Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ወፍጮ’

በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮን የወደመው ወፍጮ የዋልድባ ገዳም ንብረት ነው | ፲፱ እናቶች ተሰውተዋል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 12, 2022

😠😠😠 የጨለማ ዘመን ኢትዮጵያ 😢😢😢

💭 በደደቢት ከተማ፤ በጌታችን ልደት ዕለት ሃምሳ ዘጠኝ እናቶችና ሕፃናት በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮኖች ተጨፍጭፈው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል።

ከሁለት ቀናት በኋላ ደግሞ በማይ ጸብሪ ከተማ ግራኝ መሀመዳውያኑን የክርስቶስ ተቃዋሚዎች አጋሮቹን ጋብዞ ለዋልድባ መነኮሳት እህል ሲፈጭ የነበረውን የወፍጮ ቤት አውድሞ እናቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደላቸው። ምን ዓይነት ሰይጣናዊነት ነው፤ ጃል?! እነ ግራኝና ጭፍሮቻቸው ምን ያህል ከሃዲዎች፣ አረመኔዎችና ደፋሮች ቢሆኑ ነው!? ዓይናችን እያየ? ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን ፈቃዱን አግኝተው ነውን? ወደ አሜሪካ የሚጓዙት አውሎ ነፋሳት መነሻቸው ይህ አካባቢ መሆንን ደርሰውበታል። ከወራት በፊትም አንድ ሺህ የሚሆኑ ጽዮናውያን አባቶችን ከዋልድባ ገዳም እንዲባረሩ ያደረገውም እርኩሱ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ መሆኑም ግልጽ ነው። ግራኝ በገዳማቱ ላይ ጥቃት እንደሚፈጽም፣ የኑክሌር መሳሪያ ካገኘም (ምናልባት በቅርቡ በቱርክ የሚገኙትን የአሜሪካ የኑክሌር መሣሪያዎች ኦሮሚያ በተሰኘው ሲዖል ለማስፈር ከእብዱ ኤርዶጋን ጋር ሳይስማማ አልቀረም)በአክሱም ጽዮን ላይ ምንም ሳያመነታ ሊጠቀም እንደሚችል ከሦስት ዓመታት በፊት አውስተን ነበር።

👉 “ግራኝ ዐቢይ ከሜንጫ ወደ ሚሳኤል ተሸጋገረ | ሰሜን ኢትዮጵያን ለመደብደብ ተዋጊ አውሮፕላኖችን ሊሸምት ነው

ዋይ! ዋይ! ዋይ! በእውነት ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ በጣም ጨለማማው ዘመን ነው! ይህን የጨለማ ዘመን ለማምጣት የሠሩት ሁሉ የገሃነም እሳት ወላፈን ይጠብቃቸዋል። ፻/100%!

_________ቅዱስዮሐንስ________

Posted in Ethiopia, Faith, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: