንኮል ገዳም ገብተው ከገዳሙ ሊቃዉንት የብሉያትንና የሐዲሳትን ትርጓሜ እንዲሁም ስርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል። ከዚያም ብፁዕነታቸው አባ ሳሙእል ዘዋልድባ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ያደረገ ቅዱስ ሄኖክ የመረጠውን ምናኔ፤ አባ እንጦንስና መቃርስ የተከተሉትን የምንኩስና ሕይወት በሰፊው ተጓዘበት።

ነፍሱን ነፍሴ ሆይ እነሆ ለክርስቶስ ታጨሽ የቅዱሳንን ቀንበር እነሆ ተሸከምሽ የመላእክትን ንጽህና ትጠብቂ ዘንድ ዛሬ በእግዚአብሔርና በቅዱሳኑ ፊት ቃል ኪዳን ገባሽ ቃልኪዳንሽን ብትጥብቂ እግዚአብሔር ይደሰትብሻል ባትጠብቂ ግን አጋንንት ይዘብቱብሻል በማለት መከራን በራሱ ላይ ያበዛ ነበር የጣመ የላመም አይመገብም ነበር ይልቁንም ከገዳሙ የሚሰጠዉን መቁኑን ተቀብሎ ለሌሎች

ሰጥቶ የዱር ቅጠል ይመገብ ነበር። ትጋቱንና የምናኔ ሕይወቱን ያዩ መናንያን አበው መነኮሳት የእነሱን የምንኩስና አክሊል እንዲቀበል ፈልገው የገዳሙን አበ ምኔት /ኃላፊ/ አባ መድኃኒነ እግዚእን ይመክሩና ይለምኑ ነበር አባ መድኃኒነ እግዚእም የሚያየዉንና ከመነኮሳቱም የሰማዉን ተቀብሎ በጊዜው ለምንኩስና ከተዘጋጁት አስራ ሁለት ከዋክብት ደቀ መዛሙርት ዉስጥ አንደኛው እንዲሆን ወስኗል።

ከምንኩስና ሥርዓቱም በኋላ እነዚህ አስራ ሁለት ከዋክብት ለሁለት ተከፍለው አምስቱን ከዋክብት በወሎ፣ ትግራይ እና ኤርትራ ሲመድቧቸው ሰባቱን ከዋክብት ደግሞ በሌላው የኢትዮጵያ ክፍል በበዛዉም በጎጃም በጎንደር እንዲሁም በጣና አካባቢ እንዲያገለግሉ እንዲያስተምሩ አሰማርተዋል። አባታችን አባ ሳሙኤል በገድላቸው እንደምንመለከተው “ፀሐይ ሳሙኤል ዘዋሊ” ይላል ‘ዋሊ’ የዋልድባ ገዳም የቀድሞ መጠሪያ ስሙ ነው ዋልድባ ገዳም በጣም ተዳክሞ በነበረበት ዘመን ተነስተው ዋልድባን ከጥፋት የታደጉ መናንያንን በማሰባሰብ እንደገና ያስፋፉ በመሆናቸው ዘዋሊ ይሏቸዋል፤ ሳሙኤል ዘደብረ ዓባይም ይሏቸዋል የደብረ ዓባይን ገዳም የመሰረቱት እሳቸው ስለሆኑ።

አባታችን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ከዚህ ዓለም በምናኔ ተለይተው ግርማ ሌሊቱን ድምፀ አራዊቱን ፀብዓ አጋንትን የሌሊት ቁር የቀን ሐሩርን ታግሰው የጽድቅን ጎዳና ተከትለው ብዙ የብዙ ብዙ ገድል በመሥራት ልዩ ልዩ ተአምራትን አድርገዋል ይህም በገድልና በተአምራት መጽሐፋቸው በሰፊው ተመዝግቦ ይገኛል። ከነዚሁም ጥቂቶቹን ብንጠቅስ አባታችን አቡነ ሳሙኤል፤ ባሕርን የከፈለበት ጊዜ አለ፣በጌታ መንበር ፊት እየቀረበ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋርም የሚያጥንበት ጊዜ አለ፣

በሰማያዊት ኢየሩሳሌምም ሆኖ ከእነ ቅዱስ ጴጥሮስ እና ከሁሉ ቅዱሳን ጋር አንድ ላይ ማዕድ የሚቀርብበት ጊዜ አለ፣ በእጆቹ የያዛቸው መጻሕፍትም ሳይርሱ ወንዝ የሚሻገርበት ጊዜ አለ፣ በተለይ በጸሎቱ ሰዓት የእምቤታችንን ምስጋና ሲጀምር ከምድር አንድ ክንድ ከፍ የሚልበት ጊዜ አለ፣ በቤትም ሆኖ ምስጋናዋን ሲጀምር የቤቱ መሰረት እየተናወጠ ዝናብ እንደያዘ ደመና፤ ቤቱ ከምድር ከፍ ብሎ የሚቆምበት ጊዜ አለ፣ መንፈስ ቅዱስም በብርሃን ሰረገላ እየወሰደው ወደ ተለያዩ ገዳማት ያደርሰዉና የጌታን ሥጋ እና ደም እንዲቀበልና እንዲያቀብል ያደርገው ነበር።

