እነዚህ ድንቅ ሥዕሎች ከአሜሪካዋ ቦልቲሞር፣ ሜሪላንድ ዋልተርስ ቤተ መዘክር ድህረ ገጽ የተገኙ ናቸው። ከምስጋና ጋር።
ወደዚህ ድህረ–ገጽ ዛሬ እንዴት እንደገባሁ አላውቅም፤ በወቅቱም ስለ ሌቀ መላእክት ሚካኤል የምፈልገው ነገር አልነበርም፤ ግን ያው ጠባቂያችን ሚካኤል በዛሬው ዕለት እንደ ድንገት ወደዚህ መራኝ። ይህ እራሱ ተዓምር በመሆኑ ቀኑን ሙሉ ተደስቼ ነበር የዋልኩት፤ በአልተባበሩት መንግሥታት የተከሰተውን አሳዛኝ ዜና እስከምሰማ።
የብዙ ጥንታውያን ሥዕሎችና ምስሎች ስብስብ በተለያየ መልክ ቢኖረኝም፡ እነዚህን አስደናቂ ሥዕሎች ግን ለመጀመሪያ ጊዜ ማዬቴ ነው። እንደዚህ ዓይነት የስብከት እና የቅዳሴ ሥርዓት እንደዚህ ከመሰሉ ድንቅ ባለቀለም ሥዕሎች ጋር ከ400 ዓመታት በፊት በሚያስገርም መልክ አባቶቻችን ሲፈጽሙ ነበር። በጣም አስደናቂና የሚያኮራ ነው!
በተጨማሪም ሁሉም ሥዕሎች ላይ የሚታዩት መልአክትና ቅዱሳን የኢትዮጵያውያን ገጽታ እንዲኖራቸው ተደርገው ነበር የተሠሩት። ፈረንጁም በአገሩ ይህን ነው ከአድናቆት ጋር እያሳየ ያለው። ታዲያ ይህን የሚያዩ ሠዓሊያን ወገኖች፡ መልአክቱንና ቅዱሳኑን ሁሉ ፈረንጅ አስመስለው አሁን ሲስሉ እጅግ በጣም አያሳዝንምን? አያንገፈግፍምን? ምን ነክቷቸው ይሆን? በእውነት፡ አባቶቻችንን ምን ያህል ቢንቋቸው ነው? የሚያሰኝ ጉዳይ ነው።
እነዚህ በድርሳነ ሚካኤል አነሳሽነት የተሠሩት ድንቅ ሥዕሎች የኢትዮጵያ ሥነ ጥበብ በአበበበት በ 17 ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ ነበር በጎንደር ከተማ የተሠሩት። በወቅቱ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ፍርድ ቤት እና ተጓዳኝ መኳንንቶች ቋሚ መኖሪያ በጎንደር አድረገው ነበር።
እነዚህ በብዙ ቀለማት ያሸበረቁና የሚያበሩ 49 ሥዕሎች የወቅቱን የበለጸገ የሥነ ጥበብ ባህል ያንጸባርቃሉ። የእጅ ጽሑፉ በሊቀ መላእክት ሚካኤል ተአምራት እና 49 ደማቅ ቀለም ባላቸው የእግዚአብሔርን ገጸ–ባህሪያት በሚያሳዩ ሥርዓት ትምህርቶች ላይ ያተኮረ እንዲሁም በቅዱስ ሚካኤል የተፈጸሙ ተዓምራቶችን አጣምሮ የያዘ ነው
የእጅ ጽሁፎቹ ክፍሎች እንደ ተለመደው በቅዱስ ሚካኤል ወርሃዊ የበዓል ቀናት ይነበቡ ነበር፤ እናም ሥዕሎቹ በምንባቡ ጎን አብረው ይቀርቡ ነበር።
አርቲስቶቹ፡ እንደ ጥንታውያኑ የብራና ባለሞያዎች ሳይሆኑ፡ ልክ እንደ ሠዓሊዎች የሠለጠኑ ነበሩ። እናም የእነሱ ሥነ ጥበብ ከዘመናዊ የግድግዳ ሥዕሎች ጋር ሊዛመድ ይችላል ማለት ነው።
ከ አርባ ዘጠኙ ሥዕሎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
- + ቅዱስ ሚካኤል መካን የነበረችውን ሴት ልጅ እንድትወልድ ረዳት
- + ቅዱስ ሚካኤል ለዓይነ ስውሩ ብርሃን ሲሰጠው
- + ቅዲስ ሚካኤል እርኩስ መንፈስ ከቤተክርስቲያኑ ሲያስወጣ
- + ቅዱስ ሚካኤል አንድ የተቸገረ ሰው የበዓል ቀኑን እንዲያከብር ሲረዳው
- + ቅዱስ ሚካኤል በኃጢአተኞች ምትክ ሲለምን / ሲማልድ
- + ሰማእት ኤፎሚያ (3ኛው ክፍለ ዘመን) ለሰይጣን የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል ስታሳዬው እንደ ቁራ ሸሽቶ በረረ፤ ከዛም፡ ሰይጣን በአራት ሴቶች ተምስሎ እንደገና ሲመጣ፤ ቅዱስ ሚካኤል በላዩ ላይ ወጣበት
Courtesy of The Walters Art Museum
የኢትዮጵያ ልጆች ይህችን የ ቅ/ ሚካኤል ዕለት እናስታውስ!
