በዋሽንግተን ዲሲ የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ነበር ይህ ክስተት የተፈጠረው። መፈክሮቹ ጥሩዎች ናቸው። ግን በአንዳንዶች ዘንድ ይህን ወራዳ ግለሰብ “አንቱም” “ዶክተረም” ብሎ ለመጥራት የተደረገው ሙከራ ተገቢ አይደለም። እስኪ ይታየን፤ ለአሜሪካ ብልጽግና እና ደህንነት ተግቶ በመሥራት ላይ ያሉትንና በሕዝብ የተመረጡትን ሃገር–ወዳዱን ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን “አንተ” ይሏቸዋል፤ ለኢትዮጵያ ውድቀት ተግቶ በመሥራት ላይ ያለውንና ያልተመረጠውን ፀረ–ኢትዮጵያ ግለሰብ ግን “አንቱ”። ምን ዓይነት ቅሌት ነው?! እኔ እንደተረዳሁት፤ ይህን እራስ አፍቃሪ/ ናርሲስት ግለሰብ በ“አንቱ” እና “ዶ/ር” መልክ የሚጠራ ወገን ልክ እንደ ግብዝ ደጋፊዎቹ ነፍሱን ቀስ በቀስ ቆርሶ በመጣልና በማድከም የአብዮትን የሥልጣን እድሜ ለማራዘም ብሎም ሰውየው በሕዝብ ላይ የሚሳለቅበትን ዘመን ለማስቀጠል አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ከወዲሁ ሊያውቀው ይገባል። በአለፉት ሁለት ዓመታት በሃገራችን ሕዝብ ላይ ያን ሁሉ ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ ሰቃይና መከራ ያመጣውንና የኢትዮጵያ ጠላት ሆኖ በግልጽ የሚሠራውን ይህን ወሮበላ ግለሰብ ማክበርና መፍራት ተገቢ አይደለም፤ ኢትዮጵያዊነትን ማርከስ ነው የሚሆነውና ፥ ጠቅላይ ሚንስተርነቱንም ሕዝብ የሰጠው አይደለምና።
ሌላው አስገራሚ ክስተት፦ ጉግል አስተርጓሚ ገብታችሁ በእንግሊዝኛው “Abiy Ahmed“ ብላችሁ ብትጽፉ በአማርኛው “ዶ/ር አብይ አህመድ” በሚል መልክ ተተርጉሞ ይነበባል። ይህ በአማርኛው ቋንቋ ብቻ እንጂ በሌሎች ቋንቋዎች የለም። ይህን እንግዲህ ለአውሬው የጉግል ተቋም ተቀጥረው የሚሠሩ የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች የሆኑ የገዳይ አብይ ደጋፊዎች ፕሮግራም ያደረጉት መሆኑ ነው። በአፋጣኝ ብታርሙት ይሻላችኋል!