ብፁእ አባታችን ዉዳሴዋን ቅዳሴዋን ሲያደርስ እመቤታችን የፍቅሯ ምልክት ይሆነው ዘንድ ነጭ እጣንና የሚያበራ እንቁ ሰጥታቸዋለች። አባታችንም እነዚህን ስጦታዋች የምትሰጭኝ ምን ስላደረግሁ ነው? ብለው በጠየቋት ጊዜ እጣኑ የምኡዝ ክህነትህ ዕንቁው የንጽህናህ የድንግልናህ የቅድስናህ ናቸው ብላ ተርጉማላቸዋለች።

መራሄ ብሉይ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤልም የሁል ጊዜ ጠባቂው ነዉና በሁሉም ነገር ይረዳዉና እንደ ጓደኛም ያማክረው ነበር።

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባን የዱር አራዊት ሁሉ ይገዙለትና ይታዘዙለት እንደነበረ በዚሁ በገድል መጽሃፋቸው በሰፊዉ ተተንትኗል ይልቁንም ሁለት አናብስት የሁል ጊዜ አገልጋዮቹ ነበሩ። ከአንዱ ገዳም ወደ አንዱ ገዳም ከቦታ ቦታ ሲዘዋወሩ እሳቸው በአንዱ አንበሳ ተቀምጠው ጻሕፍቶቻቸውን በሌላው አንበሳ ላይ ጭነው እንደሚጓዙ ገድላቸው ያስረዳል። ሌሎቹም አራዊት አባታችንን ሲያዩአቸው እናቱን እንዳየ እንቦሳ በደስታ ይፈነጩ ነበር።

በመግቢያችን እንደገለጽነው የዋልድባ ገዳም የተመሰረተው በጥንታውያን አበው ቢሆንም አባታችን አባ ሳሙኤል ሲገቡ ገዳሙ ምድረ በዳ ሆኖ እስከ መጥፋት ደርሶ ቋያ በቅሎበት የወባ ትንኝ መፈልፈያ ሆኖ እንደ ነበረና ቅዱስነታቸው ሲገቡ ግን የተበተኑትን መነኮሳት ሰብስበው ዋልድባን እንደገና አደራጅተዉና አድሰው አቀኑት የተባህትዎ ኑሮንም አጠናክረው የመናንያን መነኮሳት አበው መሰባሰቢያና መፍለቂያ ከማድረጋቸውም በላይ ዋልድባን እንደ መሶብ አንስተው አስባርከዋታል።

ጻድቁ አባታችን ወንጌልን ለማስፋፋት በየሀገሩ ዞረው አስተምረዋል ብዙ የትሩፋትንም ሥራ ሠርተዋል ጣና ውስጥ በሚገኙ ገዳማትና ማን እንደአባ ያሳይ እንዲሁም ገሊላ ቦታዎች በምድር ዉስጥ ጉድጓድ ቆፍረው እየገቡ ከእህልና ዉሀ ተለይተው ሁለትና ሦስት ሱባኤ ይፈጽሙ ነበረ።

ከሁለት ቅዱሳን ወንድሞቻቸው ከአባ ሳሙኤል ዘወገግና ከአባ ብንያም ዘታህታይ በጌምድር ጋር በመሆን ምድረ ከብድና ዝቋላ በመሄድ ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጋር በተገናኙ ጊዜ ብዙ ተአምራት እንደተደረገላቸው መጽሐፈ ገድላቸው ያስረዳል እንዲሁም ደግሞ በኤርትራ

የሚገኘዉን ገዳም ከመሰረቱት ከአቡነ ፊልጶስ ጋር እንደተገናኙና የእግዚአብሔርን ክብር ይጨዋወቱ እንደነበር በገድላቸው ተጽፏል።

ጻድቁ አባታችን በሰኔ 21 በእመቤታችን የእረፍት ቀን በመካነ ጸሎታቸው ላይ እያሉ ጌታችን መድኃኒታችን ተገለጸላቸው። ወዳጄ ሳሙኤል ሆይ ሰላምታ ይገባሃል ። የሚል ድምጽ ሰሙና ደንግጠው ቆሙ። ጌታችን ቀረብ ብሎ የእናቴ የድንግል ማርያም በዓል ነውና እንድትቀድስ ብሎ አዘዛቸው። አባታችንም እኔ ኃጢአተኛ ነኝ ለመቀደስ አልበቃሁም በማለት ነው ከቤተ መቅደስ አገልግሎት የተለየሁት ብለው መለሱለት። ጌታችንም ስለዚህ ትህትናህ ነው እንድትቀድስ የመረጥኩህ አላቸው። ወዲያዉኑ አባታችን ከፈጣሪያችን ሥርየትና ቡራኬ ተቀብለው ቅዳሴ