የድምጽ ሰጪ አገሮች ሰንጠረዡም በኢትዮጵያ ሦስት ቀለሞች፤ +አረንጓዴ፣ xቢጫና —ቀይ ያሸበረቀ ነው። አረንጓዴ፤ አረቦች የሰረቁት የእስላም ቀለም ሆኗል፤ ቢጫ ገለልተኞች፣ ቀይ ደግሞ አመሪካና እስራኤል የደገፉት ናቸው። በጣም አስገራሚ ነው!
(የ ሄጌል Thesis–Antithesis–Synthesis ሞዴል)
ወንድሞቻችንን በባርነት ከምሸጡት፣ እህቶቻችንን ከፎቅ እየወረወሩ ከሚገድሉት አርቦች በማበር የኢትዮጵያን የድጋፍ ድምጽ በተባበሩት መንግሥታት እንድንሰጥ ተደርገናል። ዓጼ ኃ/ ሥላሴም ተምሳሳይ ድርጊት ከፈጸሙ በኋላ ነበር፤ ኢትዮጵያችን በጣም አስከፊ በሆነ መልክ እንድትራቆትና እንድትደቅ ሁለት ትውልድም እንዲጠፋ የተደረገው።
የግድ አሜሪካንና እስራኤልን መደገፍ የለብንም፡ ለዚህም እንደነ ቤኒን፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያ፣ ሌሶቱ፣ ማላዊ፣ ጊኒ ኤኳተሪያል፣ ፊሊፒንስ፣ ኮሎምቢያ፣ ፓናማ፣ አውስትራሊያ፣ አርጀንቲና፣ ቦስኒያ፣ ፖላንድ፣ ሮማኒያ ወዘተ የመሳሰሉት 35 አገሮች በገልተኝነት ድምጽ ከመስጠት መቆጠብ ነበረብን።
የሚያሳዝነው እስራኤልን ወይም አሜሪካን አለመደገፋችን ሳይሆን አረቦችን መደገፋችን ነው!
አገራችን ከፍየል አገራት ጋር አብራ መሰለፍ አልነበረባትም። ያልተባበሩት መንግሥታት በሊቢያ ስለሚካሄደው የባርነት ንግድና በእስላም አገሮች የሚታየው የክርስቲያኖች ጭፍጨፋን ልክ እንደዚህ በደንብ መውገዝ ነበረበት እንጂ ኢምባሲ ተዛወረ አልተዛወረ እንደ ትልቅ ነገር ተቆጥሮ የተለየ ሤራ መጠንሰስ አልነበረበትም። ወስላቶች!
እስራኤላውያን ለክፉም ሆነ ለበጎ በተለይ በኢትዮጵያውያን ላይ ልዩ የሆነ አትኩሮት ነው ያላቸው። ግብጽም፡ ልክ እንደ ቀድሞው በደስታ ጮቤ ትረግጣለች፤ ፍርሀት የተጫነው የመረጋጋት መመሪያ ሠርቶ አያውቅም።
ከ800 ዓመታት በፊት በመሀመዳውያን ላይ ቅስም የሚሰብር ድል የተቀዳጀቸው ስፔይን (በዚህም፤ ኢትዮጵያ፡ ስፔይንና ፖርቱጋልን በመርዳት በይፋ የማይታወቅ ከፍተኛ ሚና ተጫውታለች፤ ሌላ ጊዜ..) ያው በካታላንውያን በኩል ኃይለኛ ፈተና ገጥሟታል፤ በዛሬው ዕለት በካታሎኒያም የተካሄደው ምርጫ ብዙ መዘዝ አለው። ካታሉኒያ + ቫሎኒያ + ባቫሪያ + ኤርትራ + ኦሮሚያ + ክሮአስያ + ስኮትላንድ + ቱርክ + ዩክሬየን + ኩቤክ — እነዚህ ግዛቶች የአመጸኞቹ አለቃ ሰይጣን በክርስቲያን ሕዝቦች ላይ እንዲያምጹ ያዘጋጃቸው ግዛቶች ናቸው። በጌታችን ልደት ዋዜማም ይህ ሁሉ መከሰቱ ያለምክኒያት አይደለም።
ይህን የታህሳስ ፲፪ ፥ ፪ሺ፲ ዓ.ም ዕለትን በደንብ እናስታውስ።
የሊቀ መልአኩ የቅዱስ ሚካኤል ረድኤት በረከቱ አይለየን!!!