Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 5, 2023
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 መርቆርዮስ 👉 ዮሴፍ 😇 መድኃኔ ዓለም
✞ ጥንተ ስቅለት ፥ መጋቢት ፳፯/27፣ ፴፬/34 ዓ.ም.✞
የዛሬ አንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ ሰባ አምስት ዓመት በዕለተ ዓርብ መጋቢት ፳፯/27 ቀን ፴፬/34 ዓመተ ምሕረት (፶፻፭፻፴፬/5534 ዓመተ ዓለም) የክብር ባለቤት ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ዓለም ድኅነት በሥጋ የተሰቀለበት ዕለት ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ እንደተጻፈው፡ “ከስድስት ሰዓት ጀምሮም እስከ ዘጠኝ ሰዓት ዓለም ሁሉ ጨለማ ሆነ”[ማቴዎስ ፳፯፥፵፭] ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ባየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች። እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት። ሐዋርያጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ፤ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች፤ በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር። እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋር አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡ [፩ ጴጥሮስ ፫፥፲፰፲፱]
እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ፣ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሡን ሰውቶ ያዳነን የመንግሥቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ የከፈተልን ለእርሱ ስግደት አምልኮት ይገባዋል።
ለዘለዓለሙ የመስቀሉም በረከት በላያችን ይደር፤ አሜን።
(የመጋቢት ፳፯ ቀን ስንክሳር )
❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፺፩]❖❖❖
- ፩ እግዚአብሔርን ማመስገን መልካም ነው፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህም ዝማሬ ማቅረብ፤
- ፪ በማለዳ ምሕረትን፥ በሌሊትም እውነትህን ማውራት
- ፫ አሥር አውታር ባለው በበገና፥ ከምስጋና ጋርም በመሰንቆ።
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: Addis Ababa, Aksum, Anti-Ethiopia, Axum, ሑዳዴ, መታሰቢያ, መንፈሳዊ ውጊያ, መድኃኔ ዓለም, ምሕላ, ሰማዕታት, ሰቆቃ, በገና, ባንዲራ, ተራሮች, አሕዛብ, አቤል ተስፋዬ, አክሱም, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, እምነት, ኦርቶዶክስ, ክርስቲያኖች, ወንጀል, ዐቢይ ጾም, ዘ-ብሔረ አክሱም, ደመና, ጠላት, ጦርነት, ጭካኔ, ጭፍጨፋ, ጸሎት, ጽዮናውያን, ጽዮን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, Ethiopia, Genocide, Massacre, Prayers, Tewahedo, Zion | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 2, 2023
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 😇 ተክለ ሐይማኖት 👉 መርቆርዮስ 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
- ❖ ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
- ❖ ኒቆዲሞስ የአይሁድ አለቃ ነው። ዮሐንስ ፫፥፩
- ❖ ኒቆዲሞስ መምህረ እስራኤል ነው። ዮሐንስ ፫፥፲
- ❖ ኒቆዲሞስ ምሑረ ኦሪት ነው። ዮሐንስ ፯፥፶፩
ኒቆዲሞስ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ድል ማድረግን ወይም አሸናፊነትን ያመለክታል፡: ኒቆዲሞስ ፈሪሳዊ፥ ከአይሁድ አለቆችና መምህራና አንዱ ነው። በወንጌለ ዮሐንስ ምዕራፍ ሦስት ከፈሪሳውያን ወገን የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የተባለ አንድ ሰው እንደነበረና እርሱም በሌሊት ወደ ጌታችን መጥቶ እንደተማረ ተጠቅሷል። (ዮሐ ፩–፪)
በአይሁድ አለቆች ፊትም ”ሕጋችን አስቀድሞ ሳይሰማ የሠራውንም ሳያውቅ በሰው ይፈርዳልን?” በማለት ስለ መድኃኔዓለም ክርስቶስ የተናገረ እሱ ነው። እነርሱ ግን በክርስቶስ እግዚአብሔርነት ያመኑበት ኦሪትን የማያዉቁ ስሑታን እንደሆኑ ያስቡ ስለ ነበር ”አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን? ከገሊላ ነቢይ እንደማይነሳ መርምርና እይ“ አሉት እንጂ አልተቀበሉትም። ዮሐ ፯፥፵፰–፶፪። ኒቆዲሞስ የአርማትያስ ሰው ከሚሆን ከዮሴፍ ጋር በመሆን የጌታችንን ቅዱስ ሥጋ በንጹሕ በፍታ ገንዞ በአዲስ መቃብር ቀብሯል። ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ”ቀድሞ በሌሊት ወደ ጌታችን ኢየሱስ ሄዶ የነበረዉ ኒቆዲሞስም መጣ፤ ቀብተውም የሚቀበርበትን መቶ ወቄት የከርቤና የሬት ቅልቅል ሽቶ አመጣ።” እንዳለ። ዮሐ ፲፱፥፴፱። በዚህም ኒቆዲሞስ ከምክረ አይሁድ ያልተቀላቀለ መሆኑ ይታወቃል።
የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ የሌሊት ተማሪው ኒቆዲሞስ ዮሐንስ ፫፤፪
ከፈሪሳዊያን ወገን የሆነ የአይሁድ አለቃ የሆነ ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው በሌሊት ወደ ጌታ እየሄደ ይማር ነበር ኒቆዲሞስ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የሌሊቱን ጊዜ ለትምህርት ለምን መረጠ ?
፩/ ኒቆዲሞስ መምህር ስለነበር ስማር ሰዎች ቢያዩኝ ውዳሴ ከንቱ መምህር መባል ይቀርብኛል ብሎ ነው እኛስ ዛሬ የዘላለም ህይወት የሚሰጠንን ቅዱስ ቃል በትህትና መማር ሲገባን ለምድራዊ ክብር ብለን በቀን ጊዜያችን መማር ያልቻልን ስንቶቻችን ነን ስለዚህ ቀን ጊዜአችንን በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል።
‹ ማንም ሊሰራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለችና › ዮሐንስ ፱፤፬
፪/ .ኒቆዲሞስ የአይሁድ መምህር ስለነበር እንዳያዩት ፈርቶ ሌሊት እየመጣ ይማር ነበር እኛስ ዛሬ ልባችን የተረዳውን እውነት በግልጥ እንዳንፈጽም በፍራቻ በይሉኝታ የምንሰውር ስንቶቻችን ነን
‹ፍጹም ፍቅር ፍርሃት የለውም ፍርሃት ቅጣት አለውና› ፩ ዮሐንስ ፬፤፲፰ ፍርሃትን አስወግደን ለእውነት ልንቆም ይገባል።
፫/ ኒቆዲሞስ ከቀን ልብ ይልቅ የሌሊት ልብ የተካተተ ስለሆነ በሙሉ ልቡ በማስተዋል ለመማር ስለፈለገ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ ይልቅ የማታውን መረጠ ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን በማስተዋል ከልብ ሆነን የምንማር የሰማነው ቅዱስ ቃል በህይወታችን ፍሬ እንዲያፈራ ቅዱስ ቃሉን ከልብ ሆነን በማስተዋል ልንሰማ ይገባናል ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ልብ መልካም መሬት ተብⶀል
‹ በመልካም መሬት የተዘራውም ይህ ቃሉን ሰምቶ የሚያስተውል ነው› ማቴ ፲፫፡፳፫
አንዳንዶቻችን ጸሎት እያደረግን እንኳን አንደበታችን የእግዚአብሄርን ቃል ይነዳል ልባችን ሌላ ቦታ ይንጎዳጎዳል በማህበር ጸሎትም አብረን እየጸልይን በመሃል ሳይን አውት አርገን ልክ ሲፈጸም አለቀ እንዴ ብለን ሳይን ኢን የምናደርግ አንጠፋም።
፬/ ሌሊት ጨለማ ነው ብርሃን የለም ይህም የኃጢአት ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስ በሌሊት መምጣቱ በኃጢአት እንዳለ ንስሃ እንደሚፈግ ያስረዳናል ዛሬስ ስንቶቻችን ነን ቅዱስ ቃሉን ስንሰማ በተአምኖ ኃጢአት በንስሃ ውስጥ ሆነን የምንሰማ ያለንስሃ የምንሰማው ቃል በህይወታችን ፍሬ የማፍራት እድሉ ጠባብ ነው ምክንያቱም በንስሃ ከልባችን ያልጸዱት ክፉ ምኞቶች እንደ እሾህ ሆነው ያንቁታልና
‹ሌላውም በእሾህ መካከል ወደቀ እሾህም ወጣና አነቀው› ማቴ ፲፫፤፰ ተብሎ የተጻፈው ለዚህ ነው።
፭/ ሌሊት የቆየው ኪዳን ወይም የብሉይ ኪዳን ምሳሌ ነው ኒቆዲሞስም እኔ ምሁረ ኦሪት እንጂ ምሁረ ወንጌል አይደለሁም ወንጌልን ካንተ እማር ዘንድ ያስፈልገኛል ሲል በሌሊት ይመጣ ነበር ብሉያት ከሓዲሳት ጋር ተዋህደው ሲተረጎሙ ሰሙና ወርቁ ተጣምሮ የሕይወት ትምህርት ያስገኛል አንዳንዶች ዛሬ ብሉያት ጭራሽ አያስፈልጉም ሲሉ ይደመጣሉ ነገር ግን እንደ ኒቆዲሞስ ሁለቱን ኪዳናት አዋህዶ መጓዝ ትክክለኛው መንገድ ነው ለዚህም ነው ጌታ ሲያስተምር‹እውነት እላችኋለው ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ ከህግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ አታልፍም› ማቴ ፭፤፲፰ በማለት አበክሮ የተናገረው ኒቆዲሞስ ምንም እንኳን የቀኑ ክፍለ ጊዜ ባይመቸውም በሌሊቱ ሰአት ለመማር ችⶀል እኛም ከሱ ተምረን ከልብ ካለቀሱ እንባ አይጠፋምና ምንም ስራ ቢበዛብን ለቅዱስ ቃሉ ጊዜ አይጠፋምና ህይወት ለሚገኝበት ትምህርት ጊዜ ልንሰት ይገባል።
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: Abel Tesfaye, Addis Ababa, Aksum, Apostel, Axum, ሌሊት, ሑዳዴ, መምህር, መንፈሳዊ ውጊያ, መዝሙር, መጽሐፍ ቅዱስ, በገና, ተዋሕዶ, ኒቆዲሞስ, አቤል ተስፋዬ, አዲስ አበባ, ኢትዮጵያ, ኢየሱስ ክርስቶስ, እምነት, ኦርቶዶክስ, ክርስትና, ወንጌል, ዐቢይ ጾም, ዮሐንስ, ጽዮን, ፈሪሳውያን, Begena, Gospel, Jesus Christ, John, Learning, Lent, Mezmur, Nicodemus, Pharisee, Psalms, Spiritual Warfare, Teaching, Tewahedo | Leave a Comment »