ገቡ። ሥርዓተ ቅዳሴዉን አድርሰው ከፍሬ ቅዳሴው ደርሰው ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ፣ ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ፣ ጎሥዓ ልብየ ቃለ ሠናየ ባሉ ጊዜ የሚቀድሱበት ቤተ ክርስቲያን አንድ ክንድ ከስንዝር ከምድር ለቅቆ እንደ ደመና በአየር ላይ ቆመ። ቅዳሴው ተፈጽሞ እትው እስኪባልም ድረስ እንደቆመ ቆይቷል። ከቅዳሴው በኋላም ጌታችን ከሰው ልጆች የተወለዱትን ሁሉ ወደፊትም እስከ

ምጽዓት ድረስ የሚወለዱትንም እልፍ አእላፋት መናንያን መነኮሳት ሰብስቦ በአምላካዊ ሥራው ሕያዋን አድርጎ አሳያቸው።አቡነ ሳሙኤልም በመገረም አምላኬ ፈጣሪየ ሆይ ይህንን ያህል ግዛት ያለው ሰው ከምን የመጣ ነው? ብለው ጠየቁት። እነዚህ እስከ እለተ ምጽዓት ድረስ የሚወለዱ ልጆችህ ናቸው።በአንተ እጅ እንዲባረኩም አምጥቻቸዋለሁ ባርካቸው በማለት ነግሯቸዋል። የአቡነ

ሳሙኤልን ስም የሚጠራ መታሰቢያቸዉን የሚያደርግ በአማላጅነታቸው የሚያምን ሁሉ ተባርኳል።

የአባታችን በረከት ከሁላችን ጋር ይደር። የአባ ሳሙኤል ቃል ኪዳናቸው፣ እረፍታቸውና

ዓመታዊ ክብረ በዓላቸው የአባታችን የእረፍት ጊዜ ሲደርስም በተወለዱ በአንድ መቶ ዓመት በምናኔ በተባህትዎ እና በምንኩስና ከዚህ ዓለም ተለይተው ግርማ ሌሊትን ድምፀ አራዊትን ፀብአ

አጋንንትን የቀን ሐሩር የሌሊት ቁሩን ታግሰው ራቡን ጥሙን ችለው መላ ዘመናቸውን የተቀበሉትን ፀዋትወ መከራ አይቶ ገነት መንግሥተ ሰማያትን ያወርሳቸው ዘንድ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አባታችን ካሉበት በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃንና ሰማእታትን አስከትሎ መጥቶ በህይወት ሳሉ የሰጣቸዉን ቃል ኪዳን በእረፍታቸዉም

ደግሞ ስምህን የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በጸሎትህ በአማላጅነትህ ያመነ፣ በመቃብርህ በመካነ አፅምህ የተማፀነ የአንተ ቤተሰብ ሆኖ አንተ የገባህበት አገባዋለሁ። ርስት መንግሥተ ሰማይን አወርሰዋለሁ ብሎ ቃል ኪዳን ሰጣቸው። ንጽሕት ጽዕድት ነፍሳቸው በእደ መላእክት በመዓዛ ገነት ከሥጋዋ ተለየች። ቅዱሳን መላእክትም በነብዩ በዳዊት ቃል መዝ.፻፲፮፥፲፭ “ክቡር ሞቱ ለጻድቅ

በቅድመ እግዚአብሔር” እያሉ በታላቅ ዝማሬ፣ በይባቤ፣ በእልልታና በሕይወት ወደ ዘለዓለም የእረፍት ቦታ አስገቧት። ጻድቁ አባታችን በተወለዱ በመቶ ዓመታቸው ታህሳስ ፲፪/12 ቀን ማክሰኞ ከቀኑ በዘጠኝ ሰዓት ዋልድባ አብረንታንት አርፈዋል።

ስለ አባታችን አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ ይህንን አጭር ጽሁፍ ስናቀርብ አቅጣጫ ለማመላከት ያህል ሲሆን መላዉን በገድል መጽሐፋቸውና በስንክሳር ያገኙታል።

በመስከረም ፮/6 ፍልሰተ አጽማቸው ነው፤ ይህም ከአብረንታንት ወደ ደብረ ዓባይ የፈለሰበት ነው፣ ታህሳስ ፲፪/12 እረፍታቸው ነው እንዲሁም ወር በገባ ፲፪/12 ደግሞ ወርኃዊ በዓላቸው ነው።

የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሳሙኤል ረድኤት በረከት አማላጅነት አይለየን!!!

ወስብሃት ለእግዚአብሔር!

ወለወላዲቱ ድንግል!

ወለመስቀሉ ክቡር!

ይትባረክ አምላክ አበዊነ!

👉 ሙሉውን በPDF ለማንበብ

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፯፥፭፡፮]✞✞✞

“እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።

እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፤ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።”

✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፯፥፴፡፴፩]✞✞✞

“በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፤ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።

መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች።

እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።

እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፤ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።”

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

%d bloggers like this: